Telegram Web
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 48)
----------
17፤ ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።

18፤ ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤

19፤ ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፥ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።
        👉 መቅደሲቱ ወደ መቅደስ
''ኪሩቤል የሚጋርዷት መቅደስ አንቺ ነሽ " እንዲል ቅ.ኤፍሬም አንድም  ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ  አንተ ወታቦተ መቅደስከ እንዲል መዝ 131፥8
እንደሚታወቀው በዓመት በዓመት በሚሰጠው ስብከት ትምህርት  እና በገድላት በታሪክ መጻሕፍት እንደተረዳን ቅድስት ንጽሕት እመቤታችን የስእለት ልጅ መሆኗን ሁሉም ይረዳል ሐናም ቃሏ ሳይታበል ልቧ በልጅ ፍቅር ሳይታለል የመለኮትን እናት አማናዊት መቅደስ እመቤታችንን ለቤተ መቅደስ  ሰጥታለች
ሐና ሆይ በብዙ ገዓር በብዙ ልመና በብዙ ውጣ ውረድ ያገኜሻትን ምትክ የለሽ አንዲት ቅንጣት ታናሽ ብላቴና ድንግልን መስጠት እንዴት ቆረጥሽ ? ! ለልጅ ያለሸ የእናትነት ፍቅርሽስ መቸ ተፈጸመ ? ልብሽስ እንዴት ሳይለወስ ቀረ ?
የልጅ ፍቅርም አልጠገብሽም ጠግበሻል እንዳንልማ ታናሿ ብላቴና ድንግል አፏ  እህል ሳይለምድ ሆዷ ዘመድ ሳይወድ ገና በሦስት ዓመቷ ከእቅፍሽ መለየቷ ትልቅ ማረጋገጫ ነው
እኛ የምናውቀው የእናት አንጀት እንዲህ አይደለምና
ሐና ሆይ እኔ ግን ላንቺ አንክሮ አለኝ
ማን ይሆን ?
የልጁን ፍቅር ትቶ
ልጁን ከእቅፉ ለይቶ
በገባው ቃል ኪዳን ተገኝቶ
የመጀመሪያውን እሽት
ገና በሦስት ዓመቷ
መስጠት የሚቻለው ?
ኦ ወዮ እንደምን ያለ መጥዎተ ርእስ (ራስን መስጥት ነው)
ለዚህ አንክሮ ይገባል
ሐና ሆይ መቅደሲቱን ወደ መቅደስ መውሰድሽ ትክክል ይሆን ? በእርግጥም ትክክል ነው ምክንያቱም  ስእለት ብጽዐት ነውና "የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ " የሚለው የአበው ብሂልም ላንቺ ይመስላል እኔ ግን ሳስበው ሰው ወደ መቅደስ የሚሔደው ለመቀደስ ነው( ቀ ይጠብቃል) የድንግል መሔድ  ግን ለምን ይሆን ? እርሷ እንደሆነች ከዕለተ ልደት እስከ ዕለተ ዕረፍት እንከን አልባ ንጽሕት ቅድስት ናት
ታዲያ ወደመቅደስ የወሰድሻት ለምን ይሆን ?
ነገሩ እንዲህ ነው እኛ ወደመቅደሱ መቅረብ ቢሳነን በመዓዛ ቅድስናዋ በመዓዛ ንጽሕናዋ አማንዊት መቅደስ እመቤታችን አማናዊ መቅደስ ክርስቶስን ወደእኛ ማቅረብ ፈልጋ ነው
ታላቁ የድኅነት ምሥጢርም ይህ ነው እኛም በመቅደሰ ርእሱ እንቀደስ ዘንድ ነው ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ወደመቅደስ ገባች ስንልም
በመቅደሰ ርእሱ እንቀደስ ዘንድ  አማናዊ መቅደስ ክርስቶስ በእመቤታችን ማኅጸን ለተዋሕዶ አደረ ማለት ነው  ክርስቶስ በማኅጸነ ድንግል አደረ ማለትም በልጅነት በሀብታት በምሥጢራት ከብረናል ማለት ነው
መቅደሲቱ ወደ መቅደስ ገባች የስእለት ልጅ ናትና አንድም መቅደሲቱ ወደመቅደስ ገባች     በፍጹም ተዋሕዶ እንኖር ዘንድ
   " መቅደሲቱ በመቅደሰ ርእሱ እንደኖረች                                                    በመቅደሰ ርእሱ ያኑረን " ።
በመ/ር አብርሃም ፈቃዴ

@Ewuntegna
@Eeuntegna
@Ewuntegna
" ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤"
(መዝሙረ ዳዊት 45:10)

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”

«ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል፡፡»

ማህሌተ ጽጌ
እንኳን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት ቀን (በዓታ ለማርያም) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
  ✝️  የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

✝️ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

✝️ ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡
ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

       ቅዱስ ኤፍሬም

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ያልተሰጠህን አትሻ

የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፡፡ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል። አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፡፡ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡

ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፡፡ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡

ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ "በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል" ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡

ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፡፡ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው:: አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው፡፡ በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ::

ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
" በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤"

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:8)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
"እውነት ምንድን ነው?"ዮሐ.፲፰፥፴፰  ጳላጦስ ክርስቶስን ሲጠይቀው ጥያቄ ስለ እውነት ነው።
እውነት ክርስቶስን ስለ እውነት ጠየቀው።
እውነት ከባለቤቱ መገለጥ የተነሣ የሚታወቅ እምነት ነው።
እውነት ክርስቶስ ነው።
እውነት መስቀል ነው።
እውነት ኦርቶዶክሳዊ፦ኅብረት፣ሐዋርያዊነት፣አንድነት፣ኲላዊነት ነው።
እውነት ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማፍቀርና ምረረ ገሀነመ እሳትን መጥላት ነው።
እውነት ዘለዓለማዊነት ነው።
እውነት ምንድን ነው?

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
" ክፉ የሆነች ልማድ ሳበችኝ፣ በታዘዝኩላት ጊዜም በማይፈታ ማሰሪያ አሰረችኝ፡፡ ማሰሪያውም በእኔ ዘንድ የተወደደ ነው፤ ልማድ፣ በወጥመዷ ፈጽማ አሰረችኝ፡፡ በታሰርሁ ጊዜም ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ በማዕበሉም ያሰጥመኛል፤ በዚህም ደስ ይለኛል፡፡ ጠላት ሰይጣንም ዘወትር ማሰሪያዬን ያድስልኛል፤ በመታሰሬ ፈጽሞ ስደሰት አይቶኛልና፡፡ ኅፍረትና ጉስቁልኛ ሸፈነኝ፤ እኔ በፈቃዴ ታሰርሁ፤ ማሰሪያዬንም በቅጽበት በመበጣጠስ ከወጥመድ መውጣት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን አልሻም፤ እኔ በቸልተኝነትና በስንፍና የተያዝኩ ነኝና፡፡ ክፉ ለሆነች ልማድም የተገዛሁ ነኝና፡፡ እኔ ጎስቋላ በሆነ ስቃይ የታሰርሁና ለበጎ ነገር የማልጠቅም ሰነፍም ነኝ፡፡ እኔ አሁን ወደ አንተ ካልተመለስኩ እንደምትፈርድብኝ አውቃለሁና ወደ እኔ ትመለስ ዘንድም በእንባ እለምንሃለው፡፡ ስለዚህም ቁጣህን ከእኔ አዘግይ፤ ወደ አንተ መመለሴን፣ ንስሐ መግባቴንም ጠብቅ፤ አንተ ማንኛውም ሰው በእሳት እንዲቃጠል አትሻምና!! እንኪያውስ በምሕረትህ እታመናለው፣ በይቅርታህም እጸናለሁ፡፡ "

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ጌታ ሆይ አንተ ለራስህ አድርገኸናል፤
በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ልባችን እረፍት የለውም

የአውግስጢኖስ ኑዛዜ 1፡1
"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ። ብቻችሁን አትምጡ። ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ ፣ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቁም ። ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም ። ወራሾቻችሁ አይሆኑም ። ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ። አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ፣ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ ፣ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንዲስሙ አስተምሯቸው ፣ ዕጣኑን ያሽትቱ ፣ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ፣ ቃጭሉን ይስሙ ፣ ደውል ሲደውል ይስሙ ፣ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተ ክርስትያናቸው ምን እንደሆነች ፣ በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ፣ ይማሩ ። ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ፣ ወደ ማኅበር ስትሔዱም ይዛችኋቸው ሒዱ ፣ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ ። እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

       አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል (#ታኅሣሥ_19)

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡

ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንተ ብቻ በእግዚአብሔር መስመር ላይ ትክክለኛ መንገድ ላይ ሁን እንጅ እግዚአብሔር ቆየ ማለት አላየም ማለት አይደለም።እግዚአብሔር ዘገየ ማለት እያማረና እየተዋበ ነው።ብቻ ትክክለኛው መንገድ እና አቅጣጫ ውስጥ ሆነህ ጠብቀው እንጅ እሱ በትክክለኛው ሰዓት ትክክለኛ ዋጋህን ሊሰጥ ይመጣልና ምንግዜም ታምነህ ጠብቀው።
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ

ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፡፡ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁኖ ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ አፍሬም ትለዋለች : እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድስኒ ትለዋለች በዕለት ሰኑይ ክርክር አልቋልና ባርከኒ ይላታል፣፣ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ትለዋለች፡፡ ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሓፊ ነው፡፡ እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ብሎ ይጀምል፡፡

አክሊለ ምክሕነ፡፡

አክሊል የወዲህኛው ፤ ምክሕ የወዲያኛው::

ወቀዳሚት መድነኒትነ፡፡

ቀዳሚት የወዲህኛው ፡ መድኃኒት የወዲያኛው።

ወመሠረተ ንጽሕነ፡፡

መሠረት የወዲህኛው፤ ንጹሕ የወዲያኛው፡፡

ኮነ በማርያም ድንግል።

በማርያም ድንግል ሆነልን አለ፡፡ ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን ፤ ከመሳፍነት ኢያሱን ፤ ከደናግል ኢሊያስን አስከትላ መጥታለች፡፡ ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ብትባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻልህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የድኅነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤሊያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል ፣ የንጽሕናችን መሠረት መሆን አልተቻለህም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ ፤ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ፡፡

ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይውት የሚባል ጌታ  አኃዜ ዓለም በአራኈ ኩሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረት ዓለም !ይጸውር ድደ ወይነብር ፈረ እንዲል፤ መሠረተ ዓለም የሚባል ጌታ ፣ በድንግል ማርያም ተሰማልን፡፡ ትላንት ስሟን አላነሳም ዛሬ ስሟን አነሣ በአንግዳ ልማድ እንግዳን ዕለቱን ስሙን እየጠሩትም ፣ ከዋለ ካደረ በኋላ ስሙን ይጠሩታል በዚያ ልማድ ፣ ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው : ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተግታለች፡፡ ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና፡፡

አንድም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው ለጊዜው ለናት ላቲ ጸጋ ሁና ተስጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁላ ጸጋ ሁና ተስጥታለችና አንድም መርሕ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ምእመናን መርታ ገነት መንግስተ ሰማያት አግብታለችና::

አንድም ልዕልት ማለት ነው፡፡ ሮም አርያም ማለት ልዑል ማለት እንደ ሆነ፡፡ እርሷንም መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሐይምናን ሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ፤ ወተሐሰዩ ቤተ ይሁዳ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡

እንተ ወለደት ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ፡፡

መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው  አካላዊ ቃልን በወለደች በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡

እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ፣፣

ዘኮነ ሰብእ በአንተ መድኃኒትነ፡

እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ፡፡

ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ሐራ ጥቃቃል ሥጋ ኮነ ያለውን ይዘው ወደ ታች ተለወጠ ይላሉና ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው::

ስለዚህ ነባር ማኅተመ ድንግግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡

ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡

መንክር ኅያለ ወሊዶታ ዘኢይትነገር፡፡

ድንቅ የሚሆን የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና  ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን
::

@ewuntegna
@ewuntegna
2025/01/01 01:37:07
Back to Top
HTML Embed Code: