ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም ሲሉ የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አስታወቁ‼️
“የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አለ” የሚለውና ተደጋጋሚ የሆነ በተወሰኑ አካላት የሚነሳ ውንጀላ ፍፁም ሀሰት እና ግጭት ለመቀስቀስ ምክንያት ለመፍጠር ነው፤ የኤርትራ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ በሉዓላዊ ግዛታቸው ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲሉ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል።
ሚኒስተሩ አክለው ከዚህ ቀደም በብዙ አጋጣሚዎች በማያሻማ መልኩ እንደተገለጸው፣ ኤርትራ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም፤ በመሰረቱም ስምምነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ ኤርትራ በህወሓት የፖለቲካ አንጃዎች ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም ይህም በትግራይ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ እና ሊወገድ የማይችል ስቃይ ያስከትላል ሲሉ ተደምጠዋል።
በቀይ ባህር ዙሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ሌት ተቀን የሚያወጡት የማያቋርጥ ግጭት ቀስቃሽ መግለጫዎች ለአላስፈላጊ ውጥረቱ አባባሽ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል ያሉ ሲሆን ይህ ያለምንም ማወላወል በጠንካራ ሁኔታ መወገዝ አለበት ሲሉም የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አቶ የማነ ገብረመስቀል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት አስታውቀዋል።
@Esat_tv1

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣርና የቁርዓን ውድድር የፊታችን እሑድ በአዲስ አበባ ይካሄዳል‼️
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እና ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት በመጪው እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2017 በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
"ቁርአን - የእውቀትና የሰላም ምንጭ" በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ የማጣሪያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ቁርዓን በሁሉም መስክ የሰዎችን ሕይወት በቀና መንገድ በመምራት ለማህበረሰብ ከፍታ መሰረት መሆን የቻለ ነው።
በዚህ አግባብ ውድድሩ ይህን የቁርዓን ክብርና ከፍታ ለመግለጥ የተዘጋጀ መሆኑን መናገራቸውን አሐዱ ከምክር ቤቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ውድድሩ ቁርዓንን በልቦናቸው የተሸከሙ ሃፊዝ ወጣቶችን ለማበረታታትና ቀጣይ ተተኪ ትውልዶችን ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የዛሬው ውድድር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ማጣሪያ አልፈውና ተወክለው በመጡት መካከል ሲሆን፤ ዋናው ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እሑድ መጋቢት 7 ቀን 2017 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ አመልክተዋል፡፡
በዚሁ ቀን በርካታ አማኞች የሚታደሙበት ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ ሥርዓት "ከኢፍጣር እስከ ቁርዓን" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በሁለቱ ታላላቅ መርሐ ግብሮች ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Photo
"ፌደራል መንግስቱ በትግራይ ክልል የሚታየውን ውጥረት በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል"‼️
🗣 ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከፕሪቶሪያው ሥምምነት መፈጸም በኋላ አንጻራዊ ሰላም እየታየበት የነበረው የትግራይ ክልል ሁኔታ የፌደራል መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ሥምምነት መሠረት ታጣቂ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ፣ አካታች የሆነ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት አለመመስረቱን ተከትሎ ህወሓት የእርስ በእርስ ፍትጊያ ውስጥ ገብቶ በትግራይ ክልል ውጥረት መንገሱን ይገነዘባል፡፡ በእርግጥ ይህ ሁኔታ እንዳይፈጠር በመስጋት የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ ተተግብሮ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ደጋግመን ያቀረብነውን ማሳሰቢያ ሳይሰማ በዝምታ ያለፈው ፌደራል መንግስቱ አሁን ለተፈጠረው ቀውስ ድርሻውን መውሰድ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ኢዜማ በፓርቲው የውስጥ ጉዳይ ላይ የትኛውንም አስተያየት የመስጠት ፍላጎቱ የለውም፡፡ ሆኖም በህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በክልሉ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች እየሄዱበት ያለው ግትር፣ ግጭት ቀስቃሽ ህገወጥ እንቅስቃሴ ግን በጠቅላላው እንደሀገር በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ንፁሀን ዜጎች ላይ የሚያመጣውን ምጣኔ ኃብታዊ፣ ማኀበራዊ ብሎም የሰላምና የደኀንነት አስከፊ አደጋ በቅጡ እንረዳለን፣ ያሳስበናልም፡፡
ትግራይ ክልል አሁን ላለበት ውስብስብ ችግር የተዳረገው መሳሪያ ማንሳትን የተሻለ አማራጭ አድርጎ በሚወስደው ህወሓት የተነሳ መሆኑ እየታወቀ አሁንም የፓርቲው አመራሮች ምንም ሳይፀፀቱ ስልጣንን ጠቅልሎ በመያዝ ግብግብ ውስጥ ገብተው ለሌላ ዙር ግጭት የሚጋበዙ ከሆነ በተለይ በትግራይ ውስጥ ያሉ ዜጎች ሊረዱት የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ ይህ ስብስብ በምንም አይነት ሁኔታ ለማኅበረሰቡ ጥቅም የቆመ እንዳልሆነ ነው፡፡ በዚህ የፖለቲካ ሥልጣን ጥምን ለማርካት በሚደረግ መገፋፋት ውስጥ ባለመሳተፍ እንዲሁም ግጭት የሚቀሰቅሰውን የትኛውንም ኃይል በግልፅ በመቃወም የክልሉ ነዋሪ በአንፃራዊነት ያገኘውን ሰላም ሊያስጠብቅ ይገባል፡፡ በተግባር መሬት ላይ በግልፅ እንደሚታየው ጥቂት ግለሰቦች የዜጎች ሰላምና ደኀንነት ሳያስጨንቃቸው የግል ሥልጣን ለመጨበጥ ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ወዳድ ዜጎች ሁሉ በአንድ ላይ በመቆም ይህ ቡድን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማስጠንቀቅ ደግሞም የትኛውም ፀብ አጫሪ ተግባሮቹ ላይ ባለመሳተፍ የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው ማሳየት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡
በተለይ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በክልሉ የተፈጠረውን ትርምስ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ሊያስቆም ሲገባ ይህን አለማድረጉ ሳያንስ አሁንም ራሱን እንደሩቅ ተመልካች በመቁጠር በጉዳዩ ላይ ተጨባጭ መፍትሔ እንዲመጣ አለመስራቱ ብሎም የፕሪቶሪያው ስምምነትን በአግባቡ እንዲፈፀም ባለማድረጉ ንፁሀን ዜጎች በህይወታቸው እና በአካላቸው ዋጋ እየከፈሉ መምጣቱ ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን አውቆ አሁንም ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በሚያስችል ህጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ የመንግስትነት ሚናውን እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 05/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ሱዳን ተፋላሚዬን ትደግፋለች በሚል ከኬንያ የሚገቡ ምርቶችን በሙሉ አገደች‼️
ሱዳን ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት ከሠራዊቱ ጋር እየተዋጋ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ)ን በናይሮቢ ማስተናገዷን ተከትሎ ከኬንያ የሚገቡ ምርቶችን በሙሉ አገደች።
ባለፈው ወር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና ተባባሪዎቹ በሱዳን ትይዩ መንግሥት የመመስረት ፍላጎት እንዳላቸው የሚገልጽ መመስረቻ ቻርተር በኬንያ ተፈራርመዋል።
የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ምርቶቹ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ የጣለው እገዳ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እና "ብሔራዊ ደህንነቷን ለመጠበቅ" ነው ብሏል።
በጦርነት የምትታመሰው ሱዳን ሻይ፣ የምግብ እቃዎች እና የመድኃኒት ምርቶችን ጨምሮ በርካታ ምርቶችን ከኬንያ ታስገባለች።
የሱዳን ንግድ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ከኬንያ በሁሉም ወደቦች፣ አየር መንገዶች፣ እና መሸጋገርያ ኬላዎች የሚመጡ ማንኛውም ዓይነት ምርቶች ከዛሬ ጀምሮ ተጨማሪ መመርያ እስኪሰጥ ድረስ ታግደዋል" ብሏል።
አስከትሎም "ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እገዳውን በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ" አዝዟል።

ወደ ሀገር አቀፍ የቁርኣን ሒፍዝ ውድድር በታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር 5 ሲመጡ ምዕመናን ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች‼️
👉የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፈቃድ አስተባባሪዎች ፍተሻ ትብብር ማድረግ
👉የሰላት መስገጃ እና ጥላ ይዘው ይምጡ
ማንኛውም ለደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ
👉የ CAR PASS ያላቸው ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን ጊዮን ሆቴል ጊቢ ውስጥ እና እስታዲየም አካባቢ መኪና እንዲያቆሙ::
👉የ CAR PASS ካላቸው እንግዶች ውጭ ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን በአቅራቢያ ባሉ በኮሪደር ልማቱ በተሰሩ አልያም ሌሎች ምቹ በሆኑ ስፍራዎች መኪና እንዲያቆሙ::
👉ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋራት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ እናደርጋለን:: ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል::
👉ከፕሮግራሙ አላማ ውጭ ማንኛውም ተግባር ተቀባይነት የሌለው መሆኑ
በከተማችን የትራንስፖርት ችግር መኖሩ የሚታወቅ በመሆኑ የግል ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን
👉ፆመኞችን ወደ ዝግጅቱ ሲመጡ እና ሲመለሱ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ትብብር ቢያደርጉ::
👉ለኢፍጣር የተዘጋጁ ምግቦችን ከመብልነት ውጭ መጠጦችን ከመጠጥነት ውጭ በመጠቀም ማባከን እና ከዝግጅቱ ዓላማ ውጭ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባራችንን ለሌሎች አርአያ በመሆን ማሳየት

ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እግድ የተጣለባቸው ሀገራት እነማን ናቸው ?
የትራምፕ አስተዳደር 43 ሀገራት ላይ የቪዛ እግድ መጣሉ ተነግሯል። እግዱ ሦስት ክፍሎች ያሉት መሆኑን ጊዜያዊ እቅዱ እንደሚያሳይ ተዘግቧል።
በዚህም በመጀመሪያው ምድብ ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የተከለከሉት ውስጥ ሶማሊያ እና ሱዳን ይጠቀሳሉ። ሰሜን ኮሪያም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በከፊል እግዱ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ደግሞ ኤርትራ፤ ደቡብ ሱዳን እንዲሁን ማይናማር ይገኙበታል። በዚህም የእነዚህ ሀገራት ዜጎች በቱሪስት፣ በትምህርት እና መሰል ቪዛዎች ተከልክለዋል።
ሌሎች ወደ 26 የሚደርሱ ሀገራት ደግሞ የጸጥታ ሁኔታቸው ወይም ለአሜሪካ መንግስት በ60 ቀናት ውስጥ በሚሰጡት መረጃ ላይ ተንተርሶ የሚወሰን እግድ ቀርቧል።
የሀገራቱ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ሊቀንስ እንደሚችል ተነግሯል።
🔗ሙሉ የሀገራቱ ዝርዝር በምስሉ ተያይዟል።

ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ አሸናፊዎቹም እያንዳንዳቸው የመኪና ሽልማት ተበረከተላቸው‼️
‘ቁርዓን - የእውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሐሳብ በሁለቱም ጾታዎች ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
በዚሁ መሠረት በወንዶች ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሳላሀዲን አብዱረህማን እንዲሁም በሴቶች ከአማራ ክልል ሀፍሷ ከድር የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ሁለቱ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
2ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች ለወንዶች የሀጅ ማድረግ ስጦታ ሲሆን ለሴቶች 500ሺ ብር ይበረክታል።
3ኛ ለወጣ ተወዳዳሪም የ300ሺ ብር ሽልማት ይበረከታል።