#ጸሎትና_ትህትና
#ጸሎትና_ትህትና አብረው የሚያያዙ ነገሮች ናቸው። ወደ እግዚአብሔር በጸሎት መቅረብ ያለብን በትህትና ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጸሎት በተናገረበት ክፍል በሉቃ ፲፰፥፩_፲፬ ላይ ያስተማረን፥ትህትናን ከጸሎታችን ጋር #እንድናዋህድ ነው። ፈሪሳዊው ራሱን በመካብ በሌላው ላይ ጣቱን በመቀሰር #እግዚአብሔር_ሆይ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም ፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ #አመሰግንሃለሁ ፤» ይል ነበር። ፈሪሳዊው ከሌላው ለመብለጡ ማስረጃ አድርጎ ያስቀመጠው፥ ጦሙንና አሥራቱን ነበር ። #ቀራጩ ግን ወደ እግዚአብሔር የቀረበው በተለየ መንገድ ነበር ፤ #በትህትና ነበር የቀረበው፤ « ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን #ኃጢአተኛውን #ማረኝ_እያለ_ደረቱን_ይደቃ_ነበር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌውን ሲደመድም፥ ከፈሪሳዊው ይልቅ ያ #ቀራጭ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ በመናገር እንዲህ ይለናል። #ራሱን_ከፍ የሚያደርግ ሁሉ #ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።»
#_ሰናይ__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤10
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ ስምንት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ስንወድቅ አጋንንት ፈጥነው ያጠቁናል ፣ ተገቢ ባይሆንም ቅሉ ተገቢ እንደ ሆነ በማስመሰል የተባሕትዎ ሕይወትን ይዘን እንኖር ዘንድ ያሳስቡናል፡፡ የጠላቶቻችን ዓላማ በውድቀታችን ላይ ቍስልን ለመጨመር ነው፡፡
ያለ ሐኪም የተፈወሱ ጥቂት ናቸውና ሐኪሙ ይረዳህ ዘንድ ችሎታ እንደ ሌለው ሲነግርህ ፣ ቀጥሎ ወደ ሌላው ዘንድ መሄድ ይገባሃል፡፡ እንግዲያውስ ማንኛውም መርከብ የሰለጠነ ነጂው አብሮ ሳለ የስጥመት አደጋ የሚያጋጥመው ከሆነ ነጂው [ ቋትለኛው ] ሳይኖር ሲቀር ፈጽሞ ይጠፋል ብለን ስንናገር ከእኛ ጋር በመቃረን የሚያስብ ማን ነው?
ከመታዘዝ ትሕትና ይገኛል ፣ ከትሕትናም መቲረ ፈቃድ [ ፈቃድን መተው ] ይገኛል ፤ ስለ ትሕትናችን ብሎ ጌታ የሚያስበንና ከጠላቶቻችን የሚያድነን ነውና፡፡ [ መዝ.፻፴፭ ፥፳፫ ] ስለዚህ ከመታዘዝ ፈቃድን መተው ይገኛል ብለን መናገርን የሚከለክለን የለም ፣ በዚህ የተነሣ የትሕትና ግብ ተገኝቶአልና ነው፡፡ ሙሴ የሕግ መጀመሪያ እንደ ሆነ ሁሉ ትሕትናም የመቲረ ፈቃድ መጀመሪያ ነው ፤ ማርያም ምኩራብን ፍጹም [ የተሟላ ] እንዳደረገች ሴት ልጅም እናቷን ፍጹም [ የተሟላ ] ታደርጋለች፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊

🔥2❤1
🕊
[ † እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ማር ገላውዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት † 🕊
† ቅዱስ ገላውዴዎስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘ በድሮው የሮም ግዛት በአንጾኪያ [አሁን ሶርያ ውስጥ] ነው:: አባቱ አብጥልዎስ የሮም ቄሣር የኑማርያኖስ ወንድም ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ያደገው በቤተ መንግሥት ውስጥ ነው::
ወቅቱ መልካምም ክፉም ነገሮች ነበሩት:: መልካሙ ነገር በቤተ መንግሥት አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ልዑላኑ አብዛኞቹ በፍቅረ ክርስቶስ የታሠሩ ነበሩ:: ከእነዚህ መካካከል "ቅዱስ ፋሲለደስ: ቅዱሳኑ :- ፊቅጦር: ቴዎድሮስ: አባዲር: አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: እስጢፋኖስ . . ." ነበሩ:: ቅዱሳቱ "ማርታ: ታውክልያ: ኢራኢ: ሶፍያ. . ." ነበሩ::
አስቸጋሪው ነገር ደግሞ ነጋ መሸ ኑሯቸው ጦርነት ነበር:: የዘመኑ የፋርስና የቁዝ መሪዎች ጦረኞች ነበሩና ዕለት ዕለት ፍልሚያ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ገላውዴዎስ የተመሠከረለት አርበኛና የተባረከ ንጹሕ ክርስቲያን ሆኖ አድጓል:: ከልጅነቱ ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናቱ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት ታሽቷል:: እርሱ የነገሥታቱ ቤተሰብ ነው:: ማዕዱ በየዓይነቱ ሞልቶ ካልመሸ እህል አይቀምስም:: ጸሎቱ ስሙር: ስግደቱ ከምድር: አኗኗሩ በፍቅር ሆነ:: በዚያውም ላይ በድንግልናው የጸና ኃያል ነበር::
በጊዜው የቅዱስ ገላውዴዎስን ያህል መልኩ ያማረ [ደመ ግቡ] በአካባቢው አልነበረም:: ይህ ግን ሊያታልለው አልቻለም:: ሁሉ በእጁ ቢሆንም ለእርሱ ግን ብቸኛ ምርጫው ሃይማኖተ ክርስቶስ ነበር::
ቅዱስ ገላውዴዎስ ለጦርነት ወጥቶ ሲመለስ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ሃይማኖቱን ክዶ: ሕዝቡን ለጣዖት ሲያሰግድ: ክርስቲያኖችን ሲገድል ደረሰ::
† ቅዱሱ ኃያል የጦር ሰው ነውና ንጉሡን መግደል ሲችል ተወው:: በዚያ ሰሞንም ለገላውዴዎስ ሁለት ምርጫዎች ቀረቡለት :-
፩. ክርስቶስን ክዶ የንጉሡ ተከታይ መሆን:
፪. በክርስትናው ደሙን ማፍሰስ::
የቅዱሳኑ ምርጫቸው የታወቀ ነውና ታስሮ ወደ ግብጽ ተጋዘ:: በዚያ ከመኮንኑ ጋር ስለ ሃይማኖት ተከራክረው መኮንኑ ስለተበሳጨ ቅዱሱን በረዥም ጦር ጐኑን ወጋው:: ዘለፍ ብሎ ነፍሱን ሰጠ:: ሕዝበ ክርስቲያኑ በድብቅ መጥተው የቅዱሱን ሥጋ ሽቱ ቀብተው: ከዝማሬ ጋር ገነዙት:: የጓደኛው እናት ቅድስት ሶፍያ መጥታ ወደ ሶርያ ወስዳዋለች::
† ተወዳጅ: ኃያል: ቡሩክና መልካም ሰው ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት በሆነባት በዚሕች ዕለት በመላው ኦርቶዶክሳውያን ይከበራል::
† አምላካችን የቅዱሱን መንኖ ጥሪት: ትዕግስት: ጸጋና በረከት ያሳድርብን:: አሜን::
🕊
[ † ሰኔ ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት [ሕይወቱ መላእክትን የመሰለ]
፪. አንድ ሺ ሰማንያ ስምንት ሰማዕታት [የቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበር]
፫. አባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት
፬. እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮጵያዊት [የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እህት]
፭. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤቱ [ግብጽ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፫. ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፬. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
† " የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው :- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: " † [መክ. ፲፪፥፩-፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤3
በሰማይ ሰልፍ ሆነ ውጊያው ተጀመረ
#በሚካኤል ነገድ #ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
#ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በኃይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
#ዳቢሎስ አልቻለም #ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳነም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው ሀይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን ሀይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ
#ቅዱስ_ሚካኤል ከሚመጣብን
ክፉ ነገር ይጠብቀን አሜን
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#በሚካኤል ነገድ #ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
#ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በኃይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
#ዳቢሎስ አልቻለም #ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳነም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው ሀይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን ሀይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ
#ቅዱስ_ሚካኤል ከሚመጣብን
ክፉ ነገር ይጠብቀን አሜን
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤13🙏3👍1
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ከክርስቲያን ሃይማኖት የተለዩ ናቸው ! ]
🕊 💖 🕊
❝ በእግዚአብሔርነቱ ኀይል ሕያው ሲሆን ፤ ደክሞ ተሰቀለ ከሙታንም ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ዳግመኛ ሞት የለበትም ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተነሥቶ በክብር በተገለጠ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ይህ ስለእርሱ እንደ ተጻፈ ዐውቀዋልና። [ዮሐ.፪፥፳፪ ። ፪ቆሮ.፲፫፥፬ ]
በክብር ተገለጠ የተባለ መለኮት አይደለም ኵለንታ አካሉ ፥ ኵለንታ ባሕርዩ ክብር ነው እንደምን ከበረ ይባላል? ከድንግል በነሣው ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በሥጋ ከበረ ተባለ እንጂ። እንግዲህም በክብር ይገለጣል ተባለ እንጂ ወደ ሰማይ ዐርጓልና ከአብም በመተካከል ተቀምጧልና። [ዮሐ.፩፥፲፬ ፡ ፪፥፲፱ ፡ ፲፪፥፳፰ ፡ ፲፫፥፴፩-፴ ]
ሁሉን ይገዛ በሁሉ ይፈርድ ዘንድ በኋላ ዘመን ዳግመኛ በሥጋ ይመጣልና ፤ ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል ፥ በቀናች ሃይማኖት የጸኑትን ደስ ካሰኙት ከሰማዕታት ፤ ከነቢያት ከሐዋርያት ጋር ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት በክብር ያኖረዋል ፤ ውዳሴ ከንቱን በመውደድ ከሃይማኖት የወጡትን ግን ከአይሁድና ከሕግ አፍራሾ ሁሉ ጋር በገሀነም በሥቃይ ያኖራቸዋል እሊህም ወደ ዘለዓለም ኵነኔ ይሔዳሉ። [ ማቴ.፳፭፥፴፩-፵፮ ፡ ግብ.ሐዋ.፩፥፲፩ ። መዝ. ፷፪ (፷፩)፥፲፪ ። ሮሜ.፪፥፮—፲ ]
በተራበ በተጠማ በታመመ በደከመ ጊዜ መለኮት ከትስብእት ተለየ ፤ መለኮትስ ተዋሕዶት ቢሆን ድንቅ ድንቅ ሥራ በሠራ ነበር እያሉ ባለማወቃቸው ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ነው የሚሉ አሉ። እንዲህ ከቀናች ከክርስቲያን ሃይማኖት የተለዩ ናቸው ።
እኛ ግን ባለመለየት አንድ አካል ፤ አንድ ባሕርይ እንደሆነ እናምለን ፤ ግን በፈቃዱ ሥጋውን መከራ እንዲቀበል አደረገ። ሰዎች የተዋሐደው ሥጋ ምትሐት ነው ፤ እውነተኛ ሥጋ አይደለም እንዳይሉ ፤ ስለዚህም እንዲታመም አደረገው። [ ኢሳ.፶፫፥፪-፬ ። ዮሐ.፲፥፲፰ ። ሉቃ.፳፬፥፲፱-፳፩ ] ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

❤1
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ ዘጠኝ ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ሐኪሙን ለማግኘትና ከእርሱም ርዳታ ለመቀበል የሚሞክሩ ታማሚ ነፍሳት ፣ ከዚያም ደግሞ ሌላ በማማረጥ ሙሉ በሙሉ ሳይፈወሱ እርሱን የሚተዉ ፣ ቅጣቶች ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይገባቸዋል፡፡
አንተን ወደ ጌታ ካቀረበህ ከእርሱ እጅ አምልጠህ አትሩጥ ፣ ከቶም በሕይወትህ እንደ እርሱ ያለ የምታከብረው አይኖርምና፡፡ ሌላው ነፍሱን ለአደጋ ልምድ ለሌለው ወታደር ከክፍለ ጦሩ መነጠሉና በአንድ ውጊያ ውስጥ መሳተፉ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ለአንድ መነኵሴም ከነፍስ ፈቃዳት ጋር በሚደረግ ተጋድሎ ብዙ ልምድና ተሞክሮ ሳይኖረው የሚፈጸም የጽሙና [ የተባሕትዎ ] ሕይወት ሙከራ ያለ አደጋ [ አደጋ የተለየው ] አይሆንም፡፡ አንዱ ሥጋውን ያስገዛል ፣ ያጋልጣል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ፣ አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል ይላል፡፡ [ መክ.፬፥፱ ] ይኸውም ፣ ለአንድ ልጅ ከአባቱ ጋር በመሆን መለኮታዊ ኃይል በሆነው በረድኤተ መንፈስ ቅዱስ እየታገዘ ከዝንባሌዎቹ ጋር መታገል ይሻለዋል ለማለት ነው።
ከሚመራው የተለየ ዓይነ ሥውር ፣ ከእረኛው የተለየ መንጋ ፣ መንገድ መሪውን ያጣ ሰው ፣ አባቱን ያጣ ልጅ ፣ በሽተኛ ሐኪሙን ፣ መርከብም ነጂውን ፣ ካጣ ሁሉም አደጋ ላይ ናቸው፡፡ ❞

ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል +.pdf
35.6 KB
†
[ ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል ]
† † †
💖 🕊 💖
[ ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል ]
† † †
💖 🕊 💖
†
[ " ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች " ]
▪
- [ በመከራ ውስጥ ያለ የሚጸልየው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ፦ " በጠራሁህ ጊዜ ቅረበኝ ! " ]
- [ በጠራሁህ ጊዜ በምህረትና በይቅርታ ቅረበኝ ! ]
[ በሊቀ ማእምራን ቀሲስ ፕ/ሮ መምህር ዘበነ ለማ ለሰኔ ሚካኤል የተሰጠ ትምህርት ]
------------------------------------------------
❝ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: ❞ † [ራዕ.፲፪፥፯]
❝ ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።❞ [ራእ.፲፰፥፩]