Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ሰላም ውድ ቤተሰቦቸ ለእናንተ አሪፍ የ online ስራ መስራት ለምትፈልጉ በሙሉ ታላቅ የምስራች አለኝ!

የ C3ai campany በአሁኑ ወቅት እንደዚህ እየቀጠረ ነው ያለ፣ በትርፍ ሰዓታችሁ ብቻ በየዕለቱ ዕለታዊ ገቢ በየ ሳምንቱ ደግሞ ሳምንታዊ ደመወዝ እንዲሁም አመታዊ ኮንትራት መፈራረም የምትችሉበትን መንገድ በደንብ የተሟላ ነው።

ስለሆነም ይህንን ታላቅ እድል ተጠቅማችሁ አሁኑኑ በስራ አጥነት የተቸገራችሁ፣ ምን ልስራ ብላችሁ የተጨነቃችሁ፣ የቤት ኪራይ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ፣ የወር አስቤዛ የቸገራችሁ በሙሉ በዚህ ካንፓኒ በመስራት ሕይዎታችሁን የተሻለ ማድረግ ትችላለሁ።

መስራት የማትፈልጉ ያለ አይመስለኝም። የበለጠ ደግሞ በ
@Ngbaeke_Habe_Tnte_Neger ላይ አናግሩኝ። ሁሉንም ነገር አስረዳችኋለሁ።
ስራውን አንድትጀምሩ አደርጋችኋለሁ። ተቀጥራችሁ ጥሩ ገቢ ታገኛላቸሰሁ።

ኑ እንነጋገር 👇
@Ngbaeke_Habe_Tnte_Neger
🇪🇹🇪🇹🇪🇹፳፻፲፯|201፯🇪🇹🇪🇹🇪🇹
             በዓለ ጥምቀት
  💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️
"🙏በጊዜው በዘመኑ ሁሉ ከአብ ጋር ትክክል የባሕርይ አምላክ ሲሆን ሰው እንደመሆኑ በሥጋ አካል በየጥቂቱ አደገ፤
በመለኮቱ ፍጥረቱን ሁሉን የሚያከብር ሲሆን ለሰው እንደሚገባ በዮርዳኖስ  በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ!🙏"
🕯ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ🕯

" በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።"
(የማርቆስ ወንጌል 1:9)

ይህን ቀድሞ ያወቀ ዳዊትም እንደህ ሲል አስቀድሞ ጠየቀ👇

"ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ። አድባር አንፈራጹ ከመ ሐራጊት ወአውግርኒ ከመ መስአ አባግዕ።
👉ምንተ ኮንኪ ባሕር ዘጎየዪኪ ወአንተኒ ዮርዳኖስ ዘገብእከ ድኅሬከ።👈"
መዝ 113፥2-5

✟✟✟💚✟✟✟💛✟✟✟✟✟✟

                    እንኳን
ለአምላካችን ለጌታችን ለመድኃኒታችን    
         ✟ ለኢየሱስ ክርስቶስ  ✟
             የጥምቀት በዓል
              👉በሰላም 💚
              👉በጤና   💛
              👉በፍቅር  ❤️
     🙏አደረሰን🙏አደረሳችሁ 🙏

መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል!
         💚  ሠናይ 💛 በዓል ❤️
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@EthioBetecrstian


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ጌታችን ጥምቀት


እነሆ በዚች ዕለት በውኃ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት እጠመቃለሁ፡፡ ውኃው የኃጢአትን እድፍ የማጠራበት ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስም መሬታውያኑን ሰማያውያን አደርግበታለሁ፡፡ በእሳቱም የኃጢአት እሾህን አቃጥልበታለሁ።

ዮሐንስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ በታላቅ ፍርሀትና መንቀጥቀጥ በብዙ ትሕትናም በጌታ ኢየሱስ ራስ ላይ እጁን ዘርግቶ አጠመቀው፡፡ ሰነፎች አይሁድ ይህን ባዩ ጊዜ ዮሐንስ ከክርስቶስ ይልቅ እጅግ ይከብራል፡፡ ክርስቶስም ከእርሱ ያንሳል፡፡ እንዲህስ ባይሆን ኑሮ ከእርሱ ባልተጠመቀም ነበር አሉ፡፡

እግዚአብሔር አብም የአይሁድን ሐሳብ ያውቃልና ይህችን ሐሳብ ከልቡናቸው ያርቅ ዘንድና እርሱ በመለኮቱ ክብር ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ የሚወደው ልጁ እንደ ሆነ ያስረዳቸው ዘንድ ወደደ፡፡

ስለዚህ ሰማይን ከፍቶ መንፈስ ቅዱስን በርግብ አምሳል ሰደደ፡፡ በራሱ ላይም ተቀመጠ፡፡ በታላቅ ቃልም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ብሎ ተናገረ። ዳግመኛም በሥጋ የተወለደው እርሱ በመለኮቱ ክብር ከእኔ ጋር አንድ ነው፡፡ ከቀደመ ግብሩ ሳይለወጥ ሰው ሆኗልና፡፡ እኔ የወለድሁት ማርያም ከወለደችው የተለየ አይደለም፡፡ በጎል የተኛው ሰብአ ሰገል ከሰገዱለት ልዩ አይደለም፡፡ እርሱ በኔ ህልው ነው፡፡ እኔም በእርሱ ህልው ነኝ፡፡

በሥጋውም ተገልጦ ይታያል፤ በመለኮቱ ተኣምራትን ያደርጋል፡፡ ከማርያም በሥጋ ለተወለደው ልደቱ አባትን አትፈልጉ፡፡ ከዓለም ሁሉ በፊት ከኔ ለተወለደው ልደቱም እናትን አትመርምሩ፡፡ መለኮቱንም ከትስብእቱ አትለዩ፡፡

በእርሱ መጨመርና መለየት የለበትምና፡፡ ክርስቶስ ብቻውን አምላክ ብቻውንም ሰው አይምሰላችሁ፡፡ ሰው የሆነ አምላክ ነው እንጂ፡፡ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ወልድ ዋሕድ በተጠመቀ ጊዜ እግዚአብሔር አብ እንዲህ በማለት ተናገረ።

ዳግመኛም የወልድ ፊቱ በደብረ ታቦር በተለወጠ፣ መልኩም እንደ ፀሐይ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ባበራ ጊዜ እግዚአብሔር አብ እንዲህ አለው፡፡ ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት››፡፡

ይቀጥላል.....

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 55-67)

#ይቀላቀሉን!
@Ethio_Betecrstian
✞ ፀሐየ ጽድቅ ✞:


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ካልዕ ድርሳን ስለ ጌታችን ጥምቀት


የተወደዳችሁ ማኅበረ ምእመናን ወንድሞች ሆይ ለሐዲስ ልደት ቅድስት የምትሆን የጥምቀት ውኃ በሚቀደስበት ዕለት የነቢዩ የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ በገዳመ ዮርዳኖስ የሰበከውን ስብከት ስሙ፡፡ ከይሁዳ ሀገሮች ከሰማርያና ከኢየሩሳሌም አውራጃዎች ሁሉ አሕዛብ ወደ እርሱ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ እርሱ ሊጠመቁ ለመጡት አይሁድ በታላቅ ቃል አሰምቶ እንዲህ አላቸው፡፡

ዳግመኛም እንዲህ አላቸው እኔ በውኃ ለንስሓ አጠምቃችኋለሁ። ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስ ለኃጢአት ሥርየት ያጠምቃችኋል፡፡ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ ይበረታል፡፡ ከዓለም ሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው፡፡ ከእኔ በኋላ የሚመጣው በእጅጉ ከእኔ ይበልጣል፡፡ ልዕልናውን ልናገር አይቻለኝም፡፡ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ጌታየ ነው፡፡ የእግሩን ጫማ ማዘቢያም (ማሠሪያ) እፈታ ዘንድ አይቻለኝም፡፡

ዮሐንስ የጌታ ጫማ ያለው ምንድን ነው? እንደዚህ ያለውስ ሰው ስለ መሆኑ ሲናገር ነው፡፡ እንደሚበረታ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፡፡ ጌታ ከእርሱ ዘንድ ወደ እርሱ ለመጡት ሁሉም እንዲህ እያለ ሰበከ፡፡

እነርሱ ግን ዮሐንስ ሆይ ስለምን ራስህን ታሳንሳለህ? ብለው ዮሐንስን ተቃወሙት፡፡ እውነተኛ ነቢይ ሆይ አንተ የታላቁ ካህን የዘካርያስ ልጅ አይደለህምን? አንተ በኤልያስ የተመስልህ አናብስት ከፊትህ የሚሸሹልህ አይደለህምን?

ነቢይና ቅዱስ ሆይ አንተ መልአኩ ገብርኤል ስለ ልደትህ በቤተ መቅደስ የተናገረልህ አይደለህምን? አንተ የእግዚአብሔር የጸጋው ሀብት በላዩ የበዛለት ዮሐንስ አይደለህምን? ስለምን ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ ይበረታል ትላለህ? ከአንተ የሚበልጥ የለም አሉት፡፡

ያን ጊዜ ዮሐንስ ለጌታው እንደ ሚታዘዝ ትሑት አገልጋይ ዝቅ ዝቅ አለ፡፡ በፊታቸውም እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ፡፡ እናንተ የማታውቁትን ትናገራላችሁ፡፡ እኔ ደግሞ የማውቀውን እናገራለሁ፡፡ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ ብርቱ ነውና፡፡ እኔም በዚህ ሰማያዊ ንጉሥ ፊት መንገዱን ልጠርግ ተልኬያለሁና፡፡ እኔ በዚህ ንጉሡ ፊት አገልጋይ ነኝ፡፡

ዳግመኛም እንዲህ አላቸው፡፡ እኔ በቤት ውስጥ በማዕዘን ላይ እንደ ተቀመጠ መብራት ነኝ፡፡ እርሱ ግን ለሁሉ እንደሚያበራ ፀሐይ ነው፡፡ በእኔ ላይ ያደረው የሕይወት መንፈስ ነው፡፡ እርሱ ግን ለሁሉ ሕይወትን የሚያድል ነው፡፡ እኔ ንስሓን የምሰብክ ነኝ፡፡

እርሱ ግን ኃጢአትንና በደልን ሁሉ ይቅር የሚል ነው፡፡ እኔ ስለ እውነት እናገራለሁ፡፡ እርሱ ግን በእውነት ፍርድ ምሕረትን ለጻድቃን ይሰጣል፡፡ ስንዴውን ወደ ጎተራ እንደሚሰበስብ ቅዱሳንንም ወደ እርሱ ይሰበስባቸዋል፡፡ ገለባውን በእሳት እንደሚያቃጥልም ኃጥአንን ወደ ዘለዓለም እሳት ይሰዳቸዋል፡፡

እኔ በውኃ ለንስሓ አጠምቃችኋለሁ፡፡ ጽዋውንም ውጩን አጥበዋለሁ፡፡ እርሱ ግን የጸጋውን ሀብት ይሰጣል፡፡ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስም ያጠምቃችኋል፡፡ የመለኮቱን ብርሃንም በላያችሁ ላይ ያወጣል፡፡ ለመንግሥቱ የበቃችሁም ያደርጋችኋል፡፡

ዮሐንስ ወደ እርሱ ይጠመቁ ዘንድ ለመጡት አሕዛብ እንዲህ ሲላቸው እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፡፡ እነሆ ዮሐንስ ከእርሱ በኋላ የሚመጣው ከእርሱ ፈጽሞ እንደሚበልጥ ይህን ነገር በጆሯችን ነገረን፡፡ የዮሐንስ ነገሩ እውነት እንደ ሆነና እንዳልሆነ ዐይተን እናውቅ ዘንድ አሁን ይቆየን ተባባሉ፡፡

ይህን ሲነጋገሩም እነሆ ጌታ መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ከሰዎች እንደ አንዱ ቆመ፡፡ ዮሐንስም ባየው ጊዜ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፡፡ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው፡፡ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እሱ ከእኔ ይበልጣል ያልኋችሁ ይህ ነው፡፡ ኃጢአታችንና በደላችንን ሁሉ ይቅር የሚል የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው፡፡ ክርስቶስም መጥቶ ከእርሱ ይጠመቅ ዘንድ ራሱን ወደ አጥማቂው ዮሐንስ ጎንበስ አደረገ፡፡

ዮሐንስም የሚያደርገውን አይቶ ታላቅ ፍርሀትን ፈራ፡፡ ደነገጠ ተንቀጠቀጠም፡፡ እንዲህም አለው፡፡ እኔ ታጠምቀኝ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ አንተ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ይህ ግብር ምንድን ነው? አቤቱ ጌታዬ ሆይ እኔ ስለ አንተ ለአሕዛብ ነገርኋቸው፡፡

እኔ በውኃ ለንስሓ አጠምቃችኋለሁ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን እርሱ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል አልኋቸው፡፡ እኔ መምጣትህን ተናገርሁ፡፡ ልዕልናህንና የኃይልህንም ጽናት አብዝቼ ተናገርሁ፡፡ አንተ ግን እንደ እንደ ተራ ሰው ሆነህ ወደ እኔ ትመጣለህ፡፡

አቤቱ ጌታ ሆይ አንተ በሰማይ የንጉሥ ልጅ ነህ፡፡ በምድርም አንተ ንጉሥ ነህ፡፡ ነገር ግን በአንተ ላይ የማየው የንጉሥ ምልክት ምንም የለም፡፡ ክብርህ ወዴት አለ? የመንግሥትህ ልዕልናስ ወዴት አለ? መላእክቶችህስ ወዴት አሉ? ሠራዊቶችህስ ወዴት አሉ? ዐይኖቻቸው ብዙ የሆኑ አርባዕቱ እንስሳስ ኪሩቤልስ ወዴት አሉ? ክንፎቻቸው ስድስት የሆኑ ሱራፌልስ ወዴት አሉ? ለአንተ የሚገዙት ወዴት አሉ? ማኅበረ ቅዱሳን ወዴት አሉ? የልዕልናህ ግርማስ ወዴት አለ? አቤቱ ጌታ ሆይ ንገረኝ::

ይቀጥላል....

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 89-103)

#ይቀላቀሉን!!
@Ethio_Betecrstian
በሁላችሁ ዘንዳ በዓል እንደት ዋለ? የቻላችሁ ውሏችሁን በፎቶ አጋሩነ?
ጥምቀትን በዚህ መልኩ አክብረናል እኛ!

ከሸዋ ደማቋ ደብረ ብርሃን ከተማ!


እናንተስ!

@Ethio_Betecrstian
2025/01/21 04:17:39
Back to Top
HTML Embed Code: