Telegram Web
❥::::::::::እህቴ ሆይ!:::::::::::❥

አላህ ይዘንልሽ እና እወቂ
አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚከተሉትን ሴቶች መርገማቸውን ታውቂያለሽን?

1) ☞ቅንድብ አስቀንዳቢ
2) ☞ቅንድብ ቀንዳቢ
3) ☞ዊግ (አርቴፊሻል ፀጉር) ቀጣይ
4) ዊግ አስቀጣይ
5) ☞ንቅሳት ተነቃሽ
6) ☞ንቅሳት ነቃሽ

እንዳትረሺ እህቴ አላህ የሰውን ልጅ ባማረ ሁኔታ ነው የፈጠረው፡፡
አላህ እና መልክተኛው የረገሙት እኮ ፈላህ አይወጣም፡፡ ከነዚህ ውስጥ ካለሽበት አላህ የባርያዎቹን ንስሃ ተቀባይ ነውና ዛሬውኑ በንስሃ ተመለሽ፡፡ አላህ ወደ እርሱ በንሰሃ የሚመለሱትን ይወዳል

💌::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::💌👇

@fidake_jemaa
@fidake_jemaa
@fidake_jemaa
ሴት ልጅን ከመጉዳትህ በፊት
የእህትህን ፈገግታ አስታውስ‥

@fidake_jemaa
Forwarded from 2 وبيجوت Tube (Assifen😍😍)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 169 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,798 የላብራቶሪ ምርመራ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,805 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 111 ወንድ እና 58 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 168 ኢትዮጵያውያን እና 1 የአሜሪካ ዜጋ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 138 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 11 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 5 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው አስራ ሁለት (12) ሰዎች (10 ከአማራ ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 262 ደርሰዋል።

@fidake_jemaa
‍ ❥ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

 أَبِي هُرَيْرَةَ ، قَالَ : سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : مَا أَكْثَرُ مَا يُدْخِلُ النَّاسَ الْجَنَّةَ ؟ قَالَ : " تَقْوَى اللَّهِ وَحُسْنُ الْخُلُقِ

ረሱል ﷺ ከሰዎች በብዛት ጀነት ሚገቡት የትኞቹ ናቸው ተብለው ሲጠየቁ፦
የሰው ልጅን በብዛት ጀነት የሚያስገባው
☞አላህን መፍራትና
☞ሰናይ ስነ ምግባር ነው፡፡ ብለዋል።

አል ቲርሚዚ 2004
📚ኢብኒ ማጃህ 4246📚
❀ـــــــــــــ🍃🌸🍃ــــــــــــ❀
🌹 @fidake_jemaa 👈
🌹 @fidake_jemaa 👈
🦋............🍃🌹🍃..........🦋
🌍 የመላይካዎችን ዱአ ለሚፈልግ ሰው ቀላል መንገድ

➠ ስምንት ሁኔታዎች ላይ መላይካዎች ላንተ ዱአ ያደርጉልሀል እናም እንዳትዘናጋ


🕌 ⓵ መስጊድ ቁጭ ብለህ ሰላት በምትጠባበቅበት ወቅት

🏥⓶ የታመመን ስትጠይቅ

🕋⓷ በሰላት ላይ የመጀመሪያው ሰፍ ስትቆም

🕔⓸ ሙስሊም ወንድምህን ስትዘይር

🙏⓹ በሩቅ ለወንድምህ ዱአ ስታደርግ

🏬⓺ ሰዎችን መልካም ነገር ስታስተምር

💧⓻ በውዱእ ላይ ሆነክ ስትተኛ

🍔⓼ ሱህር ስትበላ

@fidake_jemaa
@fidake_jemaa
@fidake_jemaa 👈
ሴት ልጅ ብዙ ነገር ነች
👉 ልጅህ ነች
👉 እህትህ ነች
👉 መካሪህ ጓደኛህ ነች
👉 የትዳር አጋርህ ነች
👉 የልጆችህ እናት ነች
👉 #እናትህ_ነች

በሷ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ይቁም⛔️🔞
@fidake_jemaa
@fidake_jemaa
@fidake_jemaa
Forwarded from وبيجوت Tube (La Hadry)
።።።።።።።።።።። ውብ መልእክት ።።።።።።።።።።።

አንድ ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እብድ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
እብዱ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው ሬሳ ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳን አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው አላህን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የአላህ በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም?
:
ሕይወት ምንድን ነው?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
1. ሆስፒታል
2. እስር ቤት
3. መቃበር ቦታ
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።
:
ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን።
ስለ ሁሉም ነገር 🍂አልሀምዱሊላህ !!!


እስኪ ለሚወዱት ሁሉ #ሼር

Join👇join👇join👇join

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
⊰━━━━━━⊱🌸
👇👇👇👇
🌟 @Hubi_Resulilah 🌟
🌟 @Hubi_Resulilah 🌟
⊰━━━━━━⊱🌸
💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
❥::::::::::::::::የጀነት_ስሞች::::::::::::: ❥
1) ጀነት
2) ዳሩ ሰላም
3) ዳሩል ኹልድ
4) ዳሩ ሙቃማህ
5) ጀነቱል መእዋ
6) ጀናት ዓድን
7) ዳሩል ሐየዋን
8) አል ፊርደውስ
9) ጀናቱ ነዒም
10) መቃሙል አሚን
11) 'መቀዓድ ሲድቅ'
12) 'ቀደመ ሲድቅ'

▒▒▒ ጀነት ▒▒▒
•የጀነት ፀጋዎቿ ያልቁብኛል ብሎ ጭንቀት ፤ እለያታለው ብሎ ስጋት የለም; ፀጋዎቿ
ዘውታሪ ሞትም የለምና!
ዱንያ ላይ የቱን ያክል ገንዘብ ቢኖርህ ገንዘብህ ቢትረፈረፍ ንብረትህ ቀድሞህ
ይጠፋል አልያም ትተኸው ትሄዳለህ ።
•በጀነት ውስጥ ልክ እንደ ዱንያ ጠላት የለም ለወደፊት ማሰብ የሚባል ነገርም የለም
፤ ሁሉ ነገር እንደፈለክ ነው; ጥላቻ የሚባል ነገርም ከልብ ላይ ይወገዳል ።
• በጀነት ውስጥ ልክ እንደ ዱንያ ኑሮ እንድትሞላልኝ ብለህ ሰበብ ለማድረስ ደፋ ቀና
ማለት የለም; ጀነት ውስጥ አሏህ ነፍስህን የምትፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቷልና
•••
------------------------------------------------
ጌታችን ሆይ! ለጀነትህ ብቁ ባንሆንም ጀሐነምን መቋቋም አንችልምና በሰፊው
እዘነትህ ጀነትህን ወፍቀን 🤲

እስኪ ለሚወዱት ሁሉ #ሼር

Join👇join👇join👇join

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
⊰━━━━━━⊱🌸
👇👇👇👇
🌟 @Fidake_jemaa 🌟
⊰━━━━━━⊱🌸
💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
አስገራሚ ታሪክ
ለኢስላም ጠላትነቱ የታወቀ አንድ ሰው ነበር፡፡ በጊዜው በቦታው ላይ ማንም ያልመለሰለት ሶስት ታዋቂ ጥያቄዎች ነበሩት፡፡ ባግዳድ ላይ ካሉ አዋቂዎች አንዳቸውም ጥያቄውን የመለሰለት አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ሰውዬው እስልምና ላይ በግልፅ ይቀልድ ነበር፡፡ ኢስላምንና ሙስሊሞችን መንገድ ላይ በህዝብ ፊት ያጥላላ ነበር፡፡ አንድ ቀን ትንሽዬ ልጅ እድሜው ገና 10 የሆነ ታዳጊ ልጅ ሰውዬው ሶስቱ ጥያቄዎችን ደጋግሞ በማንሳት መንገድ ላይ በህዝብ ፊት ሙስሊሞች ላይ ሲጮህና ሲቀልድ ይሰማዋል፡፡ ይህ ታዳጊ የ 10 አመት ልጅ ሰውዬው ተናግሮ እስኪጨርስ በዝምታ ከጠበቀ በሗላ ሰውዬውን ሊጋፈጥ ወሰነ፡፡ ልጁ ወደ ሰውዬው ፊት ለፊት በመራመድ “ጥያቄዎችህን እኔ እጋፈጣቸዋለሁ” በማለት አሳወቀው፡፡ ሰውዬው ጎንበስ ብሎ ልጁን ሲያየው ይበልጥ ማፌዙን ተያያዘው “የ 10 አመት ልጅ እኔን ሊጋፈጠኝ ነው፤ በቃ እናንተ ህዝቦች ማድረግ የምትችሉት ይህንን ብቻ ነው!!!?” በማለት ይስቃል ይሳለቃል፡፡ ይህ ታዳጊ ልጅ በአላህ ፈቃድ ጥያቄዎቹን ለመመለስ በትዕግስት የሰውዬውን ምላሽ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ በመጨረሻም ሰውዬው “እስቲ እንስማህ” በሚል የፌዝ ሞራል የዚህን ታዳጊ ልጅ ጥያቄ ተቀበለ፡፡ የአካባቢው ሰዎች ባጠቃላይ ለአንዳንድ ጉዳያቸው በሚሰባሰቡበት ግልፅ የስብሰባ ቦታ ተሰባሰቡ፡፡ ሰውዬው ከፍ ያለ ቦታ ወጣና ድምፁን ከፍ በማድረግ የመጀመሪያ ጥያቄውን አቀረበ “ባሁን ሰዐት ፈጣሪያቹ ምን እያደረገ ነው?” ይህ ትንሽዬ ልጅ ለትንሽ ጊዜ አሰበና ጥያቄውን ይመልስለት ዘንድ ሰውዬውን ካለበት ከፍታ ቦታ ላይ ወደ ታች እንዲወርድና እሱ ከፍ እንዲል ጠየቀው፡፡ “ምን? እኔ ወደ ታች እንድወርድ ትፈልጋለህ?” ትንሹ ልጅ “አዎ ጥያቄህን እንድመልስልህ ትፈልጋለህ አይደል ካለህበት ውረድ” አለው፡፡ ሰውዬው ካለበት ከፍታ ቦታ ወደ ታች ወረደ ትንሹ ልጅ ትንሽ እግሩን በመጠቀም ከፍታው ቦታ ላይ ወጣና ለጥያቄው ምላሹን ሰጠ “ያ አላህ! በነዚህ ህዝቦች ፊት አንተ ምስክሬ ነህ፡፡ ካፊር ወደ ታች እንደሚሆንና ሙስሊም ከፍ እንደሚል የገባኸውን ቃል አደረከው” አለ፡፡ ሰዎች ባጠቃላይ በምላሹ ተገርመው “ተክቢር…አላሁ አክበር” አሉ፡፡ ሰውዬው በጣም አፈረ በድርቅና ሁለተኛውን ጥያቄ ጠየቀ “ከፈጣሪያቹ በፊት ምን ይገኝ ነበር” ትንሹ ልጅ በደንብ አሰበና ለሰውዬው ከ 10 ጀምሮ ወደ ዃላ እንዲቆጥር ይጠይቀዋል፡፡ ሰውዬው ቆጠረ “10፣9፣8፣7፣6፣5፣4፣3፣2፣1፣0” ልጁ ጠየቀ “ከ 0 በዃላ ምን ይመጣል” ሰውዬው “አላውቅም…..ምንም” አለው፡፡ “በትክክል ከአላህ በፊት ምንም አልነበረም፤ እርሱ ፍፁምና የማይሞትም ነው፡፡” ሰዎች በድጋሚ “ተክቢር!!…አላሁ አክበር” በማለት ለልጁ አድናቆታቸውን ገለፁ፡፡ የሰውዬው ፊት ቢለዋወጥም ሶስተኛ ጥያቄውን ከማቅረብ ወደ ዃላ አላለም “ፈጣሪያቹ ወደ የትኛው አቅጣጫ ነው የዞረው?” በማለት የመጨረሻ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ ትንሹ ልጅ አሰበ አሰበና ሻማ ይዘውለት እንዲመጡ ጠየቀ፡፡ በጥያቄው መሰረት ሻማ ቀረበለትና አበራው፡፡ ሰውዬው “በዚህ ሻማ ደግሞ ምን ልታረጋግጥልን ነው?” በማለት ጠየቀ፡፡ ልጁም “ይህ የሻማ መብራት ወደ የትኛው አቅጣጫ ነው የሚበራው?” ሲል ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ ሰውዬው “በሁሉም አቅጣጫ” ሲል መለሰለት ልጁም “የአላህ ኑር(ብርሃን) የትም ቦታ አለ፤ እርሱ በእውቀቱ ሁሉም ቦታ አለ፡፡ እርሱ(በእውቀቱ) የማይገኝበት ቦታ የለም” በማለት መለሰለት፡፡ የተሰበሰቡ ሰዎች ባጠቃላይ በተክቢር ቦታውን አቀለጡት፡፡ ሰውዬውም በልጁ መልስ በመገረምና ለጥያቄዎቹ ምላሹን በማግኘት እስልምናን በመቀበል የልጁ ተማሪ ሆነ፡፡ ይህ ትንሽዬ ልጅ ማን ነበር? ከመሪዎቻችን ከእስልምና ምሁሮች አንዱ የሆኑት ኢማሙ አቡ ሀኒፋ ናቸው፡፡

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share#Join us #Forward
----------------------------------

@Fidake_jemaa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ወጣት በመጠጣቱ ምክንያት ዝሙተኛ ሆኖ እህቱን ያስረገዘዉ ወጣት ታሪክ #በኻሊድ #አል #ረሻድ
በጣም አስተማሪ ታሪክ 4 Mb .ስልክህ አንድ ብር ካለዉ ማዉረድ ይችላሉ ለኸይር 1 ብር ነይተን እናዳምጠዉ😭
----------------------------
#SHARE_AND_SUPPORT_US

@Hubi_Resulilah
ገንዘብ በፀጋ እና በፈተና መካከል
፨፨፨፨
ቲርሚዚ እንደዘገቡት ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት የተራቡ ተኩላዎች በበግና ፍየል ውስጥ ሲለቀቁ ከሚያደርሱት ጥፋት የበለጠ የሰው ልጅ ለገንዘብና ክብር ያለው ጉጉት ያጠፋዋል፡፡››
ያለፉት ደጋግ ሙስሊሞች (ሰለፎች) የገንዘብን ፈተና በእጅጉ ይፈሩ ነበር፤ ኸሊፋው ዑመር (ረ.ዐ) እሳቸው የስልጣን ዘመን የእስልምናን መስፋፋት (ፉቱሐት) ሲያዩ፤
“ይህን ነገር ከነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እና ከመጀመሪያው ኸሊፋቸው አቡበክር (ረ.ዐ) አላህ ያዘገየው ለነርሱ መጥፎ ፈልጎላቸው አይደለም፤ ለዑመርም የሰጠው ደግሞ ጥሩ ስለሻለት አይደለም” በማለት ያለቅሱ ነበር፡፡

የህያ ኢብን ሙዓዝ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፡- “ገንዘብ ጊንጥ ነው፤ ከነደፈህ መርዙ ይገድልሃል፤ ስለዚህ መድሃኒቱን ካላወቅህ አትያዘው፡፡” መድሃኒቱ ምንድን ነው ተብለው ተጠየቁ? “ሐላል ከሆነ ምንጭ መውሰድና በተገቢው ቦታ መጠቀም ነው” ሲሉ መለሱ፡፡

በሌላ በኩል ....
ኢስላም በአላህ ላይ መመካትን ቢያዝበትም ስንፍናን ደግሞ አጥብቆ ይከለክላል፡፡ ኢስላም የሰው ልጅ ተንቀሳቅሶና ጥሮ ግሮ ሲሳዩን እንዲፈልግ ያስተምራል፡፡

ኸሊፋው ዑመር (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹አንድ ሰው ሳይሠራና ሳይንቀሳቀስ ቁጭ ብሎ አላህ ሆይ! ሲሳዬን ስጠኝ አይበል፤ ምክንያቱም ሰማይ ወርቅና ብር እንደማታዘንብ በእርግጥ አውቃችኋል፡፡››

መሐመድ ቢን አል-ሙንከዲር ስለ ገንዘብ ሲናገሩ ‹‹ሐብት አላህን ለመታዘዝ ጥሩ አጋዥ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ገንዘብን አለመፈለግ ወይም ድንበር ባለፈ ቸርነት ሰዎችን ለማማለልና የበላይነትን ፍለጋ ገንዘብን መለገስ ዙህድ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ዙህድ ማለት የዱንያን ርካሽነትና የአኺራን ውድነት በመረዳት ዱንያን ችላ ማለት ነው፡፡ ይህች ዓለም (ዱንያ) ጥቂት ቆይታ እንደጤዛ የምትረግፍ መሆኗንና አኺራ ደግሞ እንደ ዱር የምትቆይ መሆኗን ያወቀ ሰው ይህችን ሸጦ ያችን ለመግዛት ያለው ፍላጎት ይጨምራል፡፡
ሰለፎች ዱንያን ችላ ማለታቸው ሐራም ላይ ላለመውደቅ ካላቸው ፍራቻ የተነሳ ነበር፤

ሙዘሚል እንዲህ አሉ፡- ሱፍያን አሥ-ሠውሪይ ሥጋ በእንቁላል እየበሉ እያለ ደረስኩ፤ ስለዚህ ነገርም አናገርኳቸው እሳቸውም “እኔ ጥሩ ምግብ እንዳትበሉ አላዘዝኳችሁም፤ ሐላል ሥሩ ጥሩም ብሉ፤” አሉኝ፡፡
ዓሊይ ኢብን ፉደይል አባቴ ፉደይል (አላህ ይዘንላቸው) አብደላህ ኢብን ሙባረክን (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- አንተ ዱንያን ችላ እንድንል ታዘናለህ፡፡ ነገር ግን ከኹራሳን (ኢራን) እቃዎችን ወደ መካ እያመጣህ ስትሸጥ እናይሃለን፣ ይህ እንዴት ነው? ሲሉ ጠየቋቸው ኢብኑል ሙባረክም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “የዓሊ አባት ሆይ! እኔ ይህን የማደርገው የሰውን ከመከጀል ራሴን ለመጠበቅና ጌታዬን ለመታዘዝም እንዲያግዘኝ ስል ነው፡፡”

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share@Join us #Forward
----------------------------------

@Hubi_Resulilah
ሺ ጊዜ የንግግር ጠቢብ ቢኮንም የፍልስጤሞችን ጀግንነት በሰው ልጅ ቋንቋ መግለጽ አይቻልም።
┈┈❈••✦ ✾ ✦••❈┈┈

የ19 ዓመቱ መሽቀርቀር የሚወድ እና ብዙ ጊዜ ሰልፊ ፎቶ መነሳት የሚያስደስተው አዳዲስ ልብሶችና እስማርት የሞባይል ስልኮችን የሚቀያየር ዑመር አቡ ለይሊ የተባለ ወጣት ከወደ ፍልስጤም ለመስጂደል አቅሳ ክብር ህይወቱን አሳልፎ ሰጠ። የቱንም ያክል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማረከው ወጣት ቢሆንም
በኢስላም ላይ ያየውን ውርደት አይቶ ለማለፍ ዘመናዊ ቁሶቹ አባብለው እንዲታገስ ሊያደርጉት አልቻሉም።
ወደ አቅሷ ጉዞ ማድረግ ጀመረ የመስጊዱ በር በእስራኤል ወታደሮች መዘጋቱን ተመለከተ። በሩን ክፈቱልኝ ሲልም ጠየቀ። ወታደሮቹም አንከፍትልህም ነበር መልሳቸው። መስጂዱ የእኛ ነው እናንተ ስለዚህ በርም ሆነ ስለ መስጊዱ ምን አግብቷችሁ ነው አዛዥ የሆናችሁት? በመለት ጮኸ። እንደማይከፍቱለት ነገሩትና እንቢ ካለ እርምጃ እንደሚወስዱበት አስፈራሩት።
ከመስጊዱ ትንሽ ራቅ ብሎ ከተጓዘ በኋላ አንዱን የአይሁድ ወታደር መሳሪያውን ቀምቶ አካባቢው ላይ ባሉ የእስራኤል ነፍሳት ላይ ሁሉ በራሳቸው ጥይት ከገደላቸው በኋላ ከአካባቢው ተሰወረ ። እሱን ለማግኘት ከ300 በላይ የእስራኤል ጦር ተሰማራ። በመጨረሻ በአንድ ከሀዲ ፍልስጤማዊ ጠቋሚነት ተደብቆ የነበረበትን ቦታ የእስራኤል ወታደሮች በከባድ መሳሪያ ሳይቀር መደብደብ ጀመሩ።
እጅ ሳይሰጥ አንድ ጥይት እስክትቀረው ድረስ ብቻውን ከመቶ በላይ የእስራኤል ወታደር ጋር ተታኩሶ ሸሂድ ሆኗል። በቤቷ ደብቃው የነበረችው የአንዲት አሮጊት ቤት በዶዞር እንዲፈርስ ተደርጓል።
ዑመር አቡ ለይሊን የአይሁድ መገናኛ ብዙሃኖች ሳይቀሩ የፍልስጤም እራንቦ ብለውታል።
ለአቅሷ የተሰውትን ጀግኖች ሁሉ አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይሸልማቸው።

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share#Join us #Forward
----------------------------------

@Hubi_Resulilah
#ጀነት_መግባት_ትፈልጋለህ ወይ ብየ #ብጠይቅክ_እርግጠኛ_ነኝ አዎ ብለህ እንደምትመልስልኝ እናም አልጠይቅህም። ይልቅስ ጀነት #ለመግባት ምን #አስቀድመሃል? ምንስ #አስከትልሃል? በማለት እጠይቅሃለሁ!

#እኛም ጀነትን እንመኛለን እነዚያ ድንቅ ትውልዶች እንደተመኙት፤ ግን በኛና በነሱ መሃል ያለው ልዩነት እንደ ሰማይና እንደምድር ነው። እነሱኮ በቀን ስኣታት የቲሞችን በማብላትና በማልበስ፤ የተቸገረን በመርዳት፤ የታመመን በመጠየቅ፤ የሞተን በመቅበር፤ ባሪያን ነፃ በማውጣት እንዲሁም ሌሎች ኢባዳዎችን ያከናውናሉ።
አዳራቸውን ደግሞ ለጌታቸው በመስገድና ጌታቸውን በማወደስ ቁርኣን በመቅራት ያነጉ ነበር።

#እስኪ በአላህ ይሁንብን እኛ የምናልማት ጀነት እነሱ የለፉላትን ነውን? ታዲያ እውነት ጀነት ከሆነች አላማችን የህይወታችን ግብ እሷ ከሆነች ይህ ሁሉ መሽመድመድ ምን ይሉታል? በአላህ ይሁንብኝ ከመካከላችን ይኖራል ፋቲሀን እንኳን አሳምሮ መቅራት የማይችል እና ታዲያ በየትኛው ስራችን በምንስ ልፋታችን ነው ጀነትን መውረስ የምናልመው??

#እህት ወንድሞቸ እስኪ ከተኛንበት እንቅልፍ እንንቃና ዲናችንን እንወቅና ለእስልምናችን እንኑር።

#በዝቺ ቅጠቢስ በሆነች ዱንያ አንታለል! አብሽሩ አትፍሩ አትዘኑ አትተክዙ ምን እበላለሁ ምን እለብሳለሁ አትበሉ።
አላህ እሱ እንደሚንከባከበን ቃል ገብቷልና፦
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ
ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡(20:132)

#አላህ ሆይ ለፈጠርከን አላማ አኑረን!!🙏

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share#Join us #Forward
----------------------------------

@Hubi_Resulilah
💫ነፍስህን የፈለከውን ያህል ልቀቃት እንዳስፈለጋት ትፈንጥዝ የሚመችህንና የምትወደውን ሁሉ አድርግ መጨረሻ ለይ ግን መፀፀትህ አይቃርም"::

"وحيل بينهم وبين مايشتهون"

🎖ነፍስህን በታቻላህ መልኩ እንድትታጋስ አድርጋት የፈለጋችውን ሁሉ ሳይሆን የተፈቃደላትን ስጣት አንዴ በኢበዳ አንደንዴም በፆም በቂርአት ስያሽህም በእውቀት እየስታጋስክ አቆያት በመጫረሻ ትደሳታለህ ሽልማትህም ይህ ይሆናል::

"و لكم فيها ماتشتهي أنفسكم "

#ዱንያ ላይ ያማረ ነገር ሁሉ ዘላቂ አይደለም ይጠወልጋል ይደርቃል ይፈርሳል -

ውበት ሁሉ ባለበት ጠፋጭ ሁሉ በታቀመሳበት ምቾት ሌለም ሁሉ ዛለቂ በምሆንበት ጀነት ምትክ እሳትን መግዛት ምንኛ የከፋ ውድቀት ነዉ?

#አላህ_ሆይ ነፍሶቻችን በሻነፍን ግዜ ከመንገድህ ሊያስወጡን በቀረቡም ጊዜ በፍቅርህ በእገዛህ ትታድለን ዛንድ እንማፀናለን:: ያረብ

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share#Join us #Forward
----------------------------------

@Hubi_Resulilah
Forwarded from وبيجوت Tube (АЛИ ოσɦムოოε∂) via @like
አሰለሙ አለይኩም ወራህማቱላህ
ወበራከቱህ ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች የሼክ ካሊድ አልራሺድን የህይወት ታሪክ አጠናቀን ጨርሰናል ታሪኩን እንደወደዳችሁት አልጠራጠርም። ዘሬ ደግሞ ምርጥ ታሪክ ይዘን ቀርበናል።
#የታሪኩ_ርዕስ
#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነው
የዓቲካን ተከታታይ ታሪክ ይዘን ቀርበናል!
ኢንሻአላህ ታሪኩ ሰኞ ይጀመራል።
አንዴ የጫካ ንጉስ የሆነው አንበሳ ቀጪኔዎችን ሁሉ እንደሚበላ ተናገረና ወሬው ከ ዝሆን ጆሮ ደረሰ ዝሆኑም በሩጫ ይቀውጠው ጀመር በዚ መሐል ፍየል ታገኘውና ለምን እንደሚሮጥ ትጠይቀዋለች ዝሆንም ይልቅ ራስሽን አዲኚ እኔ ራሴን እያዳንኩ ነው አንበሳ  ቀጪኔዎችን በሙሉ እንደሚበላ ዝቷል ለዛ ነው የምሮጠው አለ ፍየሏም በመገረም ታዲያ አንተ ዝሆን እንጂ ቀጪኔ አይደለህ?  አለችው እሱም ባክሽ ዝሆን መሆኔን አቃለው ግን አንበሳ ቀጪኔዎቹ በሙሉ እንዲሰበስቡለት ውክልና የሰጠው ለ አህያ ነው
እኔ ደግሞ ውክልና የተሰጠውን አካል አላምንበትም ምክኒያቱም የተሳሳተ ውሳኔ ሊወስን ይችላልና

#ልብ በል የህይወትህን ውሳኔ በሌሎች አካል ላይ አታድርገው ምናልባት አንተ በማትፈልገው መንገድ ሊወስኑ ይችላሉና የሕይወት መንገድህን በራስህ እጆች ጀምር አለበለዚያ አጨራረሱ እንደምትፈልገው አይነት ላይሆንልህ ይችላልና!!

#SHARE በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
----------------------------------
#Share#Join us #Forward
----------------------------------

@Hubi_Resulilah
``ኩ ራ ት`` አደገኛ በሽታ !!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የሚገርም ምክር ከታለቁ ዓሊም አንደበት
"ሀሰኑል በስሪይ" ተማሪዎቻቸውን ከ ኩራት እንዲርቁ እንዲህ
በማለት መከሯቸው ፡፡

➊⇨ በጣም ምቹ በሆነ ስፍራ ላይ ስትሆኑ ኩራት ወይም ከመጠን
ያለፈ ደስታ አይሰማቹ ..አባታችን አደም (ዐለይሂ ሰላም) አጣጥመውት
ከነበረውጀነት አይበልጥምና !!

➋⇨ በጣም ብዙ ዒባዳ ስለምትሰሩ ኩራት አይሰማቹ..ያን ሁሉ
ዒባዳ ሲያከናውን የነበረው የኢብሊስ መጨረሻ አስታውሱ !

➌⇨ ከተከበሩ ሷሊህ ሰዎች ጋር ስለምትቀራረቡ ኩራት አይሰማቹ
ነብዩን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አግኝተው የነበሩ ግን እሳቸውን ያልተከተሉ ሙናፊቆች ምን እንደደረሰባቸው አስታውሱ፡፡ !!

⇨ ረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም " ጀነት አይገባም በቀልቡ ውስጥ የጎመንዘር ፍሬ የምታክል ኩራት ያለበት" ብለዋል.!!
ይህም ማለት ያለ ምንም ቅጣት ጀነት ከሚገቡት አይሆንም ማለት ነው።

አሏሁ ተዓላ ከኩራት ይጠብቀን አሚን!!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

#ⓈԊムЯ£ በማድረግ የአጅሩ ተካፍይ ይሁኑ#
---------------------------------------
@ⓈԊムЯ£_&_ⓈƱΡΡΣЯイ__ƱⓈ➣
---------------------------------------

@Hubi_Resulilah
2025/02/18 01:37:45
Back to Top
HTML Embed Code: