Telegram Web
በዓለ ንግስ ጥር 18

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን
ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ
እንዲያነቡት ተጋሩት

ጥር 18 ቀን በዕለተ ቅዳሜ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ በገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ሕጉ ስለሚከብር እርስዎም የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በማክበር እንዲገኙ ስንል በልዑል እግዚአበሔር ስም ጠርተንዎታል ።

አድራሻ :- ከቦሌ ገርጂ ት/ቤት 100 ሜትር ገባ ብሎ
፣ ለሁሉም ሼር አድርጉ 🙏
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

† ጥር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊 † ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ † 🕊

መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው : አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ፯ ዓመታት
ስቃይ በኋላ ተሰይፏል:: ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ :-

- ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ [ አንስጣስዮስ ] እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም [ ልዳ ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፳ ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት [ የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ ] ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና ፸ ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ ዐውደ ስምዕ ] ደረሰ::

- ከዚያም ለተከታታይ ፯ ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: ፫ ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::

- ከ፯ ዓመታት መከራ በኋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: ፯ አክሊላትም ወርደውለታል::

†  ዝርወተ ዓጽሙ  †

- ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ  ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: ፸ ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ [ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ] አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::

- በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::

- በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ [ ደብረ ይድራስ ] ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: [ ምቅናይ ]

- እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይህቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው::

- ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: ፹ው ነገሥታት ግን አፈሩ::


🕊 †  ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባው  † 🕊

- 'ጃንደረባ' የሚለው ቃል በግዕዙ 'ሕጽው' ተብሏል:: ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን የተለመደ እንጂ እንግዳ አይደለም:: መድኃኒታችን እንዳለው በተፈጥሮ የሆኑ: ሰዎች እንዲያ ያደረጉዋቸውና ራሳቸውን ስለ ጽድቅ ጃንደረባ ያደረጉ ብዙዎች ናቸውና::

- ኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ቅዱስ ባኮስም [ አንዳንዴ አቤላክ / አቤሜሌክም ይባላል] :-
- በ፩ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ኢትዮዽያ ተወልዶ ያደገ
- ነገሥታቱንና ሃገሩን በሙያው ያገለገለ
- በተለይ ከ፴፬ እስከ ፵፮ ዓ/ም ለነገሠችው ንግሥት ሕንደኬ ገርስሞት በገንዘብ ሚንስትርነት ያገለገለ
- በገንዘቧ ላይ ሁሉ አዛዥ [ ታማኝ ] የነበረ
- ጃንደረባ በመሆኑ ለንግሥቲቱና ቤተሰቧ ቅርብ የነበረ
- መጻሕፍትን የሚያነብና የሚመረምር
- ዘወትር ወደ ኢየሩሳሌም እየሔደ ከቅዱሳት መካናት የሚሳለም በጐ ሰው ነበር::

- በግብረ ሐዋርያት ምዕ.፰፥፳፮ ላይ እንደ ተጠቀሰው ቅዱሱ ከኢየሩሳሌም ለፋሲካና ለእሸት በዓል ነበር የሔደው:: ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልዾስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል:: በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ: በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቁዋል::

- ክርስትናን ለኢትዮዽያ በ፴፬ ዓ/ም አምጥቷል:: "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ: ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል::

- ቀጥሎም ሃብቱን ንቆ [ መንኖ ] : ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድ ወንጌልን ሰብኮ በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ዐርፏል:: [ ተሰውሯል የሚሉም አሉ ]

" በእውነት ለቅዱስ ባኮስ ክብር ይገባል:: "


🕊 †  ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን  † 🕊

+ ይህ ቅዱስ ሰው :--

- እጅግ የተመሠከረለት ሊቅ
- በፍጹም ትሕርምት የኖረ ገዳማዊ
- በርካቶችን ወደ ክርስትና ያመጣ ሐዋርያዊ
- ለአእላፍ ምዕመናን እረኛ የሆነ የንጽቢን [ ሶርያ ] ዻዻስ
- ለጀሮ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የሠራ ገባሬ መንክራት
- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንትን ያፈራ ታላቅ መምሕር
- ለክርስቶስና ለእመቤታችን ታጥቆ የተገዛ የፍቅር ሰው
- እጣቶቹ እንደ ፋና የሚያበሩለት ማኅቶት
- ራሱን ዝቅ አድርጐ በቆሸሸ ልብስ የሚኖር የትህትና ሰው ነው::

- በ፫፻፳፭ [፫፻፲፰] 325 (318) ዓ/ም: በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡና አርዮስን ሲያወግዙ እርሱ አንዱ ነበር:: በሥፍራውም ሙት አስነስቶ ሕዝቡን አስደምሟል:: በዚያም የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ሠርቶ ወደ ሃገሩ ተመልሶ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::


🕊 † ደናግል ማርያ ወማርታ  †  🕊

- በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ ፪ እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት- ከኃጢአት የተመለሰች': ፪ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::

- በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፩ ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት [ ድንግሊቱ ] ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::

- ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::

- በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ፸፪ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::

- ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ፬ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ
"እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: [ ዮሐ.፲፩ ]
- ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ [ ጌታ ከመሰቀሉ ፮ ቀናት ] በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: [ዮሐ.፲፪፥፩ ]

- በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ፫ መቶ ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::

- በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::

- ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: [ ቅዳሴ ማርያም] ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች::

- ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች:: ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ በዓሏ ከእህቷ ቅድስት ማርታ ጋር ይከበራል::

❖ ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡

🕊

[  † ጥር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት (ዝርወተ ዓጽሙ ]
፪.ቅዱሳት ደናግል ማርያ እና ማርታ [ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ]
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘንፅቢን [ከ፫፻፲፰ቱ]
፬.ቅዱስ ባኮስ ኢትዮዽያዊ [ አቤላክ / አቤሜሌክ ]

[  † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ ረባን ]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ከ፸፪ቱ አርድእት

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
እንኳን ለሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

#ጥር_18_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_የአመት_ነው
#አጥንቱ_የተበተነበት_ደሙ_የፈሰሰበት

70 ነገስታት ያፈሩበት እለት ነው
ጥር 18 " ዝርወተ ዓጽሙ " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ #ዝርወተ_አጽሙ' ትባላለች በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው
#ቅዱስ_ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕታት የሚል ጽሑፍ ተገኘ  ስለዚህም ይሕቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና #በክርስቶስ እመኑ ብሎ አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ የሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን 🙏🙏🙏
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሹ በመከራ ግዜ ፈጥኖ ይድረስልን
አጥንታችንን ለመፍጨት ደማችንን ለማፍሰስ የተነሱትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያፍዝዝልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን

         #መልካም__በዓል🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት  ❞ 

🕊  💖                 💖  🕊

❝  ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ  ሰብእ  መድኀኒት ...

ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም  መድሃኒት ናት። በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ  ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።

ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ ሃብት ] አከማቹ። ❞

[    ቅዱስ ያሬድ    ]


እግዚአብሔር ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ አወቅሁ። ❞ [ መዝ.፻፬፥፲፪ ]


  🕊   ክብርት ሰንበት  🕊


💖                     🕊                    💖
🕊                      💖                     🕊

እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል [ ለዝርወተ ዓጽሙ ] በሰላም አደረሳችሁ።

💖

ሥለ ርትዕት ሃይማኖት ነብስህን የለወጥካት
የተዋህዶ መልካም ሽታ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ይድረስህ ሰላምታ፡፡

🕊                        💖                      🕊

❝ የልዳው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ለአንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ የተወደደው የልጅዋ የኢየሱስ ክርስቶስና የድንግል ማርያም ዕውነተኛ ምስክር ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ልዩ ልዩ ሥቃዮችን የታገሥህ ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡

ሥጋህ ለአራት ለስድስት ክፍል የተከፋፈለው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ናርዶስ ከሚባል የሽቱ አበባ ይልቅ መዓዛህ ይጥመኛልና ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ❞

[ መልክአ ጊዮርጊስ ]

የሰማዕቱን ፍቅር በልቦናችን ያሳድርብን፡፡ በምልጃውና በቃል ኪዳኑ ይማረን፡፡


🕊                        💖                      🕊
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞  [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]

             [   ክፍል -  ዘጠኝ  -    ]

            💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ክፉ የጎልማሳነት ምኞት  ]


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]


🕊                        💖                      🕊
                             👇
🕊

[  † እንኳን ለጻድቅ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊 †  አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን  † 🕊

† በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን [ በተለይ ከ፲፫ኛው [13ኛው] እስከ ፲፭ኛው [15ኛው] መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው] የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
- ክርስትና ያበበበት::
- መጻሕፍት የተደረሱበት::
- ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
- ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ :-

¤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤ አባ ሰላማ ካልዕ::
¤ አቡነ ያዕቆብ::
¤ ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

በተጨማሪም :-

¤ ፲፪ቱ [ 12ቱ ] ንቡራነ ዕድ::
¤ ፯ቱ [ 7ቱ ] ከዋክብት::
¤ ፵፯ [ 47ቱ ] ከዋክብት::
¤ ፭ቱ [ 5ቱ ] ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ፯ቱ [7ቱ] እና የ፵፯ቱ [47ቱ] ከዋክብት አስተማሪ: የአበው ፫ቱ [3ቱ] ሳሙኤሎች [ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ] : የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ::

ከእነዚህ ቅዱሳን የጻድቁ ፍሬዎች አንዱ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ናቸው:: ጻድቁ አንዳንዴ "አፍቀረነ እግዚእ" እየተባሉም ይጠራሉ:: ትርጉሙም "ጌታ ወደደን" እንደ ማለት ነው::

ያፍቅረነ እግዚእ የነበሩት በ፲፬ኛው [14ኛው] መቶ ክ/ዘ ሲሆን ቁጥራቸው ከ፯ቱ [7ቱ] ከዋክብት ነው:: ጻድቁ ከልጅነት ጀምሮ በሥርዓቱ ከማደጋቸው ባሻገር እጅግ የተማሩ እንደነበሩም ይነገርላቸዋል::

ለምናኔ ከወጡ በሁዋላ ከኖሩባቸው ቦታዎችም ፫ቱ [3ቱ] ተጠቃሽ ናቸው:: የመጀመሪያውና ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው ደግሞ ደብረ በንኮል ነው:: ጻድቁ በዚህ ገዳም ከታላቁ ቅዱስ አባ መድኃኒነ እግዚእ ሥርዓተ ገዳምን : ትኅርምተ አበውን : ተጋድሎተ ቅዱሳንን አጥንተው ለመዓርገ ምንኩስና በቅተዋል::

በገዳሙም ለተወሰነ ጊዜ አገልግለው ወደ ጣና አካባቢ ከአቡነ ያሳይና ከአባ ሳሙኤል ዘዋሊ ጋር መጥተዋል:: የመምጣታቸው ምክንያትም ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስና ገዳማትን ለመመሥረት ነው::

ሶስቱ ቅዱሳን ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በሁዋላ አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ ደግሞ ማንዳባን አቀኑ:: ያፍቅረነ እግዚእም ጌታ ባዘዛቸው መሠረት ጣና ውስጥ ገዳም አቅንተው ኑረዋል:: ይህ ገዳማቸው ዛሬም ድረስ በስማቸው ይጠራል::

ጻድቁ አፍቀረነ እግዚእ ፫ኛው [3ኛው] የሚታወቁበት ገዳም ማኅበረ ዴጌ [ጻድቃነ ዴጌ] ሲሆን ገዳሙ በአክሱም ዙሪያ ይገኛል:: እርሳቸው ፫ሺ [3ሺ] ቅዱሳን የተሠወሩበትን ገዳም በማገልገላቸውም ዛሬም ድረስ በአካባቢው የታወቁ ሆነዋል::

በተረፈም አክሱም አካባቢ ሌሎች ገዳማትን እንዳቀኑም ይነገርላቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌልና ገዳማትን በማስፋፋት ከኖሩ በሁዋላ በዚህች ቀን ዐርፈው ለክብሩ : ለርስቱ በቅተዋል::

† አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ይቅር ብሎ በረከታቸውን ያሳድርብን::

🕊

[  † ጥር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ [አፍቀረነ እግዚእ ዘጉጉቤ - ጣና ውስጥ - ከሰባቱ ከዋክብት አንዱ]
፪. አባ ባሱራ
፫. ቅድስት ኔራ
፬. ቅድስት በርስጢና
፭. አባ ዝሑራ

[   † ወርሐዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላዕክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ [ታቦታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 አካባቢ ይገኛል]
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

† ቅዱሳንን ታስቡ ዘንድ ቸል አትበሉ::

" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::"
[መዝ.፴፮፥፳፰-፴፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2025/01/27 03:54:01
Back to Top
HTML Embed Code: