Telegram Web
አስደሳች ዜና ከሱና ዩኒቨርሲቲ
ልዩ የክረምት ስልጠና ለሃይስኩል ተማሪዎች ለሁለቱም ፆታ

-ፊቅሁል ዒባዳ
-በአቂዳ/ተውሒድ
-ቁርአን ተፍሲር እና ሲራ
-ኢስላማዊ አዳብ/አኽላቅ
-መሰረታዊ የእስልምና እውቀት
-የህይወት ክህሎት (ተርቢያ)፡ በጊዜ አጠቃቀም ፤ ስሜ  ታዊ ብልህነት ፤ ዲጂታል ሚድያ እና የሥራ ፈጠራ ባህል

በየሁለት ሳምንቱ በታላላቅ ዓሊሞች እና ኡስታዞች የሙሀዶራ ፕሮግራም በቤተሰብና ቀድሞ ለሚመዘገብ ቅናሽ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን ገቢው ለሱና ዩኒቨርሲቲ ማጠናከርያ ይውላል

ምዝገባ አድራሻ፡- ጀሞ ሶስት አዲሱ ሰዒድ ያሲን 2ኛ ፎቅ አዋሽ ባንክ ባለበት መግቢያ
ወይም በስልክ ቁጥራችን በ 0935332424/ 0990452838/ 0990442838 በመደወል መመዝገብ ይቻላል
የምዝገባ ጊዜ
ከሰኔ 24-30, 2017 ዓ.ል ይካሄዳል
ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ለገጠመው!

ከአነስ ኢብኑ ማሊክ (رضيﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ እያሉ ዱዓ ያደርጉ ነበር፦

﴿اللهمَّ لا سهلَ إلا ما جعلتَه سهلًا، وأنت تجعلُ الحَزْنَ إذا شئتَ سهلًا﴾

“አላህ ሆይ! አንተ ቀላል ካደረግከው ነገር ውጭ ቀላል የለም፡፡ አንተ ሀዘንን ከሻህ ቀላል ታደርጋለህ፡፡”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 2886



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 0⃣7⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ዱኒያ የተረገመች ናት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ألا إنَّ الدُّنيا ملعونةٌ ملعونٌ ما فيها، إلّا ذِكرُ اللَّهِ وما والاهُ، وعالِمٌ، أو متعلِّمٌ﴾

“አዋጅ! ዱኒያም ዱኒያ በውስጧ የያዘችው ነገር የተረገመ ነው። አላህን ለማውሳት አጋዥ የሆኑ ነገሮች፣ ዓሊም ወይም ተማሪ ሲቀሩ።”

📚 ሶሂህ አትርጊብ፡ 3244



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
⚠️ አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ? ⚠️

ኤሌክትሪክ ጠቀሜታው የላቀ ቢሆንም በጥንቃቄ ጉድለት በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ ለሞትም ይዳርጋል፡፡ ታዲያ ሁሌም እራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በኤሌክትሪክ ቢያዝ ወዲያውኑ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ህይወቱን ሊያድን የሚችልበት አግባብ አለ።

⛔️ አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ?

የኤሌክትሪክ ምንጭን ማጥፋት ወይም ቆጣሪ ብሬከር መመለስ

ይህ የመጀመሪያውና ዋነኛው እርምጃ ሲሆን፤ የቆጣሪ ብሬከሩ የት እንዳለ ካወቁ በፍጥነት ማጥፋት እና የኤሌክትሪክ ፍሰት መቆሙን ሲያረጋግጡ ብቻ ወደ ተጎጂው መቅረብ፤

ኤሌክትሪክን ወዲያውኑ ማጥፋት ካልቻሉ ተጎጂውን ከኤሌክትሪክ ምንጭ ለማራቅ ደረቅ እና ኤሌክትሪክ የማያስተላልፍ (non-conductive) ነገር ይጠቀሙ፤

በፍፁም ባዶ እጅዎን ወይም እርጥብ ነገርን አይጠቀሙ!

ለምሳሌ:- ደረቅ የእንጨት ዘንግ፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ እጀታ፣ ወፍራም ጋዜጣ ወይም መጽሐፍ፣ ወይም የጎማ ምንጣፍ መጠቀም ይችላሉ።

ተጎጂውን አይንኩ! በኤሌክትሪክ የተያዘ ሰው ሰውነታቸው ሊያስተላልፍ ይችላል፤

የኤሌክትሪክ ንዝረት የቆዳ ላይ እና ውስጣዊ ቃጠሎ ሊያስከትል ስለሚችል የተቃጠለውን ወይም የተጎዳውን የሰውነት ክፍል በቀዝቃዛ (በረዶ ባልሆነ) ውሃ በማቀዝቀዝ ንጹህና ደረቅ በሆነ ጨርቅ ይሸፍኑት።

የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም ይደውሉ፤

ያስታውሱ‼️

የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ሁኔታ ሲመለከቱም አደጋው ከመድረሱ በፊት በአቅራቢያዎ ካለ የተቋማችን የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በአካል ወይም በጥሪ ማዕከሉ 905 እና 904 በመደወል አልያም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ያሳውቁ!

የእርስዎ ደህንነት ቀዳሚ መሆኑን አይርሱ❗️
እራስዎን ከአደጋ ይጠብቁ❗️
ኤሌክትሪክን በቁም ነገር ይዩት🚫

#Safety_First_Always - #ሁልጊዜም_ቅድሚያ_ለጥንቃቄ⚠️

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
" የዓሹራ ቀን ፆም ያለፈን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል»ረሱል ﷺ
ቀኑ የአሹራ 10ኛ ቀን ሲሆን ከፊት ወይም ከሗላ አንድ ቀን እንድንጨምር ታዘናል
የፊታችን ቅዳሜ 10ኛው ቀን ይሆናል!!
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #58 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣8⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
በመልካም ስራ የበለጠህን መመልከት ጥሩ ነው። በዛውም የተሰጠህን እድል መጠቀም ብልህነት ነው!

ከአብደላህ ቢን ዓምር (رضي الله عنه) ተይዞ፡ አንድ ሰው ረሱል (ﷺ) እንዲህ በማለት ጠየቃቸው፦

﴿يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ الْمُؤَذِّنِينَ يَفْضُلُونَنَا. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " قُلْ كَمَا يَقُولُونَ، فَإِذَا انْتَهَيْتَ فَسَلْ تُعْطَهْ﴾

“አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሙዓዚኖች በደረጃ በለጡን። ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉት፦ ‘እነሱ ሙዓዚኖች የሚሉትን ተከታትለህ በል፤ ስትጨርስ (የምትፈልገውን ከአላህ) ጠይቅ ትሰጣለህ።’”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 524



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 0⃣9⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ስልጣን አገልጋይነት ነው
~
አንድ ሰው አጠቃላይ የሃገር መሪም ይሁን ከዚያ ባነሰ ታች ላይ የሚገኝ የስልጣን እርከንም ላይ ይሁን ስልጣኑ ያሻውን ለማድረግ ነፃ የሚያደርገው ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቀመጠ የቅጥር ሰራተኛ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል። ስለዚህ በየትኛውም የኃላፊነት ወንበር ላይ የተቀመጣችሁ ወገኖች ባጠቃላይ በተግባር የህዝብ አገልጋይ ተቀጣሪ ሁኑ። እንጂ ስልጣናችሁን ህዝብን ለማጉላላትና ለማንገለታታት፣ ራስን በተለየ ለመጥቀም አትጠቀሙበት። ይህንን እውነታ አጉልቶ የሚያሳይ አንድ ታሪክ ልጥቀስ።

አቡ ሙስሊም አልኸውላኒይ ረሒመሁላህ ከኸሊፋው ሙዓዊያ ቢን አቢ ሱፍያን ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ ገቡና

* "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ የቅጥር ሰራተኛ!" አሉ።
- በዙሪያው የነበሩት ሰዎች "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ አሚር (አዛዥ) በል!" አሉ።
* እርሳቸው ግን "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ የቅጥር ሰራተኛ!" አሉ።
- ሰዎቹ እንደገና "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ አሚር (አዛዥ) በል!" አሉ።
* እርሳቸው ግን አሁንም "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ የቅጥር ሰራተኛ!" አሉ።
- ሰዎቹ ለሶስተኛ ጊዜ "አሰላሙ ዐለይከ! አንተ አሚር (አዛዥ) በል!" አሉ።

ሙዓዊያ በዚህን ጊዜ ፡ "አቡ ሙስሊምን ተውት፤ እርሱ የሚለውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው" አሉ።

ከዚያም አቡ ሙስሊም ለሙዓዊያ እንዲህ አሉ፡- "አንተ የነዚህ በጎች ጌታ ለጥበቃቸው የቀጠረህ ቅጥር ሰራተኛ ነህ። የተጎዱትን ብትንከባከብ፣ የታመሙትን ብታክም እና ጉልበተኞቹን ከደካሞቹ ብታቅብ ጌታህ ደሞዝህን ይሞላልሃል። ነገር ግን የተጎዱትን ባትንከባከብ፣ የታመሙትን ባታክም እና ጉልበተኞቹን ከደካሞቹ ባታቅብ ጌታህ ይቀጣሃል!" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 2/125] [ታሪኹ ዲመሸቅ፡ 27/223፣ 67/218]

አዎ ስልጣን፣ ሹመት፣ አለቅነት ተጠያቂት ነው። ሸክም ነው። ስለዚህ ትንሽም ይሁን ትልቅ ኃላፊነት ላይ የተቀመጠ ሁሉ ልቡ እንዳያብጥ፣ ጥጋብ እንዳይሰማው አላህን ያስብ። ነፍሲያውን ይርገጥ። ትእቢቱን ያስተንፍስ። አገልጋይነትን፣ ትህትናን ይላበስ። ይህ ሲሆን የአላህ እገዛ ከሱ ጋር ይሆናል። ከአላህም ዘንድ ከሰውም ዘንድ የተወደደ ይሆናል።
=

Via Ibnu Munewor




https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
የአማኝ ነገሩ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.﴾

“የአማኝ ጉዳይ አስገራሚ ነው። ነገሩ ሁሉ መልካም። ይህ ደግሞ ለአማኝ እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ሲያጋጥመው ያመሰግንና ለሱ መልካም ይሆንለታል። ችግር ሲያጋጥመው ይታገስና ለሱ መልካም ይሆንለታል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2999



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1⃣0⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ወንጀል በምድር ላይ የበሽታ መብዛት ምክንያት ነው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لَمْ تَظْهَرِ الفاحشةُ في قومٍ قَطُّ؛ حتى يُعْلِنُوا بها؛ إلَّا فَشا فيهِمُ الطَّاعونُ والأوجاعُ التي لم تَكُنْ مَضَتْ في أسلافِهِم الذينَ مَضَوْا﴾

“በህዝቦች ውስጥ ፀያፍ ተግባር በአደባባይ ግልጽ አድርጎ የሚፈጽም አንድም አካል አይኖርም፤ ከዚህ በፊት በነበሩት ቀደምቶቻቸው ያልነበረ ወረርሽኝ ወይም በሽታ በመካከላቸው የሚሰራጭ ቢሆን እንጅ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 7978



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1⃣1⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
የላቀ ምንዳ ያለው ሐዲስ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إذا مَرِضَ العَبْدُ، أوْ سافَرَ، كُتِبَ له مِثْلُ ما كانَ يَعْمَلُ مُقِيمًا صَحِيحًا﴾

“አንድ ባሪያ በታመመ ወይም መንገደኛ በሆነ ግዜ፤ ጤነኛና በሀገሩ ነዋሪ በነበረበት ግዜ ይስራ የነበረውን መልካም ስራ አምሳያውን (በምንዳነት) ይመዘገብለታል።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2996

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

Telegeram፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

Whatsup፦ https://bit.ly/486xnrS

Facebook፦ https://bit.ly/41zEZkk

Instagram፦ https://bit.ly/4arMbTx

X፦ https://bit.ly/41tIUPv

Youtube፦ https://bit.ly/3UTTSwh

Tik tok፦ https://bit.ly/442V9nM
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣2⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
2025/07/07 21:21:26
Back to Top
HTML Embed Code: