Telegram Web
🕊

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

🕊  †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!  †  🕊


🕊  † ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ †  🕊

† ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው::

ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው::

ስሙ የግብር [በሥራ የሚገኝ] ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው::

ቅዱስ መርቄሎስ በ፷ [60] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው::

በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ::

ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል::

ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?"

ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል::

🕊  †   ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ  †   🕊

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ፭መቶ [500] ዓመት አካባቢ የነበረ
¤ እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ
¤ ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት
¤ በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ
¤ ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት
¤ ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት
¤ መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና
¤ በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው::

† ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል::

† እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን::

[  † ሐምሌ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት]
፪. ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ
፫. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፬. ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት
፭. ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም

[  †  ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል

" እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ:: " † [፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
#እግዚአብሔር_ሰው_ይፈልጋል!"

#ልቡ_ንጹሕ የኾነውን፣ አሳቡ የተቃናውን፣ ማግኘት የማይለውጠውን፣ #ይቅርታ አድራጊውን፣ ለእውነት ተቆርቋሪውን፣ ተለሳልሶ የማይናደፈውን፣ #ለፍቅር ዋጋ የሚከፍለውን፣ አድሮ የማይቀለውን፣ በየወንዙ አቋሙን የማይለውጠውን፣ ለጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደውን፣ ለቆዳው ሳይኾን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን፣ #የሃይማኖት_አባቶችን የሚያከብረውን፣ ለመታዘዝ ራሱን ያዘጋጀውን፣ ክስና ክርክርን የናቀውን፣

#ልጄ_ኹይ_ሰው_ኹን ፩ነገ ፪፥፪

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
12
💖

[    🕊   ክብርት ሰንበት   🕊 ]

" ንጉሥ ከእርሱ ርቀን የነበርን እኛ ቤዛችን በሚሆን በልጁ ሕማም ከእርሱ ምን ያህል ክብር እንዳገኘን ዐወቅህን? ሞት ጠፋ ፣ ዲያብሎስም ድል ተነሣ ፣ ሲዖል ታወከ ፣ በኃጢአት የተፈረደው ፍርድ ተፋቀ ፣ ሰይጣን ያመጣው ስሕተት ጠፋ። እንዳልነበረም ሆነ ገነት ተከፈተ ትንሣኤ ተገለጠ"

[ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

[   ❝ ይህች ዕለት የተቀደች ናት  ❞  ]


❝  ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ  ሰብእ  መድኀኒት ..."

ይህች ዕለት የተቀደች ናት ። ለሰው ልጆችም  መድሃኒት ናት። በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ  ትሁነን። እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።

ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ። መዋደድን ገንዘብ አድርጉ። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ። ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ [ ሃብት ] አከማቹ። ❞

[    ቅዱስ ያሬድ    ]


🕊  ክብርት ሰንበት   🕊   ]


🕊                        💖                     🕊
                        †                             

† [   ያን ጊዜ ጥበብ ትሠወራለች  ]

" ምልክቱስ እነሆ እንዲህ ያለ ወራት ይመጣል ...

🕊

" የሚጣፍጠውም ውሃ ይመራል ፤ ወዳጆችም እንደ ጠላት ድንገት እርስበርሳቸው ይጋደላሉ። ያን ጊዜ ጥበብ ትሠወራለች። ምክርም ወደ ማደሪያዋ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለች። በብዙ ሰዎች ዘንድ ይፈልጓታል ነገር ግን አያገኟትም። በዚህ ዓለምም ኃጢአት ስንፍና ትበዛለች።

ካንዲቱ አገር አቅራቢያዋን አንዲቱን ሀገር በውኑ አንቺ ያለፈ ደግ ሰው አለን ? ወይስ እውነት የሚሠራ ሰው አለን ? ብላ ትጠይቃታለች። ያችም የለም ትላታለች። በነዚያም ወራቶች ሰው ሞትን ይመኛል አያገኝም። "

[ ዕዝራ ሱ . ፫ ፥ ፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
👏3
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

†      🕊    እንኳን  አደረሰን    🕊     †

†  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ  ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †

🕊                        💖                       🕊


🕊       [   ድምፀ ተዋሕዶ   ]        🕊


▷     "  ም ሥ ጢ ረ   ሥ ላ ሴ  " 

[   ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬


❝ በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። ዓይኑንም አነሣና እነሆ ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ❞ [ ዘፍ.፲፰፥፩ ]

                     🕊                     

❝ ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል ❞ [ ዮሐ.፲፭፥፳፮ ]



🕊                       💖                   🕊
👍1
4
                        †                             

†      🕊    ዘላለም ሥላሴ    🕊     †

†  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ  ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †

🕊                        💖                       🕊


❝ በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ፤ ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል ፣ እርሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም። ❞

[  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ]


†      🕊    እንኳን  አደረሰን    🕊     †


🕊                        💖                       🕊
2
🕊

[ †  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]


🕊   †  ሥሉስ ቅዱስ   †   🕊

በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::


🕊   †  ታላቁ አባ ሲኖዳ  †   🕊

የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :-

¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::]

ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

🕊   † አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ  †  🕊  
[GIYORGIS_OF_SEGLA]

ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::

ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው::

ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር ፵፩ [41] ድርሰቶችን ደረሰ:: [መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ]

ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች :-

፩. ሊቀ_ሊቃውንት
፪. በላዔ_መጻሕፍት
፫. ዓምደ_ሃይማኖት
፬. ዳግማዊ_ቄርሎስ
፭. ጠቢብ_ወማዕምር

ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ፷ [60] ዓመቱ በ፲፻፬፻፲፰ [1418] ዓ/ም  በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ ፯ [7] ቀን ነው::

የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

🕊

[ †  ሐምሌ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ [ሥላሴን ያስተናገዱ]
፪. ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
፫. ታላቁ አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን ሁሉ አለቃ]
፬. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ [ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ]
፭.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ [ምጥው ለአንበሳ]
፮. አባ መቃቢስ
፯. አባ አግራጥስ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፪. አባ ባውላ ገዳማዊ
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

" እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ :- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: " [ዕብ.፮፥፲፫] (6:13)

" የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [ቆሮ.፲፫፥፲፬]  (13:14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2025/07/14 00:41:14
Back to Top
HTML Embed Code: