Telegram Web
#ባጭሩ

ልቤን በሀሳብ መድፌ ጠቃሁ፣
ሲፈስ እንዳያዩት ደም አነባሁ።

#BamU
#ባጭሩ

መሰለኝ ተሳሳትኩ፣
አዘንኩ ወይ ተደሰትኩ?
የለም፥ ይልቅ ተማርኩ።

#BamU
#ባጭሩ

የዚህ ዓለም እውነተኛ ገዢ ፍርሃት ይባላል (ማነው? የት ነው ያለው? ለሚለው በየጓዳዎቻችን ብንንጎዳጎድ አናጣውም)።

#BamU
#ባጭሩ

የሆነ አጥብቆ የሚወደው ነገር (ምንም ይሁን ምን) ያለው ሰው ከብዙው የሰው ዘር ተብዬ እሩቅ እንደሚጓዝ ነው የማምነው። "እንዲያው ለብ ያልክ ስለሆንክ አውጥቼ ልተፋህ ነው" የሚለውን ዓረፍተ-ነገር በተለየ ከምወዳቸው ሀሳቦች መሃል ያካተትኩም ለዚያ ነው።

#BamU
#ባጭሩ

"ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር" የሚል መፈክር የሚመስል ሀሳብ (አቋም?) የሚያራምዱ ሰዎች አጋጥመውኝ፣ "እና ለምንድነው የምትኖሩት?" ብዬ ጠይቄአቸው አላውቅም ነበር። አሁን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልጠይቃችሁ፣ ለመኖር ትበላላችሁ፤ ለምንድነው የምትኖሩት?

#BamU
#ባጭሩ

ስጋማ ቢያንሰው ነው
ምን ቢቃጠል ቢነድ፣
ጥንተ አመሉ'ኮ ነው
ከአልጋ ሲሉት ካመድ።

#BamU
#ባጭሩ

ሁሌም "አሃ" የማስባል ያክል የሚደንቀኝ መልእክት ካላቸው ሀሳቦች መካከል አንዷ ጂም ሮን (Jim Rohn) የሚባል አሜሪካዊ ሰው (ባለብዙ ሞያ) የሆነ ትምህርታዊ ንግግሩ ላይ ሲላት የሰማሁት ዓ.ነገር: "it's easy to pay the price when the promise is clear." የምትል ናት። በአብዝሃኛው የሕይወታችን ሁነቶች ውስጥ የምትሰራ አጠቃላይ ህግ እንደሆነች አምናለሁ።

#BamU
#ባጭሩ

ጭልጥ... እልም: እንደጭጋጋማ ቀን ጉዞ፣
አንድ እርምጃ ተረግጦ ለቀጣዩ ተስፋን ይዞ!

#BamU
#ባጭሩ

እንደማንም ሰው ነኝ ስጋ እንደለበሰ፣
ሹመት ማዕረግ አልቦ የተግበሰበሰ።

#BamU
It's not that I have a reason not to believe in God; it's the helplessness of innocent people that makes me doubt the existence of any holy spirit within us.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
(በበዓለ_ልደት(ገና) የተጻፈ የጉዞ ማስታወሻ..)

በዓል ነዉና እየጨፈሩ ነዉ...ሰማይ በጥይት ሩምታዎች ደብለቅለቅም ብሏል፨ፀጉራቸዉን አበጥረዉ አንገታቸዉ ላይ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ዶቃዎች ተሰድሮ የተሰራ ትልቅ መስቀል አለ...አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ደማቅ ናቸዉ፨ግንባራቸዉ ላይ የታሰረ:ጃኬትላይ: የመሳሪያ ጫፍና እጅ ላይ የተጠቀለለ ባንዲራ...እዚህ ብዙ ነዉ፨አንዲት የጎረቤታችን ሴት ህፃን ልጇን እያባረረች ከመኃላቸዉ ለማዉጣት ትዞራለች፨ብቻዋን ትነጋገራለች፨
ምን ሆነሽ ነዉ ?አልኳት

"ነጠላና ጋቢዎቼን እየቀደደ ጨረሳቸዉኮ" አለችኝ እጇ ላይ በባንዲራ ሦስት ቀለማት የተሸመነ ቁራጭ የነጠላ ጨርቅ ይዛ፨

እዚህ ቀኑ ረጅም ቢሆንም ቶሎ ይመሻል፨አይጋጩም!! በጥበቃና ሰቀቀን መሃል ሰከንዶች ዘላለም ናቸዉና፨ፀሐይ ወደቤቷ ስታዘቀዝቅ ደግሞ ምድር በፍጥነት በጥቁር ጨለማ ትዋጣለች፨ብርሃን የጨለማ ብቻ ሳይሆን የሕይወትም ጠላት ሊሆን ስለሚችል ከመሸ በኋላ አይፈቀድም፨

ሕይወት እዚህ ለእናቶች ትከብዳለች፨ከአንድ ቤት ሁለት ልጆች መች ተቃራኒ ሃይሎችን እንደሚቀላቀሉ አይታወቅም፨

"የገደለዉ ባልሽ የሞተዉ ወንድምሽ:
ሃዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽም አልወጣ፨

እንዲሉ ኮሽ ባለ ቁጥር የእልፍ እናቶች ልብ አብራ ትዘላለች፨

ተስፋ ለወጣቶች ሩቅ ናት፨መጨረሻዉ የማይታወቅ ጉዞ ነዉ፨ መቼ ያበቃል? ለሚለዉ መልስ የለም፨የገረመኝ እዛም ዉስጥ ግን ዉበት አልነጠፈችም...እዚህ ረጅም መንገድ ዳር ዳር ለፈገግታ የሚሆኑ የደስታ ድንኳኖች ተራርቀዉም ቢሆን ይተከላሉ፨ለምሳሌ ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉና እርሱን ሰበብ አድርጎ ከጦርነት ወሬ ዞር ይባላል፨ሕይወት የትኛዉም ኑረታዊ መልክዐምድር መኃልም የምትፈስበት ጅረት ያስገርማል፨

አባቶች ጋር ዝምታ ነግሷል፨ወንድነት ዋጥ ያደረገዉ ብዙ ግን ወደ ዉስጥ የተያዘ ጩኸት ያዘለ አስፈሪ ዝምታ፨ቀዝቃዛዉ አየር እንዳከናነባቸዉ ነጭ ጋቢ ዉስጣቸዉ የሚታይ አይደለም፨ቅኔ ነዉ ዝምታ!! እንዲል ባለቅኔዉ፨

መሳሪያ የታጠቀች ፀጉሯ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሸርብ ሸብ ያደረገች ሴት ማየት የሚሰጠዉ ስሜት ገና ቃላት አልተሰሩለትም፨

እርሷን ሁሉም ይጠብቋታል፨ድምቀታቸዉ ናትና ሲሄዱ ከፊትና ከመኃል ናት...መንገዶች ዳር ዳር ቆመዉ ለሚያዩዋት ብላቴናዎች ደማቅ ፈገግታዋን እየለገሰች አለፉ፨

(....አላለቀም)

✍️አንቺንአየሁ ገብሬ(𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮)

https://www.tgoop.com/yeesua_queen
..የቀጠለ ማስታወሻ
የወታደሩ ሚስት....

የልጅነት ባሏ ነዉ፨ገና ነፍስ ሳታዉቅ ቤተሰቦቻቸዉ ልጅህን ለልጄ ተባብለዉ የዳሩለት ሚስቱ ነች፨የብረት መዝጊያ የሆነ ባል ነዉ ያላት፨ጎጇቸዉን ከቀለሱ በኋላ በፍሬ ተባርከዋል፨ሦስት ሴቶች ልጆች አሏቸዉ፨
ባለሙያነቷ ያስደምመኛል፨ምግቧን ላደነቀ ሁሉ መልሷ አንድ ነዉ፨
እርሱ ነዉ ያስተማረኝ!!
ለመጀመሪያ ጊዜ እንጀራ መጋገርና:ዶሮ መስራት ያስተማራት እርሱ መሆኑን ስትነግረኝ መገረም ያጀበዉ ሳቄን ማቆም አልቻልኩም፨

"አንቺ ሳቂ ምን አለብሽ፨እኔ አዲስ ቀሚስ ተገዝቶልኝ ስቦርቅ የዋልኩበት ቀን ሰርጌ መሆኑን ሳላዉቅ ተድሬ ነዉ" ነበር ያለችኝ፨

ባሏ በሰፈሩ የተከበረ አባወራ ነዉ፨አራሽና ተኳሽ!!ክላሽንማ እርሱ ይያዛት ተብሎ የሚሞካሽ ወንድ!!ከቀናት መሃል በአንዱ ሃገር ጥሪዋን በሰፊዉ አስተጋባች፨ልብ ሰባሪ ጥሪ ነበር!!እንደ አድዋ ለሃገራችሁና ለሃይማኖታችሁ ስትሉ ተዋጉ ተብሎ ነጋሪት አይጎሰም:ሕዝበ አቢሲኒያ ሁሉ በአንድ ቃል ሆ ብሎ ወረኢሉ አይከት ነገር ጦርነቱ አድዋ ላይ አብረዉን ከዘመቱ ወንድሞቻችን ጋር ነዉ፨ከፍቶታል፨ክላሹን ወልዉሎ የሚሄድበት ጦር ሜዳም አይደለም፨

መሳሪያ ለታጠቁ ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተላልፏል፨መዝመት አልያም ትጥቃቸዉን ማስረከብ፨በጦርነቱ ባያምንበትም በተከበረበት ሃገር መሳሪያዉን አስረክቦ የፈሪ ተረት እየተተረተበት ሴት ልጆቹ ፊት እንደማይቆም ያዉቀዋል፨የልጆቹን ጉንጭ ስሞ ሚስቱን አቅፎ ተሰናበታት፨
አኬልዳማ!!


ሄደ፨ረጅም የስቃይ ወራት በብዙ የተተራመሱ ወሬዎች ተሞልተዉ አለፉ፨ጥቂት ጊዜ ብቻ ደዉሎላታል፨ጦር ሜዳ መድረሱን ሲነገራት የመጨረሻ ወሬያቸዉ ነበር፨ ከጊዜያት በኋላ እልፍ አዕላፍ ነፍሳት ረግፈዉ ከመንግስት ቴሌቭዥኖች የፕሪቶራያ ስምምነት ጉዳይ ተሰማ፨
...
የሄዱ ወታደሮች ተመለሱ ተባለ፨የሞት ዜና:አካላቸዉ የጎደለ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ:እንደ አካል ደኅና እንደ መንፈስ የተሰበሩ ወታደሮች ተመለሱ ተባለ፨ፈለገችዉ ከእነርሱ መኃል የለም፨
የት ሄደ ሞ...ቷ..ል ??አለቻቸዉ፨

አላየነዉም፨ ካምፕ እንደገባን ነበር የተለያየንዉ ከዛ በኋላ ስለእርሱ የምናዉቀዉ ነገር የለም አሏት፨

አጠገቧ ከቆመ ታጣቂ መሳሪያዉን ነጥቃዉ አስርት ጥይቶችን ወደሰማይ አከታተለች፨ጩኸቷን በጥይት ድምጽ አጀበችዉ፨የሞቱ ወታደሮች ለቅሶ ላይ ተገኘች፨ቁስለኞቹን ጠይቃለች፨ሃዘንተኞችን ለማጽናናትም ነበረች፨

ዓመታት አለፉ፨ጉድ የተባለላቸዉ እልቂቶች እየደበዘዙ ሰዎች ወደየእለት ኑሮቸዉ ተመለሱ፨"አባዬስ? እያሉ ከሚጠይቋት ልጆቿ ጋር ብቻዋን ቀረች፨ሞቱም ኑሮዉም አልተሰማም፨ዓመታት ሲደራረቡ በሕይወት ቢኖር ኖሮ እንዴት እስከዛሬ ?ትላለች፨ቁርጡን አልሰማችምና ደግሞ ጭላንጭል ተስፋ ታባብላታለች፨

እሳት ከሚነድበት ምድጃ አጠገብ ተቀምጣ በሃሳብ ሄዳ ነበር ያገኘኋት፨የማዉቀዉ ቀይ ፊቷ ማዲያት ወርሶታል፨ቢነግሩኝ የማላምነዉ አይነት መጎሳቆል ገጿ ላይ ይነበባል፨ሁለተኛዋ ልጇ ታናሿን አዝላ ከወዲያ ወዲህ ትላለች፨
እንዴት ነሽ ?ብቻ ነበር ማለት የቻልኩት፨

"ተይኝ እስኪ የእኔን መኖር ኑሮ ብለሽዉ ነዉ፨
እንደዉ ለልጆቼ ቆሜያለሁ አ"ለችኝ

የዚች ሴት ጎጆና ልብ ዛሬም ክፍት ሆኖ ይጠብቃል፨ብዙ የሃገሬ እናቶች ጎጆዎች የቀሩ ልጆቻቸዉን ጥበቃ ክፍት ናቸዉ፨ለነገሩ ሃገርስ ጥበቃ ላይ አይደለችምን....ምድሯን ከሚፈስባት የልጆቿ ደም የሚታደጉላት ልጆች፨

አንቺ ምስጢራዊት ምድር ለትንሳኤሽ ያብቃሽ ብዬ ተመኝቻለሁ፨

✍️አንቺንአየሁ ገብሬ (𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮)

https://www.tgoop.com/yeesua_queen
#ባጭሩ

ላጠራር እንዲያመች ለስም ሰው ብንሆን፣
አይነታችን ቢታይ፣ እንደ ቁጥራችን ቢልዮን!

#BamU
የኛ ትዉልድ የኑረት መልክ ፍጥነት ይበዛዋል፨ሁሉ ነገሮቻችን ይፈጥናሉ፨በዚህ የሰዉ ልጅ ፍላጎት የተነሳ የገበያዉም ትኩረት ፈጣንና:የማያስጠብቁ ነገሮችን ማቅረብ ሆኗል፨ሰዓቱ እንኳን ገና ሳይነጋ እየጨለመብን የተቸገርን ጥቂቶች አይደለንም፨በዚህ መኃል ከደበዘዙ ልምዶቻችን አንደኛዉ መጻሕፍትን ማንበብ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነዉ፨

እናም ሃሳቤ ምን መሰላችሁ፨አንዳችን ያለንን ለሌላኛችን ብንሰጣጥ ማጣታችንን አይቀንስም ብላችሁ ታስባላችሁ?ስለዚህ ቤታችን ዉስጥ challenge ልንጀምር ነዉ፨

ነገሩ ያነበብናቸዉን መጻሕፍት አጠር ያለ ዳሰሳ ማዘጋጀት ሲሆን አንዴ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን የተለያዩ መጻሕፍትን እየመረጥን በዙሮች የሚቀጥል ይሆናል፨

ዉድድሩ በተመረጡት መጻሕፍት ላይ
✍️የመጽሐፉን  ጠቅለል ያለ ይዘትና ጭብጥ
✍️መጽሐፉ በእናንተ እይታ ያላችሁን ሃሳብ
✍️ከመጽሐፉ የወደዳችሁትን ክፍልና የሰጣችሁን ግንዛቤ 
በአጠቃላይ መጽሐፉን ይገልጻል የምትሉትን አጠር ባለ መልኩ መጻፍ ነዉ፨

ዳኞችም እናንተዉ ናችሁ፨አሪፍ ገልፆታል ለምትሉት: ጸሐፊዎች ለራሳችሁም ድምጽ በመስጠት ጭምር ብዙ የተወደደዉን እንሸልማለን፨

ለዛሬ የተመረጠዉን መጽሐፍ ማታ 03:00 የምናሳዉቅ ይሆናል፨

ዝግጁ ናችሁ?

https://www.tgoop.com/yeesua_queen
Forwarded from ...ነጠብጣብ 💙 (𝖊𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 💙)
🔥🔥 ዴርቶጋዳ

ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ

የመጀመሪያ ዙር መጽሐፋችን እነሆ...

የምናዉቀዉን ከማጋራት ባሻገር አጓጊ ሽልማቶችም እናንተን ይጠብቃሉ፨

ቻናላችን 1500 subscriber ሲደርስ ጽሑፍ ማስገቢያ ጊዜዉ የሚጠናቀቅ ይሆናል፨

ጽሑፍ ለማስገባት @bluessoulmate

https://www.tgoop.com/yeesua_queen
#ባጭሩ

እስስ... ፀጥ፣
እንደወንድ እንባ ዋጥ፣
የምናደርጋት
መውደድ ወይ ጥላቻ፣
አለቻ አለቻ
ከፍርሃት ስርቻ።

#BamU
#ባጭሩ

አቀማመጡ እንጂ በመንታ በመንታ
ዘውትር ካንዱ ጋር ነህ ወስንም አመንታ!

#BamU
"ኧረ ተው ፈጣሪ !የብልጽግና መክፈቻውን ቁልፍ ስጠን።የት ይሆን የተደበቀው? ራስ ደጀን ተራራው አናት ላይ ወይስ ኦሞ ሸለቆ ዉስጥ ?

ባሌ ተራሮች ላይ ወይስ አሚባራ መተሃራ ላይ፡ሰላሌ ሜዳ ላይ ነዉ ወይስ ዋግኸምራ ሰሀላ ሰየንት፡ከፋ ሚዛን ቴፒ ከጥቅጥቅ ጫካዉ ዉስጥ ነዉ ወይስ ኦጋዴን አሳይታ ዱፍቲ ነዉ:ከቀዝቃዛው ስፍራ ጎጃም ጮቄ ደጋ ዳሞት ነው ወይስ አለት እንደ ሽሮ ወጥ ከሚንተከተክበት ኤርታኣሌ:

ጣና ወይስ ሻላ ሃይቅ ስር ነዉ፡
ዳዋ ገናሌ ሸበሌ ወንዝ ውስጥ ወይስ ሶፍሞር ዋሻ ጥግ:ጦሳ አንባሰል አድዋ ተራሮች ላይ ነው ወይስ ጋምቤላ ቤንሻንጉል ጉምዝ፡የተቆለፈበትን ቁልፍ ያስቀመጥክበትን እባክህ ንገረን?እባክህ አሳየን..?

ከየትኛው ገዳም ሱባኤ እንግባልህ?ደብረ ሊባኖስ:ዝቋላ:ደብረ ቢዘን:ሬማና ራማ:ምሁር ኢየሱስ:ሐይቅ እስጢፋኖስ:ዳጋ ወይስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ:
ከየትኛው ደብር ቆመን ምሕላ እንያዝልህ?ተድባበ ማርያም ወይስ መርጡለማርያም:
አክሱም ጽዮን ወይስ አራዳ ጊዮርጊስ:

ወንድሞቻችንስ እዉነት በመሰላቸዉ መንገድ ከየትኛዉ መስጊድ አዛን ይጥሩልህ:አል-ነጋሽ:ጀጎል:አኑዋር:ወይስ ሾኔ መስጊድ:ስንት ጊዜ ሶላት ያድርሱልህ?
ሰባቱ አጽዋማት አነሱህ ጌታ ሆይ?
መራብ ለምደንዋል እንጨምርልሃለን።የወንድምቻችን በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ካነሰ እነሱም ይጨምራሉ።ላለፈ ላገደመው ለወጣው ለወረደው ሁሉ ቁጭ ብድግ ማለት መስገድ መሰለፍ እንደሆነ ለምደንዋልና ንገረን ጌታ ሆይ የምትፈልገውን !"

ዝጎራ
✍️ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ

https://www.tgoop.com/yeesua_queen
2025/03/06 07:47:18
Back to Top
HTML Embed Code: