Telegram Web
ስትበደር ኒያህ ምንድነው?

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن أخَذَ أمْوالَ النّاسِ يُرِيدُ أداءَها أدّى اللَّهُ عنْه، ومَن أخَذَ يُرِيدُ إتْلافَها أتْلَفَهُ اللَّهُ﴾

“የሰዎችን ገንዘብ ለመክፈል በማሰብ የያዘ (የተበደረ) አላህ እንዲከፍል ያስችለዋል። ለማጥፋት (ላለመመለስ አስቦ) የያዘ ሰውን ግን አላህ (የራሱንም ንብረት) ያጠፋበታል።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2387



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 2⃣6⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
👍1
ቁርኣን «ፍጡር» ነው?

አላህ የታላላቅ ባህርያት ባለቤት ነው። ከባህርያቱ አንዱ መናገሩ ነው። ንግግሩ የእውቀቱ ክፍል ነው። የአላህ እውቀት ደግሞ የተፈጠረ አይደለም። እናም ቁርኣን ፍጡር ሳይሆን የአላህ ቃል ወይም እውቀቱ ነው እንላለን።
ይህ የሱንናህ ዑለማዎች ስምምነት ነው።

♦️ «ቁርኣን ፍጡር ነው» የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው ጀዕድ ኢብን ዲርሃም የተባለ ከ46-124 ሒጅራ የኖረ የኹራሳን ሰው ነው።

እንደሚባለው ጀግድ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሶርያ ደማስቆ ከመጣ በኋላ ታቢዒዩ ወሕብ ኢብን ሙነቢህን አግኝቶት ነበር። ከዚያም ወህብን በተደጋጋሚ ስለ አላህ ባህርያት ጥያቄ ሲያነሳበት አላህ ካልጠበቀው ይህ ባህሪው ጥምመት ላይ እንደሚጥለው አስጠንቅቆታል።

በኋላ ጀዕድ ውዝግቡን ቀጥሎበት በአላህ ባህርያት ዙሪያ ከዚያ በፊት ያልተሰሙ አዳዲስ ቃላቶችን መናገር ጀመረ። ለመጀመሪያ ጊዜም ❝ቁርኣን ከጊዜ በኋላ የመጣ በመሆኑ ፍጡር ነው!❞ አለ። አላህም በቀጥታ ሙሳን አላናገረውም፤ ኢብራሂምንም ፍፁም ወዳጁ አድርጎ አልያዘም ሲል አስተባበለ።

በወቅቱ ኸሊፋ የነበረው ዑመር ኢብን ዐብዱልዓዚዝ ነገሩን ሲሰማ እንዲታሰር ትዕዛዝ አወጣበት። ጀዕድም ወሬው ቀድሞ ደርሶት ነበርና ወደ ኢራቅ በመሄድ ተደበቀ። በዚያም በድብቅ አስተሳሰቡን ማሰራጨት ቀጠለበት።

በሒሻም ዘመን የኢራቁ አስተዳዳሪ ኻሊድ ኢብን ዐብዱላህ ስለ ጀዕድ መረጃ ሲያፈላልግ ቆይቶ ደረሰበትና በ124 ሒጅራ በዐረፋ ቀን ህዝቡን ሰብስቦ ❝ሰዎች ሆይ! አላህ ዑድሂያችሁን ይቀበላችሁ። እኔ ግን ዛሬ የማቀርበው ዑድሂያ ጀዕድ ኢብን ዲርሃም ነው።❞ አለና በፊታቸው አረደው።
(ሲየር አዕላም አን-ኑበላዕ 5/433)

♦️ ከጀዕድ በኋላ አገልጋዩ የነበረው የሰመርቀንዱ ጀህም ኢብን ሰፍዋን አስተሳሰቡን በማስቀጠል «ጀህሚያህ» የተባለውን አንጃ ፈጠረ። ቀጥሎ ዋሲል ኢብን አጣዕ የሚባል ኢራቃዊ በጀህሚያ ላይ ጭማሪ በመፍጠር «ሙዕተዚላ» የተሰኘውን አንጃ አቋቋመ።

በ218 ሒጅራ አል-መዕሙን ኢብን ሐሩን አር-ረሺድ የተባለው ኸሊፋ የሙዕተዚላዎችን አቂዳ በመቀበል ቁርኣን ፍጡር አይደለም የሚሉትን ዑለማዎች ሁሉ አሰረ። ሆኖም በዚያው ወራት በድንገት ሞተና ወንድሙ አል-ሙዕተሲም ተተካ።

♦️ አል-ሙዕተሲም ተመሳሳይ አቂዳ ስለነበረው የቁርኣንን ፍጡርነት ያልተቀበሉ በርካታ ዑለማዎችን ገደለ። ከዚያም ኢማም አህመድ ኢብን ሐንበልን በማስጠራት ❝ቁርኣን ከጊዜ በኋላ የመጣ በመሆኑ ፍጡር እንደሆነ አምኘየበታለሁ። አንተም የማትቀበል ከሆነ ቅጣት ይጠብቅሃል።❞ አላቸው።

ኢማም አህመድም ለኸሊፋውና ዙሪያውን ለከበቡት ለሙዕተዚላዎች ❝ቁርኣን የአላህ የእውቀቱ አካል ነው። ቁርኣን ፍጡር ነው ማለት እውቀቱ ቀድሞ አልነበረውም እንደማለት ነው። ቃሉ ከጊዜ በኋላ ቢወርድልንም ቀድሞ እሱ ዘንድ ነበረ። አላህ በቃሉ ይፈጥራል። ቃሉ ፍጡር ቢሆን ፍጡር ፍጡርን ሊፈጥር አይችልም ነበር። አላህም «መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው።» በማለት ትዕዛዙንና ፍጥረቱን ለይቶ ነግሮናል። ይህም ቃሉ ፍጡር አለመሆኑን ያሳያል። እናም የአላህ ቃል ፍጡር ነው ያለ በእርግጥ ክዷል።❞ በማለት በዝርዝር ተናገሩ።
(አል-ሚህና 45-53/ መሳዒል 2/153- ኢብን ሐኒዕ)

ሆኖም አል-ሙዕተሲም ቀድሞ በሙዕተዚላዎች አስተሳሰብ ተሸንፎ ነበርና በኢማም አህመድ ላይ ብዙ ግርፋትና እስር አደረሰባቸው።

♦️ በ227 ሒጅራ አል-ሙዕተሲም ሲሞት ልጁ አል-ዋሲቅ ተተካ። እሱም የሙዕተዚላዎችን አቂዳ ስለተቀበለ በኢማም አህመድ ላይ እስርና ግርፋቱን ቀጠለበት። በኋላ ግን ኢማም አህመድ ጋር ባደረገው ክርክር ለዘብተኛ አቋም ይዞ እስርና ግርፋቱ እንዲቆም አደረገ። የሙዕተዚላ ዑለማዎችንም ከቤተመንግስቱ አስወጣቸው።

♦️ በ232 ሒጅራ አል-ዋሲቅ ሲሞት ወንድሙ አል-ሙተወኪል ተተካ። እሱ ደግሞ የሱንና ተከታይ ነበርና ሙዕተዚላዎችን አሰረ። የሙዕተዚላ ዳኞችንም በማንሳት በሱንና ዑለማዎች ተካቸው። ኢማም አህመድንም ወደ ማስተማራቸው እንዲመለሱ አደረገ።
(ታሪኽ አል-ባግዳዲይ 2/344)

የቁርኣን ፍጡር የመባል ጉዳይ በዚህ መልክ የተጀመረ ሲሆን ዛሬም አህባሾችን ጨምሮ ይህንን የተሳሳተ አረዳድ የሚከተሉ አሉ።

♦️ ከላይ ኢማም አህመድ ያነሱትን ጨምሮ ቁርኣን ፍጡር አለመሆኑን የሚያስረዱ 5 ማሳያዎችን እናንሳና እንቋጨው።

🔵 አንደኛ፡- አላህ ትዕዛዙን ከፍጡር ለይቶ መናገሩ ነው።

አላህ በአል-አዕራፍ 54 ላይ፦

❝ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው።❞

በማለት ተናግሯል። የአላህ ትዕዛዝ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ለያይቶ አያስቀምጠውም ነበር።

🔵 ሁለተኛ፡- ቁርኣን የአላህ እውቀት መሆኑ ነው።

ይህንንም፦

❝እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን አትከተል።❞
(አል-በቀራህ 120)

በማለት ተናግሯል። የአላህ እውቀት ደግሞ ቀድሞም የነበረ ባህሪው እንጅ ከጊዜ በኋላ የመጣ ፍጡር አይደለም።

🔵 ሶስተኛ፡- አላህ በቃሉ ፈጣሪ መሆኑ ነው።

ይህንንም፦

❝ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ሁን« ነው! ወዲያውም ይሆናል።❞
(አል-በቀራህ 117)

በማለት ገልፆታል። ቃሉ ፍጡር ቢሆን ፍጡር ፍጡርን ሊፈጥር አይችልም ነበር።

🔵 አራተኛ፡- ቁርኣን ፍጡር ከሆነ አላህ ቀድሞ ስም አልነበረውም እንደማለት ነው።

አላህ፣ አር-ረሕማን፣ አር-ረሒም እና ሌሎች ስሞች አሉት። እነዚህ ስሞች ቃል በመሆናቸው ቃሉ ፍጡር ከሆነ አላህ ከንግግሩ በፊት ምንም ስም አልነበረውም እንደማለት ነው።

🔵 አምስተኛው፡- የአላህ ቃል ጠባቂ መሆኑ ነው።

ነቢዩ ﷺ ❝መንገድ ላይ በሆነ ቦታ ስታርፉ “አላህ ከፈጠረው ነገር ክፋት በፍፁም ቃሉ እጠበቃለሁ” በሉ።❞ ብለዋል።
(ሙስሊም 2708)

የአላህ ቃሉ ፍጡር ከሆነ ፍጡርን ለጥበቃ መለመን ሽርክ ይሆናል። እንዲሁም ፍጡርን ፍጡር ሊጠብቀው አይቻለውም።

ኢማም ቡኻሪይ ይሄንን ሐዲስ መበጥቀስ ❝ሐዲሱ የአላህ ቃል ፍጡር አለመሆኑን ያሳያል። ከእሱ ውጭ ያለው ሁሉ ግን ፍጡር ነው።❞ ብለዋል።
(ኸልቅ አፍዓል አል-ዒባድ 143)

♦️ ቁርኣን የአላህ ቃል ነው ስንል ቃሉን፣ ፊደሉን፣ ንግግሩን፣ ትርጉሙን ለማለት ነው። ነገርግን እኛ የምንቀራው ድምፅ፣ የፃፍንበት ቀለም፣ የተፃፈበት ወረቀት እነዚህ ፍጡራን ናቸው።

ኢብን ተይሚያህ ስለዚሁ ሲናገሩ «እኛ የምንቀራው ድምፁ ፍጡር ነው። ምክንያቱም ነቢዩ ቁርኣንን በድምፃችሁ አስውቡት ብለዋል። ንግግሩ ግን የአላህ ነው።» ብለዋል።
(አል-ፈታዋ 12/53)

ኢብን ቀዪም ስለ ፊደሎቹ ተጠይቀው ❝ፊደሎቹን በሁለት ከፍለን እናያቸዋለን። ሰውየው በድምፅ የሚቀራቸው ከሆኑ እነሱ ፍጡር ናቸው። ነገርግን የቁርኣኑ ፊደሎች ፍጡር አይደሉም።❞ ብለዋል።
(አስ-ሰዋዒቅ አል-ሙርሰላህ)

በጥቅሉ ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑን ማመን ከእምነት ክፍሎች አንዱ ሲሆን ኢማም አል-አጁሪይ

❝ቁርኣን የአላህ ቃል ወይም ንግግር ነው። ቃሉ ፍጡር አይደለም። ምክንያቱም ቃሉ የእውቀቱ አካል ነው። የአላህ እውቀት ደግሞ ፍጡር አይደለም። በመጨረሻም ቃሉ ወደ እሱ ተመላሽ ነው። ይህ የሁሉም የሱንናህ ዑለማዎች አቋም ሲሆን በዚህ ያስተባበለ ከኢስላም የወጣ እንጅ የለም።❞ ብለዋል።
(አሽ-ሸሪዓህ 1/84)

አላህ የበለጠ ያውቃል!


ሰል ማን



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 2⃣7⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
1
የንግድ በረከት ሰበቡ…

ከሐኪም ቢን ሂዛም (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿البَيِّعانِ بالخِيارِ ما لَمْ يَتَفَرَّقا، فإنْ صَدَقا وبَيَّنا بُورِكَ لهما في بَيْعِهِما، وإنْ كَذَبا وكَتَما مُحِقَتْ بَرَكَةُ بَيْعِهِما﴾

“ተገበያዮች እስካልተለያዩ ድረስ በምርጫ ላይ ናቸው። ‘እውነትን ከተናገሩና ያለበትን ነውር’ ግልፅ ካደረጉ ግብይታቸው ይባረክላቸዋል። ‘ያለበትን ነውር ከደበቁና ከዋሹ’ የግብይታቸው በረካ ትነሳለች።”

📚 ቡኻሪ (2079) ሙስሊም (1532) ዘግበውታል



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎቹ ለሚታወቀው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት!

- ሀሩን ሚዲያ፥ ግንቦት 17/2017

የየሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቲሞችን በመንከባከብ እና ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማስተማር ላበረከቱት አስተዋጽኦ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የተሽከርካሪ ስጦታው የተበረከተው የበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸውን በሚደግፉ አካላት እና በሥም ባልተጠቀሱ የቅርብ ወዳጆቻቸው አነሳሽነት መሆኑን ሚንበር ቲቪ ዘግቧል።

በመድረኩ ላይ የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቅርብ ወዳጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በተለይ ለየቲሞች ድጋፍ በማሰባሰብ ለበርካታ ሺሕዎች መድረስ ችለዋል። በዋነኝነት ከሚታወቁበት የቲሞችን ከመደገፍ ጎን ለጎን ወጣቶች የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ እገዛ እንደሚያደርጉ በቅርበት የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በመሠረቱት የሲር ለና የበጎ አድራጎት ሥራቸውን አጠናክረው በመቀጠል በበዓላት በሺዎች ለሚቆጠሩ የቲም ሕፃናት የአልባሳት ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል በመዘዋወር ከ385 በላይ ንፁህ የውሃ ጉድጓዶችን በማስቆፈር በርካቶች እንዲጠቀሙ አድርገዋል።

© ሀሩን ሚዲያ



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍41
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2⃣8⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
#ለወንድማችን ግርማ እንድረስለት! እናሳክመው

ወንድማችን ግርማ ስሜ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም አሁን ላይ ቁሞ መራመድ ሆነ
ሽንት መቆጣጠርም እያቃተው ነው

ይህ ወጣት ወንድማችን ቤተሰብ በሚያሳርፍበት እድሜው የአልጋ ቁራኛ ከመሆኑ በፊት በአሁን ሰአት በአስቸኳይ ከሀገር ውጪ ህክምና መከታተል ያስፈልገው ስለሆነ
ሁላችንም በቻልነው አቅም ህይወቱን እንታደግለት! የቻልነውን እናድርግለት
ለማገዝ የምትፈልጉ በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ
1000195406228 ግርማ ስሜ
በቴሌ ብር 0923642316 አልያም በመደወልም ማግኘት ትችላላችሁ
👍1
የመጀመሪያዎቹ አስር የዙልሒጃ ቀናቶች ያላቸው ትሩፋት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما من أيامٍ أعظمُ عندَ اللهِ ولا أحبَّ إليه العملُ فيهنَّ من هذهِ الأيامِ العشرِ فأكثروا فِيهنَّ من التهليلِ والتكبيرِ والتحميدِ﴾

“ከነዚህ አስር (የዙልሂጃ) ቀናቶች የበለጠ አላህ ዘንድ ትልቅ የሆነና የተወደደ ቀን የለም። በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ተህሊል ‘ላኢላዓሃ ኢለላህ’፣ ተክቢር ‘አላሁ አክበር’፣ ተህሚድ ‘አልሃምዱሊላህ’ ማለት አብዙ።”

📚 አህመድ ዘግበውታል ሰነዱን አህመድ ሻኪር ሶሂህ ብለውታል፡ 5446



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣9⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
1446ኛው የኢደል አድሀ አረፋ በዓል ግንቦት 29/2017 ዕለተ ጁምአ እንደሚከበር ታወቀ።

-ሀሩን ሚዲያ፣ ግንቦት 19/2017

የሳኡዲ አረቢያ የስነፈለክ ባለሙያዎች ዛሬ አመሻሽ የዙልሂጃህ ወር አዲስ ጨረቃ ማየታቸውን ተከትሎ በ የኢደል-አድሀ (አረፋ) በዓል ግንቦት 29/2017 በዕለተ ጁምአ ተከብሮ ይውላል።

በዚህም ወርቃማዎቹ 10 ቀናቶች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች በጾም፣በኢባዳና በቅዱሱ የመስጂደልሀረም በመሰባሰብ የሀጅ ስነስርዓት ያከናውናሉ።

© ሀሩን ሚዲያ



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
#ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁዑን

#የመስጂዳችን ታላቁ ሙዐዚን ሸኽ ኸሊል (ረሂመሁሏህ) ባለቤት የነበሩት እናታችን ፋጤ ባደረባቸው ህመም ቆይተው በዛሬው ዕለት ወደ ማይቀረው አለም ወደ  አኼራ ሄደዋል 

  ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው  አላህ መፅናናቱን እና ብርታቱን ይወፍቃቸው::

እናታችን ፋጤንም  አላህ ምህረትን እንዲለግሳቸው፣ መልካምን መስተንግዶ በአኼራ ከሚቸራቸው እና ማረፊያቸው በጀነተል ፊርዶስ ከሆኑት ባሮች ይመድባቸው ዘንድ  ዱአችን  ነው::
😭😭😭
ፈትህ አባቦራ መስጂድ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 0⃣1⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣6⃣
የመጀመሪያዎቹ አስር የዙልሒጃ ቀናቶች ያላቸው ትሩፋት!

ከነቢዩ (ﷺ) ሚስቶች አንዷ እንዲህ ትላለች፦

﴿كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَصُومُ تِسْعَ ذِي الْحِجَّةِ وَيَوْمَ عَاشُورَاءَ، وَثَلَاثَةَ أَيَّامٍ مِنْ كُلِّ شَهْرٍ ؛ أَوَّلَ اثْنَيْنِ مِنَ الشَّهْرِ وَالْخَمِيسَ﴾

“ረሱል (ﷺ) የዙልሂጃ ዘጠነኛውን ቀን የአሹራን ቀን ይፆሙ ነበር። እንዲሁም ሁሌ በየወሩ ሶስት ቀናቶችን በወር ውስጥ የመጀመሪያውን ሰኞና ሐሙስ ቀናቶች ይፆሙ ነበር።”

📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 2437



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣2⃣ #ዙልሒጃ 1⃣4⃣4⃣6⃣
2025/07/13 18:45:10
Back to Top
HTML Embed Code: