🕊 💖 🕊
[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ ! ]
❝ ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እም ኩሉ ሕዝብ ❞
[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። ] [አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]
" በመላእክት ፊት እዘምርልኻለሁ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ። " [መዝ.፻፴፯፥፪ ]
🕊 💖 🕊
ቤተ ክርስቲያንን “ ቅድስት ” አላት ስለምን ቢሉ ?
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና ፤ አንድም ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ አክብሯታልና። አንድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለምእመናን ይሰጥባታልና፡፡ አንድም በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና።
“ ማኅደረ ስብሐት ” [ የምስጋና ማደሪያ ] አላት ፦
የልዑል እግዚአብሔር ምስጋና በጸሎተ ኪዳን ፣ በስብሐተ ነግህ ፣ በጸሎተ ቅዳሴ ፣ በማሕሌት ፣ በሰዓታት ፣ በሰባቱ ጊዜያት ኹሉ ይነገርባታልና።
“ የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] ” አላት ፦
የመንግሥቱ ወንጌል በሚነገርበት ፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጸለዩትን ጸሎት ለማሳረግ በቀን ስድስት መቶ በሌሊት ስድስት መቶ መላእክት ይጠብቋታልና።
“ እመ ኵሉ ሕዝብ ” የሕዝብ ኹሉ እናት ይላታል ፦
እናት ልጆቿን እንድታሳድግ ፣ እንድትጠብቅ ፣ ወደ ቀና ጐዳና መርታ እንድታደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ይልቁኑ በሥጋውና በደሙ እናድግባታለን ፤ በርቱዕ ትምህርቷ ከክሕደት እንጠበቅባታለን ፤ በመጨረሻም ወደ አምሳያዋ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መርታ ታደርስናለችና። [ ገላ.፬፥፳፮-፳፯ ] ❞
🕊 † በዓለ ሕንጸታ † 🕊
💖 🕊 💖

❤2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ምክረ ቅዱሳን ] 🕊
▷ " ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ! "
[ 💖 አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
-------------------------------------------------
❝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ፥ አቤቱ ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ ?
ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ። ❞
[ መዝ . ፵፪ ፥ ፩ - ፫ ]

❤4
ሰኔ____21
እንኳን #ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሰኔ ጐልጐታና ሕንጸተ ቤተ ቤተክርስቲያን (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችኹ
#ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏😢😢
ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው #ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ #የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም #ቃል_ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ።
#ድንግል_ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን
የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው #በልጅሽ ፈት ቁሚልን ።
#እናታችን__ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ።
ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ #በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ #እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ።
ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው። ደምህ ይጋርደን #ሐጢአታችንን_አታስብብን
የእናታችን እረድኤት በረከት ፍቅር አይለየን አሜን 🙏🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤18
† † †
[ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሰን ፥ አደረሳችሁ ! ]
🕊 ሰኔ ጎለጎታ 🕊
💖
" ምሕረትን የምትለምኚ ድንግል እናቱ ፤
አንድያው ልጅሽ አያጥፋን በከንቱ ! "
"በእንቲአነ በሊዮ ሰአሊተ ምሕረት እሙ ፤
ኢታማስን ግብረ እዴከ እንተ ለሐኮ ቀዲሙ ! " [ አርኬ ]
[ ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭. ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
፮. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር [ሰማዕት]
፱. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
†
[ ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ ]
" አባቱን የሚረግም ፥ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ። ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ። ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት ፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።" [ ምሳ.፴፥፲፩]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊
† ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ::
ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት ፪ [2] ነገሮችን አሳየ :-
፩. አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::
፪. ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት [ፓትርያርክ] ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ ፫ [3] ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ
"ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት"እንደ ማለት ነው::
ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ::
¤ አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:
¤ ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:
¤ ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:
¤ ሐዋርያት ድንግልን ከበው:
¤ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው::
"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር
ዐረገ::
🕊 † ሰኔ ጐልጐታ † 🕊
ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል:: ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን
"ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው:: ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::
እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ [መግደሉ] ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች::
ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . . የገደልኩሽ እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው::
እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::
ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::
🕊
[ † ሰኔ ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፭. ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
፮. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፯. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፰. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር [ሰማዕት]
፱. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርኃዊ በዓላት ]
፩፡ አበው ጎርጎርዮሳት
፪፡ አባ ምዕመነ ድንግል
፫፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
፬፡ አባ አሮን ሶርያዊ
፭፡ አባ መርትያኖስ
፮፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] (62:1-3)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

❤3
እናቴ ማርያም
"#የኃጢአቴ ቁስል ያላንቺ ጸሎት እንዳይድን ልዑል እግዚአብሔር ያውቃልና፣ #ኃጢአቴ ከዓለም ሁሉ ኃጢአት እንዲበልጥ ተረዳ፣ ንጽሕናሽ ደግሞ ከቅዱሳን ሁሉ ንጽሕና #እንዲበልጥ እንዲበዛ ዐወቀ። ስለዚህም #ፍቅርሽን በልቡናዬ ጨመረ። ጽኑ ቁስል ያለ ጽኑ ዕፁብ ድንቅ መድኃኒት እንዳይጠግ ያውቃልና።
...የእግዚአብሔር የጥበቡ ርቀት ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ? ...ደግነቱና ይቅርታውንስ ማን ይናገራል #በኃጢአት ቁስለኞች ፊት መድኃኒት አዘጋጀ። ተቀብተው በእርሱ እንዲድኑ ነው።
ድንግል ሆይ፤ የእኔን አመንዝራነቴን እናገራለሁ ያንቺን ንጽሕና የልጅሽኝ ቸርነት #አወራለሁ። ድንግል ሆይ የኔን ስሕተት ያንቺን ማማለድ የልጅሽንም መታገስ #እናገራለሁ። ድንግል ሆይ የኔን ስንፍና ያንቺን ምክር የልጅሽንም ይቅርታ እናገራለሁ።"
የፍቅሯ ኃይል ካረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአንደበቱ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የልመና ቃል
(አርጋኖነ ማርያም ዘአርብ)
#መልካም__ቀን🙏

❤16
†
[ ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ ! ]
🕊
❝ ካይንሽ የፈሰሰው የዕንባ ጎርፍ : በፊትሽም የተንጠባጠበው በልጅሽ በወዳጅሽ ፊት ይቁም፡፡ የሠራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ ፥ አዕምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ:: የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ ሰዓት እንኩዋን ሃጢዓት ለመስራት አላቁዋረጥሁም፡፡
በሰውና በመላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ፡፡ በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ፡፡ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፡ ፍዳ የተነሳ የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ::
ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትችይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ:: ዘወትርም ከእኔ እንዳትርቂ አወቅሁ:: እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼም አይደለም በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በዕደ ሕሊና ያዝሁሽ በዕደ ሥጋ አይደለም::
እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ ፥ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡ ❞
[ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]