@EotcLibilery ይሄን chanal መግዛት ሚፈልግ ሰው በውስጥ መስመር ያናግረኝ
@yesadikusitota
Waga 40k diridr alew gin ewntegha gexi bicha yimta litadekimugh atimitu

🔴 የሰው ዋጋ || እጅግ ድንቅ ትምህር...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
✝የሰው ዋጋ✝
Size:-90.7MB
Length:-1:37:59
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Size:-90.7MB
Length:-1:37:59
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ልደተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡
(ከሰንበት ትምህርት ቤታችን የሰሌዳ መጽሔት ተለቅሞ የተዘጋጀ፡፡)
#ልደቱና_ብሥራቱ
አባቱ ዘካርያስ (ከአብያ ምድብ የኾነ ሊቀ ካህን ነው)፤ እናቱ ዘካርያስ (ከአሮን ነገድ ነበረች)፤ ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፡፡» /ሉቃ.1÷5-7/፡፡
ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር በጸሎት ይጠይቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዐት /ዘጸ.3ዐ÷6-8/ ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት /ዕጣ ወጥቶለት/ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው /ከዕጣን መሥዋዕት ማቅረቢያው/ በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ በፍርሃት ተዋጠ፡፡ መልአኩ ግን «ዘካርያስ ሆይ አትፍራ ጸሎተህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ ብዙዎቹም በእርሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና» በማለት ብሥራት ከነገረው በኋላ ስለሚወለደው ልጅ አራት ነገሮችን ነገረው /ሉቃ.1÷13-17/፡፡
ሀ. የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፡
ለ. በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡
ሐ. ከእስራኤል ወገን ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል፤
መ. ለጌታ የሚገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኃይል በጌታ ፊት ይሔዳል፡፡
ዘካርያስ ይህንን ከመልአኩ በሰማበት ወቅት እርሱ ሸምግሎ፥ ሚስቱም አርጅታና የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ በዚያም ላይ መካን ነበረችና «ይህን በምን አውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች» በማለት ጥርጣሬውን በጥያቄ መልክ አቀረበ፡፡ በዚህን ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለው «እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬያለሁ፤ እነሆ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም» አለው፤ በዚህም መሠረት ዘካርያስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ መስማትም ሆነ መናገር አልቻለም ነበር፡፡ መልአኩ እንደነገረውም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡
ይህ ከሆነ ከስድስት ወር በኋላ የቅዱስ ዮሐንስን መፀነስ ለዮሐንስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችንን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት ኤልሳቤጥ መፀነስዋንም ነግሯት ነበር፡፡ «... እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወራት ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና» ብሏት ነበር፡፡ እመቤታችንም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ የነገራትን ለማየት በዚያው ሰሞን ፈጥና ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች፡፡ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ስታቀርብላት እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ተከሰተ፤ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማኅፀኗ ያለው ጽንስ ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- «አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሏልና፡፡... »፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን አስመልክቶ በድጓው ላይ ባስተማረው ትምህርት «አእሚሮ እምከርሠ እሙ ሰገደ ወልደ መካን ለወልደ ድንግል» «ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ አውቆ የመካኒቱ /የኤልሳቤጥ/ ልጅ ለድንግሊቱ /ለእመቤታችን/ ልጅ ሰገደ» ብሏል፡፡
#የቅዱስ_ዮሐንስ_ልደት (ሉቃ.1÷67-80)
ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ በስምንተኛውም ቀን ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ እናቱ ግን ለዘካርያስ በቤተ መቅደስ «የሕፃኑ ስም ዮሐንስ ይባላል» ብሎ ያናገረ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት «ዮሐንስ መባል አለበት» አለች፡፡ ዘካርያስን ለልጁ ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ «ስሙ ዮሐንስ ነው» ብሎ ጻፈ ወዲያውም አንደበቱ ተፈታ፡፡ (ዮሐንስ ማለትም ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ማለት ነው፡፡)፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ይናገር ጀመር፡፡ በዚህም ምክንያት ጎረቤቶቹ ሁሉ በፍርሃት ተመሉ፡፡ ነገሩም በይሁዳ አውራጃ ሁሉ ተወራ፡፡ የሰሙትም ሁሉ «ይህ ሕፃን ምን ይሆን?» እያሉ በመገረም ጠየቁ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ስለ ሕፃኑ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትንቢት ተናገረ /ሉቃ.1÷67-79/
«አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና፤ እንደዚሁም የኃጢአታቸው ሥርየት የሆነውን የመዳን ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ» በማለት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆን ማለትም ከእርሱ ቀድሞ የሕዝቡ ልብ ጌታችንን እና ትምህርቱን እንዲቀበል የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያስተምር ተናገረ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መንገድ ጠራጊነት በቅዱስ ገብርኤልና በአባቱ በዘካርያስ ብቻ ሳይሆን ቀድሞም በሌሎች ነቢያት ትንቢት የተነገረለት ነበር፡- ነቢዩ ኢሳይያስ «የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል «የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ...» /ኢሳ.4ዐ ÷3/ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡

Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለ ሲሆን ኢያሱ ደግሞ በሐዲስ ኪዳን ይመሰላል ። ይህም ማለት በሙሴ የነበሩ ኪዳን የተሰጣቸው አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ፣ ፳ኤል በኢያሱ የተሥፍው ወራሽና ተከፍይ ሁነዋል ። በጊዜው በአካለ ነፍስ የነበሩት ኪዳናውያን እለ አብርሃምጨ ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ሌሎችም ልጆቻቸው ምድረ ርስትን ለመውረስ በተሥፍ የቀሩ ቢሆንም በኢያሱ ሐዲስ ኪዳን ምሳሌነት በተነገረ ምሥጢር መንግሥተ ሰማይ የገቡ በአካለ ነፍስ በኢያሱ ክርስቶስ ነውና ።
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለበትም ምክንያት ከግብጽ እስከ ከነዓን ድረስ መና እያወረደ ፣ ውኃ እያፈለቀ ዓርባ ዘመን ቢመግብ ቅሉ ምድረ ርስት መግባት አልቻለም ነበር ። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነፍሳት ጻድቃን ምሳሌ ነውና ። በኢያሱ በሐዲስ ኪዳን መመሰሉ ግን በነፍሳት የተመሰሉ ፳ኤል ዘሥጋን ምድራዊ ርስትን በማውረሱ በኋላ ዘመን ኢያሱ ክርስቶስ መንግሥተ ሰማያትን ለማውረሱ ምሳሌ ሆነው ። (ከምዝ ነአምን ገጽ 231)
ከሊቃውንት መጽሐፍ አስተማሪ ጹሑፎች ዘወትር ያገኛሉ ቤተሰብ ይሁኑ #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ ።

Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
❤️በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ
በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም
የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ
መልሱ ይለቀቃል። በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል
ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
👇👇👇
@metehafe_kedusawi_teyake