@EotcLibilery ይሄን chanal መግዛት ሚፈልግ ሰው በውስጥ መስመር ያናግረኝ
@yesadikusitota
Waga 40k diridr alew gin ewntegha gexi bicha yimta litadekimugh atimitu

🔴 የሰው ዋጋ || እጅግ ድንቅ ትምህር...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
✝የሰው ዋጋ✝
Size:-90.7MB
Length:-1:37:59
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Size:-90.7MB
Length:-1:37:59
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
❤2
#ልደተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡
(ከሰንበት ትምህርት ቤታችን የሰሌዳ መጽሔት ተለቅሞ የተዘጋጀ፡፡)
#ልደቱና_ብሥራቱ
አባቱ ዘካርያስ (ከአብያ ምድብ የኾነ ሊቀ ካህን ነው)፤ እናቱ ዘካርያስ (ከአሮን ነገድ ነበረች)፤ ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፡፡» /ሉቃ.1÷5-7/፡፡
ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር በጸሎት ይጠይቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዐት /ዘጸ.3ዐ÷6-8/ ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት /ዕጣ ወጥቶለት/ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው /ከዕጣን መሥዋዕት ማቅረቢያው/ በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ በፍርሃት ተዋጠ፡፡ መልአኩ ግን «ዘካርያስ ሆይ አትፍራ ጸሎተህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ ብዙዎቹም በእርሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና» በማለት ብሥራት ከነገረው በኋላ ስለሚወለደው ልጅ አራት ነገሮችን ነገረው /ሉቃ.1÷13-17/፡፡
ሀ. የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፡
ለ. በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡
ሐ. ከእስራኤል ወገን ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል፤
መ. ለጌታ የሚገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኃይል በጌታ ፊት ይሔዳል፡፡
ዘካርያስ ይህንን ከመልአኩ በሰማበት ወቅት እርሱ ሸምግሎ፥ ሚስቱም አርጅታና የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ በዚያም ላይ መካን ነበረችና «ይህን በምን አውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች» በማለት ጥርጣሬውን በጥያቄ መልክ አቀረበ፡፡ በዚህን ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለው «እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬያለሁ፤ እነሆ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም» አለው፤ በዚህም መሠረት ዘካርያስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ መስማትም ሆነ መናገር አልቻለም ነበር፡፡ መልአኩ እንደነገረውም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡
ይህ ከሆነ ከስድስት ወር በኋላ የቅዱስ ዮሐንስን መፀነስ ለዮሐንስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችንን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት ኤልሳቤጥ መፀነስዋንም ነግሯት ነበር፡፡ «... እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወራት ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና» ብሏት ነበር፡፡ እመቤታችንም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ የነገራትን ለማየት በዚያው ሰሞን ፈጥና ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች፡፡ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ስታቀርብላት እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ተከሰተ፤ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማኅፀኗ ያለው ጽንስ ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- «አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሏልና፡፡... »፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን አስመልክቶ በድጓው ላይ ባስተማረው ትምህርት «አእሚሮ እምከርሠ እሙ ሰገደ ወልደ መካን ለወልደ ድንግል» «ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ አውቆ የመካኒቱ /የኤልሳቤጥ/ ልጅ ለድንግሊቱ /ለእመቤታችን/ ልጅ ሰገደ» ብሏል፡፡
#የቅዱስ_ዮሐንስ_ልደት (ሉቃ.1÷67-80)
ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ በስምንተኛውም ቀን ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ እናቱ ግን ለዘካርያስ በቤተ መቅደስ «የሕፃኑ ስም ዮሐንስ ይባላል» ብሎ ያናገረ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት «ዮሐንስ መባል አለበት» አለች፡፡ ዘካርያስን ለልጁ ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ «ስሙ ዮሐንስ ነው» ብሎ ጻፈ ወዲያውም አንደበቱ ተፈታ፡፡ (ዮሐንስ ማለትም ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ማለት ነው፡፡)፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ይናገር ጀመር፡፡ በዚህም ምክንያት ጎረቤቶቹ ሁሉ በፍርሃት ተመሉ፡፡ ነገሩም በይሁዳ አውራጃ ሁሉ ተወራ፡፡ የሰሙትም ሁሉ «ይህ ሕፃን ምን ይሆን?» እያሉ በመገረም ጠየቁ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ስለ ሕፃኑ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትንቢት ተናገረ /ሉቃ.1÷67-79/
«አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና፤ እንደዚሁም የኃጢአታቸው ሥርየት የሆነውን የመዳን ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ» በማለት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆን ማለትም ከእርሱ ቀድሞ የሕዝቡ ልብ ጌታችንን እና ትምህርቱን እንዲቀበል የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያስተምር ተናገረ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መንገድ ጠራጊነት በቅዱስ ገብርኤልና በአባቱ በዘካርያስ ብቻ ሳይሆን ቀድሞም በሌሎች ነቢያት ትንቢት የተነገረለት ነበር፡- ነቢዩ ኢሳይያስ «የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል «የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ...» /ኢሳ.4ዐ ÷3/ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡

❤1
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለ ሲሆን ኢያሱ ደግሞ በሐዲስ ኪዳን ይመሰላል ። ይህም ማለት በሙሴ የነበሩ ኪዳን የተሰጣቸው አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ፣ ፳ኤል በኢያሱ የተሥፍው ወራሽና ተከፍይ ሁነዋል ። በጊዜው በአካለ ነፍስ የነበሩት ኪዳናውያን እለ አብርሃምጨ ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ሌሎችም ልጆቻቸው ምድረ ርስትን ለመውረስ በተሥፍ የቀሩ ቢሆንም በኢያሱ ሐዲስ ኪዳን ምሳሌነት በተነገረ ምሥጢር መንግሥተ ሰማይ የገቡ በአካለ ነፍስ በኢያሱ ክርስቶስ ነውና ።
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለበትም ምክንያት ከግብጽ እስከ ከነዓን ድረስ መና እያወረደ ፣ ውኃ እያፈለቀ ዓርባ ዘመን ቢመግብ ቅሉ ምድረ ርስት መግባት አልቻለም ነበር ። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነፍሳት ጻድቃን ምሳሌ ነውና ። በኢያሱ በሐዲስ ኪዳን መመሰሉ ግን በነፍሳት የተመሰሉ ፳ኤል ዘሥጋን ምድራዊ ርስትን በማውረሱ በኋላ ዘመን ኢያሱ ክርስቶስ መንግሥተ ሰማያትን ለማውረሱ ምሳሌ ሆነው ። (ከምዝ ነአምን ገጽ 231)
ከሊቃውንት መጽሐፍ አስተማሪ ጹሑፎች ዘወትር ያገኛሉ ቤተሰብ ይሁኑ #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ ።

❤3👎1
እንኳን ለሐዋርያት (የሰኔ) ጾም ፍቺ፤ እንዲሁም ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ፡፡
✤✤ #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ወሥርዐተ_ማኅሌት_ዘሐምሌ_፭፡፡
✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ፤ በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡
✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፤ ነገዱ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ነው አባቱ ዮስአል ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀ የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ፡፡ በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዐት እየተማረ እስከ 3ዐ ዓመቱ ቆየ፡፡ በ3ዐ ዓመቱ የአይሁድን ሸንጐ አባል ሆኖ ተቈጠረ፡፡
✤ #ለአገልግሎት_አጠራራቸው
✤✼ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኳውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ «ዐለት» ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ (ማቴ 26፥34) ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለየው ጊዜ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለትም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡
ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17
✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡
በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኀኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1
የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም ነበር፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡
ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር ሄደ፥ ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየም በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ።
በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡
ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2,ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፤ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም. ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ54 ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያሳለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡

❤3
✤ #እረፍታቸው
የቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመኑ ሊፈጸም ሲቃረብም እንዲህ ኾነ፤ በዘመኑ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፤ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡
በዚህ ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› ሲል ቢጠይቀው ጌታችንም ‹‹ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው። ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው እንጂ›› ሲል መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር። ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል፤›› (ዮሐ. ፳፩፥፲፰) በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መኾኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡
በሮማውያን ሕግ ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ የሮም አገር ተወላጅ ከኾነ የወንጀሉ ክብደትና ቅለት እየታየ ግርፋት ወይም ሞት ይፈረድበታል እንጂ በአንድ ወንጀል ሁለት ቅጣት አይቀጣም ነበር፡፡ ወንጀለኛው የውጪ አገር ዜጋ (ከሮም ውጪ) ከኾነ ግን ለምሳሌ ቅጣቱ ግርፋት ከኾነ ከተገረፈ በኋላ እስራት ይጨመርበታል፤ ቅጣቱ ሞት ከኾነም ከገረፉት በኋላ በመስቀል ወይም በሌላ መሣርያ ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ አልነበረምና በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡
እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡
✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል (እንደ አምላኬ አልሰቀልም ብሎ) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡
#አቢያተ_ክርስቲያናቱ፤
#ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ-ወጳውሎስ፤ ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መስመር መንገድ ላይ የሚገኝ፡፡
#ሰዋስወ_ብርሃን_ቅዱስ-ጳውሎስ_ገዳም፤ ከ3ቱ መንፈሳውያኝ ኮሌጆች አንዱና ዋነኛው የሚገኝበት፡፡ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ 18ት ማዞሪያ ብላችሁ ስትሄዱ የሚገኝ፡፡