tgoop.com »
United States »
Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት » Telegram Web
የኢትዮጵያን የትምቧሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎችን ለማጠናከር የተደረገው ጥናት ውጤት ይፋ ሆነ
-----------------------
ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች መንስኤ የሆነውን ትምባሆን የመጠቀም ልምድን ወይም ሱስን መከላከል በኢኮኖሚና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ጫና በማቃለል ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ነው ሲሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተናገሩ። የፌዴራል የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ዛሬ ሲካሄድ በቆየው የኢትዮጵያን የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎችን ለማጠናከር በቀረበ ምክረ-ሃሳብ ላይ ነው ይህን ያስገነዘቡት።
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የምክክር ጉባኤውን ሲከፍቱ እንዳሉት፣ የትምባሆ ሱስ ተላላፊ ላልሆኑት እንደ ስኳር በሽታ፣ የልብ ህመምና የመተንፈሻ አካላት ችግሮች መንስኤ ነው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ትምባሆ ለኢኮኖሚና የማህበረሰብ ጤና ቀውስ ዋና መንስኤ እንደሆነ አስታውሰዋል። “ስለዚህም፣ ይህን የሃገሪቱን አምራች ዜጎች ተጠቂ እያደረገ ያለ ችግርን ለማስወገድ የጤና ሚ/ር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንና ሌሎች አጋር አካላት በተከታታይ በማጥናትና በመከላከሉ ረገድ እያደረጉት ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑ ሁላችንንም ያበረታታናል፣” ብለዋል።
ሚ/ር ዴኤታው እንዳሉት በተደረገው ጥናትና ተከትሎም በተወሰደው እርምጃ፣ ከ21 ዓመት በታች ያሉ ወጣት ታዳጊዎች ትምባሆ እንዳያገኙ፣ ሰው በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሲጋራ እንዳይጨስ፣ እና በሌሎችም እርምጃዎች አጥጋቢ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል። “ህ/ሰቡን ስለ ትምባሆ አደገኛነት ትምህርት በመስጠት፣ የአመጋገብ ባህላችንን እንዲሻሻል በማድረግ፣ የአካል እንቅስቃሴዎች እንዲዘወተሩና የአካባቢያችንንም ፅዳት በመጠበቅ ረገድ ያልተቋረጠ ትምህርት በመስጠትም ብዙ ስራ ተሰርቷል፣” ብለዋል፣ ሚ/ር ዴኤታው።
ዶ/ር ደረጀ በመጨረሻም የኢትዮጵያን የትምቧሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎችን ለማጠናከር የተደረገውን ጥናት ላከናወኑ አካላት፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለዓለም የጤና ድርጅት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ “የአዋቂዎች የትምባሆ አጠቃቀም ዳሰሳ (Global Adult Tobacco Survey-GATS) ጥናት በአስተማማኝ ምርምር ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ጤና ማሻሻያ ተግባራትን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሌላ ማረጋገጫ ነው” ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፋ የጤና ጉዳት እንዲሁም ለሞት ከሚዳርጉ ግንባር ቀደም መንስኤዎች አንዱ የሆነው ትምባሆን የመጠቀም ልምድ በየዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት፤ እንዲሁም በዚህ ሳቢያ በሚመጡ ተዛማጅ የጤና እክሎች ወደ 7 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን እያጡ ነው ብለዋል። ጨምረውም 1.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ በመጋለጥ ሳቢያ በሚመጡ በሽታዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ አስገንዝበዋል።
ትምባሆን የመጠቀም ልምድ በሃገራችን እያስከተለ ያለውን ችግርም እንደሚከተለው አሳይተዋል። “እ.ኤ.አ. በ 2016 በኢትዮጵያ በተከናወነው የመጀመሪያው ዙር የGATS ጥናት መሰረት 5% (3.4 ሚሊዮን) አዋቂ ኢትዮጵያውያን የትምባሆ ተጠቃሚዎች እንደነበሩ ያሳያል። በሌላ በኩል የ2016 (እ.ኤ.አ.) ሪፖርት እንዳመለከተው ትምባሆ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በሚመጡ የጤና ችግሮች ሳቢያ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ17,000 በላይ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን ያመለክታል።”
ዶ/ር መሳይ በጥናቱ የተገኘውን ውጤትም በሚከተለው ሁኔታ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የችግሩን ጉልህነት እና አጣዳፊነት በመገንዘብ የትምባሆ አጠቃቀምን ለመከላከል ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎችን ወስዷል። በዚሁ መሰረት የዓለም ጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ማዕቀፍ (WHO FCTC) በ2004 ዓ.ም በማስፅደቅ ወደስራ ተገብቷል። በተጨማሪም በዚህ ማዕቀፍ ላይ በመመስረት በ2019 ዓ.ም ጠንካራ የትምባሆ ቁጥጥር ህጎችን ያካተተ አዋጅ በማስፅደቅ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ አዋጁም የሚከተሉትን ጠንካራ ህጎች አካቷል፤ (1) ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ቦታዎች 100% ከትምባሆ ጭስ-ነጻ ፖሊሲ፣ (2) ነጠላ-ሲጋራ ሽያጭ ክልከላ፣ (3) ጣዕም ያላቸው የትምባሆ ምርቶች እና የኤሌክትሮኒክስ ሲጋራዎች እገዳ፣ (4) የትምባሆ ማሸጊያ ካርቶኖች ላይ 70% የሚሸፍኑ ሥዕላዊ የጤና ማስጠንቀቂያዎችን አስገዳጅ ማድረግ ይገኙበታል።
እንደ ዶ/ር መሳይ አባባል የሁለተኛው ዙር የGATS ጥናት የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ከተከናወነ ከስምንት አመታት በኋላ በመሆኑ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተደረጉ ለውጦችን ለመገምገም እና ተጨማሪ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለመለየት ታሳቢ ተደርጎ ነው። “ይህ ጥናት በትምባሆ አጠቃቀም ለውጦች፣ ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ ለሲጋራ ጭስ የመጋለጥ ደረጃን፣ ትምባሆ ተጠቃሚዎች ማጨስ ለማቆም የሚያደርጉት ጥረት፣ በተጨማሪም ማህበረሰቡ ትምባሆ በመጠቀም እንዲሁም ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ መጋለጥ ስለሚያመጣው የጤና ጉዳት ያለውን የግንዛቤ ደረጃ ለመዳሰስ ያስችላል” ብለዋል፣ ዋና ዳይሬክተሩ።
በመጨረሻም በጥናቱ ውጤት መሰረት ኢትዮጵያ ትምባሆን ከመቆጣጠር አንጻር ከፍተኛ እመርታ ብታሳይም፣ ብዙ መከናወን ያለባቸው ስራዎች እንዳሉ አመላካች መሆኑን አስምረውበታል።
በመሆኑም የጥናቱ ውጤት ላይ ተመስርተን ያሉብንን ክፍተቶች በመለየት፤ ለፕሮግራም እና ለፖሊሲ ግብአት በመጠቀም የዜጎቻችንን ጤና መጠበቅ፣ መጪው ትውልድ በትምባሆ ሱስ ውስጥ እንዳይወድቅ ማድረግ እንዲሁም ኢትዮጵያን በትምባሆ ቁጥጥር ውስጥ ግንባር ቀደም ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ሄራን ገርባ፣ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በዋናነት፣ እንዲሁም በሌሎች ድርጅቶች አጋርነት የተሰራው የምርምር ስራ ውጤታማነቱ ሁሉንም ሊያስደስት ይገባል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ስለጥናቱ ሲገልጹም፣ የአዋቂዎች የትምባሆ አጠቃቀም ዳሰሳ (Global Adult Tobacco Survey-GATS) በማስረጃ ላይ የተመሰረተ፣ ፖሊሲ ማውጣትን የሚደግፍና የዓለም ጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ስምምነትን በመተግበር ላይ ያለውን ሂደት የሚለካ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ጥናት ነው ብለዋል። “በGATS 2024፣ ኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥርን ለማጠናከር ባደረገችው ጥረት አበረታች ውጤቶችና ክፍተቶችን ለማወቅ ተችሏል ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል።
የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው በአሁኑ ወቅት 4.6 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን (በጉልምስና ደረጃ ላይ ያሉ ወይም በተለምዶ አዋቂዎች)፣ ትምባሆ የሚጠቀሙ ሲሆን፣ በጾታ ረገድ ሲታዩ 8.8 በመቶዎቹ ወንዶች፣ 0.5 በመቶዎቹ ደግሞ ሴቶች ናቸው፣ እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ።

ዋና ዳይሬክተር ሄራን እንደሚሉት በዚህ ጥናት የትምቧሆ አጠቃቀም በሴቶች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ከስምንት ዓመታት በፊት (በእ.ኤ.አ 2016) የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፣ 2.1 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች በአጫሽነት ሲመዘገቡ፣ በአሁኑ ሰዓት በተገኘው የጥናት ውጤት መሰረት፣ ቁጥራቸው ወደ 0.5 በመቶ ወርዷል።
ለግማሽ ቀን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና በዓለም የጤና ድርጅት በጋራ የተደረገው የምክክር አውደ ጥናት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ በጥናቱ የተገኘውን ውጤት አስመልክተው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በጥናቱ ሂደት ላይ በአመራርነት የተሳተፉ ተመራማሪዎችና የስራ ሃላፊዎች በተለይም አቶ ቶሎሳ ገመዳና አቶ ኪሩቤል ተስፋዬ በጥናቱ የተገኙ ውጤቶችን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመቀጠልም ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችንና ማብራሪያዎችን ያስቀደመ ጥልቅ ውይይት በተሳታፊዎች ተደርጓል።
በኢሊሌ ሆቴል በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ ቁጥራቸው ከ80 በላይ የሚደርሱና ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ተመራማሪዎችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።
www.ephi.gov.et/news

ኢንስቲትዩቱ በዓለም አቀፍ የትግበራ ልምምድ መድረክ (global simulation exercise) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያን ወክሎ ከአፍሪካ 3፣ ከዓለም ደግም 21 ሀገራት በሚሳተፉበት GHEC “Exercise Polaris” በተባለ የዓለም አቀፍ የትግበራ ልምምድ መድረክ (global simulation exercise) ላይ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በመሳተፍ ላይ ነው፡፡
የትግበራ ልምምዱ መጋቢት 25 እና 26/2017 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከሰቱ የሚችሉትን አዳዲስ አደገኛ የቫይረስ ተህዋሲያን ወረርሽኝ የመከላከል፣ የመቆጣጠር እና ምላሽ የመስጠት አቅምን ለመፈተሽ ዓላማ ያደረገ ሲሆን በሕብረተሰብ ጤና ዝግጁነት፣ በቅኝትና በሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበር ላይ የሚሰሩ የኢንስቲትቱ ስትራቴጅክ ከፍተኛ አመራር፣ባለሙያዎች፣ እና የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የቅርንጫፍ ቢሮ በማስተባበርና በመገምገም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
Ethiopia is participating in GHEC Exercise Polaris from April 3-4, 2025.
The WHO head quarter (HQ) Geneneva has facilitated a global Health Emergency Corpus (GHEC) Simulation Exercise “Exercise Polaris” from April 3-4, 2025.GHEC is the body of experts in ministries and agencies at work on health emergencies and response coordination.
Ethiopia is one of the 21 countries in the world and the third country to participate in Exercise Polaris.
The exercise aimed at testing the Coordination capacity of countries to control an emerging viral pandemic threat through strategic decision-making, team deployments and information-sharing to contain the pandemic threat.

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አካሄዱ
በጉብኝቱም የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶክተር ታደለ ቡራቃ፣ የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች
ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ ዶ/ር መልካሙ አብቴ፣ ዶ/ር ሳሮ አብደላ እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያን የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ አስተዳደር፣ የበሽታ ክትትልና የወረርሽኝ ምላሽ ሥርዓቶችን ለማዘመን እያከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ እንደሆነ ጠቁመው ወባን ጨምሮ ወቅትን ጠብቀው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከሰቱ ወረርሽኖችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናከሮ መቀጠል እንደሚገባ እንዲሁም በሕብረተሰብ ጤና ምርመር እና ላቦራቶሪ አቅም ግንባታ በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም አበረታች መሆናቸዉን ገለጸዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከሌሎች ተቋማት ጋር እደረገ ያለውን ቅንጅታዊ ስራ በማጠናከር መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በኢንስቲትዩቱ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ምሁራንና ባለሙያዎችም ተገቢው ጥቅማ ጥቅም እና ማበረታቻ እንዲያገኙ የተጀመረው ጥረት ለውጤት እንዲበቃ ቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊውን ጥረት እንደሚያደርግ የተከበሩ ዶ/ር ታደለ ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው ለተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶች እና ወረርሽኞች ምላሽ በመስጠትና የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተፅእኖዎችን በመቀነስ ረገድ ዉጤታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጠንካራ የሕብረተሰብ ጤና እና የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥር ሥርዓት ለመገንባት እና ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የተለያዩ ጤና ሥጋቶችን እና የወባን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየደረጃው ካሉ ጤና መዋቅሮች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የህብረተሰብ ጤና ምላሽ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት ቅኝትና ምላሽ፣ በሪፌራልና ማጣቀሻ ላብራቶሪ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ከፌዴራል እስከ ክልሎች እያጎለበተ ያለዉ አቅም፣ እያከናወናቸው ያሉ ችግር ፈቺ የህብረተሰብ ጤና ምርምር እና የጤና መረጃ ቅመራና ትንተና ስራዎች በጉብኝቱ በሰፊው ታይተዋል። ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ የማይከናወኑ ተላላፊ በሽታዎችን ለመለየትና እና በስርዓተ ምግብ ላይ ለሚደረጉ ምርምሮች የሚረዱ የላቁ ላብራቶሪ ምርመራዎች በኢንስቲትዩቱ መጀመራቸው የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና ችግሮችን በመለየት ተገቢውን ምላሽ መስጠት ማስቻሉን፣ እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር ከጤና ሚኒስቴር ክክልል ጤና ቢሮ እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ የምላሽ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን በመስክ ምልከታው ለመረዳት ተችሏል፡፡
በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው የተገኙ ጥንካሬዎች እና ስኬቶች አበረታች መሆናቸውን እና አጠናክሮ በመቀጠል እንደሚያስፈልግ በመግለጽ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የበለጠ ማረጋገጥ እንደሚገባም የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡