#የጥምቀት_በዓል_አከባበር_በአዲስ_አበባ_ከእንጦጦ_ጋራ_ጥግ_እስከ_ጃንሆይ_ሜዳ_
በአዲስ በአበባ ያሉ ገዳማትና አድባራትም በቦታ ርቀት እስከ ተለያዩበት ቀን ድረስ በእንጦጦ ጋራ ጥግ በአንድ ላይ በመፈናኘት ያድሩ ነበር፤ ኋላ ከቦታ ርቀት በኋላ የተቀሩት በጃንሆይ ሜዳ ማደር ጀምረዋል፡፡ እያደረም ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሲመሠረቱ ከጃንሆይ ሜዳ በተጨማሪ ለአጥቢያቸው በሚቀርብ ቦታ ማደር ጀመሩ፡፡
፠ በዓለ ጥምቀት በጃን ሜዳ (ጃንሆይ ሜዳ) መከበር የጀመረው ከ1887 ዓ.ም. አንስቶ መሆኑ ይነገራል፡፡ ስያሜውምና አጀማመሩም ጃንሜዳ የሚለው ጃን፥ ጃኖ ከሚለው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ነገሥታት ለመሾም ለመሻር፣ ዳኝነት ለመስጠት፣ ሊቃውንትን ለመሾምና፣ ዐዋጅ ሲያስነግሩ በቤተ መንግሥታቸው አቅራቢያ በሚገኝ ሜዳ ላይ የጃኖ ድንኳን ተክለው ያስነግራሉ፤ ይህም ሜዳ ከጃኖ ጋራ እየተናበበ የቦታ መጠሪያ ሁኗል፡፡ ለምሳሌ፤
‹‹ጃን ተከል›› በጎንደር ነገሥታት፤
‹‹ጃን መራቂ›› በላስታ ነገሥታት፤
‹‹ጃን ተራራ›› በአማራ ሳይንት በአፄ በዕደ ማርያም
‹‹ጃን ሜዳ›› በደብረ ታቦርና በአዲስ አበባ ናቸው፡፡
፠ አዲስ አበባ መዲና በሆነችበት ሰዓት ‹‹መሐል ሰፋሪ‹‹ የሚባሉ የመኳንንት ጕባኤ በዚሁ በጃንሜዳ በስውር ዐድማ የሚያደርጉበት ሆነ አድማውን ሲያደርጉም በጃን ሜዳ ያለው የጃኖው ድነኳን ከሩቅ እንዳይታይ በማቅ ይሸፈን ነበር፡፡ እቴጌ ጣይቱ ይህን የመሰለ ሜዳ የክፉ ምክር መምከሪያ ሆኖ ከሚኖር ተባርኮ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቢሆን ብለው ለአፄ ምኒልክ ሃሳብ አቀረቡላቸው፤ አፄ ምኒሊክም ማለፊያ ብለው ሐሳባቸውን በመቀበል ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ እንዲሆን አዘዙ፡፡ እንዲሁም የአፄ ምንሊክ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ መሆኑን በግንቦት 10 ቀን 1901ዓ.ም. ዐዋጅ ያስነገሩበት፤ ‹‹ንሥረ ተፈሪ›› የተባለው የመጀመሪያው አውሮፕላንም በ12921ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያረፈውም በዚሁ ሜዳ በመሆኑ ጭምር ስያሜው ጃንሆይ ሜዳ ተባለ፡፡
፠ በ1887ዓ.ም. በዓለ ጥምቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ በጃን ሜዳ በሕብረት ያከበሩት የመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን፣ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበሩ፡፡
፠ እስከ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ መን ድረስ ግን ታቦታቱ ወደ ቀበና ወንዝ (አፈ ንጉሥ ጥላሁን ሰፈር፤ ከፈረንሳይ ኤምባሲ በታች) ከከተራው አንስቶ አድረው በጥምቀት ዕለት ወደ ጃንሜዳ ይመለሱ ነበር፡፡
ሌሎችም በየሰበካቸው በሚገኝ አምች ቦታ ሲያከብሩ ቆይተው በ1939ዓ.ም. ከንሜዳ እጅግ በጣም ብዙ ያልራቁት (የካ ሚካኤልና ቅዱስ ዑራኤል) በንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደርጎ ወደ ጃናሜዳ እንዲመጡ ተደርጎ ነበር፤ ሆኖም ሕዝብ እየበዛ ስላስቸገረ በየአቅራቢያቸው እንዲያድሩ ተድርጓል፡፡
፠ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ በ1936 ዓ.ም በስፍራው የውኃ ቧንቧ እንዲዘረጋ፣ ባሕረ ጥምቀት ገንዳ በግንብ እንዲሰራ፣ የኤሌክትረክ መብራት በቦታው እንዲገባ አድርገዋል፡፡ ዙሪያውን በግንብ ተሰርቶ በቧንቧ የብረት ማገር ውብ ሆኖ እንዲታጠርና በዐፀድና በአበባዎች እንዲያጌጥ አድርገዋል፡፡ ይህ ቦታ ኋላ በ1994ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለታል፡፡
፠ እስከ ቅርብ ጊዜያትም ድረስ ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱ ታቦታት ከነድርባቸው ነበር፤ ለምሳሌ ቀቀጨኔ ደብረ ሰላም ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነበረ፤ ኋላ ግን ድርብ ታቦታት ቀርተው ዋናውን ይዘው የሚወርዱ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ….. ባሕረ ጥምቀት (አብሕርተ አጥማቃት) አሉ፡፡
፠ እስከ 1958ዓ.ም. በምስካየ ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ማኅበርና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የታሪክ ድርሰትና ስብከት ክፍል አስተባባሪነት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሐዋርያዊ ድርጅት፣ ከሊቃውንትና ከመምህራን፣ ከሰዋስወ ብርሃንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተውጣጡ መምህራን በባሕረ ጥምቀቱ የስብከተ ወንጌልና፣ የመዝሙርና የድራማ መርሐ ግብር ያቀርቡ ነበር፡፡ በ1959ዓ.ም. አካባቢ ጥቂት ሰንበት ት/ቤቶች የደንብ ልብስና ነጠላ በማድረግ ታቦታቱን አጅበው አውጥውና አጅበው በመመለስ የበዓሉ ድምቀት እየሆኑ መጡ፡፡
በአሁኑ ወቅት በጃንሜዳ የሚያድሩ ታቦታት 12 ናቸው እነርሱም፤
1ኛ. መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤
2ኛ. ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤
3ኛ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤
4ኛ. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ.፤
5ኛ. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.፤ (የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦተ ወደ ጥምቀተ ባሕር ስለማይወጣ ሕዝቡና ሰ/ት/ቤቱ አብሮ ነው የሚያከብረው)
6ኛ. መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
7ኛ. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.፤
8ኛ. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (አብሮም ቅዱስ ሚካኤል ይወርዳል)፤
9ኛ. ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.፤
10ኛ. ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ.ክ.፤
11ኛ. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤
12ኛ. ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (ቀበና 18 ፓርክ አጠገብ)፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
@Nigatu5

#ቃና_ዘገሊላ_ጥር 1️⃣2️⃣❤️
🥀⛪️ #እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን🙏
✳️ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን #መድኃኒታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል #ከጌታ_ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡
በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ #ከድንግል_ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ ›› ‹‹ የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች ›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ #በተጨማሪ_ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ ( ተገቢ ስላልሆነ ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና ( ሉቃ 1÷28 ) ማንም ሳይነግራት #የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ ወደ ወዳጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ "ወይንኬ አልቦሙ" "ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል" አለችው፡፡ እርሱም መልሶ "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?" #ጊዜዬ_ገና_አልደረሰም" አላት፡፡
✳️እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ ( #ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን "ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን #መልካሙን_እስከ አሁን አቆይተሃል" አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡ "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?" ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል፡፡ ክብር ይግባውና #አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
✳️በተናጠል ስንመለከት #አንቺ_ሴት" ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል"(ዘፍ 2÷23) በመሆኑም #ጌታ_አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡ ‹‹ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡ #ይህ_ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡ ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡- የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር "የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?"#ትወልጃለሽ_ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡ በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ #ጌታችን_ቀርቦ "የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?" አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡
✳️ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ ( ሉቃ 8÷28-29 ) ስለሆነም ‹‹ #አንቺ_ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹ አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡ ‹‹ ጊዜዬ አልደረሰም ›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ #ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡- እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡ ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡ #ይሁዳ_ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት ፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡
✳️እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል #የድንግል_ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡ ነገር ግን የእናቱን #የድንግል_ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡ እናታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡ ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትም እንዴት አብልጣ አታማልድ? ከእናታችን #ከቅድስት_ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን አሜን

#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ #ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3#ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡
#በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው
#ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡
#በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡
፠ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡
፠ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡
፠ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን (ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡
፠ እናቴ ሆይ አናንያ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋjት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መጽሐፍ እኔን ፋቀኝ...›› ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግሥተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈጽምና ድል እንነሣ›› አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ እያለች እየነገረችው ሳለ አንሠተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡
፠ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤
* በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡
* ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡
* ዐሥራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡
* በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው
* የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡
* በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡
(ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡)
፠ ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡
፠ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡
፠ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
፠ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው።

Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢