Telegram Web
ፍም እሳት እንደመጨበጥ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يأتي على الناسِ زمانٌ، الصابرُ فيهِم على دينِه، كالقابضِ على الجَمْرِ﴾

“በሰዎች ላይ ትዕግስትን የሚጠይቅ ዘመን ይመጣል። አንድ ሰው ዲኑ ላይ ፀንቶ (ታግሶ) መቆየት ፍም እሳት እንደመጨበጥ የሚሆንበት።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 2260



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 1⃣3⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ጥሪ አደርጋለሁ! Waamichan Taasisa!
🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯

እውነት ለዑለሞቻችን የሚታሰብ ከሆነ የሚከተሉትን በአፋጣኝ እንዲተገበሩ ጥሪ አደርጋለሁ።እነርሱም: -

1)  ለሁሉም ዑለሞቻችን የአካዳሚክ ትምህርት የሚያገኙበትን፥ የአስተዳደርና አመራር፥ የሀገሪቱንና የሙስሊሞችን ታሪክ፥ ነባራዊ ሁኔታን፥ ስነማህበረሰብ ሳይንስና የችግር አፈታት ስልቶች ዙሪያ ላይ እውቀትና ግንዛቤያቸውን የሚያሳድጉበትን መንገድ በአጫጭር ስልጠና፥ በኦንላይንና በርቀት ትምህርት ወይም በየመስጊዱ ኢማሞችን በየዘርፉ የማብቃት ስልቶች ይቀየሱ።ከነርሱ ዉስጥ ደግሞ ለመብቃት ቅርብ የሆኑት ደግሞ ተለይተው የአጭር ጊዜ ተከታታይ ስልጠና ይሰጣቸው።

2) በተግባር ደረጃ ደግሞ ሰፊና በነጻነት የሚሠሩበት የዑለማ ምክር ቤት መዋቅርን አሁን ካለው ለይስሙላ ከተቀመጠው መዋቅርና አካሄድ ወጥቶ ከፌደራል እስከ መስጂድ የተዋቀረ የራሱ በጀትና አቅም ያለው ሆኖ ይዋቀር!

3) ዓሊሞች የአስተዳደርና የአመራር ልምድ እንዲያገኙ በመላ ሀገሪቱ በሁሉም መስጂዶች በአስገዳጅ ደረጃ የመስጂድ ኢማሞችን በመስጂዱ የአስተዳደር  ኮሚቴው ዉጭ የሆኑበት አሰራር ተሽሮ በመስጂድ ኮሚቴ ዉስጥ እንዲሳተፉ ይደረግ።

4) በሁሉም እርከን ለእርከኑ የሚመጥን የአስተዳደር ተሞክሮ ያላቸው  ዓሊሞች፥ ኢማሞች፥ ዱዓቶችና መሻይኮች እየተመረጡ በመጅሊስ ዉስጥ የመጅሊስ የሥራ አስፈጻሚ አባል ይደረጉ።

5) በሀገር ዓቀፍ ደረጃ መሪና አስተዳዳሪ የመሆን ከፍተኛ ተስፋ የሚጣልባቸው ዓሊሞችና ዱዓቶችን ከየክልሉ መርጦ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የሚያሰለጥን የመጅሊስ የአመራር ማሰልጠኛ ማዕክል ይቋቋም።

6) የመስጂድ ኢማሞች፥ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ቃዲዎች፥ ዑለሞችና ዱዓቶች የግድ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ እንዲሆኑ ቢቻል ቀድሞ ከኢልሙ ጎን ለጎን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዲግሪ የተመረቁ የሚሆኑበት ሁኔታ ይታሰብበት።አልያም ሁለቱንም በአንድነት ያጣመረ ዩኒቪርሲቲ ይቋቋም።

ከላይ ይሁን ሁሉ ያነሳሁነት የሚከበሩ፥ የሚደመጡና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ዓሊምም መሪም የሆኑ የሰላት(የመስጂድ) ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ኢማም(መሪ) እንዲኖሩን ከመፈለግ ነው።

ዓሊሞች ይህን ያሟሉ ስልም አካዳሚክ የተማሩ ሁሉ የመሪነትና የአስተዳዳሪነት ብቃት አላቸውም እያልኩ አይደለም። ለመሪነትና አስተዳዳሪነት የራሱ ስነልቦና፥ የተነሳሽነት፥ የእውቀት፥ የክህሎትና የልምድ ዝግጁነት እንደሚያስፈልግ አጥቼው አይደለም።

Waamichan Taasisa
🎯🎯🎯🎯🎯
Dhuguma Ulamaa'ota keenyaaf kan yaadamu yoo ta'e kanneen itti aanan kun hatattamatti akka raawwataman waamichan taasisa. Isaa isaanis:-

1) Tooftaaleen ulamaa'onni keenya hundi barnoota akaadaamii ittiin argatan, ga'umsa hooggansaa, seenaa biyyaa fi Muslimootaa, haala qabatamaa, saayinsii hawaasaafi maloota rakkoo furuu irratti beekumsaafi hubannoo isaanii karaa ittiin gabbifatan leenjii gaggabaabaa, barnoota toora onlaayiniifi fageenyaa ykn masjiidatti imaamota roga hundaan ga'oomsuuf tooftaaleen dandeessisan haa diriiran. Isaan keessaa ammoo kanneen ga'oomuutti dhihoo ta'an adda ba'anii leenjiin gabaabaan walitti fufaan haa kennamuuf.

2) Sadarkaa hojii qabatamaatti ammoo caaseffamni Mana Maree Ulamaa’otaa bal’aafi bilisaan keessa hojjachuu danda'an adeemsa caaseffama fakkeessaa ykn kan maqaa qofaa amma jiru keessaa ba'ee, federaalaa hanga masjiidaatti kan baajataa fi dandeettii mataa isaa qabu ta'ee haa caaseffamu!

3) Hayyoonni muuxannoo bulchiinsaa fi hooggansaa akka horataniif, masjiidota guutuu biyyattii hunda keessatti sadarkaa dirqisiisaatti hojmaatni imaammanni masjiidaa koree koree bulchiinsa masjiidaatiin ala itti ta’an haqamee koree masjiidaa keessatti akka hirmaatan haa godhamu.

4) Roga maraanuu aalimonni, imaamoonni, du'aatonnii fi mashaa'ikkan rogichaa muuxannoo bulchiinsaa qaban filatamanii majlisa keessatti miseensa koree hojii raawwachiiftuu majlisa haa taasifaman.

5) Sadarkaa biyyalessaatti Giddugalli leenjii hooggansa Majlisaa aalimotaafi du'aatota gaggessaafi bulchiinsa akka ta'an abdataman naannolee mara irraa filee xiqqaatu waggaa lamaaf leenjisu haa ijaaramu.


6) Imaamonni masjiidaa, manni murtii sheri'aafi qaadiin, ulamaa’onniifi du'aatonni dirqama barnoota ammayyaa kan baratan akka ta'an, yoo danda'ame ammoo duursee ilmiidhaan cinaatti dameewwan barnootaa garaa garaatiin digiriidhaan kan eebbifaman  haalli isaan itti ta'an itti haa yaadamu. Yookaan ammoo Yunivarsiitiin lamaan isaaniiyyuu walitti hammate haa hundaa'u.

Kanin kanaa olitti waan kana mara kaase aalimoota dhageettii qaban, dhiibbaa uuman, aalimas hoogganaas ta'an, kan salaata (masjiidaa) qofa osoo hin taane imaamota (gaggeessaa) waanuma maraa akka qabaannu barbaaduu irraa ka'ee tani.

Aalimonni kana haa guuttatan yoon jedhu kanneen akkaadaamii baratan marti dandeettiifi ga'umsa gaggeessummaafi bulchinsaa qabu jechaa hin jiru.

Gaggeessummaafi bulchiinsaaf qophaa'ummaa xiinsammuu, kaka’umsaa, beekumsaa, dandeettii fi muuxannoo mataasaa akka barbaachisu wallaalee miti.

Via Ahmedin jebel
2
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1⃣4⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ሰዎችን በምታዝበት መልካም ነገር ተግባሪ ወይም ከምትከለክልበት መጥፎ ነገር የምትቆጠብ ሁን። አለበለዚያ ግን…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُجَاءُ بِالرَّجُلِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، فَيُلْقَى فِي النَّارِ، فَتَنْدَلِقُ أَقْتَابُهُ فِي النَّارِ، فَيَدُورُ كَمَا يَدُورُ الْحِمَارُ بِرَحَاهُ، فَيَجْتَمِعُ أَهْلُ النَّارِ عَلَيْهِ، فَيَقُولُونَ : أَيْ فُلَانُ، مَا شَأْنُكَ ؟ أَلَيْسَ كُنْتَ تَأْمُرُنَا بِالْمَعْرُوفِ، وَتَنْهَى عَنِ الْمُنْكَرِ ؟ قَالَ : كُنْتُ آمُرُكُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَلَا آتِيهِ، وَأَنْهَاكُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَآتِيهِ﴾

“በቂያማ ቀን አንድ ሰው ይቀረብና እሳት ውስጥ ይጣላል። ከዚያም ሆድ እቃው ይዘረገፍና ልክ አህያ ወፍጮውን ይዞ እንደሚዞረው ይዞት ይዞራል። የእሳት ሰዎች ከሱ ዘንድ ይሰበሰቡና እከሌ ሆይ! ምን ነካህ በመልካም ታዘን፣ ከመጥፎ ትከለክለን አልነበረምን ሲሉት እንዴታ! ነገር ግን በመልካም እያዘዝኩ አልፈፅመውም ነበር። ከመጥፎ እየከለከልኩ እፈፅመው ነበር ይላል።”

📚 ቡኻሪ (3268) ሙስሊም (2989) ዘግበውታል



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1⃣5⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
የዓሊሞች ሞት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ اللَّهَ لَا يَقْبِضُ الْعِلْمَ انْتِزَاعًا يَنْتَزِعُهُ مِنَ الْعِبَادِ، وَلَكِنْ يَقْبِضُ الْعِلْمَ بِقَبْضِ الْعُلَمَاءِ، حَتَّى إِذَا لَمْ يُبْقِ عَالِمًا اتَّخَذَ النَّاسُ رُءُوسًا جُهَّالًا، فَسُئِلُوا فَأَفْتَوْا بِغَيْرِ عِلْمٍ، فَضَلُّوا وَأَضَلُّوا﴾

“አላህ ዒልምን ‘እውቀትን’ ከሰዎች ልብ ውስጥ መንጭቆ አይወሰደውም። ነገር ግን ዓሊሞችን ‘አዋቂዎችን’ በማንሳት ‘በሞት በመውሰድ’ ዕውቀትን ይወስደዋል። ዓሊም ‘አዋቂ’ የሚባል እስከማይኖር ድረስ። ሰዎች ጃሂል ‘መሀይም’ የሆኑ አላዋቂዎችን መሪ አድርገው ይይዛሉ። ይጠየቃሉ ያለ እውቀት መልስ ይሰጣሉ። ለራሳቸው ጠመው ሌሎችንም ያጠማሉ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 100



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #59 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
👍1
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1⃣6⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ወሳኝ ዱዓእ!

ከአቡበከር ሲዲቅ (رضي الله عنه) ተይዞ፡ የአላህ መልዕክተኛን (ﷺ) እንዲህ በማለት ጠየኳቸው፦

﴿عَلِّمْنِي دُعَاءً أَدْعُو بِهِ فِي صَلَاتِي قَالَ : " قُلِ : اللَّهُمَّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي ظُلْمًا كَثِيرًا، وَلَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ فَاغْفِرْ لِي مَغْفِرَةً مِنْ عِنْدِكَ، وَارْحَمْنِي إِنَّكَ أَنْتَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ﴾

“በሶላት ውስጥ ስሆን የምለውን ዱዓእ ያስተምሩኝ። እንዲህ በል አሉኝ፦ ‘አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በጣም ብዙ በድያታለሁ። ካንተ በስተቀር ወንጀልን የሚምር የለምና፤ ካንተ ዘንድ የሆነ ምሕረትን ለግሰኝ። አንተ መሐሪና አዛኝ ነህና እዘንልኝም።’”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 834



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1⃣7⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
የሰላሟ ሐገር መካ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَإِنَّ هَذَا بَلَدٌ حَرَّمَ اللَّهُ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ، وَهُوَ حَرَامٌ بِحُرْمَةِ اللَّهِ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَإِنَّهُ لَمْ يَحِلَّ الْقِتَالُ فِيهِ لِأَحَدٍ قَبْلِي،﴾

“ይህን ሐገር (መካ) አላህ ምድርንና ሰማያትን የፈጠረ ቀን አከበረው። እስከ እለት ትንሳዔ ቀን ድረስም የተከበረ አድረጎታል። በውስጡ ለኔም ከኔም በፊት ለነበረ አንድም ሰው ውጊያ አልተፈቀደለትም።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1834



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
2025/07/13 02:55:03
Back to Top
HTML Embed Code: