Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ኪዳነ ምሕረት......😊
12
🥰126👍3
“አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።”
  — መዝሙር 31፥3

ለሰዎች አጋሩ🙏🙏

For Your #Profile

#profile #wallpaper #በዓል #Telegram #user
#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

ለኦርቶዶክሳዊ Wallpaper  ይቀላቀሉ👇🙏
https://www.tgoop.com/aserorthodoxwallpaper

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
27🥰3
❤️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፫ 🙏
​​#አባ_ለትጹን

ሰኔ 17 ዳግመኛም ታላቁ አባት አባ ለትጹን አረፈ። ይህም አባት ከብህንሳ አገር ነበር ጐልማሳ በነበረ ጊዜም “ነፍሱን ሊያድናት የሚሻ ይጣላት ነፍሱን ስለ እኔ የጣላትም ያገኛታል ለዘላለም ሕይወትም ይጠብቃታል” የሚለውን በ #ቅዱስ_ወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የሕያው ንጉሥን ቃል ሰማ ወዲያውኑ ልቡ ስለ #እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ዘላለማዊ ተድላ እንደ እሳት ነደደ።

#ቅዱስ_ቁርባንንም ተቀብሎ እስዋሕት ወደሚባል ገዳም ሔደ በጾም በጸሎትና በስግደት ታላቅ ተጋድሎን ያለ ማቋረጥ ይጋደል ጀመር ሰባት ሰባት ቀንም ይጾም ነበረ። የ #እግዚአብሔርም መልአክ ተገለጸለትና የምንኵስና ልብስን ያለብሰው ዘንድ ወደ አባ ኤስድሮስ እንዲሔድ አዘዘው እርሱም መልአኩ እንዳዘዘው ሔደ አባ ኤስድሮስም በልብሱና በአስኬማው ላይ አርባ ቀኖች ጸለየ ከዚያም በኋላ ልብሱንና አስኬማውን አለበሰው በገድል መጠመድን ጨመረ።

ከዚህም በኋላ በመምህሩ ፈቃድ ወጥቶ እየተጋ እየጾመና እየተጋደለ ብቻውን ኖረ። ከእርሱም አቅራቢያ የሆነ አንድ ገዳም ነበረ የገዳሙን መነኰሳትም ይጐበኛቸው ነበር። በአንዲት ዕለትም ወደዚያ ገዳም ሔደ አበ ምኔቱንም ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው መነኰሳቱም በዙሪያው ሆነው ያለቅሱ ነበር። አባ ለትጹንም የሰይጣን ሠራዊትን ከበውት ደስ ሲላቸው አያቸው።

አባ ለትጹንም አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድን ነው ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው እርሱም መነኰሳቱን ከአጠገቡ እንዲርቁ አዘዛቸው።

ከዚህም በኋላ ያደረገውን በደሉን ሊነግረው ጀመረ እንዲህም አለው ከእኔ አስቀድሞ እንደርሱ ያለ ማንም ያልሠራው ኃጢአትን ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሔድሁ ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል ብዬ በድፍረት በቁርባኑ ላይ የምቀድስ ሆንኩ። ለጠላሁትም በቍርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ አሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል ከእናቴም ጋራ ዐሥር ጊዜ ተኝቼ አለሁ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆድዋ ውስጥ ገደልሁት ኃጢአቴ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም። ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲአሠቃይዋት አባ ለትጹን አያት። አባ ለትጹንም ልቅሶን አለቀሰ።

አባ ለትጹን “ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም” የሚለውን የ #ቅዱስ_ወንጌልን ቃል አሰበ። አባ ለትጹንም ስለዚህ ኃጥእ ሰው ነፍስ ክብር ይግባውና #ጌታችንን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊአሠቃያት ጀመረ።

የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤልም መጥቶ አስነሣውና እንዲህ አለው ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ንፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና #እግዚአብሔር ዕውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደ ሆነ #እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም።

ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ ያን ጊዜም ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወርዶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠ ከባሕርም አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ #ሚካኤልን አዘዘው እርሱም አድኖ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን ፊት አቆመው።

#ጌታችንም የመረጥሁህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለ ሆነ ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ አለው። አባ ለትጹንም እንዲህ ብሎ መለሰ መሐሪና ይቅር ባይ #ጌታዬ_ፈጣሪዬ_ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት።

ከዚህም በኋላ #ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ #ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት በከበሩ እጆቹም ዳሠሣት እንዳልተፈጠረችም አደረጋት። ይቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን አለ። አባ ለትጹንም ስለ ይቅርታውና ቸርነቱ ገናናነት #መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው።

ከዚህም በኋላ #ጌታችን አባ ለትጹንን የመረጥሁህ ለትጹን ሆይ በዕውነት እነግርሃለሁ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ በስምህ መባ ለሚአስገባ ወይም የተራበ ለሚያበላ የተጠማ ለሚያጠጣ የተራቆተ ለሚያለብስ ወይም ገድልህን ለሚጽፍ እኔ የሁሉንም ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ ስማቸውንም በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ በጎ ዋጋቸውንም እሰጣቸዋለሁ #ጌታችንም ይህንን ብሎ ወደ ሰማያት ዐረገ።

ቅዱስ አባ ለትጹንም እጅግ ደስ አለው ወደ በዓቱም ተመልሶ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ። #እግዚአብሔርንም አገለገለው። መልካም ገድሉንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በተጋዳይ በአባ ለትጹን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
24🙏5
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
² ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።

³ አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
⁴ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፥ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።

⁵ እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።
⁶ ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።

⁷ ተነሥ፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
⁸ ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።

ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
🥰1912🙏7
ዕጣው የወጣላት እኅት!😊

የወጣው ዕጣ ቁጥር  #ዕጣ0023  ነው።
60🔥8👏6
የኅሊና ዳኛ

እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ፣ ኹል ጊዜ ንቁና ትጉ የኾነ ዳኛ ያስቀመጠው ስለ ምንድን ነው ብለኅ ብትጠይቀኝ፣ ከሰው ወገን ይኽን የ'ኅሊና ዳኛ'ን የመሰለ፣ እንቅልፍ የለሽ ዳኛ ስለሌለ ነው ብዬ እመልስልሃለኹ፤ ዳግመኛም፣ የውጪ ዳኞች በገንዘብ፣ በውሸት በመደለል፣ የሐሰት ፍርድ እንዲሰጡ በማስፈራራት፣ እንዲኹም በሌሎች መጠነ ብዙ ምክንያቶች፣ ርቱዕ የኾነ (ያልተዛባ) ውሳኔአቸውን ሊያጣምሙ ይችላሉ፤ የ'ኅሊና ዳኛ'ን ግን በእነዚኽ በገለጽናቸው ምክንያቶች በምንም መንገድ የሚደለል አይደለም፤ ጉቦ ብንሰጠው፣ ልንዋሸው ብንሞክር፣ ብናስፈራራው፣ ሌላ ሌላም ብናደርግ እንኳ፣ ይኽ የ'ኅሊና ዳኛ' ለምናስበውና ለምንሠራው ኀጢአት ምንም ሳይጠመዝዝ እውነተኛ ፍርድን ይሰጣል፤ ኀጢአት የሠራ ሰው፣ ሌላ ሰው ባይወቅሰውም እንኳ፣ ርሱ ራሱ ራሱን ይወቅሳል፤ አንዴ ወይም ኹለቴ ብቻ አይደለም፣ መላ ዘመኑን እየደጋገመ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ኅጢአት የሠራነው ከረዥም ዘመናት በፊት ሊኾን ይችላል፤ የኅሊናችን ዳኛ ግን ያን የሠራነው ጥፋት ፈጽሞ አይረሳውም።

የኅሊና ዳኛ ኀጢአት ከመሥራታችን በፊትም ይኹን በኋላ ምንም ሳይሸፋፍን በግልጽ ይወቅሰናል፡፡ በተለይ ደግሞ ከሠራነው በኋላ፡፡ ኀጢአት በምንሠራበት ሰዓት ግን ይኸን ዳኛ አጥርተን አንሰማውም፡፡ ይኸውም በምንሠራው ክፉ ሥራ ስለምንሰክር ነው፡፡ ኀጢአት መሥራታችንን ባቆምን ጊዜ ግን ወድያው የጸጸት ሽመሉን ይመዠልጣል፡፡ ይኽም በቀጥታ ምጥ ከያዛት ሴት ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ እርጉዝ ሴት ምጥ የያዛት ጊዜ እጅግ አስጨናቂ የኾነ ሕመም ይሰማታል፡፡ ከወለደች በኋላ ግን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዕረፍት ይሰማታል፡፡ በወለደችው ልጅ ታላቅ ሐሴት ይሰማታል፡፡ ኀጢአት ስንሠራ ግን ከዚኹ ተቃራኒ ነው፡፡ በሐሳብ የፀነስነውን ኀጢአት በግብር እስክንወልደው ድረስ “ደስታ" ይሰማናል፡፡ ከፉው ልጃችንን (ኀጢአታችንን) በግብር ከወለድነው በኋላ ግን በልጃችን ፊት ከፍተኛ ሐፍረት ይሰማናል፡፡ ምጥ ከያዛት ሴት በላይም ያሰቃየናል፡፡

ስለዚኽ ልጆቼ! ይኽን ከፉ መሻት ከመዠመርያ አንሥተን ከመቀበል እንከልከል፡፡ ከተቀበልነው እንኳ ገና ፍሬ ሳያፈራ ሳለ ከውስጣችን (በገቢር ሳንገልጥ) እንግደለው፡፡ ይኽን ማድረግ ሳንችል ቀርተን ልጃችንን በገቢር ከወለድነው ግን በንስሐና በዕንባ እንዲኹም ራሳችንን በመውቀስ እንግደለው፡፡

(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 49-50)

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks
63👍5🥰1🎉1
ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለህ፤

ሳታጎድል ሁሉን ትመግባለህ፤

ዝም ሳትል ለሁሉ ታስባለህ፤

ሳታጎድል ለሁሉ ትሰጣለህ፤

ሳትነጠፍ ለሁሉ ታረካለህ፤

ሳትዘነጋ ሁሉን ታስባለህ፤

ሳትተኛ ሁሉን ትጠብቃለህ፤

ቸል ሳትል ሁሉን ትሰማለህ፤

ሳትቀበል ለሁሉ ትተዋለህ።

#ቅዳሴ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ



ኦ አምላክ ሆይ እንዳንተ ያለ ማነው?እንደ "አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።"
ዘዳ ፴፫÷፳፮
65👍4👏3🕊1
ሰላም እንዴት ናችሁ ሰሞኑን ስለጠፋን ይቅርታ🙏🙏🙏

ነገሮች ስላልተመቻቹልን ነበረ።

መዝሙረ ዳዊቱም ይቀጥላል።
👍279
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የጽድቄ አምላክ በጠራሁት ጊዜ መለሰልኝ፥ በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፤ ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ።
² እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ?

³ እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
⁴ ተቈጡ፥ ነገር ግን ኃጢአትን አታድርጉ፤ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፤ ዝም በሉ።

⁵ የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በእግዚአብሔርም ታመኑ።
⁶ በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።

⁷ በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።
⁸ በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።


ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
22🕊3🥰2👍1
" ማቀርቀሬን ሰበርክ አልኩኝ ቀና
በርትቼ ተራመድኩ እንደገና
በጥላቴ ፊት ሞገስ ሆንከኝ
ለባሪያህ እድል ሰጠህኝ "

21🙏1
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል
² የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።

³ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።
⁴ አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።

⁵ በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
⁶ ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።

⁷ እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።
⁸ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።

⁹ በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
¹⁰ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።

¹¹ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
¹² አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።

ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
21👍3🥰1
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።
² ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ማረኝ፤ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።

³ ነፍሴም እጅግ ታወከች፤ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
⁴ አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።

⁵ በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
⁶ በጭንቀቴ ደክሜያለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።

⁷ ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
⁸ ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።

⁹ እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
¹⁰ ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቍሉ፤ ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም ይፈሩ።

ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊


ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
19👍7
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥
² ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሩዋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
³ አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህስ ካደረግሁ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥

⁴ ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብሆን፥ ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ብሆን፥
⁵ ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።

⁶ አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፥ በጠላቶቼ ላይ በቍጣ ተነሣባቸው፤ አቤቱ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ።
⁷ የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፥ በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ።

⁸ እግዚአብሔር በአሕዛብ ይፈርዳል፤ አቤቱ፥ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
⁹ የኃጥኣን ክፋት ይጥፋ፥ ጻድቁን ግን አቅና፤ እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል።

¹⁰ እግዚአብሔር የጽድቅ ጋሻዬ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው።
¹¹ እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፥ ኃይለኛም ታጋሽም ነው፥ ሁልጊዜም አይቈጣም።

¹² ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይስላል፥ ቀስቱን ገተረ አዘጋጀም፤
¹³ የሞት መሣርያንም አዘጋጀበት፥ ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ።

¹⁴ እነሆ፥ በዓመፃ ተጨነቀ ጉዳትን ፀነሰ ኃጢአትንም ወለደ።
¹⁵ ጕድጓድን ማሰ ቈፈረም። ባደረገውም ጕድጓድ ይወድቃል።

¹⁶ ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥ ዓመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።
¹⁷ እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለሁ።


ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊


ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
17👏1
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም ዐደረሳችሁ የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ አይለየን።😊
61🙏15🥰2
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።
² ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።
³ የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥

⁴ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?
⁵ ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።

⁶ በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
⁷ በጎችንም ላሞችንም ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥

⁸ የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።
⁹ አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።

ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
12👍2
እንዴት አመሻችሁ?

የዛሬ በዓል የት አሳለፋችሁ?
🙏15🥰41
ከጠቀማችሁ

በ Telegram Package ከ Telegram ሳትወጡ የምትፈልጉትን የ Youtube Video Search በማድረግ ማውረድ የምትፈልጉ ሰዎች በውስጥ አናግሩኝ መንገዱን አሳያችኋለሁ😊

◉ መዝሙር
◉ ስብከት
◉ ግጥም እና ሌሎችን ለማውረድ የ Youtube ዳታ ካሌላችሁ በ telegram package የምታወርዱበት System ነው።


ከጠቀማችሁ ብለን ነው።
የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩን😊

@Eduttttt ወይም @Yenelene
11🤣1
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
ይቀጥላል....😊
መዝሙር 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።
² በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።

³ ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥ ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ።
⁴ ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና፤ ጽድቅን እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።

⁵ አሕዛብን ገሠጽህ፥ ዝንጉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘላለም ደመሰስህ።
⁶ ጠላቶች በጦር ለዘላለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውም በአንድነት ጠፋ።

⁷ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ
⁸ እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።

⁹ እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው።
¹⁰ ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

¹¹ በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ፤
¹² ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።

¹³ አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ፤
¹⁴ ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።

¹⁵ አሕዛብ በሠሩት ጕድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።
¹⁶ እግዚአብሔር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው፤ ኃጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ።

¹⁷ ኃጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ።
¹⁸ ድሀ ለዘላለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘላለም አይጠፋም።

¹⁹ አቤቱ፥ ተነሥ፤ ሰውም አይበርታ፥ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።
²⁰ አቤቱ፥ ፍርሃትን በላያቸው ጫንባቸው፤ አሕዛብ ሰዎች እንደ ሆኑ ይወቁ።

ለሰዎች ማጋራት አትርሱ🙏
ይቀጥላል....😊

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks
15
2025/07/08 20:11:44
Back to Top
HTML Embed Code: