Telegram Web
የእመቤታችን ድንግልና በተመለከተ ለጠየቀችን

ለሁለቱም መልስ በአጭሩ በአጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል። ይህን ቪዲዮ ስመለከተው የተናገርሁት ጥቅስ ስሐተት መሆኑ ተረዳሁና ጥቅሱን ብቻ ከማስተካክል ለምን ሀሳቡንስ ትንሽ ጨመር አላደርግበትም ብዬ ነው ይህችን ጽሑፍ የሞነጫጨርኩት።

ጥቂት የማይባሉ በተለይ በእኛ ሀገር ያሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና ላለመቀበል የሚያነሷቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ አንደኛው ይህች ልጅ የጠየቀችው ነው። በዚሁ አጋጣሚ በጽሑፍም ትንሽ እናብራራው። ሌሎች ምክንያቶቻቸውን ደግሞ አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ጊዜ ማየት ይቻላል።

ዮሴፍ እጮኛዋ ለምን ተባለ?
ጠባቂዋ እንዲሆን።

የሚጠብቃትም ከሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ነው። የመጀመሪያው እንዲሁ በድንግልና ጸንሳ ብተገኝ ኖሮ በድንግልና መጽነሷን የሚያረጋግጡበት መንገድ ስለማይኖራቸው በሕጋቸው በምንዝር የተያዘች ሴት ላይ የሚፈረደውን ፍርድ ፈርደው በድንጋይ ወግረው እንዳይገድሏት ነው። ታዲያ ይህንን ለማድረግ እጮኛዋ ሳይሆን መጠበቅ አይችልም ወይ የሚል ቢኖር ያኛውማ የበለጠ ያስቀጠዋል። እንዲያውም እርሱንም ጭምር አመነዘረ ብለው አብረው ተቀጭ ያደርጉት ወይም ይወግሩት ነበር እንጂ እርሷን ለመጠበቅ ወይም ከሚያመጡት ጉዳት ለማዳን አያስችለውም ነበር። እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል ካልን ይህን የሚያውቅ ጌታ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ሕግ በኦሪቱ ሰጥቶ ነበር።

“ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ። ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። በተሳለችም ጊዜ ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበት ነገር ከአፍዋ በወጣ ጊዜ ባል ያገባች ብትሆን፥ ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል። ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርስዋ ላይ ያለውን ስእለትዋን ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበትን የአፍዋን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።”/ዘኁ 30 ፡ 2 -8/

በዚሁ አጋጣሚ ቪዲዮው ላይ ምዕራፍ 28 ለማለቴም ይቅርታ እጠይቃለሁ። በርግጥ ይህችን ለመጻፍም ምክንያቴ ይኼው ስሕተት ነው።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያለው መሠረታዊ መልእክት አንድ ነገር ነው። ይሔውም አንዲት ሴት በድንግልና ለመኖር ብጽዓት ቢኖራት ያን መጠበቅ ስለምትችልበት እና ስለማትችልበት ሁኔታ ማብራራት ነው። ከዚህ ውስጥ ብጽዓት ስትገባ አባቷ አይሆንም ካላት ታገባለች፤ እግዚአብሔርም ብጽዓቷን እንደሻረች አይቆጥርባትም። አባቷ ዝም ካለ ግን የድንግልና ብጽዓቷን ጠብቃ ትኖራለች ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከታጨች በኋላ ለእጮኛዋ ብጽዓቷን ነግራው ከተቀበለ ከእጮኛዋ ጋር ሆና ብጽዓቷን ለመጠበቅ መብት ይሰጣታል። እርሱ እንደሰማ ከተቃወመ ግን እጮኛዋ ባሏ ይሆናል ብጽዓቷም ይሻራል፤ በእግዚአብሔርም እንደበደለኛ አትቆጠርም ማለት ነው።

ይህን መነሻ ይዘን ዮሴፍ ባሏ ሆኖ የሚኖርማ ቢሆን ኖሮ “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ብላ መልአኩን ለምን ትጠይቀው ነበር? ስለዚህ ወዳጄ ሆይ አስተውል፤ ከላይ በኦሪቱ የተቀመጠው ቃል መጀመሪያም የተሠራው ይህን የእመቤታችን እና የዮሴፍ እጮኝነት እድፈት የሌለበት መሆኑን ለማመልከት እና በኦሪት ሕግ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማመልከት ነው ማለት ነው።
ሌላው እመቤታችን ካለምንም ወንድ በድንግልና ላለመጽነሷ ምን ማረጋገጫ አለ ከሚል ጥርጣሬም ነጻ እንድትወጣ የሆነችውም እመቤታችን ከዮሴፍ ጋር በመኖሯ ነው። ስለዚህ በድንግልና መጽነሷን ከመልአክክ ብሥራትም ጭምር በመረዳት በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ መሰናከያ እንዳይሆን ጠባቂዋ ዮሴፍ ነበረ። ለዚህ ነው መልአኩም “እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ” ያለው። እንዲህ ብሎ መልአኩ ለምን አሳሰበው ብለን ብንጠይቅ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው እውነታ ነው።

ሌሎች እንደሚሉት ሚስቱ ብትሆን ሊፈራ አይችልም። ሚስቱ ሳትሆንስ ለምን ይፈራል ብንል ደግሞ ሊያስፈራው የሚችለው ሁለት ነገር ነው። አንደኛው ብጽዓቷን አስፈረስክ ወይ? ተሳሳትክ ወይ የሚለው የሚያስፈራው ነው። ከእርሱ ጋር ካልሆነ ደግሞ ከአንተ ጋር በሚስትነት ካልኖረች ከማን ጸነሰች የሚለውንም ይፈራዋል። ምክንያቱም ይህን ሊመልሰው የሚችል አይደለምና። እንደተጻፈውም የሆነውን ሙሉ በሙሉ የሚያውቀው ጌታ ከተወለደ በኋላ ነውና። ስለዚህ ዮሴፍ የፈራው እመቤታችን በድንግልና ለመኖር በብጽዓት የምትኖር ስለሆነና እና በዚህም ጸንታ እንድትኖር ዮሴፍ ጠባቂዋ ሆኖ ስለተሰጠ ነው።
ጌታ እመቤታችንን ልክ ዮሐንስ መጠምቅን በበረሃ እንደጠበቀው በአምላካዊ ከሃሊነቶ እርሷን ሰውሮ እና ጠብቆ መወለድ ይችል ነበር። ያን ቢያደርገው ኖሮ ግን አምላክነቱን ቀርቶ አምላክ ሰው መሆኑንም ለማመን ያስቸግር ነበር። ለምን ምትሐት አለመሆኑን፤ እርሷም ኃይል አርያማዊት አለመሆኗን በምን ይታውቅ ነበር? ምትሐት ነው ቢሉስ? ከርሷ አልተወለደም ቢሉስ? እነዚህ ሁሉ በታወቀ ለታሪክ በመመዘገብ እና በሰዎች መካከል መደረግ ነበረበት ። ስለዚህ ዮሴፍ ሦስተኛው የጠበቃት ደግሞ በምትሐት እና መሰል ነገር ጸነሰች ወለደች ተብሎ የጌታ አምላክነት ከሌላ መንፈስ እና ከመሳሰሉት ጉዳቶችም እንዳይያያዝ የጠበቃት ዮሴፍ እጮኛዋ በመሆኑ ነው። ስለዚህ ዮሴፍ በትክክል የእመቤታችን እጮኛ ጠባቂዋ ነው። ለጌታችን በድንግልና መጸነስ እና መወለድ የመጀመሪያው ምስክር እርሱ ሆነ፤ ለዚህም የተመረጠ ሆነ ማለት ነው፤ በእውነት የዚህ ጻድቅ ሰው በረከቱ ይድረሰን።

@EotcLibilery
🔴 ቅዱሳንን ማገልገል || እጅግ ድንቅ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ቅዱሳንን ማገልገል
             
Size:-123.5MB
Length:-2:13:23

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ዘመቻ 50K#

በዐቢይ ጾም  የተለያዩ ትምህርቶች ፤ስብከቶች፤መጽሐፎች ፤አስተማሪ እና ወቅታዊ አጫጭር ጽሁፎች እንለቃለን

እርስዎም ይህ EOTC ቤተመጻሕፍት ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድና እንዲቀላቀሉ ቤተሰብ እንዲሆኑ በተለያዩ ግሩፖችና ቻናሎች ላይ  ሼር በማድረግ ይተባበሩ!
ሁላችንም በእግዚአብሔር ስም እንተባበር

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
EOTC ቤተ መጻሕፍት pinned «#ዘመቻ 50K# በዐቢይ ጾም  የተለያዩ ትምህርቶች ፤ስብከቶች፤መጽሐፎች ፤አስተማሪ እና ወቅታዊ አጫጭር ጽሁፎች እንለቃለን እርስዎም ይህ EOTC ቤተመጻሕፍት ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድና እንዲቀላቀሉ ቤተሰብ እንዲሆኑ በተለያዩ ግሩፖችና ቻናሎች ላይ  ሼር በማድረግ ይተባበሩ! ሁላችንም በእግዚአብሔር ስም እንተባበር @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery»
📣 ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን ቻናል በኛ ቻናል  ማስተዋወቅ ለምትፈልጉ ሰዎች ማስታወቂያ ቻናላችን ላይ በተመጣጣኘ ዋጋ እንሰራለን🤝 ......

በሰዓት
🔻 ለሙሉ ቀን = 2
150 ብር (24 ሰዓታት)
🔻ለ2 ሙሉ ቀን = 250 ብር

🔸 ለሳምንታዊ = 800ብር   + 3 pin
🔸 ለ2 ሳምንታት = 1200 ብር + 5 pin
🔸 ለ 1 ወር =  2000 or + 10 pin

VIP

🔷 ለሳምንታዊ = 1000 ብር (Daily Repost 4 + pin )

👇in box
@yesadikusitota

🔰 ማሳሰቢያ፡ ክፍያው የሚከፈለው ቅድሚያ ነው ከዛ post ይጀመራል እርሶ  የፈለጉትን መርጠው ምርትና አገልግሎቶን  ለብዙሃን ተደራሽ ያድርጉ📢
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🔴 ፈጽሞ አትጨነቁ ! || እጅግ ድን...
Enqo silassie
ፈጽሞ አትጨነቁ
             
Size:-123.5MB
Length:-1:41:49

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዓላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆሙ ምእመናን ጠየቁ !

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና መልእክቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ እና መንግስትም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ቲኤምሲ ያነጋገራቸው ምእመናን ገልጸዋል።

ማናቸውም ቤተ እምነቶች መብቶቻቸው እንዲከበር እንደሚፈልጉትና የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ በነጻነት ማስተላለፍ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው እንደህነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ ምእመናኑ በተመሳሳይም ሁሉም ቤተ እምነቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት እና አስተምህሮ ባከበረ መልኩ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ነጻነታቸውን ተጠቅመው በማናቸውም መልኩ ሃይማኖታቸውን እንዲያራምዱ ሕገ መኖግስታዊ መብታቸው ቢሆንም የሌላውን እምነት ማንቋሸሽ፣ ማኮሰስ እና ማጥላላት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ቀስቃሽና ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ባለፉት ጊዜያት ከአንዳንድ የሌሎች ቤተ እምነት ተከታዮች ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ንዋያተ ቅድሳት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በምታስተምቸው ትምህርቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች ሲተላለፉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

በተለይም መዋቅራዊ ድጋፍ እየተሰጠው በሚመስል መልኩ የጥላቻ ንግግሮች ተባብሰው መቀጠላቸው እና ይኹው ጥላቻም በኤሌክቶሮኒክስ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን በሜንስትሪም እና በመጽሐፍትም ጭምር ሲካሄድ መቆየቱ እና እየተካሄደ መሆኑ በርካታ ምእመናንን ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑ ተመላክቶአል።

መንግስት እነዚህን የጥላቻ አራማጆች እና ጸረ ሃይማኖት ግለሰቦችን በሕግ አግባብ እንዲጠይቅም ምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።

@EotcLibilery
Audio
የዐቢይ ጾም ጉዞ
           ክፍል 1  
Size:-103.3MB
Length:-1:51:39

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም  ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)

፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)

ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤
*ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
*ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤

፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ#አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡

፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
#በግብፅ_300_ዓመታት_#በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥
ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡
፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤
ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡

አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
አመ ፭ሱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ዋዜማ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ሃሌ ሉያ-
አባ አባ ክቡር ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክቡር፤ ብእሴ እግዚአብሔር፤ ተሰምዓ ዜናከ ውስተ ኲሉ ምድር፤ ድርገተ ኮንከ እንተ ላዕለ ኃይል፤ አባ፤ ጸሊ በእንቲአነ።

ምልጣን
ተሰምዓ ዜናከ ውስተ ኲሉ ምድር፤ ድርገተ ኮንከ እንተ ላዕለ ኃይል፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።


አመላለስ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤(2)
አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ፤(4)

💠ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።


💠እግዚአብሔር ነግሠ፦

ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።


💠ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር።

  💠ሰላም፦
አበው ቅዱሳን እለ ደብር ወገዳም፤ አስተምህሩ ለነ፤ ነሃሉ ወትረ በሰላም።

💠አመላለስ፦
እለ ደብር ወገዳም እለ ደብር ወገዳም/፪/
አስተምህሩ ለነ ነሃሉ ወትረ በሰላም/፬/

ዓዲ (ወይም)
💠ሰላም
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት፤ አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም።

💠አመላለስ፦
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት/፪/
አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም/፪/

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
አመ ፭ሱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ማህሌት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።


ዚቅ
ላህም መግዝዕ ተጠብሐ፤ ጽዋዓ መድኃኒት ተቶስሐ፤ አግብርት አግብርት አግብርት ይረፍቁ፤ ውስተ ሕፅኑ ለመርዓዊ፡፡

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።


ዚቅ
ወይሁቦ ጸሎቶ ለዘጸለየ፤ ወባረከ ዓመተ ጻድቃኑ፡፡


ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት፤ እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት።



ዚቅ(ሌላ)
ማርያም ቤዛ ብዙኃን፤ ሕይወተ ኮነት ለኲሉ ዓለም፤ ፍሥሐነ ለእለ አመነ፡፡

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።

ዚቅ
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ ከመ አዕዋፍ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ጽሑፍ፡፡

ወረብ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ/፪/
'ኀበ ዓምደ ወርቅ'/፪/ ስሙ ጽሑፍ/፪/


መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ሰላም፤ ዓቃቤ ሥርዓት ዘሤመ ወማዕፆ ሕግ ዘዓቅም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መነኮስ በምግባረ ሠናይ ፍጹም፤ እንበለ መብልዕ ወስቴ እንዘ ትትጋደል በጾም፤ ነጺራ ትዕግሥተከ አንከረት ገዳም፡፡


ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ፤ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ፤ ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ።

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ/፪/
ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ/፬/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከርሥከ ዘተሴሰየ ኅብስተ፤ አኮ ኅብስተ ምድራዌ እንተ ያመጽዕ ሐኬተ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኲሉ ይንዕዱከ ከሡተ፤ ብርሃነ ለዕውራን ወለሐንካሣን ፍኖተ፤ ወለበሐማን ቃለ ዘኮንኮሙ አንተ፡፡

ዚቅ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይከ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበስለ፤ ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይከ፤ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ  ሰማያት ዘተቀድሐ።

ወረብ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዌ ኅብስተ/፪/
አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት/፪/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ እንተ ረሰየ ህላዌ፤ ኀበ ኢሰማዕ ቦቱ ዜና ሞት ወዝክረ ደዌ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንተ ዘገዳማውያን ሠርዌ፤ ወረዱ ጊዜ ሞትከ ዑፁፋነ ፅዱል ሥርጋዌ፤ ከመ ይትቀበሉ ኪያከ መርዓዌ፡፡

ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡

ወረብ
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለገብረ ሕይወት/፪/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ብርሃነ ሰማይ ዘአገቶ፤ እለ ያዕቆብ ወዮሴፍ እስከነ ፈርሁ ቀሪበቶ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባዕል ለብዕለ ጸጋከ ዘያስተቶ፤ ኃያል ብእሲ ይንሣእ ሢመቶ፤ ወበዓለ ዕዳ ይበርብር ንዋዮ ወቤቶ፡፡


ዚቅ
ፀሐይ ፀሐይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ፤ ዘያበርህ ስኑ በውስተ ቀላይ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ዘባረኮ አግዚእ አዶናይ።


መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም መቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ፤ ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ፤ ዜና መቃብርከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ፤ ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም ዓፀድ፤ ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ፡፡

ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ፡፡

ወረብ፦
ወረደ ብርሃን ወረደ ብርሃን  ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤
ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ ጸሎቱ ለገብረ ህይወት፤

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ፦
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘእግዚአብሔር ገብር በእደ መላእክት ቅቡር፤ በኢየሩሳሌም ሀገር፤ ኀበ ኢይበጽሕ ሰብእ በእግር፤ እንበለ ዳዕሙ ዖፍ ዘይሠርር።


ምልጣን፦
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፬/

ወረብ
'ግሩማን መላእክት'/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ ህይወት/፪/


እስመ ለዓለም
ይትፌስሑ በኀበ አልቦቱ ሞት፤ይነሥኡ እሴቶሙ፤እስመ ትዕግሥት ተውህበ ሎሙ ከመ ይንሥኡ፤ብዙኅ ሕማሙ ለጻድቃን፤ ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር፤ወየዓቅብ ነፍሳቲሆሙ፤እስመ እንዘ ይነብሩ ውስተ ዓለም እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ ፤(ማንሻ-) ከመ ይንሥኡ አስበ ስብሐቶሙ፤ አክሊል ንጹሕ ዲበ ርእሶሙ


@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
2025/03/13 00:06:18
Back to Top
HTML Embed Code: