Telegram Web
ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው ፤ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ፤ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
፤ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
ወ.ሮ ሰዎች ምዕ. 8፣36_39

          
#_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
6😢4🙏3👍1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

     [   ትንሣኤውንም እናምናለን  !    ]

🕊                    💖                       🕊


❝ እኛ ግን የዳንበትን አዳኛችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ሕማሙን በፈቃዱ ስለእኛ በሥጋ ያደረገውን ሞቱን እናስተምራለን ፤ ትንሣኤውንም እናምናለን ወደ ሰማይ ማረጉንም እናስተምራለን ፤ በሙታን በሕያዋን ይፈርድ ዘንድ የሚመጣበትን ዳግመኛ ምጽአቱን ፤ እርሱ የሚያወርሳት ለዘለዓለም የማታልፍ መንግሥተ ሰማያት እንዳለች እናምናለን። [ ማቴ.፲፥፳፰-፮ ። ግብ.ሐዋ.፩፥፲፩ ]

በኦሪት የተጻፈውን ቃል ምክንያት አድርገው ለእግዚአብሔር ቀድሞ ሥጋ እንደ ነበረው የሚናገሩ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰውን በእኛ አምሳል እንፍጠር አለ በእኛ አምሳል ያለውም ስለሰው ሥጋ ነው የሚሉ አሉ። [ዘፍ.፩፥፳፮ ]

ነገር ግን እንዲህ አይደለም እርሱ ስለ ውሳጣዊ ሰውነታችን [ ነፍስ ] ተናገረ እንጂ እርሱ ሁልጊዜ በመታደስ ጸንቶ ይኖራልና። አፍአዊ ሰውነታችን [ ሥጋ ] ይሞት ዘንድ እስኪነሣ ድረስም ይፈርስ ይበሰብስ ዘንድ እንዳለው ነገሩ የታወቀ ነው ፤ ውሳጣዊው ግን አይሞትም አይፈርስም አይበሰብስም። [ ፪ቆሮ.፬፥፲፮ ]

የበቃ ቢሆን ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስዱታል ፤ መውጣት ሳይኖር ሁል ጊዜ በዚያ ይኖራል።የበቃ ባይሆን ግን ወደገሀነም ይወስዱታል ፤ ፍጻሜ ሳይኖረው ለዘለዓለም በዚያ ይኖራል። [ ማቴ.፳፭፥፵፮ ]

ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ በጎ ሥራን ቢሠራ እግዚአብሔርን እንደሚመስል እግዚአብሔር ገልጦልን ይኸን ቃል እንተረጕማለን ፤ ምድራዊ አዳምን መምሰል ገንዘብ እንደ አደረግን ሰማያዊ ክርስቶስን መምሰልን ገንዘብ እናደርጋለን ተብሎ እንደ ተጻፈ። [ ፩ቆሮ.፲፭፥፮-፵፱ ]

ውሳጣዊ ሰውነት ግን የማይለወጥ ዕውቀት ያለው ነፍስ ነው ፤ ዳግመኛም እግዚአብሔር በሥጋ ተሰውሮ ያለ ነፍስን በቸርነቱ እግዚአብሔርን የሚመስል አድርጎ ፈጠረው ፤ እግዚአብሔር ጥንቱን ሥጋ አይደለምና አይወሰንምና ጌታ እሳት ነው ፤ ብርሃንም ነው ፤ ማንም ማን አይቀርበውም ፤ ሕሊናም መርምሮ አያገኘውም አይመረመርም ከላይ ሆኖ ሰማይን ፡ ይሸፍናል ፤ ከታች ሆኖ ምድርን ይሸፍናል።

ፍጥረት ሁሉ ፤ ሰማያት በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ፤ ምድርም ፤ በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ ከብቱም አውሬውም ሁሉ የሚንቀሳቀሱትም ወፎችም ፤ የምድረ በዳ ዛፎችም ሁሉ ባሕርም ፤ ፈሳሾችም በውስጣቸውም ያሉ ሁሉ በእርሱ ጸንተው ይኖራሉ መጽሐፍ እንደ ተናገረ ሁሉም በእርሱ ተፈጥሮአልና። [ መዝ.፻፵፰፥፩—፲፬ ። ዮሐ.፩፥፫ ቆላ.፩፥፲፭-፲፰ ] ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
🕊                    💖                       🕊


[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ ! ]

❝ ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እም ኩሉ ሕዝብ ❞

[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። ] [አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

" በመላእክት ፊት እዘምርልኻለሁ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ። "  [መዝ.፻፴፯፥፪ ]

🕊                    💖                       🕊

ቤተ ክርስቲያንን  “ ቅድስት ” አላት ስለምን ቢሉ ?

የቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና ፤ አንድም ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ አክብሯታልና። አንድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለምእመናን ይሰጥባታልና፡፡ አንድም በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና።

“ ማኅደረ ስብሐት ” [ የምስጋና ማደሪያ ] አላት ፦

የልዑል እግዚአብሔር ምስጋና በጸሎተ ኪዳን ፣ በስብሐተ ነግህ ፣ በጸሎተ ቅዳሴ ፣ በማሕሌት ፣ በሰዓታት ፣ በሰባቱ ጊዜያት ኹሉ ይነገርባታልና።

“ የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] ” አላት ፦

የመንግሥቱ ወንጌል በሚነገርበት ፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጸለዩትን ጸሎት ለማሳረግ በቀን ስድስት መቶ በሌሊት ስድስት መቶ መላእክት ይጠብቋታልና።

“ እመ ኵሉ ሕዝብ ” የሕዝብ ኹሉ እናት ይላታል ፦

እናት ልጆቿን እንድታሳድግ ፣ እንድትጠብቅ ፣ ወደ ቀና ጐዳና መርታ እንድታደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ይልቁኑ በሥጋውና በደሙ እናድግባታለን ፤ በርቱዕ ትምህርቷ ከክሕደት እንጠበቅባታለን ፤ በመጨረሻም ወደ አምሳያዋ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መርታ ታደርስናለችና። [ ገላ.፬፥፳፮-፳፯ ] ❞

🕊   †   በዓለ ሕንጸታ    †    🕊


💖                   🕊                   💖
2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷ " ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ! "


[    💖    አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ    💖     ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ፥ አቤቱ ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ ?

ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ። ❞

[  መዝ . ፵፪ ፥ ፩ - ፫  ]


🕊                       💖                     🕊
4
2
ሰኔ____21

እንኳን
#ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሰኔ ጐልጐታና ሕንጸተ ቤተ ቤተክርስቲያን (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችኹ

#ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏😢😢
ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው
#ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ #የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም #ቃል_ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ።
#ድንግል_ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን
የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው
#በልጅሽ ፈት ቁሚልን ።

#እናታችን__ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ።
ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ
#በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ #እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ።
ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው። ደምህ ይጋርደን
#ሐጢአታችንን_አታስብብን

የእናታችን እረድኤት በረከት ፍቅር አይለየን አሜን
🙏🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
18
†                       †                         †

[ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሰን ፥ አደረሳችሁ ! ]


🕊 ሰኔ ጎለጎታ 🕊

💖

" ምሕረትን የምትለምኚ ድንግል እናቱ ፤
አንድያው ልጅሽ አያጥፋን በከንቱ ! "

"በእንቲአነ በሊዮ ሰአሊተ ምሕረት እሙ ፤
ኢታማስን ግብረ እዴከ እንተ ለሐኮ ቀዲሙ ! " [ አርኬ ]

[ ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭. ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
፮. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር [ሰማዕት]
፱. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
               †               

[ ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ ]

" አባቱን የሚረግም ፥ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ። ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ። ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት ፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።" [ ምሳ.፴፥፲፩]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
4
🕊 

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  ✞ 

🕊    እንኳን አደረሳችሁ     🕊

† ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   †

ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ::

ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት ፪ [2] ነገሮችን አሳየ :-

፩. አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::
፪. ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት [ፓትርያርክ] ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ ፫ [3] ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ
"ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት"እንደ ማለት ነው::

ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ::

¤ አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:
¤ ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:
¤ ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:
¤ ሐዋርያት ድንግልን ከበው:
¤ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::

በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው::
"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር
ዐረገ::

🕊  † ሰኔ ጐልጐታ  † 🕊

ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል:: ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን
"ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው:: ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::

እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ [መግደሉ] ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች::

ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . . የገደልኩሽ እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው::

እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::

ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭. ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
፮. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር [ሰማዕት]
፱. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት

[ † ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ አበው ጎርጎርዮሳት
፪፡ አባ ምዕመነ ድንግል
፫፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
፬፡ አባ አሮን ሶርያዊ
፭፡ አባ መርትያኖስ
፮፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል

" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] (62:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
Audio
👍1
9
እናቴ ማርያም

"#የኃጢአቴ ቁስል ያላንቺ ጸሎት እንዳይድን ልዑል እግዚአብሔር ያውቃልና፣ #ኃጢአቴ ከዓለም ሁሉ ኃጢአት እንዲበልጥ ተረዳ፣ ንጽሕናሽ ደግሞ ከቅዱሳን ሁሉ ንጽሕና #እንዲበልጥ እንዲበዛ ዐወቀ። ስለዚህም #ፍቅርሽን በልቡናዬ ጨመረ። ጽኑ ቁስል ያለ ጽኑ ዕፁብ ድንቅ መድኃኒት እንዳይጠግ ያውቃልና።

...የእግዚአብሔር የጥበቡ ርቀት ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ? ...ደግነቱና ይቅርታውንስ ማን ይናገራል
#በኃጢአት ቁስለኞች ፊት መድኃኒት አዘጋጀ። ተቀብተው በእርሱ እንዲድኑ ነው።

ድንግል ሆይ፤ የእኔን አመንዝራነቴን እናገራለሁ ያንቺን ንጽሕና የልጅሽኝ ቸርነት
#አወራለሁ። ድንግል ሆይ የኔን ስሕተት ያንቺን ማማለድ የልጅሽንም መታገስ #እናገራለሁ። ድንግል ሆይ የኔን ስንፍና ያንቺን ምክር የልጅሽንም ይቅርታ እናገራለሁ።"

የፍቅሯ ኃይል ካረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአንደበቱ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የልመና ቃል
(አርጋኖነ ማርያም ዘአርብ
)

             #መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
16
†                       †                         †

እንኳን አደረሳችሁ !

🕊   ማርያም ድንግል   🕊

•  እኅቶሙ ለመላእክት ፣
•  ወለቶሙ ለነቢያት ፣
•  ሞገሶሙ ለሐዋርያት ፣
•  እሞሙ ለሰማዕታት ፣
•  ተስፋ መነኮሳት ፣
•  ደብተራ ፍጽምት
•  አክሊል ንጹሕ ለካህናት ፣
•  ወላዲተ አምላክ ንጽሕት፣

°  መጽደቂቶሙ ለኀጥአን ፣
°  ናዛዚቶሙ ለኅዙናን ፣
°  ፈዋሲቶሙ ለሕሙማን !


🕊                      💖 🕊
2
2025/07/09 19:49:46
Back to Top
HTML Embed Code: