Telegram Web
~

ይህ ንጋት ለአንተ ነው ይህ ቀን ለአንተ ነው ይህች ፀሃይ የምትወጣው ለአንተ ነው።
በተሰጠህ ዛሬ እንጂ በሚመጣው ቀን ለመደሰትም ለመስራትም ቀጠሮም ሆነ መኮፈስ የለብህም።

ለነገ እቅድ የያዘ እንጂ ነገን የኖረ ማንም የለምና ዛሬን ተጠቀምባት።
መልካም ቀን ከሃላል ከስብ ጋር ይሁንልን።
~🍂

ሙሳኮ አላህ ለርሱ ብሎ ባህሩን እንደሚከፍልለት አያውቅም። ባህሩ ጋር የደረሰውም አስቦበት አልነበረም። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነበር “ጌታው መቼም በዚያ አጣብቂኝ ውስጥ  እንደማይተወው”። አቤት… የቂን፤ ዐጀብ ተወኩል ፤ “ተው(አትስጉ) ጌታዬ ከኔ ጋር ነው” የሚል ተራራ ኢማን!!  ኧረ  እንዲህ አይነት የቂን ሸልመን  ያ ወዱድ!!
✈️ታላቅ የውይይት ፕሮግራም 📣

የፊታችን ማክሰኞ በቀን 18/ 06 / 2017
🔠ከምሽቱ 3፡00 ከተለያዩ የሃገራችን ክፍል ከሚታደሙ ወንድሞች ጋር የአክፍሮት ሃይላት በተመለከተ የውይይት ፕሮግራም ይኖረናል ።

ውይይቱ የሚታደሙ
➡️ከጂንካ
➡️ከወላይታ
➡️ከጉራጌና ከሌሎች አካባቢዮችም የምናስተናግድ ይሆናል
~~
🔥 www.tgoop.com/twhidsun 😤☹️🙁☹️
🔥 www.tgoop.com/twhidsun 😤☹️🙁☹️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️
🛜ታላቁ የውይይት ፕሮግራም▶️
🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🙁
🎤
      ተ
🎁
             ጀ
▶️
                  መ
▶️
                          ረ
▶️

ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘
www.tgoop.com/twhidsun?livestream
www.tgoop.com/twhidsun?livestream
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
السلام عليكم ورحمة اللہ وبركاته

እንኳን ደስ አላችሁ

ዛዱል መዓድ ኢስላሚክ ሴንተር በ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የሚሰጡ ትምህርቶችና መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ እንዲሁም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ዌብሳይት ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወቃል ።
አሁን ደግሞ ሁሉንም በዛዱል መዓድ የሚሰጡ ትምህርቶችን፣ የፈትዋ መጠየቂያ፣ እንዲሁም ወቅታዊ መልዕክትና መረጃዎችን
ያካተተ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ልዩ አፕሊኬሽን ለዛዱል መዓድ ቤተሰቦች ይፋ ማድረጉን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

አፕሊኬሽኑን ለማውረድ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alif.zadulmead_islamic_center_app
ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَـٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِیمِ }
"ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ (መሄዱን) ለካነው።" [ያሲን፡ 39]

የጨረቃ መስፈሪያዎች የተባሉት በየ ወሩ ለ 28 ቀን የሚያልፍበት ቆይታ ነው። ቀጭን ሆና ጀምራ እያደገች ትሄድና ሙሉ ጨረቃ ትሆናለች። እንደገና እያነሰች ሄዳ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ልክ እንደ ደጋን የጎበጠ የተምር ቀንዘል ጎብጣ ትቀጥናለች። በመጨረሻ ትጠፋለች።
ወሩ 30 ቀን ሲሆን ጨረቃ ለ 2 ሌሊቶች ትደበቃለች (አትታይም)። ወሩ 29 ቀን ሲሆን ደግሞ ለ 1 ሌሊት ትደበቃለች።

ኢስላማዊው የቀን መቁጠሪያ የጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ ነው። ስለሆነም ዘካ የሚወጣው፣ የልጆች ለአቅመ መጠን መድረስ የሚወሰነው በጨረቃ አቆጣጠር መሰረት ተሰልቶ ነው። በጨረቃው አቆጣጠር አንድ አመት 354 አካባቢ ቀናት ሲኖሩት የፀሐዩ አቆጣጠር ደግሞ 365 አካባቢ ቀናት አሉት። ስለዚህ የ 11 ቀን ልዩነት አለ ማለት ነው።

ማስታወሻ፦
አንዳንዶች የጨረቃን መውጣት ስንከታተል "ጨረቃን ታመልካላችሁ" እያሉ ይከስሳሉ። ለነዚህ አላዋቂዎች የምንላቸው እናንተ የፀሐይን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገውን መቁጠሪያ የምትጠቀሙት ፀሐይን ስለምታመልኩ ነው ወይ? ለምን በራሳችሁ ላይ ትተኩሳላችሁ?
=
ኮፒ Ibnu Munewor
እንኳን ለተከበረው ወር ረመዷን አደረሳችሁ።

አላህ ከሚጠቀሙበት ባሪያዎቹ ያድርገን።


ባሳኡዲ አረቢያ የረመዷን ጨረቃ በመታየቷ ነገ ቅዳሜ march 1/2025 (የካቲት 22/2017 ዓ.ል) የመጀመሪያው የ1446ኛው አመተ ሂጅራ የረመዷን ቀን ይሆናል።

ምንጭ-
Inside the Haramain

= ረመዷን ሙባረክ =
ይህ በጋዛ በፍልስጤን ምድር ነው።

የመጀመሪያው የረመዷን ፍጥር ነው።
ንብረት ይወድማል ሀገር ይፈርሳል ደም ይፈሳል አንጥንት ይሰበራል። ነፍስ እስከ ወዲያኛው አለም ላይመለስ ይሄዳል። ይህም የዲን ፅናት ነው። ዲን ኢማን ካለን ሁሉም ነገር ምንም ነው ከባዱ ነገር ራሱ ነፍስ ከስጋው ብትለያይም ክብር ነው።


ለኢስላም ለሀገራቸው ሲሉ ሁሉንም መላ ቤተሰቡን የሸኘ እልፍ ነው። ቢሆን አሁንም በክብር አሉ በግልፅ ይዋጋሉ በግልፅ ያመልካሉ ምንም ማንንም አይፈሩም ይህ የሆነው በኢስላ ባህር ውስጥ ነው።

አላህ ፅናቱን ብርታቱን ይስጣቹ 🤲
🍂


"በጭንቅ እና በመከራ ጊዜ ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚፈልግ በድሎት ጊዜ ዱዓ ማድረግ ያብዛ።"

ረሱል (ﷺ)
‏{رَبَّنَا هَب لنَا مِن أَزوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ}
በረመዳን ወር ቀን ላይ ከወር አበባ የጠራች ሴት ቀሪውን የቀኑን ክፍል ከሚያስፈጥር ነገር የመቆጠብ ግዴታ አለባትን?
~
አንዲት ሴት የወር አበባ ላይ በመሆኗ ሳትፆም ቀርታ ቀን ላይ ከደሙ ብትጠራ ከምግብና ከመጠጥ የመቆጠብ ግዴታ እንዳለባት የሚያስቡ ብዙ ናቸው፡፡ በርግጥም ይህን አቋም የመረጡ ዐሊሞች አሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ አቋም “ለቀኑ ክብር” በሚል ወይም ጤነኛ ያልሆነን ቂያስ በመጠቀምና መሰል ምክንያት ላይ በመንተራስ እንጂ ቀጥተኛ ማስረጃ የሚደግፈው አይደለም፡፡ ፆመኛ ያልሆነን ሰው “ባንተ ላይ መመገብና መጠጣት ሐራም ነው፤ ያለበለዚያ ወንጀለኛ ነህ” ማለት ግልፅ ማስረጃ ይፈልጋል፡፡

ለምሳሌ አንዲት ሴት የወር አበባ ካየች በሷ ላይ ፆም መፆም ሐራም ነው፡፡ መፆም በሷ ላይ ሐራም የሆነባትን ሴት “መመገብም ባንቺ ላይ ሐራም ነው” ማለት ትክክል አይደለም፡፡ “መብላት የለባትም” ከተባለ ግን እራት ከበላችበት ሰዓት ጀምሮ ወይም ልክ እንደ ፆመኛ ሌሊት ተነስታ ሱሑር ከበላችበት ሰዓት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ያለ ምግብና ያለ ውሃ መቆየት አለባት ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ኋላ ቀዷ ማውጣቷ የማይቀር ከመሆኑ ጋር ነው፡፡ ይሄ እይታ ትክክል እንዳልሆነ በርካታ ዑለማኦች ገልፀዋል፡፡

ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “በቀኑ መጀመሪያ ላይ የበላ ሰው በመጨረሻውም ይብላ፡፡”
ይህ ምን ማለት ነው? በሆነ ምክንያት ፆመኛ ባለመሆኑ ሳቢያ በቀኑ የመጀመሪያ ክፍል ላይ መመገብ የተፈቀደለት ሰው በየትኛውም የቀኑ ክፍል መመገብ እንደሚችል የሚጠቁም ነው፡፡ ይህ አቋም የታቢዒዮቹ ጃቢር ብኑ ዘይድ እና አጧዕ ብን አቢ ረባሕ፣ እንዲሁም የኢማሙ ማሊክ፣ የሻፍዒይ፣ የአሕመድ በአንድ ዘገባ፣ የኢብኑ ሐዝም፣ የኢብኑ ዑሠይሚን እና የሌሎችም የብዙሃን ዑለማእ እይታ ነው፡፡
ይህ እንግዲህ በረመዳን ወር በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከወሊድ ደም የጠራችን፣ ከህመሙ ያገገመን፣ ከመንገድ የተመለሰን ሰው እና መሰል ሸሪዐዊ ዑዝር ያላቸውን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-
-
የሚያፈጥርበት ምክንያት ለሰዎች የሚሰወር የሆነ ሰው ሲመገብም ሆነ ሲጠጣ በተቻለ ከሰዎች እይታ ገለል ቢል በዲኑ በክፉ ከመጥጠርጠር ይጠብቀዋል፡፡ ዑዝሩ ወይም ሰበቡ በውል የሚታወቅ ከሆነ ግን በግልፅ ቢመገብና ቢጠጣም ችግር የለውም፡፡ ወልላሁ አዕለም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 13/2010)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
🌱አዲስ የመሀደራ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
🫴
𝚖𝚘𝚛𝚎

😬የእለቱ ተጋባዥ እንግዱች ▶️

ኡስታዝ  ሳዳት ከማል
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
  ሸይኽ   አወል ኬሚሴ
ኡስታዝ ኸድር ኬሚሴ
ኡስታዝ አቡ ሙሰሊም

😓እሁድ ማታ ከተረዊህ ሰላት በሇላ
4️⃣🔤1️⃣5️⃣


💎ፕሮግራሙ የሚካሄድበት የተሌግራም ግሩፕ⤵️
www.tgoop.com/merkezabumussa1
www.tgoop.com/merkezabumussa1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወንድም እና እህቶች ተባበሩን!

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የሞተር ታርጋ መንገድ ላይ ወድቆ ጠፍቷል የሞተሩ ባለቤት ቤተሰቡን የሚያስተዳድረዉ የእለት እንጀራዉን የሚያገኝዉ በዚሁ ስለሆነ በዚህ ኑሮ ዉድነት ስራ ከፈታ ቀናቶች ስለተቆጠረ እባካችሁ ይህን ታርጋ ያገኘ ከስር በተገለጽዉ ቁጥር ያሳዉቀን

SHARE ....SHARE .....SHARE ....SHARE

0973096262
        or
0907136729
اللهم صل و سلم وبارك على نبينا محمد و آله وصحبه .
ጥንቃቄ

ቀጥታ አካወንታችሁን ነው የሚጠልፉት ይህን
ሊንክ ተጭናቹ እንዳትገቡ አደራ ከምታምኑት  ሰውም
ጭምር ቢላክላችሁ  እንዳትነኩት የነዛ ሰዎች
አካወንት ተጠልፎባቸው ነው

ጥንቃቄ ጥንቃቄ ለሁሉም ሼር አድርጉት ይህ የነካችሁ ካላችሁ በቀጥታ አካወንታቹ ሀክ ተደርጓል ማለት ነው
scam ነው

ይህን ሁለተኛ ፎቶ ላይ ያለውን setting በማስተካከል የተጠለፈባችሁን አካወነት አስመልሱ

Settings -> devices -> በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other session  የሚለውን ተጭናቹ  ok በማለት 24  ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት 24  ሰአት ከቆይ እናንተን ሙሉ ለሙሉ የማስወገድ ሀይል አለው

ለሁሉም ሼር አድርጉት

ይህ አደራረጉ ላልገባቹ ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ
በውስጥ መስመር አናግሩኝ @twhidfirst1
«ጓደኛዬን ወደ ክርስትና ለመጥራት አስቤ በመጨረሻ ግን ለራሴ ሙስሊም ሆንኩኝ»

እውቁ ዳዒ ዩሱፍ ኢስቴስ አሏህ (ሱወ) ይጠብቀው ዛሬ ላይ በስበቡ በሺዎች የሚቆጠሩ እውነትን አውቀዋል፣ ወደ እስልምና ገብተዋል። ከሰባኪነት ወደ ዳዒነት የተቀየሩ ብዙ ናቸው። ቤተክርስትያን ለመገንባት አስበው መስጂድ የገነቡ መዓት ናቸው።

ዓላማው ሀቁ ለብዙሃኑ እንዲደርስ እውቀት ላይ ተመስርቶ በቀናነት የሚደረግ ውይይትና ክርክር ጥቅሙ ከፍተኛ ነው።
“አንዳችሁ አላመነም ‘እምነቱ ሙሉ አይሆንም’ እኔ እሱ ዘንድ ከልጆቹ ከወላጆቹ ከሰዎች በጠቅላላ ይበልጥ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ።”

ረሱል (ﷺ)
2025/03/16 21:20:43
Back to Top
HTML Embed Code: