Telegram Web
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷ " ስ ለ ተ ስ ፋ " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[                       🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ❞

[ ኢዮ . ፵፪ ፥ ፪   ]

❝ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። ❞

[ መዝ . ፳፫ ፥ ፬ ]



🕊                       💖                   🕊
2
😢3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ " የማይታየው ግን የዘላለም ነው " ] 

[                         🕊                         ]
----------------------------------------------------

" የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት ፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና ፤ የሚታየው የጊዜው ነውና ፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። " [ ፪ቆሮ.፬፥፲፯ ]


🕊                       💖                   🕊
5
🕊

[ †  እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]


🕊  †  ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ  †   🕊

ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት::

አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች::

አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች::

በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር::

ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች::

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::"

ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች::

በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ ፴፰ [38] ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር [ብርድ] ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት::

ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ :- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው::

ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ ፴፰ [38] ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም::

እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም::

አንድ ቀን ግን [ማለትም ግንቦት ፳፰ [28] አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ::

አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች::

አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን::

🕊

[ † ግንቦት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት [ ገዳማዊት ]
፪. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት ]
፫. አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ
፬. አባ ጌርሎስ [ ጻድቅና ሰማዕት ]
፭. ፵፭ "45" ሰማዕታት [ የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት ]
፮. ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

" ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: " [፩ዼጥ.፫፥፫]  (3:3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
4
#አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር
ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው
ዘወትር እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን

#አማኑኤል ማለት አማኑ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው።

« አማነ»እና «ኤል» ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛጋ ማለት ነው።

«
#ድንግል_ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ #አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ»

«ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡» ( ኢሳ 7፥14)

ክብር ፣ኃይልና ምስጋና ለአምካችን ለአማኑኤል ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።


#መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
19
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷ "  ብ ር ቱ ት ግ ል !   "

[  💖 የሶሎሞን መዝሙር 💖  ] 

[                        🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።

ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። ❞

[ ኤፌ . ፮ ፥ ፲፩ ]


🕊                       💖                   🕊
1🙏1
1
                           †                           

🕊  💖     ቅዱስ አማኑኤል        💖  🕊

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ]


❝ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው ፥ በእርሱም እታመናለሁ ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ ፥ መድኃኒቴ ሆይ ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ።

ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። ❞

[ ፪ሳሙ . ፳፪ ፥ ፫ ]

🕊

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
3
5
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

†   እንኳን አደረሳችሁ   †

†  ግንቦት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  †


🕊  †  አባ አፍፄ ወአባ ጉባ  †  🕊

አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ [ዘጠኙ]
ቅዱሳን ነው::

🕊   †  አባ አፍፄ   †  🕊

ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና በሕጻንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከ ፰ [8] ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው::

ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል:: ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር::

ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን :-

፩. ከ ፻ [100] ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት አገልግለዋል::

፪. በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን ፫፻፷፮ [366] ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል::

፫. ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል::

፬. በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል:: ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ [አፈ-ዐፄ]" ብሏቸዋል:: "የዐፄ [የንጉሥ] አንደበት ያለው" ወይም "ንግግር አዋቂ" ማለት ነው::

ጻድቁ ከ፪፻ [200] ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በዚሕች ቀን በ ፸፻፹፬ [684] ዓ/ም ተሠውረዋል:: እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::


🕊    †    አባ ጉባ   †     🕊

ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ ፳፱ [29] ቀን በ፫፻፴፮ [336] ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ::

አባ ጉባ ["ባ" ጠብቆ ይነበብ] በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ፯ [7] ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል::

በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ፰ [8] ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ፻፵ [140] በላይ ነበር::

ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል: መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል::

ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::

በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው:: [በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ- ልሳን" ማለት ነው]

ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::

🕊

[ † ግንቦት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ አፍፄ [ ከዘጠኙ ቅዱሳን ]
፪. አባ ጉባ [ ከዘጠኙ ቅዱሳን ]
፫. አባ ስምዖን ገዳማዊ [በ ፯ [7] ዓመታቸው መንነው ለ፹፩ [81] ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ]
፬. አባ ይስሐቅ ጻድቅ

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ
፪፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ
፭፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
፮፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
፯፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ
፰፡ ጉባኤ ሰማዕታት

" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: " [ማቴ.፲፥፵፩] (10:41)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
2
2025/07/14 06:17:08
Back to Top
HTML Embed Code: