#ሐምሌ 5
በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው። በረከታቸው ይደርብን አሜን!!
ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
የዮና ልጅ ስምዖን ጴጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው።
በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ አድጐ፣ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ሃምሳ ስድስት ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል።
(ማቴ. ፲፮፥፲፯ ፣ ዮሐ. ፳፩፥፲፭)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሠራው ስሕተት ንስሐ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የእርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል።
በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል።
#መልካም__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

🙏8❤3
†
🕊 💖 ዼጥሮስ ወዻውሎስ 💖 🕊
🕊
[ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]
ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነትን ከመቀበሉ ጥቂት አስቀድሞ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ከመከረው ምክር እነሆ
❝ በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ ...
ቃሉን ስበክ !
በጊዜውም አለጊዜውም ጽና !
ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።
ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና ፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።
አንተ ግን
ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ !
መከራን ተቀበል !
የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ !
አገልግሎትህን ፈጽም !
በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል።
መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ ሩጫውን ጨርሼአለሁ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። ❞
[ ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፬ ፥ ፩ ]
እንኳን አደረሳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ በረከታቸው ይደርብን !
† 🕊 እንኳን አደረሰን 🕊 †
🕊 💖 🕊

🙏2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ድምፀ ተዋሕዶ ] 🕊
▷ " የቅዱሳን አማላጅነት "
[ 💖 በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 💖 ]
[ 🕊 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ❞ [ ያዕ.፭፥፲፮ ]
🕊
❝ እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን። ❞ [ዮሐ.፱፥፴፩]
🕊
❝ አብርሃምም ቀረበ አለም። በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን ? አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን ? . . .
እግዚአብሔርም። በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ። ❞ [ ዘፍ.፲፰፥፳፫ ]
🕊
❝ ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ❞ [ ሥራ . ፯ ፥ ፷ ]
🕊
❝ ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል። ❞ [ ፪ቆሮ.፱፥፲፬ ]

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
🕊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊
🕊 † ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ † 🕊
† ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው::
ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው::
ስሙ የግብር [በሥራ የሚገኝ] ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው::
ቅዱስ መርቄሎስ በ፷ [60] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው::
በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ::
ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል::
ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?"
ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል::
🕊 † ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ † 🕊
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ፭መቶ [500] ዓመት አካባቢ የነበረ
¤ እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ
¤ ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት
¤ በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ
¤ ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት
¤ ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት
¤ መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና
¤ በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው::
† ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል::
† እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን::
[ † ሐምሌ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት]
፪. ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ
፫. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፬. ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት
፭. ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል
† " እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ:: " † [፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤2
#እግዚአብሔር_ሰው_ይፈልጋል!"
#ልቡ_ንጹሕ የኾነውን፣ አሳቡ የተቃናውን፣ ማግኘት የማይለውጠውን፣ #ይቅርታ አድራጊውን፣ ለእውነት ተቆርቋሪውን፣ ተለሳልሶ የማይናደፈውን፣ #ለፍቅር ዋጋ የሚከፍለውን፣ አድሮ የማይቀለውን፣ በየወንዙ አቋሙን የማይለውጠውን፣ ለጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደውን፣ ለቆዳው ሳይኾን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን፣ #የሃይማኖት_አባቶችን የሚያከብረውን፣ ለመታዘዝ ራሱን ያዘጋጀውን፣ ክስና ክርክርን የናቀውን፣
#ልጄ_ኹይ_ሰው_ኹን ፩ነገ ፪፥፪
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#ልቡ_ንጹሕ የኾነውን፣ አሳቡ የተቃናውን፣ ማግኘት የማይለውጠውን፣ #ይቅርታ አድራጊውን፣ ለእውነት ተቆርቋሪውን፣ ተለሳልሶ የማይናደፈውን፣ #ለፍቅር ዋጋ የሚከፍለውን፣ አድሮ የማይቀለውን፣ በየወንዙ አቋሙን የማይለውጠውን፣ ለጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደውን፣ ለቆዳው ሳይኾን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን፣ #የሃይማኖት_አባቶችን የሚያከብረውን፣ ለመታዘዝ ራሱን ያዘጋጀውን፣ ክስና ክርክርን የናቀውን፣
#ልጄ_ኹይ_ሰው_ኹን ፩ነገ ፪፥፪
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤12
💖
[ 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 ]
" ንጉሥ ከእርሱ ርቀን የነበርን እኛ ቤዛችን በሚሆን በልጁ ሕማም ከእርሱ ምን ያህል ክብር እንዳገኘን ዐወቅህን? ሞት ጠፋ ፣ ዲያብሎስም ድል ተነሣ ፣ ሲዖል ታወከ ፣ በኃጢአት የተፈረደው ፍርድ ተፋቀ ፣ ሰይጣን ያመጣው ስሕተት ጠፋ። እንዳልነበረም ሆነ ገነት ተከፈተ ትንሣኤ ተገለጠ"
[ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
[ ❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት ❞ ]
❝ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ ሰብእ መድኀኒት ..."
ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም መድሃኒት ናት። በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።
ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ ሃብት ] አከማቹ። ❞
[ ቅዱስ ያሬድ ]