Telegram Web
                          †                           

[     የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት    ]

       
🕊  በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊
             
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል። " [መዝ.፴፬፥፯]

🕊

" ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ " [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
2🥰2🙏2
Audio
3
9
🕊

[ † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊 †  ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት  †  🕊

† ቅዱስ ገብርኤል :-

- በራማ ከሚኖሩ ሊቃናት አንዱ::
- አርባብ በሚባሉ አሥር ነገዶች ላይ አለቅነትን የተሾመ::
- የስሙ ትርጓሜ "እግዚእ ወገብር" [ጌታና አገልጋይ] አንድም "አምላክ ወሰብእ" [የአምላክ ሰው መሆን] ማለት የሆነ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ያረጋጋ::
- ብርሃናውያን መላእክትን የሚመራ::
- በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብሣሪነቱ በስፋት የተነገረለት::
- በተለይ ደግሞ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ዜና ይሸከም ዘንድ ያደለው::
- ከድንግል ማርያም ጎን በፍጹም የማይርቅ::
- በፈጣን ተራዳኢነቱ ብዙ ቅዱሳንን ያገለገለ ታላቅ ቀናዒ መልአክ ነው::

በዚሕች ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ባቢሎን ልኮታል:: ሊቀ መላእክት ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስቱ ጥርስ እንዳዳነው መጽሐፍ ነግሮናል::

ይልቁኑ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል የተማረኩ ወገኖቹን መመለስ እያሰበ በሃዘን ሲጸልይ በዚሕ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ዳስሶታል:: ባርኮታል:: አጽናንቶታል:: ለዳንኤል በዋነኛነትም ሦስት ምሥጢራትን ገልጾለታል:-

፩. የቤተ እሥራኤልን ከሰባ ዘመን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ::

፪. የክርስቶስን ሰው መሆንና መሞት::

፫. የሐሳዌ መሲሕን በመጨረሻ ዘመን መምጣት ነግሮታል:: ስለዚህም እኛ ቅዱስ ገብርኤልን እንድናከብረው : በጸሎትም እንድንጠራው አባቶቻችን አዝዘውናል::

🕊 † አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም †  🕊 

† ጻድቁ ሃገራቸው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ሲሆን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ባልንጀራ ናቸው:: ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በክርስትና አድገው : ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው ወደ ገዳም መንነዋል::

ከታላቁ ኮከበ ገዳም አባ ኢላርዮን ሥርዓተ መነኮሳትን አጥንተው አባ ኤስድሮስን በረድዕነት አገልግለዋል::

ከብዙ ዓመታት ትሕርምትና ገዳማዊ ሕይወት በኋላ የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል:: በጵጵስናቸው ዘመን አንድ ከባድ ስሕተት ሠርተው ነበር::

እርሱም ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ከምእመናን የተሠበሠበውን ገንዘብ ለግል ጉዳያቸው አውለው ልብሳቸውና ቤታቸው ወርቅ በወርቅ ሆኖ ነበር:: ፈጣሪ ግን ይሕንን ብክነት ከእርሳቸው ያርቅ ዘንድ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ላከው::

እርሱም በምክንያት ከቆጵሮስ ኢየሩሳሌም ገባ:: ጓደኛ ናቸውና አሳምኖ የወርቅ ንብረቶቹን ሁሉ ወሰደ:: ለነዳያንም ሰጣቸው:: አባ ዮሐንስ ሊቁን "እቃየን ካልመለስክ" ብለው ቢይዙት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸልዮ ዐይናቸው እንዲታወር አደረገ:: አንዳንዴ የታወረ ልብ የሚገለጠው እንዲሕ ነውና::

በደቂቃዎች ልዩነት ዐይነ ስውር የሆኑት አባ ዮሐንስ አለቀሱ:: ሊቁንም "ራራልኝ : አማልደኝ?" አሉት:: እርሱም ጸልዮ አንድ ዐይናቸውን ብቻ አበራላቸው:: "ለምን?" አሉት:: "ተግሳጽ ነው" አላቸው::

ከዚያች ቀን በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ልቡናቸው ተመለሱ:: ቤታቸውን ገዳም አደረጉት:: በሚደነቅ ቅድስና : ፍቅርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ምዕመናንን አገልግለው በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል::

† የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት : የአባ ዮሐንስ በረከት አይለየን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ወደ ዳንኤል የወረደበት]
፪. አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፫. አባታችን ቃይናን [ከአዳም አራተኛ ትውልድ]
፬. አባ ማትያን ጻድቅ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫. ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

" . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም: ተናገረኝም:: እንዲህም አለ :- "ዳንኤል ሆይ! ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ::" † [ዳን. ፱፥፳-፳፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
7
#ነገ ለአንተ የተሸለ ነው"

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ #ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ #ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ #መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ #ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡
ቅዱሳን #ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ #ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም #ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት #ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።
ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ #ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!
(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)

         #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11🙏8👍1
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

[ †  እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 † አራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት † 🕊

፬ [4] ቱ ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ ስማቸው አባ አክራ አባ ዮሐንስ : አባ አብጥልማ እና አባ ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት [ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው]  ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው::

ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ እየተቀበሉ : ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ::

በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ::

በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ::

አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን
አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ዐውደ ስምዕ] አደረጉ::

በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ:: በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ ድፍረት ነበር::

መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም: በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል::

የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን አበው ሰማዕታት [አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ አብጥልማ: አባ ፊልዾስ]

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [ የእግዚአብሔር ሰው ]
፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት

" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። " [ዕብ.፮፥፲-፲፫] (6:10-13)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
4
#ሰውን_የሚጥለው_መመካቱ_ነው

#ወንድሜ ሆይ በሥራህ ሁሉ የታመንህ ሁን አገልጋይ ባልንጅሮችህን ውደዳቸው። ንጹሑን አረጋዊ መቼም መች አክብረው።

#ወንድሜ ሆይ በታላላቆች መሃል አትቀመጥ። ተቀመጥ እስኪሉህ ድረስ ቁም እንጅ በሽማግሌዎች መካከል አትቀመጥ፤ በዝቀተኛው ማዕርግ ተቀመጥ እንጅ።

#ወንድሜ ሆይ ቁጡ ወይም አንጎራጓሪ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ሐኬተኛ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ምንም ተግባር ለመፈጸም ወዲያና ወዲህ አትናወጽ። እንዳትዋረድ በሊቅ በአዋቂ መሃል አትናገር።

#ልጄ ሆይ በጽድቅህ አትመካ፤ ራስህን አታመስግን፤ ሰይጣን ትምክሕትን እንዳያመጣብህ ራስህን በፈቃድህ አዋርድ እንጅ። በትዕቢትና ትምክሕት ሰዶምና ገሞራ ወደቁ። ከእግዚአብሔር መንገድም ተሰናከሉ። ትምክሕተኛውን መነኩሴ ፈተና ያገኘዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ይለየዋል፤ የዲያብሎስ መንፈስም ያድርበታል። በሥራችሁ ሁሉ አትመኩ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ይሠራል እንጅ ከራሱ የሆነ ምንም የለምና። ነቢይ የተናገረውን አልሰማችሁምን? ፈጽማችሁ አትመኩ ታላላቅ ነገርንም አትናገሩ፤ ክፉ ነገርም ከአንደበታችሁ አይውጣ።

             #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
10
🔔

በነገራቸው ላይ 🤔

በየሥፍራው የምናየው ምዕራባዊውና ፕሮቴስታንታዊው የአነቃቂ ተናጋርያን የሞቲቬሽናል ስፒከርስ [ Motivational Speakers ] መቀላመድ ከኦርቶዶክሳዊ የነገረ ሃይማኖትና የመንፈሳዊ ሕይወት ትምህርት ጋር ምንም ዓይነት አንድነት የለውም።

ምዕራባዊው የሥነ-ልቦና ዘባተሎ ዓላማ ነገረ ሃይማኖትን ማስረሳት ፣ ከቅዱሳን የንጽሕና የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት መለየትና በመጨረሻም ወደ ፕሮቴስታንቱ የጥፋት ባህር መጨመር ነው። በሚያስገርም ሁኔታ አካሄዱ የራሱን ደረጃዎች ጥብቆ በሂደት ሊያሳካ የሚፈልገውን ድብቅ ዓላማ ለማሳካት የሚሞክር የተንኮል አካሔድ ነው። የሰይጣን የምንግዜም ዓላማ ቤተክርስቲያንን በማስረሳትና መንገዷንም በማጥፋት ሰውን ወደ ስህተት አቅጣጫ ወስዶ ከሕይወት መለየት ነው።


" እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም ፥

ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ ፤ " [ ኤፌ. ፬ ፥ ፲፬ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
7
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
             [     ክፍል ስምንት    ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
1
1
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊

[ †  እንኩዋን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ
የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 † ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት † 🕊

ቅዱስ ሚናስ [ ማር_ሚና ] በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር ፹ [80] ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው::

አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ [ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው] :-

- በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ
- በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ
- በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ
- ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ
- በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው::

እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::

የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም::

ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች::

ቅዱስ ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል::

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሚናስ [ማር ሚና] ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
፫. ቅድስት እንባ መሪና
፬. ቅድስት ክርስጢና

" ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይሕን እጽፍልሃለሁ:: ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ:: ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔርንም የመምሠል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው:: " [፩ጢሞ.፫፥፲፬] (3:14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
4
2025/07/09 14:38:05
Back to Top
HTML Embed Code: