🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
❖ ሰኔ - ፬ - ❖
[ ✞ እንኩዋን ለታላቁዋ ሰማዕት "ቅድስት ሶፍያ" እና ለቅዱስ "ዮሐንስ ዘሐራቅሊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
† 🕊 ሶፍያ [ SOPHIA ] 🕊 †
ሶፍያ [ "ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ ] በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች::
† 🕊 ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት 🕊 †
ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በ ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ዘመኑ የጭንቅ : የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር::
የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል:: ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት : ያማረ ቤት ሰርተውላት በዚያ ትኖር ነበር:: ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር::
ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን [ገዢ] ሊድሯት መሆኑን አወቀች:: ወደ ቤቷ ገብታ ፻ [100] ጊዜ ሰገደች:: ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች:- "ጌታየ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ:: አልችለውምና:: ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ" አለች::
አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ:: በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች:: ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር:: በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው:: እርሷ ስደትን አልመረጠችም::
እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች:: በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አለችው:: ንጉሡ ከመልኩዋ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ::
ሊያባብላት: ሊያስፈራራትም ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው የብረት ዘንግ ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው:: መሬት ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ፈውሷት ሔደ::
አንዴ በእሳት: አንዴም በስለት: ሌላ ጊዜም በግርፋት አሰቃዩዋት:: ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቁዋት አልቻሉም:: በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ:: ወታደሮቹም ፈጸሙት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቅድስት ሶፍያን በክብር አሳረጋት:: "ስምሽን የጠራ: መታሰቢያሽን ያደረገ ምሕረትን ያገኛል" አላት::
† 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ 🕊 †
ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው:: አባቱ ዘካርያስ: እናቱ ኤልሳቤጥ: እርሱ ደግሞ ዮሐንስ ይባላል:: የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው:: የቅዱሱ ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ የተመሰከረላቸው ደጐች ነበሩ::
ዘካርያስ አርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በ ፳ [20] ዓመቱ ነበር:: በወቅቱ ከ፪ [2] አንዱን መምረጥ ነበረበት::
፩. ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል
፪. ወይ ደግሞ በክርስትናው መሞት
ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና ፪ [2] ከባባድ ነገሮችን ፈጸመ:: በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ ጣዖት ቤቶችን አወደመ:: ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኩዋንንቱ ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው::
ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር አይደለም:: ያላደረጉት ነገር አልነበረም:: እሳቱ: ስለቱ: ሰይፉ: መንኮራኩሩ . . . ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን ገፈው በእሳት ጠብሰውታል:: እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ ይሕንን ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል::
አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🕊
[ † ሰኔ ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]
፫. ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት
፬. ቅድስት ማርያ ሰማዕት
፭. ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ [ሰማዕታት
፮. ቅዱስ አሞን ሰማዕት
[ † ወርኃዊ በዓላት ]
፩፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
፪፡ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
" እንግዲሕ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: " [ማቴ.፲፥፳፮] (10:26)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤2
#እግዚአብሔርን_አምላክህን ለማመስገን ሁኔታዎችን አትጠብቅ። ጉድለቶችህን እየተመለከትክ እና ያልተሳኩልህ ነገሮችን እያየህ አታጉረምርም፣ አምላክህን #ለማመስገን በህይወት #መኖርህ
ብቻ በቂ ነው።
ምክንያቱም የዛሬን ብርሀን ያላዩት ብዙዎቹ ናቸው! ህያው እና ቅዱስ የሆንከው የዘላለም አባት ሆይ #በሀጢያትና በበደል በጨረስነው እድሚያችን ላይ ይህን ቀን ስለጨመርክልን #እናመሰግንሃለን🙏🙏🙏
#_ሰናይ_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤11🙏4👍1
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው ! ]
🕊 💖 🕊
❝ ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር አንድ ሆኖ በመስቀል ላይ በፈቃዱ በሥጋ ሞተ።
አንድ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማሕፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደ መሆኑ በሥጋ ይህንን ሥርዓት ፈጸመ። [ ፊልጵ.፪፥፭—፱ ]
ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል ፤ አይራብም ፤ አይጠማም ፤ አይደክምም ፤ አያንቀላፋም ፤ አይታመምም ፤ አይሞትም ፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል። [ኢሳ.፴ ፵ ' ፳፰ ]
ዳግመኛ በዚያ በሲዖል ተግዘው ያሉ ነፍሳትን ፡ ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወረደ። በመለኮቱም ሲዖልን በዘበዘ ዳግመኛም ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው። በአንድ ባሕርየ መለኮት ጸንተው ከሚኖሩት ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ነው። ከሰው ከነሣው ከመለኮቱም ጋር አንድ ካደረገው ከሥጋ ጋር አንድ ነው።
በአብ ዕሪናም ተቀመጠ ፤ በማሕፀን ከአደረ ጀምሮ ከተዋሐደው ከሰው ባሕርይ ከተገኘ ሥጋው ጋር አንድ ወልድ ብቻ ነውና። ይህ ሁሉ ሲሆን አልተለወጠም ያለመለየት ከወለደው ከአብ ፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር በአንድ መለኮት ትክክልነት ከጥንት ጀምሮ በነበረበት በልዑል ጌትነቱ ባሕርይ ልዕልና ያሉ መላእእክት ሁሉ አይመረምሩትም። [ ፩ቆሮ.፪፥፮ ] ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

🙏3
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ ስድስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ በመታዘዝ የሚኖር ሰው ሁለት ወጥመዶች አያገኙትም ፣ እንዲሁም ለዘላለም የክርስቶስ ታዛዥ አገልጋይ ሆኖ ይኖራል፡፡
ሰይጣን በመታዘዝ ከሚኖሩት ጋር ፣ አንዳንዴ ሰውነታቸውን በርኵሰት በማሳደፍ ፣ ልባቸውንም በማደንደን ፣ አንዳንዴ ከወትሮው በተለየ ለቍጣ እንዲነሣሡ በማድረግ ይዋጋቸዋል፡፡ በሌላም ጊዜ የደረቁና ፍሬ ቢስ ፣ በጸሎት ዳተኞች ፣ የሚናውዙና የማያስተውሉ በማድረግ ፣ መታዘዛቸው ወደ ኋላ መቅረትን ብቻ እንጂ አንዳች እንዳልጠቀማቸው በማሳሰብ ከተጋደሎ አርቆ እንዲያለቅሱ ያደርጋቸዋል፡፡
ለእኛ በጎ ይሆኑልን ዘንድ ታስቦ የተሰጡ ነገሮች ወይም በረከቶች ዘወትር ወደ ጥልቅ ትሕትና እንዲመራቸው ያስቡ ዘንድ የሚፈቅድላቸው አይደለምና፡፡
አንዳንዶች ዘወትር በመታገሥ አሳቹን አባረሩት ፤ ዳሩ ግን ገና እርሱ እየተናገረ ሳለ ሌላ መልአክ አጠገባችን ቆሞ ፣ ከጥቂትም ጊዜ በኋላ በሌላ መንገድ ሊያታልለን ይሞክራል፡፡ አንዳንዶችን በአባታቸው ምሪት ሆነው በመታዘዝ ፣ በጸጸት ፣ በየውሃት ፣ ራስን በመግዛት ፣ በቅንዓት ተመልተው ፣ ከውሳጣዊ ሁከትና ትኵሳት ነጻ ሆነው እየኖሩ ተመለከትሁ፡፡ ነገር ግን አጋንንት ወደ እነርሱ ዘንድ መጡና ለተባሕትዎ ሕይወት ብቁ እንደ ሆኑ ፣ በጽሙናም ሕይወት ከፈቃዳተ ሥጋ ነጻ መውጣትን ፣ እንደ መጨረሻ ሽልማት እንደሚያገኙት ማሰብን በውስጣቸው ዘሩባቸው፡፡
ስለዚህም ተታለሉ ፣ ወደቡን ተዉና ወደ ባሕሩ ገቡ ፣ ማዕበል በመጣባቸው ጊዜ ግን ፣ ከወደቡ አልነበሩምና በሚያሳዝን ሁኔታ በዚህ የተበከለና ጨዋማ በሆነ ውቅያኖስ ውስጥ ለአደጋ ተጋለጡ፡፡
ይህ ባሕር በፈቃደ ሥጋ ወንዞች በኩል ወደ እርሱ ገብቶ የነበረውን እንጨት ፣ ደረቅ ሣር ፣ የበሰበሰውንም ሁሉ በድጋሚ ወደ የብስ አውጥቶ ይጥለው ዘንድ በኃይል የሚናወጥና የሚነሣሣ እንዲሁም የሚቆጣ ነው፡፡ ተፈጥሮን እንመልከት ፣ በባሕር ላይ ከማዕበሉ በኋላ ጥልቅ ጸጥታ ሆኖ እናገኛለን፡፡
አንዳንዴ ለአባቱ የሚታዘዝ አንዳንዴ ደግሞ የማይታዘዝ ሰው በዓይኖቹ ላይ አንዳንዴ ቅባትን [ መድኃኒትን ] አንዳንዴ ደግም ኖራን እንደሚያደርግ ሰው ይመስላል፡፡
“አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያፈርስ የሁለቱስ ድካማቸው ምን ይጠቅማል?” ተብሎ የተነገረ ነውና፡፡ [ ሲራክ.፴፩፥፳፰ ] [ 31፥28 ] ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]

❤4🙏3
🕊
[ † እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት † 🕊
† ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው::
† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ ታግሕስጦስና ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በኋላ ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውለድ አልቻሉም::
የአሥራ ሰባት ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው:: "ሕፃኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት" አላቸው:: ብሶይ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት:: በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ:: ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ::
ከባልንጀራው ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለሃያ አንድ ዓመታት በድንግልና : በተጋድሎ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ:: ቅዱስ ብሶይ ሃያ ስምንት ዓመት በሞላው ጊዜ መልአኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ:: በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ:: ወደ እሳትም ተጣሉ:: ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ::
ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ:: ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት:: "አይዞሕ! እኔ እስከ መጨረሻው ከአንተ ጋር ነኝ" አለው::
የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው:: ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው:: መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ:: ደሙ እየወረደ ገረፉት:: በፊትና በኋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት:: ሊቀ መላእክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው::
መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው:: የቅዱሳን ሕይወት ግርም ይላል:: ተገራፊው እያለ ገራፊው : ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል::
† ይሕንን መሰለኝ አባ ጽጌ ድንግል :-
"እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ::
ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ::
እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ" ያለው::
ቅዱስ ብሶይን ከአንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት:: አካሉን ቆራረጡት:: ዓይኑን በጋለ ብረት አወጡት:: በምጣድ ቆሉት:: በጋን ውስጥ ቀቀሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ:: በነዚሕ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኳ አላቀመሱትም:: በረሃብ ቀጡት እንጂ:: ለእርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር::
በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው:: ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ [ጋን] ውስጥ ከቶ ጣለው:: የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት : ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች:: ለሃያ ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ [ቦሃ] ደረሰች:: ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል:: በክብርም አሳርፈውታል::
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ † 🕊
† ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ [ታማኝ] የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ [ጥብዐቱ] ይታወቃል:: በ ፫፻፵ [340] ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል::
በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል:: ታስሯል:: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::
† ቸር አምላክ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ እና ከቅዱስ ያዕቆብ በረከት ያሳትፈን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::
[ † ሰኔ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ብሶይ [ኃያል ሰማዕት]
፪. ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች : በስደት ያረፈች እናት ናት::]
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
፭. ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ መርቆሬዎስና ማኅበሩ [ሰማዕታት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፮. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ : ወይስ ጭንቀት : ወይስ ስደት : ወይስ ራብ : ወይስ ራቁትነት : ወይስ ፍርሃት : ወይስ ሰይፍ ነውን?
" ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን" ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " † [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]

❤4
"#እግዚአብሔር እንደተቀበለን ፣ እንዲሁ እኛም ሌሎችን መቀበል ይገባናል። እግዚአብሔር ርኅራኄ እንዳደረገልን ፣ እንዲሁ እኛም እንዲሁ ለሎች ርኅራኄን ልናደርግ ይገባናል። እግዚአብሔር እንደሸፈነን ፣ እንዲሁ እኛም ሌሎችን መሸፈን ይገባናል።"
አቡነ ሺኖዳ
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
አቡነ ሺኖዳ
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤12
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ ሰባት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ የጌታ ልጅና ታዛዥ አገልጋይ ሆይ ለመምህርህ የራስህን ኃጢአቶች የሌላ ሰው እንደ ሆኑ አድርገህ በመናዘዝ በትዕቢት መንፈስ አትታለል፡፡
ኀፍረትን ከኀፍረት በቀር በሌላ ልታመልጠው አትችልም፡፡ ወትሮም ቢሆን አጋንንት እንዳንናዘዝ ወይም የራሳችንን በደሎች የሌላ ሰው በደሎች እንደሆኑ አስመስለን እንድንናዘዝ በማድረግ ፣ ወይም ስለ በደላችን ተወቃሾቹ ሌሎች እንደ ሆኑ እንድናስብ ማባበል ልማዳቸው ነውና ሳታፍር ቍስልህን ለሐኪሙ ግልጥ ግልጥልጥ አድርገህ እያሳየህ ፣ እንዲህ በለው ፦ “አባቴ ቍስሌ ይህ ነው ፣ ይህ በገዛ ቸልታዬ የተነሣ የመጣ ደዌ [ ሥቃይ ] ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
ለዚህ ተወቃሹ የገዛ ግዴለሽነቴ ነው እንጂ ፤ ማንም ፣ ማንም ሰው ፣ ምንም መንፈስ ፣ ምንም አካል አይደለም" በለው፡፡ በኑዛዜህ አኳኋንህና በአፍአዊ አቀራረብህ እንዲሁም በአሳብህ እንደ ተፈረደበት ወንጀለኛ ምሰል፡፡ ዓይኖችህን ወደ መሬት ጣል ፣ ቢቻልህም የሐኪሙን እግር እንደ ክርስቶስ እግር ቆጥረህ በዳኛህና በሐኪምህ እግር ላይ እንባዎችህን አፍስስ፡፡ ❞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ምክረ ቅዱሳን ] 🕊
▷ " የ ል ብ ድ ን ዳ ኔ "
[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ አንተን ብቻ በደልሁ ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ፥ . . . ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። ❞
[ መዝ . ፶፩ ፥ ፩ - ፲፪ ]

❤3