Telegram Web
2
#የምንሰጠው_ሌላው_ስለሚያስፈልገው_ነው!

አንድ ሰው እንዲህ አለ "መስጠትን ተምሬያለው ተርፎኝ ሳይሆን
#ማጣትን_ስለማውቀው ነው!" በእርግጠኝነት በአንድም በሌላም አጋጣሚ መራብን የማያውቅ ሰው የለም! የተራበን ሰው የሆነ ምግብ ስትሰጠው ምን ሊሰማው ይችላል? ብርዱ ያሰቃየውን ሰው ልብስ ስትደርብለት እንዴት አድርጎ ይደሰት! ታድያ የዚህ #ደስታ_ምንጭ ከመሆን በላይ በዚህ ምድር ምን ትልቅ ነገር ይገኛል! የተረፈህ ስለሆንክ ስለሞላህ አይደለም ግን #ስለሚያስፈልጋቸው ጥቂቷን ስጥ እና #ብዙ_ተደሰት ወንድሜ እህቴ አንቺም ካለችሽ አጉርሺ ስለሚመልሱልሽ ሳይሆን #ስለሚያስፈልጋቸው ነው!

#_ሰናይ__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
10🙏1
                        †                           

🕊    💖  ቅዱስ ታዴዎስ  💖    🕊

                         🕊                        

❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞

[ ተአምኆ ቅዱሳን ]


[ 🕊 እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  🕊 ]


🕊                        💖                       🕊
🙏1
7
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  "ድል መንሳትና የአሸናፊነት ሕይወት!"


[    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ ነገር ግን ሞት ቢሆን ፥ ሕይወትም ቢሆን ፥ መላእክትም ቢሆኑ ፥ አለቆችም ቢሆኑ ፥ ያለውም ቢሆን ፥ የሚመጣውም ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደማይችል አምናለሁ።

ኃይልም ቢሆን ፥ ከፍታም ቢሆን ፥ ዝቅታም ቢሆን ፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል የለም። ❞

[  ሮሜ . ፰ ፥ ፴፰  ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                       †                        



[      የእግዚአብሔር ፍቅር  !       ]




🕊                        💖                     🕊
4
#መልካም_አድርግና_እርሳው...

ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት
#ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም #እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

#መልካም ስታደርግ በምላሹ #መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።

እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።

#መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
11
🕊

[ † እንኳን ለዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †


🕊   †  ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ  †    🕊

†  ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " ዓምደ ሃይማኖት የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ [ግብጽ] በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ አባ ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::

ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::

ከዚያም በ፬፻፲፪ [412] ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም ፳፬ [24] ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::

በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" [ሎቱ ስብሐት!] የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ ፪ የከፈለው እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: [ላቲ ስብሐት!]

ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ [የቁስጥንጥንያ ንጉሥ] ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ፬፻፴፩ [431] ዓ/ም በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና ፪፻ [200] ቅዱሳን ሊቃውንት ተገኙ::

የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር [ቅዱስ] ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: ድንግል ማርያምም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::

የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት ፲፪ [12] አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::

† ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም "ታኦዶኮስ [የእግዚአብሔር እናቱ] ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን :-

¤ የአምላክ እናት:
¤ ዘላለማዊት ድንግል:
¤ ፍጽምት:
¤ ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::

ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::

እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች:: ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ፴፪ [32] ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ፬፻፵፬ [444] ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::

† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::

🕊

[ † ሐምሌ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ዓምደ ሃይማኖት]
፪. ቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ [ታላቅ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት]
፫. አባ ሉቅያስ ኤዺስ ቆዾስ

†  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

" የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና:: " † [ዕብ.፲፫፥፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
                       †                            

†    🕊    ቅዱስ ቄርሎስ    🕊    †


❝ ቅዱስ ቄርሎስ መላ ዘመኑን ከጥፋት ተራሮች ጋር እየተዋጋ አሳለፈ።

ስለዚህም ምክንያት ቤተክርስቲያን ስላከበራት ፤ ከፍ ከፍ ስላደረጋት ፤ አንድነቷ እንዲጠበቅ ስላደረገላት " በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር እንዳይቻላት" የዚህን ታላቅ አባት ሥራ ዘወትር ታስታውሳለች። ❞

[ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ መግቢያ ]


🕊                        💖                     🕊
🙏2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷     "  ከሐጢዓት ስለመውጣት  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[           🕊      🕊              ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬


❝ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።

ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም ፤ ❞

[  ዕብ . ፮ ፥ ፲፪ - ፫  ]



🕊                       💖                   🕊
🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                         †                         


❝ እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።

የልቤ ችግር ብዙ ነው ፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ። ድካሜንና መከራዬን እይ ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ። ❞

[  መዝ . ፳፭ ፥ ፲፮   ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
6🙏2
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[ ✞ እንኳን ለአባቶቻችን ቅዱሳን ፲፪ [ 12 ] ቱ ደቂቀ ነቢያት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]


🕊 ✞ ፲፪ [12] ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት ✞ 🕊

ነቢይ ማለት ከእግዚብሔር ተመርጦ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን] : መጻዕያትን [ለወደፊቱ የሚደረገውን] የሚያውቁ ሰዎች ሲሆኑ ሕዝቡን እንዲመሩ: እንዲገስጹም ይላካሉ:: ሕይወታቸውም በቅድስና የተለበጠ ነው:: ነቢያትን በቁጥር መግለጽ ከባድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን እንድንረዳቸው እንዲህ ትከፍላቸዋለች::

=>  በኩረ ነቢያት አዳም
=>  ሊቀ ነቢያት ሙሴ
=>  ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ
=>  ልበ አምላክ ዳዊት
=>  ፲፭ [15] ቱ ነቢያት [ከአዳም ጀምሮ እስከ ሳሙኤል]

=> ፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት [ኢሳይያስ: ኤርምያስ: ሕዝቅኤልና ዳንኤል]

፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት ደግሞ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ያሉት ናቸው:: በዚህች ቀን ታዲያ ፲፪ [12] ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት በአንድነት ይታሠባሉ:: እነዚህም :-

፩. ቅዱስ ሆሴዕ [ኦዝያ]
፪. ቅዱስ አሞጽ
፫. ቅዱስ ሚክያስ
፬. ቅዱስ ኢዩኤል
፭. ቅዱስ አብድዩ
፮. ቅዱስ ዮናስ
፯. ቅዱስ ናሆም
፰. ቅዱስ እንባቆም
፱. ቅዱስ ሶፎንያስ
፲. ቅዱስ ሐጌ
፲፩. ቅዱስ ዘካርያስ እና
፲፪. ቅዱስ ሚልክያስ ናቸው::

ቅዱሳኑ ደቂቀ ነቢያት የተባሉት

፩. የነቢያት ልጆች በመሆናቸው
፪. የጻፏቸው ሐረገ ትንቢቶች በንጽጽር ከዐበይቱ [ከነኢሳይያስ] ስለሚያንስ ነው::

በምግባር: በትሩፋት: በአገልግሎት ግን ያው ናቸው:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እሊህን ነቢያት "እለ አውኀዙ ተነብዮ በእንተ ስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ" ይሏቸዋል:: [ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መውረድ: መወለድና የማዳን ሥራ የትንቢት ጐርፍን ያፈሰሱ እንደ ማለት ነው ::]

ቅዱሳኑ ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ባሻገር ዓለማችን ላይ ከነበሩበት ዘመን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሊደረጉ ያላቸውን ነገሮችም ተናግረዋል:: የነበሩበት ዘመን በአማካኝ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ከ፱ መቶ [900] እስከ ፭ [500] ነው:: በትንቢት ደረጃም እንደነ ሆሴዕና ዘካርያስ ፲፬ [14] ምዕራፎችን: እንደነ አብድዩም አንዲት ምዕራፍ ብቻም የጻፉ አሉ::

በሕይወታቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያሻቸው ናቸውና በየጊዜው ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገሩ የእርሱን ድምጽ ለእሥራኤል [አንዳንዴም ለአሕዛብ] ያደርሱ ነበር:: ፊት አይተው የማያዳሉ ናቸውና ሕዝቡንም ሆነ ነገሥታቱን ስለ ኃጢአታቸው ይገሰጹ ነበር:: በዚህም ምክንያት ከነገሥታቱና ከሕዝቡ አለቆች መከራ ደርሶባቸዋል:: አልፎም ያለ አበሳቸው ሕዝቡ በኃጢአቱ ሲማረክ አብረውት ወርደዋል::

በመጨረሻ ሕይወታቸውም አንዳንዶቹን ክፉዎች ሲገድሏቸው አንዳንዶቹ ደግሞ በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል:: ዛሬ ነቢያት ከእነርሱ ባሕርይ በተገኘችና ብዙ ትንቢትን በተናገሩላት በእመቤታችን ምክንያት ክርስቶስ ድኅነትን ፈጽሞላቸው በተድላ ገነት ይኖራሉ:: ስለ እኛም ይማልዳሉ::

" ናጥሪ እንከ ትሕትና ዘምስለ ንጽሕና"

[ እንግዲህ እንደ ነቢያት ትሕትናን ከንጽሕና ጋር ገንዘብ እናድርግ ]

"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ"

[ ነቢያት መንፈስን ንጹሕ በማድረግ እግዚአብሔርን አይተውታልና: ፊት ለፊትም ተያይተዋልና ]

/ቅዳሴ ማርያም/

ከአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሐምሌ ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. "12ቱ" ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት
፪. ቅዱስ ሶፎንያስ ነቢይ [ዕረፍቱ]
፫. ቅዱሳን ሰማዕታት አቡቂርና ዮሐንስ [ቅዳሴ ቤታቸው]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ [ወንጌላዊው]
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]

" ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት:: በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በሁዋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሠከረ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር:: " [፩ዼጥ.፩፥፲]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
1👍1🙏1
2025/07/12 05:27:45
Back to Top
HTML Embed Code: