Telegram Web
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


          [   ክፍል  ሠላሳ ዘጠኝ  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሐኪሙን ለማግኘትና ከእርሱም ርዳታ ለመቀበል የሚሞክሩ ታማሚ ነፍሳት ፣ ከዚያም ደግሞ ሌላ በማማረጥ ሙሉ በሙሉ ሳይፈወሱ እርሱን የሚተዉ ፣ ቅጣቶች ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይገባቸዋል፡፡

አንተን ወደ ጌታ ካቀረበህ ከእርሱ እጅ አምልጠህ አትሩጥ ፣ ከቶም በሕይወትህ እንደ እርሱ ያለ የምታከብረው አይኖርምና፡፡ ሌላው ነፍሱን ለአደጋ ልምድ ለሌለው ወታደር ከክፍለ ጦሩ መነጠሉና በአንድ ውጊያ ውስጥ መሳተፉ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ለአንድ መነኵሴም ከነፍስ ፈቃዳት ጋር በሚደረግ ተጋድሎ ብዙ ልምድና ተሞክሮ ሳይኖረው የሚፈጸም የጽሙና [ የተባሕትዎ ] ሕይወት ሙከራ ያለ አደጋ [ አደጋ የተለየው ] አይሆንም፡፡ አንዱ ሥጋውን ያስገዛል ፣ ያጋልጣል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ፣ አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል ይላል፡፡ [ መክ.፬፥፱ ] ይኸውም ፣ ለአንድ ልጅ ከአባቱ ጋር በመሆን መለኮታዊ ኃይል በሆነው በረድኤተ መንፈስ ቅዱስ እየታገዘ ከዝንባሌዎቹ ጋር መታገል ይሻለዋል ለማለት ነው።

ከሚመራው የተለየ ዓይነ ሥውር ፣ ከእረኛው የተለየ መንጋ ፣ መንገድ መሪውን ያጣ ሰው ፣ አባቱን ያጣ ልጅ ፣ በሽተኛ ሐኪሙን ፣ መርከብም ነጂውን ፣ ካጣ ሁሉም አደጋ ላይ ናቸው፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
🕊                      †                        🕊

[ እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  እንኳን ለሊቀ መላእክት አኃዜ መንጦላዕት ፣ መልአከ ኃይል ፡ ሰዳዴ ሳጥናኤል ፣ መዝገበ ርህራሄ ወሳህል ፡ መልአከ ምክሩ ለልዑል… ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ።  ]

🕊

❝ በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ❞ [ ዳን.፲፪፥፩ ]



🕊                    💖                       🕊
🙏3
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል +.pdf
35.6 KB
                       †                       


[ ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
                        †                          

[ " ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች "  ]



- [ በመከራ ውስጥ ያለ የሚጸልየው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ፦ " በጠራሁህ ጊዜ ቅረበኝ ! " ]

- [ በጠራሁህ ጊዜ በምህረትና በይቅርታ ቅረበኝ ! ]

[ በሊቀ ማእምራን ቀሲስ ፕ/ሮ መምህር ዘበነ ለማ ለሰኔ ሚካኤል የተሰጠ ትምህርት ]

------------------------------------------------

❝ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: ❞ † [ራዕ.፲፪፥፯]

ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።❞ [ራእ.፲፰፥፩]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
1
2
🕊

[ ርኅሩኁና የይቅርታ መልአክ ]

የርኅራኄ መዝገብ፣ ትሑት፣ ታዛዥና ለዘለዓለም ፈጣሪውን አመስጋኝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጌታ በሚያደርገው ቸርነት ላይ ለሰው አንድ ወገን የሚሆን መልአክ ነው፡፡ [ ሄኖ.፮፥፭ ፣ ፲፪፥፭ ፣ ፲፥፲፪ ]

⇨ Michael, one of the Holy Angels, namely the one put in charge of the best part of humankind, in charge of the nation. [ሔኖ ፮፥፭]

⇨ This first is Michael, the merciful and long-suffering without an urge to harm. [ሔኖ ፲፥፲፪]

አምላካችን እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እንደ አጥር ሆኖ የሚጠብቃቸው ፣ የመልእክት አለቃቸው ፣ ምሕረት ማድረግን የተሰጠው ፣ የክብር አክሊልን የተቀዳጀ ፣ በግርማው የተፈራ ፣ የቅዱሳን ወዳጅ ፣ የኃጥአን የምሕረት አማላጅ ፣ በብርሃን መጎናጸፍያ የሚጎናጽፍ ፣ ከክብሩ ብርሃን የተነሣ ምድርን በብርሃን የሚሞላት ፣ የቅዱሳንን ጸሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ወደ እግዚአብሔር የሚያሳርግ ፣ በትንሣኤ ዘጉባኤ የመለከት ድምጽ የሚያሰማ ፣ በሰማይ ካሉ ሁሉ በላይ በማዕረግ የከበረ ፣ ድንቅ ተአምራትን የሚያደርግ ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ቀን ያደረገውን ነገር እወቁ !

፩. በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
፪. ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
፫. ቅዳሴ ቤቱን [ ግብፅ ውስጥ ]
፬. ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
፮. ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና

† ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
6
Audio
4
4
#ሰኔ_12

ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ
#የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና #ቅዱስ_ባህራንን የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ቀን #የቅድስት_አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ፣ የተባረከና የተመሰገነ #የኢትዮጵያ_ንጉሥ_ላሊበላ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮስጦስ አረፈ፣ ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ቄርሎስ አረፈ

እ️ንኳን ለታላቁ የምሕረት ሊቀ መላእክት ፣ ሩህሩሕና ትሁቱ አባታችን
#ቅዱስ_ሚካኤል ወርኃ ሰኔ መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
19🙏1
🕊

[ እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊

በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ ቅዱስ ላሊበላ: ቅድስት አፎምያና ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ይከበራሉ::

💖

🕊 † ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት †  🕊

ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ : አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ፺፱ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን ፵ ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: [ዘፍ.፵፰፥፲፮, ኢያ. ፭፥፲፫, መሳ. ፲፫፥፲፯, ዳን. ፲፥፳፩, ፲፪፥፩, መዝ. ፴፫፥፯, ራዕይ. ፲፪፥፯] ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-

፩. በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
፪. ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
፫. ቅዳሴ ቤቱን [ ግብፅ ውስጥ ]
፬. ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
፮. ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና

††† ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::


🕊   †  ቅዱስ ላል ይበላ ንጉሥ  †   🕊

† በ፲፪ [12] ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በሃገራችን የነገሠው ቅዱስ ላሊበላ:-
- በብሥራተ መልአክ ተወልዷል
- ቅዱሳት መጻሕፍትን ገና በልጅነቱ አጥንቷል
- የንጉሥ ዘር ቢሆንም በጾምና ጸሎት: በትሕርምት አድጓል
- በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም
- ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል
- በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ ነበር
- ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት የእንጀራውን ቅርፍት [ጠርዝ] ብቻ ነበር::

በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል
- በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን [ላስታን] ገንብቷል
- ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች ናቸው::

ሥራውን ከፈጸመ በኋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ: በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ በዚሕች ቀን አርፏል:: ጌታችን ስምህን ያከበረ: ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን: ከርስተ መንግስተ ሰማያት አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

††† በረከቱን: ክብሩን ያድለን::


🕊  †  ቅድስት አፎምያ  †   🕊

ከቅዱስ አስተራኒቆስ ጋር በተቀደሰ ትዳር የኖረች
- ምጽዋትን ያዘወተረች
- በፍቅረ ቅዱሳን የጸናች
- ንጽሕናዋን ጠብቃ ሰይጣንን ያሳፈረች ደግ እናት ናት:: ዛሬ የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል ታቅፋ: በትእምርተ መስቀልም አማትባ አርፋለች: ቅዱሱ መልአክም ወደ ገነት አሳርጓታል::

🕊  †  ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ  †  🕊

የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ:
- በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ:
- በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ:
- በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ:
- ምጽዋትን ያዘወተረ: አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
- በዚህች ቀን አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

† አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ በረከት ይክፈለን:: አሜን:: †

🕊

[ † ሰኔ ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፫. ቅድስት አፎምያና ባለቤቷ ቅዱስ አስተራኒቆስ
፬. ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
፭. ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሊቅ
፮. አባ ዮስጦስ ሊቀ ዻዻሳት [የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ደቀ መዝሙር]
፯. አባ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ድሜጥሮስ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ሰማዕት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፮. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: † [ራዕይ.፲፪፥፯] (12:7)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2🙏2
4
#ሚካኤል_ሆይ በጠላት ተማርከው
ለሚጨነቁትና ለሚሰቃዩት ዋስ
ጠበቃቸው አንተ ነህና በእኔ ላይ
የሚተበትቡትን የጠላቶቼን የምክር
መረብ በጣጥሰህ ጣልልኝ ነፍሴንም
ስጋዬንም ለአንተ አደራ #ሰጥቼሀለሁና

#ኃያሉ_ሚካኤል_ሆይ ኃይልህን የሰው
ኃይል ሊተካከለው አይችልምና
እንግደለው እናጥፋው የሚሉትን
ጠላቶቼን ጭጋግ በቀላቀለ በዓዉሎ
ንፋስ በትናቸው።🙏

#_መልካም__በዓል 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
16🙏3
🕊   🕯🕯🕯    💖    🕯🕯🕯   🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

🕊

❝ የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው ሚካኤል ሆይ ፦ ሰላም ላንተ ይሁን ፡ ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡

ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አዳኝነትህን በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሠውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡

በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ ፤ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪ ፊት ሰግደህ እኛ ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘላለሙ አሜን፡፡ ❞

[ መልክአ ሚካኤል ]

🕊  🕯🕯🕯    💖    🕯🕯🕯   🕊
3
2
2025/07/13 18:17:42
Back to Top
HTML Embed Code: