Telegram Web
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ምርቶችን መላክ የሚያስችል አዲስ የታሪፍ ስምምነት ድርድር ልታደርግ ነው

#Ethiopia: የአፍሪካ አገሮች ከኮታና ከቀረጥ ነፃ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካ እንዲልኩ ከሚፈቅደው የአጎዋ ስምምነት ውጪ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ብሔራዊ ጥቅሟን ያማከለ አዲስ የታሪፍ ስምምነት ማዕቀፍ በማድረግ፣ ከቀረጥ ነፃ ኤክስፖርት ታደርጋቸው የነበሩትን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን ለመላክ ከአሜሪካ ጋር ድርድር እንደምታደርግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ንግድ ትስስር ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን አበራ፣ ድርድሩ የሚደረገው አሜሪካ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ አገሯ በሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለችውን የአሥር በመቶ ታሪፍ አስመልክቶ በቀጣይ በሚደረግ ውይይት እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል።  
ምርቶችን ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ መላክ የሚቻልበት ዕድል መነሳቱን የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹በአጎዋ ምክንያት ያጣናቸውን ጥቅሞች በዚህ ማዕቀፍ ሥር ለድርድር በማቅረብ፣ ምርቶችን መላክና አገራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ድርድር ው...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143168/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
16👍4😁1
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማምረት ማቆሙ ተሰማ

#Ethiopia: በትግራይ ክልል ከሚገኙ ፋብሪካዎች ቀድሞ ወደ ሥራ ገብቶ የነበረው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ከቦርድ አባላት አሰያየም ጋር በተፈጠረ አለመግባባትና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ማምረት ማቆሙ ተሰማ፡፡  
በኤፈርት ሥር ከሚገኙ ትልልቅ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ማምረት ካቆመ ከሦስት ሳምንታት በላይ እንደሆነው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ፋብሪካው ሲሚንቶ ማምረት ያቆመበት ዋነኛ ምክንያት@ የተሰየሙ አዳዲስ የቦርድ አባላት ላይ ቅሬታ በመቅረቡና የደቡባዊ ዞን አስተዳደር ጥሬ ዕቃ እንዳይቀርብ በመከልከሉ እንደሆነ ከሪፖርተር ምንጮች ለመረዳት ተችሏል፡፡
‹‹ጥሬ ዕቃው ከእኛ እየተወሰደ ተጠቃሚ እየሆንን አይደለም፣ እንዲሁም እኛን የሚወክል ቦርድ ውስጥ አልተካተተም›› በሚል ምክንያት የተፈጠረው አለመግባባት፣ ፋብሪካውን ሥራ እስከ ማቆም አድርሶታል ተብሏል፡፡ ዋናው ምክንያት ይህ ቢሆንም ሌሎች ምክንያቶችም እንዳሉ የሚጠቁሙት ም...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143157/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
14👍6😁3👏2😢1
የዜግነት ፖለቲካ የሚያቀነቅነው ኢዜማ በብሔር ፖለቲካ አቀንቃኞች መፈተኑን አስታወቀ

#Ethiopia
መሪው ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ከመጪው ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል

ሁለተኛውን ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ሰኔ 28 እና 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ያካሄደው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ፣ የአገሪቱ ያልተረጋጋ የፖለቲካ ለውጥ እንዲሁም የብሔር ፖለቲካ ተገዳዳሪነት ያለፉት ዓመታት ፈተናዎቹ እንደነበሩ ተናገረ፡፡
ድርጅቱ 600 የሚጠጉ አባላቱ በተገኙበት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ፣ ያለፉት ዓመታት ጉዞውን፣ አሁናዊና ቀጣይ ጉዞውን አገሪቱ ከምትገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር የገመገመ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ አገሪቱ እያለፈችበት ያለው ውጣ ውረድ ያልተለየው የፖለቲካ ለውጥ እንደ ኢዜማ ላሉ የዜግነት ፖለቲካ ለሚከተሉ ኃይሎች ፈታኝ መሆኑን የጠቆመው ፓርቲው፣ ጉባዔውንም የድርጅት ክንፍ አመራሮችን ምርጫ በማካሄድ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ 
ጉባዔው አራት አበይት ጉዳዮች እንደተስተናገዱበት ፓርቲው ጠቅሷል፡፡ የሦስት ዓመታት የፓር...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143191/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
🤪1817😁5👎4🤔1
የፓርላማ አባላት ማትጊያና ጥቅማ ጥቅም እንዲስተካከልላቸው ጥያቄ አቀረቡ

#Ethiopia
ከግድያ በስተቀር ሁሉን ዓይነት ምርመራ የሚፈቅደው አዋጅ ተሰርዟል
‹‹አዋጁ ውስጥ ያለው ድንጋጌ እንዲቀር ብከራከርም የፓርቲ ዲሲፕሊን በመሆኑ አዋጁን አፅድቄያለሁ››

የብልፅግና ፓርቲ የፓርላማ አባል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚሰጣቸው ማትጊያና ጥቅማ ጥቅም በቂ ባለመሆኑ ይስተካከል ሲሉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ፓርላማው በአራተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው የዓመቱ ማጠቃለያ ሁለተኛ ልዩ ስብሳባ፣ የምክር ቤቱን የ2017 ዓ.ም. አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ለምክር ቤት አባላት በሎጂስቲክስና በትራንስፖርት አቅርቦት የታዩ መልካም ጅምሮች መኖራቸውን፣ እንዲሁም የአባላትን አቅም የሚገነቡ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት በሕግ አወጣጥ፣ በቁጥጥርና ክትትል፣ በውክልና ሥራና በዲፕሎማሲ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ተናግረዋ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143173/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
😁186👍3😢1
#ማስታወቂያ

Hanqina mallaqaa isin mudatuuf har'as' Wabii'n  furtuu keessan haa ta'u!

Tajaajila liqii  ‘Wabii Digital Finance’ Baankiin keenya  karaa telebirr   hojirraa oolche, yeroo gabaabaa keessatti fayyadamtoota hedduu  furmaata jhanqina mallaqaa taasiseera.

Tajaajila Liqii Xixiqqaa (personal loan),  battaluma bilbila harkaa keessan fayyadamuun kan argattan   yoo ta'u, Liqii Waldalee (SME loan) fi Liqii Miindaa bu'uureffate(salary loan) immoo damee baankii keenyaa isinitti dhihoo jiru irraa mirkaneessa argachuun  kan aragattan ta'a. Liqiin Bittaa Bilbila Moobaayilas (device financing) dhiyeenyatti kan eegalamu ta'a.

Isinis ammuma Appilikeeshinii telebirr fayyadamuun  ' Financial services with Siinqee Bank' kan jedhu jalatti ykn  karaa  *127#  tajaajila kana saffisaan argadha.
—————————————————-
ለሚያጋጥምዎት  የገንዘብ ችግር   ዛሬም   “ወቢ” መፍትሄ  ይሁንልዎ!

ባንካችን  በቴሌ ብር በኩል  ያስጀመረው ወቢ ዲጂታል የብድር አገልግሎት  በአጭር ጊዜ ውስጥ  ለበርካታ ተጠቃሚዎች ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

አነስተኛ የብድር አገልግሎት (personal loan )  ወዲያውኑ የእጅ ስልክዎን በመጠቀም ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የማህበራት (SME loan) እና ደመወዝን መሰረት ያደረገ(salary loan)   የብድር አገልግሎት በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ማረጋገጫ በማግኘት ተጠቃሚ የሚሆኑ ይሆናል፡፡ የሞባይል ስልክ  ግዢ ብድር አገልግሎትም (device financing) በቅርቡ የምጀመር ይሆናል፡፡

እርስዎም አሁኑኑ  በቴሌብር መተግበሪያ ' Financial services with Siinqee Bank' በሚል ስር ወይም በ*127#  በኩል አገልግሎቱን በፍጥነት ያግኙ!


#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan #Siinqee_Digital  #Financial_Inclusion  #EMPOWERED_TOGETHER
2👎1
የሠራተኞች ዝቅተኛ ደመወዝ በሦስትዮሽ ምክክር ሊወሰን እንደሚገባ ተገለጸ

#Ethiopia: ሠራተኞች የሚያነሱትን የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ አሠሪዎች፣ ሠራተኞችና መንግሥትን በማካተት የሦስትዮሽ ወገን ምክክርና ትብብር ላይ ተመሥርቶ ሊወስን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌደሬሽኖች ኮንፌደሬሽን በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅና  የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ  አዋጅ  ላይ ዝቅተኛ የደመወዝና አመች የሥራ ሁኔታን በተመለከተ፣ ትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና የግል ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና የቦርድ አባል ጌታሁን ሁሴን (ኢንጂነር) በሰጡት አስተያየት፣ የሠራተኛውን ጥቅማ ጥቅም በተመለከተ የሠራተኛ ማኅበራት በርካታ ጥያቄዎች እንደሚያቀርቡ አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ሊፈቱ የሚችሉት በአሠሪና ሠራተኛ እንዲሁም በመንግሥት ትብብር በአገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ የሦስትዮሽ ምክክር በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
 ፕሬዚዳንቱ በማብራሪያቸው አሠሪው ብቻውን ያለ ሠራተኛው...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143160/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
19👍3👏2
ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን ዋጋ ከዓለም ንግድ ድርጅት መርሆዎች ጋር ለማጣጣም አስገዳጅ መመርያ ተዘጋጀ

#Ethiopia: የገቢዎች ሚኒስቴር ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ ከዓለም ንግድ ድርጅት መርሆዎችና ኢትዮጵያ ተቀብላ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፋዊ፣ አኅጉራዊና ቀጣናዊ ስምምነቶች ጋር እንዲጣጣም የሚያደርግ አስገዳጅ መመርያ አዘጋጀ፡፡
መመርያው የማምረቻ መሣሪያዎች ወይም ማሽነሪዎች ወደ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለሚከናወን የግንባታ፣ የማሻሻያ፣ የተከላ ወይም የጥገና ሥራ፣ ወይም ለቴክኒክ ድጋፍ የሚከፈል ክፍያ፣ ዕቃው ወደ ጉምሩክ ክልል ከገባ በኋላ የሚከፈል የትራንስፖርት ክፍያ፣ ዲክላራሲዮን አቅራቢው ለገባው የፋይናንስ ስምምነት የሚከፈል የወለድ ክፍያ፣ እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ዕቃዎች ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከፈለ ቀረጥ፣ ታክስና ሌሎች ክፍያዎች እንደማይካተቱ ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ በአገር ውስጥ እንደገና ለማምረት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ እንዲሁም ዕቃውን ለመላክ በቅድመ ሁኔታነት እስካልተቀመጠ ድረስ ለማከፋፈል ወይም ለመሸጥ በገዥው የ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143154/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
12😢2
የሥራ ዕድል ፈጠራ ችግርን ለመፍታት የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተባብረው መሥራት አለባቸው ተባለ

#Ethiopia: የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት፣ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲያስችልና የሥራ ዕድል ፈጠራ ችግርን ለመፍታት የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተባብረው በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትስስርን ማላቅ፣ የግብርና እሴት ሰንሰለትን ማጎልበት፣ ዲጂታላይዜሽንና የፋይናንስ አካታችነትን ማረጋገጥ፣ የመንግሥትና የግል አጋርነት ማጠናከር፣ እንዲሁም ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ‹‹ሦስተኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉባዔ›› ከትናንት ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሲካሄድ ነው፡፡
የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ትሬድ ግሩፕ መሥራችና ኃላፊ አቶ ሙሉዓለም ሥዩም እንደተናገሩት፣ ‹‹አሁን ተጠራቅሞ የመጣውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ችግር መቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታትም የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143145/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
2👍2
ከጦርነት ባሻገር ያሉ ሰላማዊ አማራጮች ቅድሚያ ይሰጣቸው!

#Ethiopia: በኢትዮጵያ ምድር ሌላ ዙር አውዳሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ሥጋት ሲያንዣብብ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ አደገኛ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆም በስክነት መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ በሰሜንም ሆነ በምሥራቅ፣ በደቡብም ሆነ በምዕራብ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል የሚኖሩ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንጂ በመሣሪያ እንደማይፈቱ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱ ግጭቶችም ሆኑ ጦርነቶች ከዕልቂትና ከውድመት ውጪ ያስገኙት ምንም ነገር የለም፡፡ አለመግባባቶችን በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ ለማስተናገድ የሚያስችሉ በርካታ አገራዊ የሽምግልና እሴቶች ባሉባት ኢትዮጵያ፣ ፖለቲከኞች እየተንደረደሩ ወደ ግጭት የሚገቡበት መንገድ መዘጋት አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተዋጊዎቹ በተጨማሪ በርካታ ንፁኃን ሲያልቁ፣ ሲፈናቀሉ፣ ረሃብን ጨምሮ ለተለያዩ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ሲዳረጉና ዘግናኝ የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸሙባቸው እንደነበር በሚገባ የተሰነ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143165/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
👍76👏2
የሱዳኖች ክስና ያልከሰመው የአልፋሽጋ መሬት የግጭት ወላፈን

#Ethiopia: ከአዲስ አበባ እምብርት ከፒያሳ ተነስቶ እስከ ኮተቤ ዳር በግምት እንደሚሰፋ ማሳያ በማድረግ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ስላረሱት መሬት ይናገራሉ፡፡ በ2013 ይህን መሬት ከአሸተው 2,500 ኩንታል ማሽላቸውና ከብዙ የእርሻ ማሽኖቻቸው ጋር በሱዳን ታጣቂዎች ወረራ መቀማታቸውን የሚናገሩት አቶ ደረጀ በጋሻው፣ ዛሬም ድረስ ካሳም ሆነ መፍትሔ የሚሰጣቸው አለማግኘታቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከሪፖርተር ጋር ስለአወዛጋቢው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር መሬት ስለአልፋሽጋ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ሰፊ ቆይታ ያደረጉት በአካባቢው በግብርና ሥራ ተሰማርተው የኖሩትና ቦታውን በቅርበት የሚያውቁት አቶ ደረጀ፣ የሱዳኖች ሰሞነኛ ውንጀላ ሐሰተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ አልፋሽጋን ወረረችብንና የኢትዮጵያ ገበሬዎች የሱዳንን መሬት ተቆጣጠሩ እየተባለ ከሰሞኑ በሱዳኖቹ የተሠራጨው ውንጀላ፣ ከሐሰተኝነቱ በዘለለ ከበስተጀርባው ራሳቸው ሱዳኖቹና ተባባሪዎቻቸው የሚያደርጉት የጦር ዘመቻ ዕቅድ አካል ሊሆን እ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143236/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
14👍2😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ማስታወቂያ

ትርፍ እየተጋሩ ህልምዎን ያሳኩ!
****
ህልምዎን ለማሳካት በሚረዱት
የሲቢኢ ኑር ሙዷራባህ ትርፍ አጋሪ የቁጠባ ሂሳብ አማራጮች ይቆጥቡ፤
ከ67-99% ትርፍ ይጋሩ!

ጁምዓ ሙባረክ!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#CBE #cbenoor #interestfreebanking #saving #mudarabah
3
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ከፕላስቲክ አምራቾች የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

#Ethiopia
አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ ካልተራዘመላቸው ወደ ኢንቨስትመንት ቦርድ እንደሚወስዱት ተናግረዋል

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የፕላስቲክ አምራች ኩባንያዎች ለአንድ ጊዜ ጥቅም የሚሰጡ ምርቶችን እንዳያመርቱ ተብሎ የተጣለው የጊዜ ገደብ እንዲራዘምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም አለ፡፡
የባለሥልጣኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ ዋቅጅራ፣ ከአንድ ወር በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
‹‹የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ሲወጣ ረዥም ጊዜ ተወስዶና የአገሮች ተሞክሮ ታይቶ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ሥራ ላይ የነበሩ ግለሰቦችና አምራቾች እንዴት ይሆናሉ የሚለውም ታስቦበት የተዘጋጀ ነው፤›› ብለዋል፡፡
በዚህ አዋጅ መሠረት ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲክ ምርቶችን በስድስት ወራት ውስጥ ማምረትና መሸጥ እንዲያቆሙ፣ ምርቶቹን ሲጠቀም የ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143140/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
12😢6👎2😁1
#ማስታወቂያ

Herreega qusannaa Waadi'aah dubartootaaf qophaa'etti fayyadamaa !

Herreega qusannaa Waadi'aah dubartootaa 'Lil Nissah'  tajaajilli dhalarraa bilisaa baankii keenya Siinqee IHSAN    addatti  isiniif qopheesse  banattanii itti qusachuun nuwaliin  borii keessan kan milkii taasisaa.

በዋዲያህ  የሴቶች ቁጠባ ሂሳብ ይጠቀሙ !

በሲንቄ ኢህሳን  የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት፣ ባንካችን ባዘጋጀው  'ሊል ኒሳህ'   የሴቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሂሳብ በመቆጠብ ነገዎን ከእኛ ጋር  ስኬታማ ያድርጉ ፡፡

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan   #Financial_Inclusion  #EMPOWERED_TOGETHER
5
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአዋሽ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና አፀደቀ

#Ethiopia:  የአፍሪካ ልማት ባንክ የአዋሽ ባንክን የወጪ ንግድ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ የ50 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ፋይናንስ ዋስትና ማዕቀፍ አፀደቀ።
ባንኩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ያፀደቀው ይህ የዋስትና ማዕቀፍ አዋሽ ባንክ ለአስመጪዎች የሚከፍታቸው ሌተር ኦፍ ክሬዲትና መሰል የንግድ ፋይናንስ ሰነዶች ላይ በውጭ በሚገኘው ተቀባይ ባንክ በኩል ለሚነሱ የክፍያ ሥጋቶች እስከ መቶ በመቶ  ዋስትና ለመስጠት የሚያስችል ነው። 
ማዕቀፉ በዋናነት ለኢትዮጵያ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ሌሎች የአገር ውስጥ ኮርፖሬሽኖች ለሚያስመጧቸው የንግድ ዕቃዎች በአዋሽ ባንክ የሚከፈቱ እንደ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ያሉ የገቢ ንግድ ፋይናንስ ሰነዶች የክፍያ ዋስትና ለመስጠት የሚያስችል ነው። ይህም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአፍሪካ ውስጥ የንግድ ልውውጥን በመደገፍ ለአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስኬታማ ትግበራ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የአፍሪ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143233/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
9👍4😱3👏2😁2
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በአምቡላንስ ተጓጉዘው እየተፈተኑ መሆኑ ተገለጸ

#Ethiopia
ድንገተኛ ችግር ቢፈጠርና ተጎጂዎች ቢኖሩ ለጊዜው ማጓጓዣ የለም ተብሏል
በጥር ወር ወደ ትግራይ ክልል ይላክ ከነበረው ነዳጅ በሰኔ ወር በ78 በመቶ ቀንሷል ተብሏል

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በተከሰተው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ስላልተቻለ አምቡላሶችን በማስቆም እያመላለሰ እንዲፈጠቱ እያደረገ መሆኑን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡



የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ከመጀመሩ በፊት በትግራይ ክልል ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ቦታዎች ለማድረስ እንደሚቸገር ገልጾ፣ ለሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢሮው ደብዳቤ መጻፉንና ምላሽ እንዳልተሰጠው ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ሆኖም የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞችን ለመመለስና የሁለተኛ ዙር ተፈታኞችን ወደ መፈተኛ ቦታዎች ለማድረስ፣ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች አገልግሎት የሚሰጡበት ነዳጅ ስለሌላቸው፣ አምቡላንሶችን በ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143151/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
15🤔5😢2
ዘመን ባንክ ከታክስ በፊት ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ

#Ethiopia: በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ቅርንጫፎች አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ዘመን ባንክ፣ በተጠናቀቀው የ2017 የሒሳብ ዓመት በባንኩ ታሪክ ከፍተኛ ዕድገት ያሳየበትን ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለጸ፡፡
የባንኩ የ2017 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ያነገገርናቸው የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘነበ፣ ‹‹የ2017 ሒሳብ ዓመት የባንኩ አፈጻጸም እጅግ የተለየ ሊባል የሚችል ነው፤›› ብለዋል፡፡ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ቅርንጫፎችና የሰው ኃይል ውጤታማ የሚባል ሥራ ስለመሠራቱ ያመለከቱት አቶ ደረጀ፣ በሁሉም ረገድ የታየው አፈጻጸም ከዕቅድ በላይ ውጤት የተመዘገበባቸው በመሆኑ በሒሳብ ዓመቱ ባንኩ ከታክስ በፊት ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገልጸዋል፡፡
የዘንድሮ ትርፍ በአንድ ዓመት ልዩነት የትርፍ ዕድገት ምጣኔውን በ138 በመቶ ማሳደግ የቻለበት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በባንኩ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ የት...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143231/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
21👍8
2025/07/12 19:23:57
Back to Top
HTML Embed Code: