Telegram Web
የባከኑ ቀናት
ክፍል ሶስት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
<<አንተ የተመታህ..>> ብሎ ማሂር ሲነሳ አቤላ እየሮጠ ወጣ፤ ማሂርም ተከትሎት ወጣ።
<<ለምን አንቺም አትከተያቸውም?>> ራቢ።
<<አንቺ ነገር ላይ የሚችልሽ የለም፤ አሁን ኢክራም ጋር እንሂድ.. >> ዩስራ ቦርሣዋን እየዘጋጋች።
<<እ.. ዛሬ ቆየች። ጠፍቶባት እንዳይሆን ሃሃሃሃ>> ተያይዘን ወደ ኢክራም ክፍል ሄድን።
.
ብሎክ ላይ ብዙ ተማሪዎች ተደርድረዋል፤ ዩስራ ና ራቢያ የሚያውቋቸውን ሰላም እያሉ አልፈን ቀጥታ ወደ ኢክሩ ክፍል ስንገባ አንድ ልጅ ወደኛ አቅጣጫ ጀርባውን ስጥቶ ይታያል።
<<ኧረ እየተጋተተ ባልሆነ..>> ራቢ ነበረች። ወፍራም ስለሆነ ከፊቱ ማን እንዳለ መለየት አልቻልንም ግን የማውቀው ክፍት ጫማ አየሁ
<<ራ..ቢ..>>
<<እእ ምን ሆንሽ >> ፊቷን ሣታዞር መለሰችልኝ <<ኢክ..ራም የት አለች?>> አሁን ወደኔ ዞረች። እጄን ወደ ልጁ ጠቆምኳት
<<አትታይም እኮ እንዴት አወቅሽ?>> ዩስራ ግራ ተጋብታ ስታይ
<<አንተ ያምሃል እንዴ አሣልፈኝ ..>>|የኢክራም ድምጽ ተሰማ። ራቢያ በሩን አጋጭታ ወደ ልጁ መራመድ ጀመረች። እኔ እና ዩስራ እርስ በእርስ ተያይተን ተከተልናት። ልጁ ሶስታችንን ሲያይ ደነበረ፤ ምን ሊሉኝ ነው ብሎ አይኖቹን ያንከራትታቸዋል።
<<አንተ ዱዝ ምንድነው ምትጋተታት?>> ራቢ የቅድም ሃይልና ቁጣዋ ጠፍቶ በመገረም ታየዋለች።
<<ራ.ቢ.ያ.. አይደለም እኮ.. እ.እሷ..>>
<<ኧረ እሷ ናት አላሣልፍ ያለችህ አይደል?>> ዩስራ ላለመሣቅ እየታገለች።
<<አይ..አይ.. ላልፍ ስል ተጋጭተን..አ.. አይደል እንዴ..>> ከቃላቶች ጋር እየታገለ ይመስላል። እኔ ግን አልገባኝም... ይተዋወቃሉ? በጣም የፈራ ይመስላል።
<<አሃ የህንድ ፊልም ላይ እንደምታዩት ማለት ነው? ሃሃሃሃ>> ራቢ የሚያበሽቅ ሣቅ ለቀቀችበት። ራቢ የምትገርመኝ ነገራቶች ላይ ራሷን ማግለል ትፈልጋልች። የህንድ ፊልም እሷ ሣታይ እንዴት እንዲህ እንደሆነ አወቀች? አይ ራቢ..
<<በቃ ቻው>> አንገቱን ደፍቶ ከክፍሉ በፍጥነት ወጣ።
.
<<ማን ነው?>> የኔ ጥያቄ ነበር።
<<ምን አቅለታለው!>> ኢክሩ በተሠላቸ አንደበት
<<ይሄ ዱዝ፤ አንድ ክላስ ነበርን። እሱ ዘጭ ብሎ አሁንም ሰባተኛ ክፍል ነው>>
<<ኦ ስለምተተዋወቁ ነዋ እንደዛ የሆነው>> ራቢን እያየሁዋት ነበር፤ ፊቷን አዞረችብኝ።
<<ኧረ ምን እሱ ብቻ.. ይፈራታል እንጂ!>> ዩሲ አከለችበት።
<<ማለት ይፈራታል? ለምን? እንዴት ?>>
<<ኢብቲ ደግሞ የራቢያን ፀባይ እያወቅሽ>>
<<ዩስራ ምንም አታሟሙቂው! እንደውም ኑ እንውጣ ..>> ራቢ ቆጣ እንደማለት ብላ መከሰችላት።
<<ራቢ ወሬ ለመቀየር ከሆነ አንሰማሽም። በይ ራስሽ ተናገሪ>> ኢክሩ ተመቻችታ ተቀመጠች።
<<ኧረ እኔ የናንተ ዩስራ እያለሁ ምን ሰርቼ ልበላ.. አሁን ልንገራቹ በቃ! እንደናንተው እዚህ ትምርት ቤት በገባን ጊዜ አጅሬው በረከት (በሬው ነው የሚሉት) ራቢን መጋተት ፈለገ። ቢላት ቢላት ምንም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም። ታዲያ በስፓርት ክላስ ለመስራት ሜዳ የወጣን ቀን እኛ በሱሪ የመጀመሪያችን ስለነበር በጣም ፈርተን ነበር። ደብሮንም ነበር፤ ያው ረጅም ጋወን እንደርብ ነበር። በሬው የሚሉትም ደግሞ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ከሙስሊም ሴቶች ጋር መሯሯጥ ይወዳል። የዛን ቀን ተረኛ አሰሪ ራቢ ነበረች፤ እንደሌሎቹ አልሆን ስትለው እልህ ያዘውና በተማሪ ፊት ሂጃቧን አወለቀባት....>>
<<ምን ይሄ ዝፍዝፍ ልጅ>> ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ።
<<ሄይይይይ ተረጋጊ እንጂ፤ አሁን እኮ አይደለም ኢብቲ... አንቺ ና ራቢ ችኩልነታቹ መቼ እንደሚለቃቹ እንጃ>>
<<ቆይ አንቺስ ዝም ብለሽ አየሽው በሂጃቧ ሲመጣባት?>> ዩስራ ላይ አፈጠጥኩባት።
<<ኢብቲ የሆነውን ትንገረንና ትጠይቃታለሽ>> ኢክሩ ታሪክ እየተነገረ ሲወራ ይረብሻታል፤ ዝም ብላ ማድመጥ ነው የሚመቻት።
<<እእ.. እሺ ይቅርታ ዩስራ ቀጥዪ!>>
<<ከዛ ሂጃቧን ሲያወልቅባት ያዩትም ያላዩትም ይስቃሉ፣ ይጮሃሉ በቃ ድብልቅልቁን አወጡት። በዚህ መሃል ባቢ ቲሸርቱን ወረወረላት ያው ፀጉሯን ለመሸፈን ሲል። ከዛ ቡኃላ ነው ከነባቢ ጋር የተግባባነው፤ ምርጥ ልጆች ናቸው። እኔ አሞኝ ስለነበር ከሜዳው ራቅ ብዬ ነበር የተቀመጥኩት፤ ግን የሚሰሩት ይታየኝ ነበር። እስክመጣ ነው ይሄ ሁሉ የሆነው። ከዛ አስተማሪው ጋር ሄድን፤ ሁሉንም ነገርነው። ተማሪውን ዝም ካስባለ ቡኃላ <በረከት ወደዚህ ና!> ብሎ ከተማሪው ፊት አስቆመው። ራቢን <ምን እንዲቀጣ ትፈልጊያለሽ?> ሲላት <ራሴ እንድቀጣው ነው ምፈልገው> አለች። ምንም እልህ አለቀቃትም ነበር። <እሺ ተፈቅዶልሻል> ተባለች ተማሪው የምትናገረው ሲጠብቅ ከኃላው ሄደች። ምን ልታደርግ እንደሆነ ተማሪው ተነስቶ ማየት ጀመረ።
የኔ ጀግና ራቢ በምን ፍጥነት እንደሆነ ሳይታወቅ ሱሪውን አወለቅችበት...
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
🍃 🍃 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : (أوصيكم بتقوى الله عز وجل، والسمع والطاعة، وإن تأمر عليكم عبدٌ؛ فإنه من يعش منكم فسيرى اختلافًا كثيرًا، فعليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين، عَضُّوا عليها بالنواجذ، وإياكم ومحدثات الأمور؛ فإن كل بدعةٍ ضلالةٌ)

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ - (ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህ እንድትፈሩ ፣ እንድታዳምጡ እና እንድትታዘዙ አደራ እላቹሃለሁ ፣አንድ አገልጋይ እንኳን በእናንተ ላይ ቢያዝ ፣ ከናንተ ውስጥ የሚኖር በመካከላችሁ ብዙ ልዩነትን ያያል። ፣ ስለዚህ የእኔን ሱና እና ትክክለኛ የተመሩ ከሊፋዎችን ሱና አጥብቃችሁ ፣ በጠራራ ጥርስ ነክሳችሁ ያዙ ፣ አዲስ ከተፈጠሩ ጉዳዮች ተጠንቀቁ ፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ፈጠራ ጥመት ነው።)

🎨 @Habibacalligraphy
አንብቡት 👐
.
.
"LOL” ማለት ምን ማለት ነዉ?
ለመጀመርያ ጊዜ ይሄን ቋንቋ የፈጠሩት በአሜርካ SECRET SOCIETY (666)
በተባሉት ሲሆን፤ በማህበራ ደረገፆች (social networks) ላይ ብዙዎቻችን በዚህ
ቋንቋ ተታለናል።
“LOL” ማለት ለብዙዎቻችን “LAUGH OUT LOUD” መስሎን ሰላምታችን
እስኪመስል የአፍችን መፍቻ ሆኖል ::
“LOL” ማለት ግን “LUCIFER OUR LORD” ወይም ሲተረጎም
“ሉሲፈር(ሰይጣን) የኛ ጌታ” ነው እንደ ማለት ነዉ።
ሉሲፈር( LUCIFER) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም ሰይጣን፣ጣኦት ወዘተ…. ትርጉም
ይይዛል።
ስለዚህ ሰዎች በማያዉቁት መልኩ ሰይጣንን እያመለኩ እያስመለኩ ስለሆኑ፣ ከዚህ
ድርጊታችን(LOL) ከማለት እንቆጠብ።

🎨 @Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አራት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
<<ምን በተማሪ ፊት?>> ኢክሩ ደንግጣ ራቢና ዩሲን አፈራርቃ እያየች።
<<አዎ ኢክሩ አደንግጪ። በዛ ላይ የምሣ ሰዐት ደርሶ ስለነበረ ብዙ ተማሪ ተሰብስቦ ነበር። በሬው ደንግጦ ሱሪው ከፍ ሲያደርግ አስተማሪው <አውርድ!> አለውና ለተወሰነ ደቂቃ እንደዛው እንዳስቆመው።
<ሌላ ምን እንዲቀጣ ትፈሊጊያለሽ?> ራቢን ጠየቃት።
<ቅጣት ይበቃዋል፤ ግን ለኔ ሂጃብ ማለት ለእሱ አውራውን ከሚሸፍንበት ሱሪ በላይ ነው። ማንም ሰው በሂጃቤ እንዲጫወትበት አልፈቅድለትም። የከፋ ችግር ይገጥመዋል፤ ስለዚህ አርፎ ይቀመጥ። ተገቢውን ቅጣት በተማሪ ፊት መሰጠቱ ለሌሎች ትምህርት ነው። እኔ ማንም ይሁን ማንም ሂጃቤን አይደለም እጄን እንኳን እንዲነካኝ አልፈቅድለትም። አመሰግናለሁ> አለች። እኛ ከዛ ቦታ ዞር ብንልም ለትምህርት ቤቱ የሣምንት መነጋገሪያ ሆነ። ክፍል ሲገባም እነ ባቢ የሌለ ሙድ ይይዙበት ነበር። እኛም ከነ ባቢ ጋር በደንብ ተግባባን። ታዲያ ይሄ በረከትን(በሬው) እልህ ውስጥ ከተተው፤ ዝም ብሎ ነገር ይፈልጋት ጀመር። መጣላት እንደሚፈልግ ያስታውቅበት ነበር። የሆነ ቀን እኔን ጠራኝ እና በተማሪው ፊት ይቅርታ እንድትጠይቀው ካልሆነ እንደሚመታት ነገረኝ።>>
<<ጭራሽ እሷ ይቅርታ ልትጠይቀው ማለት ነው?? ኧረ ሞራል ..>> በስሜት አብሬ ለፈለፍኩ። ኢክሩ ራቢን ያቀፈችበት እጇን ወደኔ አምጥታ አፌን ያዘችኝ።
<<ኢብቲ ዝምምምምምም በይ!>> በአይኖቿ ተማፀነችኝ። ወደ ራቢ ስመለከት የሌላ ሰው ታሪክ ይመስል እሷም ተመስጣ ነበር የምትስማው።
ዩስራ ቀጣዩን ስትጀምር ትኩረቴን ወደሷ አደርጌ ማዳመጥ ጀመርኩ።
<<ከዛ እንደሚመታት ሲነግረኝ ይቅርታ እንደምትጠይቀው ችግር እንደሌለው ቀለል አድርጌ ነገርኩት። እሱ የልብ ልብ ተሰምቶት ወደ ቤትሰዐት ላይ እንደሚሆን ነገረኝ፤ <እሺ እንዳልክ> አልኩት። የማይደርስ የለምና ያለኝ ሰዐት ላይ ደረስን።
.
አስተማሪው እንደወጣ በሩን ዘግቶ ሁሉንም እንዲቀመጡ ካደረገ ቡኃላ ከተማሪዎች ፊት ወጥቶ <እኔን ይቅርታ መጠየቅ የምትፈልግ ልጅ አለች እናም በናንተ ፊት የምትለኝን ሰምቼ ይቅርታ የሚገባት ከሆነ አደርግላታለው፤ ካልሆነ የሚገባትን እሰጣታለው> አለ። ተማሪው ግራ በመጋባት ዝም ብሎ መከታተል ጀመረ። በዚህ መሃል ባቢ ወደኛ ዞሮ <ከናንተ ጋር ነው?> ግራ እየተጋባ ጠየቀን። ራቢ <ኧረ አይደለም ባቢ...ማን እንደሆነች እኛም አናውቅም> አለችው፤ አዎ እሷም አታውቅም... ያለኝን አልገርኳትም ነበር። በሩን ከፍቶ ልጆች ማስገባት ጀመረ፤ ለካ ለሌላ ክፍል ጓደኞቹም ነግሯቸዋል። ነገሩ ትንሽ ከበድ እንዳለ ገባኝ ለራቢ ልንገራት አልንገራት እያልኩ ሁለት ሃሣብ ውስጥ ገባሁ።
ተማሪው እርስ በእርሱ ይንሸኳሸኳል፤ <እሺ ነይ ወደዚህ ምን እንደምትዪኝ ሁሉም መስማት ይፈልጋል> ራቢ ላይ ሁሉም አፈጠጠ፤ ግራ ገባት። እሷ የምታውቀው ነገር ስላልነበረ እሷን አልመሰላትም። <ዩስራ ምንድነው እኔ ነው እንዴ? እእ> ምንም መናገር አልቻልኩም። ተማሪው ሁሉ ወደኛ ዞሮ መመልከት ጀመረ።
<ምንድነው አልገባኝም?>
<ራቢ ቡኃላ አስረዳሻለው ይሄን እኔ እወጣዋለሁ ብዬ ስነሳ> ያዘችኝ።
<የት ነሽ ንገሪኝ!> አፈጠጠችብኝ። መጀመሪያ መንገር እንደነበረብኝ አሁን ተሰማኝ <መልሺልኝ ዩስራ!> ጮክ አለች። <ራቢ በአላህ ልቀቂኝ መጣሁ አንዴ ..> ባቢ ዞሮ <ምን ሆናቹ ነው?> ይለናል።
<ዝም በል አንተ ደግሞ> ራቢ ነበረች፤ በጣም ተናዳለች ማለት ነው።
<ሃሃሃ ምንነው ፈራሽ እንዴ!> የበረከት ድምጽ ተሰማ ሁሉም ፊቱን ወደሱ መለስ አደረገ። በጣም ብሽቅ አልኩኝ...እጇን ምንጭቅ አድርጌአት ወደ በረከት መሄድ ጀመርኩ። ከፊት ለፊቱ ቆምኩኝ፤ <ኦውውው እሷ ፈርታ ነው አፍራ አንቺን የላከችሽ?> በንቀት አይን እያየኝ። እኔ ወደ ራቢ ስመለከት ተናዳለች፣ግራ ተጋብታለች፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ የሚሆነውን ታያለች...>>
.
ዩሲ ትረካዋን ሳትጨርስ የተማሪ ጫጫታ ስንስማ ወደ ክፍል መግቢያ ሰዐት እንደ ደረሰ ተረዳን። ዩስራ <<በቃ አንድ ቀን እጨርስላቹሃለው አሁን ወደ ክፍል እንሂድ>> ብላ ተነሳች።
<<ኧረ አልሰማሽም ምሳ ሰዐት ታሪኩን ሳጨርሺልን መብላት የለም>> ኢክሩ ሣቅ እያለች።
<<እኔም እስማማለሁ። ኢክሩ በቃ አትውጪ እኛ ሶስት ነን..>> ከኢክሩ ጋር ተቃቅፈን ተለያየን። ወደ ክፍላችን ለመሄድ ደረጃው መውረድ ስንጀምር እነ ራቢ ከሆነች ልጅ ጋር ሰላም ሲባባሉ እኔ ወደ ታች ወረድኩ። ደረጃው ላይ ተማሪ እየተተላለፈ በመሆኑ ለመቆም አይመችም ነበር። ደረጃውን ጨርሼ ፊቴን እነ ራቢ በሚመጡበት አቅጣጫ አድርጌ ቆሞኩኝ፤ ከኃላ ሲገፈትሩኝ ዞር ስል በረከትን አየሁት እኔ መሆኔን ሲያይ ደነገጠ።
<<ያምሃል ቀስ አትልም?>>
<<ሳላውቅ ነው>> በንቀት እያየኝ መለሰልኝ።
<<ምን ይመስላል ዝፍዝፍ..>>የቅድሙ የራቢ ሂጃብ እልህ አሲዞኛል። ጓደኞቹ ሲስቁበት <<ስርዐት ያዢ>> ብሎኝ ቆመ ተማሪው መሰብሰብ ጀመረ።
<<ባሊዝስ ምን ልታመጣ? ክብርህን ጠብቅ ክበረ ቢስ!>>
<<አንቺ! ምንድነው ያልሽው>> እጁን ሲሰነዝር ሽል ብዬ እኔ በተራዬ ልሰነዝር ስል ከኃላ ሌላ እጅ ያዘኝ። ዞር ስል ከማሂር ጋር ተገጣጠምን።
<<በሬው ምንድነው ከሴት ጋር ልትደባደብ ነው እንዴ?>> አፈጠጠበት።
<<ማሂ.. እናቴን ተሣፍጣኝ ነው ንቀታም ናት>>
<<አቦ ባክህ ጥፋ ከዚህ ሁለተኛ እንዳትናገራት! ነይ አንቺ ደግሞ>> እጄን ሣይለቀኝ ወደ ክፍል መሄድ ጀመርን። እሱ ከፊት በጣም እየፈጠነ ነበር፤ እጄን ስለያዘኝ እየጎተተኝ ማለት ይቻላል። ክፍል አስገብቶኝ ቦታዬ ጋር ስደርስ ለቀቀኝ። <<ቁጭ በይ!>> ሣልቃወመው ቁጭ አልኩ።
<<ከማንም ጋር እንዳትጣዪ እሱን እኔ አናግረዋለሁ>> ብሎኝ ትቶኝ ወጣ ።ግራ ገብቶኝ ቀና ስል ተማሪው አይን አይኔን ያየኛል... ልወጣ ስነሳ ባቢ ና አቤላ መጡ።
<<ኧረ ልጅት በአደባባይ ካልተደባደብኩ አልሻ?>> ባቢ አውርቶ ሳይጨርስ ራቢና ዩሲ አብረው መጡ።
<<እሺ የኔ ጀግና ለሁለት ደቂቃ ብንለያይ ድብልቅልቁን አውጣሽዋ>> ዩሲ እንደመሣቅ እያለች።
<<ዩስራ አንቺ እኮ ነሽ፤ ቅድም ያለፈ ታሪክ ነግረሽ እልህ ያስያዣት።>> ራቢ።
<<ባካችሁን ዝም በሉ። ይሄ ዝፍዝፍ ቆይ ልኩን አሣየዋለው።>>
<<ልኩንማ ሊያሳይልሽ ሄደ እኮ>> አቤላ ካጎነበሰበት ሣይነቃነቅ።
<<ማን??>> የሁላችንም ጥያቄ ነበር።
<<ኧረ <ማን?> ደስ ይላል።>> ባቢ ፈገግ እንዳለ <<እጅሽን ይዞ ይዚህ ድረስ ያመጣሽ ልጅ ነዋ!!>>
<<ምን ምን? ማን ነው?>> ዩስራ ና ራቢ አፈራርቀው አዩኝ።
<<እንዲህ ሼም ይዟትማ አልነግራችሁም..>> ባቢ ሳቅ እያለ።
<<ኧረ ባቢ እንሂድ እየረሸነው እንዳይሆን>> አቤላ ከክፍሉ ለመውጣት እየሰሰፈሰፈ ተነሣ።
<<አንተ እኮ ነህ እንከተለው ስልህ ..እሺ ጠብቀኝ>> ማሂር ጋ ለመሄድ ተጣደፉ። ገና ከክፍሉ ሳትወጡ
<<ውይይ መጣ በቃ!>> የሚል ድምፅ ሰማን፤ ራቢ። ወደ በሩ ስናይ ማሂር ነበር፤ ገብቶ ቦታው ላይ ተቀመጠ። እነ ባቢ ወደሱ ሲሄዱ ራቢና ዩስራ እርስ በእርስ ተያዩ። እኔ ባላየ አንገቴን ደፋሁ።

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አምስት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
በትምህርት ሰዐት ወሬ ብሎ ነገር የለም፤ ትኩረታችን የሚሆነው ወደ አስተማሪው ነው። የትምህርት ሰዐት አልቆ የምሳ ሰዐት ላይ ደረስን። ተማሪው መውጣት ሲጀምር ራቢ አላንቀሣቅስ አለችኝ።
<<እሺ ምን ልንገርሽ?>>
<<የሆነውን ነዋ... አይደል>> ወደ ዩስራ እየተመለከትች ዩስራም አዎንታዊ ምላሽ ሰጠቻት። መልስ ሳልሰጣት ባቢ ወደኛ መጣ <<ዛሬ አትሰግዱም እንዴ?>>
<<ኧረ ባቢ እንሰግዳለን። ምነው አብረኸን ልትሰግድ ነው? እእ>> በዛው ደብተሬን እያስገባባሁ።
<<ሃሃ ምን ጣጣ አለው ..ባይሆን ውጪ ሰው እየጠበቅሽ ነው ጥራት ተብዬ ነው።>>
<<ማንን??>> ሶስታችንም እኩል ጠየቅነው።
<<አቤት ለወሬ.. ሂጂ አንቺ>>
<<እኔ?>> ግራ እየተጋባሁ።
<<አዎ>> እኔን እየተመለከተ። እነ ዩስራ ሳያቸው እንድሄድ ነገሩኝ... ባቢን ከነሱ ጋር ትቼ ወደ ውጪ ወጣሁ። ማንንም ሣጣ ሙድ እየያዙ ባልሆነ እያልኩ ልገባ ስል <<ኢብቲ>> የሚል ድምፅ ሰማሁ። ወደሰማሁበት ስዞር ማሂር ነው።
<<እንዴ ማሂር>> ፈገግ አልኩኝ ቆሞ ሲያየኝ የተጨነቀ ይመስላል። ምን ሆኖ ይሁን ብዬ ወደ ቆመበት ሄድኩኝ።
<<አንተ ነህ የፈለከኝ?>>
<<አዎ ኢብቲ ምን መሰለሽ.. እኔ ግን በመጀመሪያ ይቅርታ..>>
<<ለምን ይቅርታ?>> ግራ እየገባኝ ጠየኩት።
<<ቅድም>> አይን አይኔን ያየኛል <<ቅድም ምን?>>
<<ቅድም እጅሽን የያዝኩት ሣላስበው ነው። እና ደግሞ ኢብቲ ያልኩሽም ጓደኞችሽ ሲጠሩሽ ስለሰማሁ ነው ይቅርታ...>>
<<ለቅድሙ ችግር የለውም፤ እኔም ሳላስበው ስለነበረ ነው። እንደውም አናደድኩህ መሰለኝ፤ በኔ ችግር አንተንም ስላስገባሁህ ይቅርታ። ግን ኢብቲ ምናምን ያልከው አልገባኝም..>>
<<ኢብቲ ስልሽ ደስ እንደማይልሽ አላውቅም ነበር። ቅድም ነው ባቢ <ለምን እጇን ያዝካት ተናዳብሃለች። ደግሞ ኢብቲ አትበላት ይደብራታል> ብሎኝ ነው። ከዛ <እና> ስለው አቤላ ደግሞ <ይቅርታ እንጠይቃት> ብሎኝ ነው።>>
<<ሃሃሃ ኧረ እነዚህ የተመቱ ሙድ ያዙ ማለት ነው>> መሣቄን ሣላቆም።
<<ማለት? እንዴት?>> ድንብርብር አለ።
<<እንዴ እኔ ኢብቲ ስላልከኝ ለምን እጣላሃለው? ራሱም እንደዛ አይደል የሚጠራኝ>>
<<እውነት! የምርሽን ነው?>>
<<አዎ ማሂ እውነቴን ነው።>>
<<ማሂ ስትዪኝ ደግሞ ደስ ይላል አጠራርሽ>>
<<ከአጠራሬ አመስለኝም <ሎጋው> እንዳልልህ ነው? እእ አትዋሽ..>>
<<ሃሃሃ አዎ ነቃሽብኝ። በናትሽ እንደነሱ አትጥሪኝ ማሂ በይኝ>>
<<ሰዎችን በማያስደስታቸው ስም አልጣራም! ችግር የለውም እሺ ማሂ ነው የምልህ>>
<<አመሰግናለሁ>> እጁን ዘረጋ።ሣየው
<<ውይ ይቅርታ>> እጆቹን ሰበሰበ.. ሃፍረት የተሰማው ይመስላል።
<<ቆይ እነዚህ ልጀችማ እንሰራላቸዋለን...>>
<<እንዳይሰሩልን ፍራ! አሁንም ባቢ ምን እንደሚሰራ አይታወቅም>> እንየው ብለን ወደ ክፍል ስንመለከት አቤላን አየነው። <<ያውልህ አቤላ>> በእጄ አቤል ወዳለበት እየጠቆምኩ።
<<ኧረ ሁሉም አሉ እንጂ ነይ እዚህ ጋር>> ብሎኝ በእሱ በኩል ሁኜ ወደ በሩ ስመለከት አቤላ፣ባቢ፣ራቢ፣ዩሲ ና ኢክራም ተሰብስበው እያዩን ነው። እንዳየናቸው ሲያቁ መሣቅ ጀመሩ። እነ ባቢ ወደኛ መጡ << አንተ ምን አባህ እየሰራህ ነው?>> ማሂ የባቢን ጆሮ ለመያዝ ይታገላል።
<<ኧረ ላሽ ራስህ እስካሁን ምን እያወራህ ነበር>>
<<በቃ ልሂድ>> ብያቸው ወደነ ራቢ አመራሁ። መሄድ ስጀምር ባቢ ምን እንደለኝ አልስማሁትም ግን አቤላ ና ማሂ ሣቃቸው ይሰማኛል።
*
እነ ራቢ ጋር ከመድረሴ ኢክሩ እየሣቀች <<ማሂር ነዋ ስሙ? በአላህ ሲገርም>> አለች።
<<ታዲያ ለዛ አይደል በአንዴ እንዲ የተግባቡልሽ>> ዩስሪ ነበረች ።
<<ራቢ ምነው?>> ራቢ ከወትሮዋ ዝም ማለቷ ገርሞኛል።
<<ምንም የኔ ውድ ጉድሽን ሁሉ ባቢ ነግሮናል።>>
<<እስካሁን እሱ እያወራቹ ነበር? ልጁ ግን እብድ ነገር ነው። አሁንም የሱ ስራ ነው እኮ ሃሃ>> ማሂ ላይ የሰራው ትዝ ብሎኝ ድጋሚ እየሳቅኩ።
<<አዎ ኢብቲ.. ለዛ እኮ ነበር የሣቅንባቹ በማታውቁት ነገር ሃሃሃ። አይ ባቢ ገና መች ሆነና ስራው ብዙ ነው...>> ራቢ።
<<ኧረ በልተን ወደ ሰላት>> ዩስራ ምሣቃችንን አወጣጣች።
<<ኧረ የቅድሙን ሣትነግሪን የምን መብላት ነው?>> ኢክሩ ምሣቃውን እየተቀበለቻት።
<<ሆሆ አንቺም እንደ ኢብቲ ስታገኝው ካልመታሁህ ብትዪሣ?>>
<<ሃሃ ራቢ ደግሞ ነገር አትረሺማ?>>
<<እንዴት ይሄን የመሰለ ነገር ትረሣለች? በትረካ መልኩ ነው ያቀረበችልኝ>> ኢክሩ
ራቢን እየተመለከተች።
<<ነገረችኝ ነው የምትይኝ እእ?>> ከበረከት ጋር የተፈጠረው ወሬ ሆኖ ኢክሩ ጋር መድረሱ እየገረመኝ።
<<አዎ ኢብቲ.. ለዛ አይደል እንዲ ሣቅ በሣቅ የሆነችው ሃሃሃሃ>>
<<እብዶች ናችሁ እኮ...>>
<<እሺ አታረሣሱ በቃ እየበላን ይነገረን ዩስሪ ጀምሪ።>> ኢክሩ ለትረካው ቸኩላለች።
<<ኧረ እየሰሙ መብላት ቀላል ነው እያውሩ መብላቱ ነው ከባድ>> ዩስራ የምሣቃችንን ደረደረች።
<<ሃሃሃሃ አይዞሽ ሁላችንም እናጎርስሻለን አንቺ ብቻ ተሪኪልን>> ራቢን እጇን አስታጥቤያት ስጨርስ እኔን ታስጣጥበኛለች።
ዩስሪ ሃይላንዱን እየተቀበለችኝ <<እሺ ግን በአንድ ነገር እንስማማ>>
<<በምን?>>
<<ስጨርስላቹ ዛሬ ኢክሩ ና ኢብቲ ሎሊፖፕ ትገዛላችሁ>>
<<እእ ኧረ ይሄማ ምርጥ ሃሣብ ነው ተስማምተናል።>>
<<ራቢ እኛ እኮ ነን የተባልነው አንቺ ብር አታወጪ ተስማምተናል ትያለሻ አናታም>>
<<እኮ አየሺልኛ ኢብቲ>> ኢክሩ ቀበል አድርጋ።
<<በቃ ጣጣ የለውም ተያቸው እንገዛለን። አሁን ሰዐት አትግደይ ጀምሪ>>
<<ቆይ ከምግቡ ጋር ቢስሚላህ ብዬ ሃሃ ሃሃ እሺ ምን ላይ ነበርን...
*
<እሷ ፈርታ ነው አፍራ አንቺን የላከችሽ?> ወደ ራቢ ስመለከት ተናዳለች፣ ግራ ተጋብታለች፤ ከተቀመጠችበት ተነስታ የሚሆነውን ታያለች። <እሺ ይቅርታ እንድትጠይቅህ ለምን እንደፈለክ ለተማሪው እኔ ልንገርልህ... በዚህ እንኳን ላግዝህ እንጂ!> ፊቱ ላይ የደስታና የኩራት ስሜቶች ይነበባሉ። ነገሩን ባልጠበቀው መልኩ ለመፍታት አሪፍ መንገድ እየተጠቀምኩ ነው። እሱ ያለውን አንድ በአንድ ደገምኩለት ማለትም መጀመሪያ ላይ ይቅርታ ልትጠይቀኝ ትፈልጋለች ያለውን ከዛም ንግግሬን ቀጠልኩ <አሁን በደንብ አዳምጡኝ የእስካሁኑ ንግግርም ሆነ ሃሣብ ከፊት ለፊታችሁ የተቀመጠው ራስ ወዳድ አሊያም ከኔ በላይ ሰው የለም እያለ የሚያንቧርቀው ክብረ-ቢስ የሆነው በረከት እንጂ የኔ ወይ የጓደኛዬ ፍላጎትም አይደለም ስለዚህ ለኔ እንዳለኝ ይሆናል። ማለትም ጓደኛዬ (ራቢ) ይቅርታ እንድትጠይቀው ካልሆነ ግን ነገሩን ወደ ጥል እንደሚቀይረው አስጠንቅቆኛል። እኔ እንዲህ አይነት ርካሽ ጥያቄ ከኔ አልፎ ራቢ ጋር እንዲደርስ አላደረኩም። እንደሌሎች ተማሪዎች ነገሩ አሁን መስማቷ ነው። ስለዚህ ነገሩን ከኔ ጋር እንፈታዋለን ምን ይመስልሃል?>
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ስድስት
(ሂባ ሁዳ)
.
<< <እንዲው እንዳማረብህ ይቅርታ ልጠይቅህ> ፈገግ አለልኝ፤ በዚህ ቅፅበት ጥሬ እህል እንደሆነ ተሰማኝ። ወደ ተማሪዎች ዞር አልኩ የሚሆነውን ለማየት የቸኮሉ ይመስላሉ። ራቢ እንደተናደደችብኝ ታስታውቃለች፤ ባቢ አጠገቧ አለ... ብዙ ጥያቄ እንዳለው አይኖቹ ይናገራሉ። ፊቴን ወደ በረከት መለስ አደረኩ ምን አልባት ይህ ቅጽበት ለሱ ድል ከማድረግ በላይ በሃሴት የተሞላ ነበር። ከታች ወደ ላይ ተመለከትኩት ትልቅ ድብ የማይ መሰለኝ... ግዝፈቱ አላስፈራኝም። ወደ ኃላ ሄድኩ፤ ከበረከት ጀርባ ቆምኩኝ። ከየት ባመጣሁት ሃይል እና ግፊት እንደሆነ ባላውቅም በቀኝ እጄ አንገቱን እንቅ አድርጌ እንዴት መሬት ላይ እንደተዘረረ አሁንም ድረስ ይገርመኛል፤ ክፍሉ በአንዴ ወደ ሁከት ተቀየረ፤ ክብ ሰርተው መሃል አስገቡን። ከወደቀበት ተነስቶ አንድ ቦክስ ሰነዘረብኝ አልሣተኝም ነበር እኔም በርግጫ አልኩት። ታውቃላቹ ያኔ አምስተኛ ክፍል እያለን ከወንዶች ጋር እንደባደብ የነበረው ጠቅሞኛል... ግን ቦክሱ አቅም አሣጥቶኝ ነበር እናም ከኃላ አንድ ልጅ ሲገፋኝ ወደኩኝ። በረከት አጋጣሚውን ለመጠቀም በጉልበቱ ተንበረከከ በቦክስ ሊደግመኝ ሲል ከኃላ ተገፋና ወደቀ፤ ሲዞር ራቢ ናት። እኔን ትቶ ሲነሣ አብሬው ተነሣሁ፤ ወደ ራቢ ተጠግቶ እጁን ሲሰነዝር እጁን ጋም አድርጋ በቴስታ መለሰችው። ትዝ ይለኛል የተማሪው ፉጨት ምናምን.. ቴስታውን መቋቋም አልቻለም እኛም አጋጣሚውን ተጠቅመን ለሁለት ቀጠቀጥነው። ከስር የተደረቡም ነበሩ.. በቃ ክፍሉ ፉጨት በፉጨት ሆነ። ከዛ እኛ ክፍሉን ለቀን ወጣን፤ በንጋታው ትምህርት ቤት ስንገባ በቃ የሌለ አከባብደው አዩን። ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ክብሮ ነን፤ በረከትም ይቅርታ ጠየቀን ግን አሁንም ድረስ ይፈራናል በቃ ይኸው ነው።>>
<<በለውውው የኔ ውዶች አኮራቹኝ>> ኢክሩ ዩሲን ስታቅፍት እኔ ራቢን አቀፍኳት።
<<አሪፍ አድርጋቹ ነው የቀጣቹት የኔ ጀግናዎች። አሁንም ቢሆን ማንም ከልኩ አያልፍም፤ በየትኛውም መንገድ እኛ ላይ እንዲደርሱብን አንፈቅድላቸውም። ነገራቶችን በቅን መንገድ እንፈታቸዋለን፤ ድንበሩ አልፎ ለሚመጣብን የሚገባውን እንሰጠዋለን። አይደል ውዶቼ >> ሶስቱንም አፈራርቄ አየሁዋቸው።
ኢክሩ ከውብ ፈገግታዋ ጋር አይን አይኔን እያየች <<ኢብቲ አንቺ እኮ አትናገሪ.. ንግግሮችሽ ሁሌም ወደ ልባችን ይገባሉ፤ ደግሞ አራት ነን አላህ እስካለያየን ድረስ..>>
<<እንዴ ሰዐቱን እዩትማ!>> ራቢ ሰዐቷን አየት አደረገች።
<<ወይኔ ሰላት ረፈደብን ገና አንድ ምሣቃ ይቀረናል እኮ.. እዛ ከሄድንማ አንደርስም በቃ እዚው እንስገድ እእ ውዶች>> ዩስራ ምሣቃዎቹን ዘጋጋች። በዩስሪ ሃሣብ ተስማምተን የክፍላችንን በር ዘግተን ሂጃብ አንጥፈን ወደ ሰላታችን ገባን፤ ስንጨርስ ከክፍል ወጥተን ዞር ዞር ማለት ጀመርን። በዛው ሎሊፖፕ ገዝተን ተመለስን። እንደለመድነው ኢክሩን ሸኝተን ወደ ክፍላችን ገባን።
*
እኛ ቦታችን ጋር ተቀመጥን እነ ባቢ ደግሞ ከፊታችን ተቀምጠው እየተተራረቡ ፈታ ያረጉናል፤ እኛ እንስቃለን ሙድ እንይዛለን። እንዲህ እያለን አስተማሪው መጣ፤ ብዛት ያላቸው ወረቀቶች ይዟል። የክፍል ሃላፊያችን እንደሆነና በቡድን ሊከፋፍለን እንደሆነ ነገረን። ጎበዝ ተማሪዎችን የቡድን መሪ እንዲሁም ጸሃፊ እንደሚሆኑ እያስረዳን አምና የሚያውቋቸው ጎበዝ ተማሪዎችን ስም መጥራት ጀመረ። አራት ተማሪዎች ተጠሩ ስምንት ቡድን ስለሆነ ተጨማሪ አራት ተማሪ እንደሚፈልግ ነገረን። <ከሌላ ትምህርት ቤት የመጣችሁ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ..> ሲል ሁሉም ዝም ሲሉ መጣሁ ብሎ ከክፍል ወጣ። ራቢ <ለምን አትሆኚም?> ብላ ተቆጣችኝ። እንደማልፈልግና ባይሆን እነሱ ለምን እንደማይሆኑ ስጠይቃቸው እነሱም እንደማይፈልጉ ነገሩኝ። ሶስታችንም የቡድን መሪ ከሆንን አንድ ላይ መሆን ስለማንችል ነው።
ባቢ <<ዱዝ ሁነሽ ነዋ ከዛ ትምህርት ቤት የተባረርሽው.. እኛማ ጠጋ ጠጋ ያልነው ቀለሜ መስለሽን አይይይይ ተበላን!>>
<<ሃሃ ባክህ አላወካትም ሚኒስትሪ በሷ ነው የምታልፈው ለዛውም ሰቅለህ>> ራቢ ጥብርር እያለች መለሰችለት። ራቢና ባቢ እየተከራከሩ አስተማሪው መጣ።
<<እሺ አሁን ስማቹን የምጠራቹ ወደዚህ ትመጣላችሁ>> ብሎ ስም መጥራት ጀመረ። ከአራቱ ተማሪዎች ሶስቱን ጠራ አንዱን ቀነሰው ከዛም ራቢያና ዩስራ ጠራ <<እንዴት እናንተን እረሳለሁ? እናንተስ እንዴት ዝም ትላላችሁ? አምናም የቡድን መሪ ነበራቹ አይደል>> ብሎ ሌላ ተማሪዎችን ጠራ... ሁለቱ አዲስ ነበሩ፤ የፈሩ ይመስላሉ። ቀጥሎ ኢንቲሣር ብሎ ተጣራ ራቢ <<ኢብቲሣምን ነው?>> ጠየቀችው። ድጋሚ ወረቀቱን አይቶ <<ይቅርታ ኢብቲሣም የት አለች?>>
<<ኢብቲ ነይ>> ዩሲ ከነሱ ጋር በመጠራቴ ደስ ብሏት፤ እኔ ግን መውጣት አልፈለኩም። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቲቸር ይቅርታ <<እኔ የቡድን መሪ መሆን አልፈልግም>> አልኩት።
<<ለምን?>>
<<በቃ ስለማልፈልግ ነው ...>>
አስተማሪው ቆጣ እያለ <<መጀመሪያ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ ስል ዝም አልሽ። ዘጠና አራት ነጥብ ይዘሽ በዚህ መሪ አልሆንም ትያለሽ?>>
<<እሺ በቃ ጸሃፊ እሆናለው በዩስራ ወይም በራቢያ ቡድን>> እየፈራሁ ነበር የተናገርኩት።
<<እኔ መች ምረጪ አልኩሽ?>> አስተማሪው ተቆጣ። ምንም አማራጭ እንደሌለኝ ሣውቅ ወጥቼ ከነ ዩሲ ጋር ተቀላቀልኩ። መዳድቦ ከጨረሰ ቡኃላ የቡድን አባላት ያለበትን ወረቀት ለየግል ሰጠን ወረቀቱን ይዘን ወደ ቦታችን ተመለስን።
አስተምሮ ሲጨርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም ተማሪ በየቡድኑ እንዲቀመጥ ካልሆነ እርምጃ እንደሚወስድ ነግሮን ወጣ። ባቢ ወረቀቶቹን ተቀብሎን የቡድኖቹን ክፍፍል ማየት ጀመረ <<በለው አቤላ ከራቢያ ጋር ነህ ብዙም አልራክም፤ እኔና አንተን የት ከቶን ይሁን>> ማሂን እያየ። የነሱን ስም ፍለጋ ቀጣዩን ወረቀት ማየት ጀመረ።
<<በለውውው እኔ ደግሞ ከዩስራ ጋር ዋው>>
<<እኔን ከኢብቲ ጋር አርጎኝ ነዋ እየው እስቲ>> ማሂር ለማየት እየቸኮለ። ባቢ ለኔ የተሰጠኝን ወረቀት ማየት ጀመረ።
<<ቲሽ ሎጋው እዚህም የለህም>> ማሂ ከፋው ከጓደኞቹ ጋር ስለተለየ መሰለኝ እኛም ዝም አልን። የሱ ስም የሌላ ቡድን መሪ ወረቀት ላይ ስለሚሆን የት ቡድን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም።
<<ቆይ እንዲ የደበራችሁ የተለያየ ቡድን ስለሆናቹ ነው? እህ... ክፍል ሁላ ባለመለያየታቹ አመስግኑ>> ቀለክ ላደርገው እየሞከርኩ። ማንም ምንም አልተናገረም ባቢ ንግግሩን ቀጠለ <<እሺ ለምን እዚው ቅርብ ቅርብ አናደርገውም እእ.. አስተማሪው ቦታ ከሚመርጥልን እኛ እንደምንፈልገው እናድርገው እእ.. በናታችሁ ዝም አትበሉ ከቀጣዩ ክላስ ቡኃላ እናስተካክላለን እሺ>> ራቢም ተስማማች።
<<እሺ>> ቀጣዩን ክላስ ከተማርን ቡኃላ ወደ ቤት ሰዐት ላይ ሁሉም ተማሪ ሲወጣ እኔና ዩስራ ውጪ ሆነን እነሱ ለአራት አስተካክለው ጠሩን።
ስንገባ ሌላ ክፍል ነው የሚመስለው። ስምንት ቡድን ሰርተው የቡድን ቁጥር ከፋፍለው ነበር። እኔ ቡድን አምስት፣ እነዩስራ ስድስት፣ ራቢ ደግሞ ሰባት አደረጉን፤ ያው እንዳንራራቅም ነው ቅርብ ለቅርብ ነን።
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ሰባት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
ዛሬ ራቢ ቆይታብናለች። እኛም በጣም ሲረፍድ ጥለናት ሄድን። ጊቢ ስንገባ በማርፈዳችን ተቀጥተን የተመታውን እጃችንን እያሻሸን ወደ ክፍል አመራን። አስተማሪው ገብቶ ማስተማሩን ጀምሮ ነበር፤ ትንሽ ካስቆመን ቡኃላ እንድንቀመጥ ፈቀደልን። ሁሉም በቡድን ቡድን ተቀምጦል ራቢም አለች። እንዴ እስካሁን እሷን ስንጥብቅ አርፍደን እሷ ግን እዚህ ናት የተመታሁትም አሞኝ ስለነበር ተናድጄ ራቢን ገፍቻት አለፍኩ። ትናንት በተነጋገርነው ቦታ ላይ ቁጭ አልኩኝ። ደብተሬን ሣወጣ ባቢን አየሁት በእጁ ሃይ አለኝ ብናደድም ፈገግ አስባለኝ ከእሱ አጠገብ ዩሲ አለች እሷ ግን አልተናደደችም ነበር። ከእነሱ ፊት ደግሞ የነ ራቢ ቡድን አለ ከራቢ ጋር አይን ለአይን ስንገጣጠም ዞር አልኩባት። አጠገቧ አቤላ አለ... ባቢ እንዳለውም አልተራራቅንም፤ ፊት ለፊት ለመተያየት እንዲመች አድርገው ነው ያስተካከሉት። <<ትምህርቱን ረሣሁት እኮ እናንተን ሣይ ብዙ ጻፋቹ እንዴ?>> ብዬ ወደ ብላክቦርዱ ሣይ ከማሂ ጋር ተገጣጠምን። እስካሁን አላስተዋልኩትም ነበር፤ ስገባም ከአጠገቡ ነበር ያልፍኩት። ደግሞ ርቀት አለን እንዴት እዛ ሊሄድ ቻለ? ..ወይ ጉድ ብዙ ነገር ሳብሰለስል አስተማሪው ሳልፅፍ አጠፋብኝ። ቀጣዩን መፃፍ ጀመረ፤ በቃ አንደኛዬን በኃላ እፅፈዋለሁ ብዬ ተውኩት። ሲያስረዳ ከደብተሬ ጀርባ አጭር ማስታወሻ መያዝ ጀመርኩ፤ ዛሬ ደግሞ አስተማሪዎች ላይ በላይ ነው የሚገቡት ምንም ክፍተት አልተፈጠረም። ይኸው የእረፍት ሰዐት ደርሶ አስተማሪው ወጣ።
<<ኡፍፍፍ ጭንቀት ሊገለኝ ነበር እኮ..>> ባቢ ከቦታው እየተነሣ።
<<ድሮም እኮ የትምህርት ነገር አይሆንልህ>> ራቢ ሂጃቧን እያስተካከለች ትመልስለታለች።
ደብተሬን አስገባብቼ ወደ በሩ በችኮላ መሄድ ጀመርኩ። ራቢ ቦርሣዋን እየዘጋች <<ኢብቲ በአላህ ጠብቂኝ...>> አለችኝ። ማሂ ወደነ ባቢ ጋር እየሄደ ነበር፤ መሃል ላይ ተገጣጠምን። ራቢም ወደኛ እየመጣች ነበር። <<በናትህ እንዳታሣልፋት>> ራቢ እንዲያስቆምላት ጠየቀችው። ማሂ ከፊቴ እንደቆመ ገፍትሬው አለፍኩ። ከክፍል ስወጣ ኢክሩ እየመጣች አገኘኋት። ተቃቅፈን ሰላም ስንባባል ራቢ መጣች... ሁለታችንንም አቀፈችን ምንም አላኳትም። ግንባሬን ሣመችኝ፤ እንደማኩረፍ እያልኩ <<በቃ አረሳሳሽ?>>
<<ኢብቲ ደግሞ ይቅርታ.. ቆይ ልንገርሽ ለምን እንዳልመጣሁ..>>
<<ኧረ ተይው ላለፈ ነገር። በርግጥ ተናድጄብሽ ነበር ግን አሁን አስጠፋሽብኝ በሰላም ከሆነ ጣጣ የለውም።>> ለማብረድ እየሞከርኩ።
<<ለዚህ እኮ ነው ልዩ ነሽ የምልሽ። ነይ በዚህ>> ዘላ ጉንጬን ሣመችኝ። እርቋት አይደለም መዝለል ስለምትወድ እንጂ.. ዩሲ ብንጠብቃትም ከክፍል ስላልወጣች ተያይዘን ወደ ክፍል ገባን። በሩን ተደግፎ የቆመው ባቢ <<ቅድም ስትጨቃጨቁ ወታቹ አሁን ተቃቅፎ መግባት ጠላትን ለማናደድ ይመስላል።>>
<<ገና ከመታረቃችን ልታጣላን ነው እንዴ ሆ!>> ራቢ ከአጠገቡ ቆማ መልስ ሰጠችው። እኔና ኢክሩ ወደ ውስጥ ገባን። ኢክሩ ዩሲን ሰላም ብላት አዲሱን ቦታችንን አሳይቻት ያለፈኝን ልትፅፍልኝ ተቀመጠች። ዩሲም እየፃፈች ነበር፤ አብረው መፃፍ ጀመሩ። እኔም እነ ባቢ ጋር ሄጄ ተቀላቀልኳቸው።
*
እንዲህ እንዲህ እያል ጊዜው ሄደ... ቁምነገር ያልተሰራባቸው ቀናት ተቆጠሩ። ከሙሉ ተማሪው ጋር ተግባባን ከነ ባቢ ጋር ደግሞ በጣም ተቀራረብን። ላየን እንደ አዲስ ተማሪ ሳይሆን ከድሮ ጀምሮ የምንተዋወቅ እንመስል ነበር። የክፍል ሃላፊያችን ካልገባ በቀር በቡድን አንቀመጥም። ሶስታችንም ከፊት ካለው ወንበር አብረን እንቀመጣለን አስተማሪ እስኪ ገባ ባለን ክፍተት እንጠያየቃለን። ዩስራ ሂሣብ ትምህርት ነፍሷ ነው፤ እኔ ደግሞ ብዙም አይደለሁም ባይሎጂ ግን የሚችለኝ የለም። ራቢ ደግሞ ኬሚስትሪ የግሏ ነው፤ በየትምህርቱ ላይ የተለያየ ቦታ መስጠታችን እኛን ጠቅሞናል። ሶስታችንም አንድ ላይ ስለምንሰራ የክፍሉ አሪፍ ውጤት እንድንይዝ ረድቶናል።
*
<<ኧረ ልጅት ምንድነው እናቷን ከገበያ እስክትመጣ የምትጠብቅ ልጅ የመሰልሽው>> ባቢ ወደኔ እየመጣ ንግግሩን ቀጠለ። ከነሱ ቀድሜ ክፍል ተቀምጬ ነበር የመጡት። በቀናት ሂደት ያልተቀየረው የባቢ ተጫዋች ምላስ ነው። <<እእ እሱ ካልተመቸሽ ደግሞ ፎንቃዋን የምትጠብቅ አፍቃሪ የመሰልሽው ይሁና>>
<<ባቢ ይሄ ከፎንቃም በላይ ነው። ከትምሮ ይሁን ከአስተማሪው አልተለየም እንጂ!>> አቤላ ተከትሎት እየገባ ጭንቅላቱን ከግራ ወደ ቀኝ ያዞራል። እንዲ የሚያደርገው እኔን ለማናደድ ሲፈልግ ነው። የምርም ግን ያናድደኛል፤ ይኸው ተሣካለት።
<<እስቲ አቤላ ነገር ከምትበላ ሂድ ብላክቦርዱን አፅዳው>> ያናደደኝን ልመልስለት እየሞከርኩ።
<<ባክሽ አልሰማሽም፤ ዛሬ እኔ አላፀዳውም>>
<<ነው?>>
<<እናቴን አዎ ኢብቲ ምን ታመጪያለሽ>>
<<ኧረ.. ምንም እንዴት እንደማስጠፋህ አሳይሃለው ...>>
<<ይኸው እየነጠረ መጣልሽ>> ባቢ ወደ ቦታው ተመለሰ፤ የባይሎጂ አስተማሪ ገባ።
<<ሄይ ሄይ ተማሪዎች ዛሬ ማን ነው የሚያፀዳው?>>
<<እኔ አፀዳለው ቲቸር>>
<<ኦውው ዛሬ ኢብቲሣም ናት>> ሲያቀብለኝ ተቀበልኩት። ለማፅዳት ወደ ብላክ ቦርዱ ከዞርኩበት ወደ ተማሪው መለስ ብዬ <<ኧረ ችግር የለውም>> አልኩ፤ አቤላን እያየሁ። ከባቢ ጋር ተጠቃቀስን።
<<ምን?>> አቤላ ግራ እየተጋባ ያየኛል። ባቢ ወደ አቤላ በመዞር <<ኢብቱ አንቺ ጥቁር ሂጃብ ስላደረግሽ ብናኙ እንዳያበላሽብሽ ብሎ ነው>>
<<እሺ አቤላ አመሰግናለው ይኸው ና አጥፋ>> ዳስተሩን አስቀምጬው ተቀምጥኩ። አቤላ እየበሸቅ አጥፍቶ ጨረሰ።
<<እናቴን ባልሰራላቹ>> ብሎኝ ወደ ቦታው ሄደ። ባይሎጂ መምህራችን የእለቱን ትምህርት ጀመረ
.
የዛሬው ትምህረት ትንሽ ውስብስብ ያለ ነው፤ በዛ ላይ አስተማሪው ቸኩሏል።
<<ኡፍ ምንድነው የሚደበላልቀው?>> ራቢ ትነጫነጫለች።
<<ራቢ ዝም ብለሽ ከተከታተልሹ ግልፅ ይሆንልሻል።>>
<<ባክሽ ዛሬ ምን እንደሚል ሁላ መረዳት አልቻልኩም በቃ ኢብቲ እንደለመደብሽ በኃላ ታስረጂኛለሽ>> ደብተሯ ላይ ጋደም አለችበት። ዩሲ እየተደገፍቻት <<ስሚ ቀጣይ ኬሚስትሪ እኮ ነው እንቅልፍ እንዳይወስድሽ ..>>
<<እሱ መች ጠፋኝ.. ነቃ ብዬ እንድማር አሁን እረፍት ላድርግ እንጂ፤ ባይሆን ዝም በሉ ና ተከታተሉት።>> አለችና ተጋደመች። ትንሽ እንደተማርን <<ለዛሬ ይበቃል ጥያቄ ያለው አለ?>> ሶስት ልጆች ጥያቄ አቀረቡለት። የነሱን ከመለሰ በኋላ..
<<ቲቸር>> ማሂ ፀጉሩን እያሻሸ ጠራው።
<<ወዬ>> ጋወኑን ለማውለቅ እየተቻኮለ <<ኧረ ምንም አልገባኝም አትደግምልኝም?>> ባይሎጂ መምህራችን ፈታ ያለ ስለሆነ ነገር አያከርም።
<<በጣም አሪፍ ኢብቲሣም ታስረዳሃለች። የናንተንም ጥያቄ እሷ ትመልስላችሁ፤ የቀረ ካለ ደግሞ ነገ እናያለን በሉ ተማሪዎች ባይ ባይ>>.. ቲቸር ፊቱን ወደኔ አዞረ።
<<ኢብቲሣም እንቺም ዛሬ አልገባሽም?>>
<<አይ ገብቶኛል ግን ሰዐት አለን አላለቀም እኮ>>
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ስምንት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
ጥናቱን እንዳጠናቀቅን መሸምደድ ያለብኝን የመድረሳ ሃዲስ ለራሴ ማነብነብ ጀመርኩ።
<<ኢብቲ ግን ምንድነው እንዲ ያጨናነቀሽ? ታውቆሻል ብቻሽን የምትለፈልፊ ነው የምትመስዪው እኮ ...>> ማሂ ግራ በመጋባት እያየኝ።
<<ወይ መለፍለፍ... ባክህ እየሸመደድኩ ነው የግድ መጨረስ ስላለብኝ ነው እኮ ማሂ>>
<<እህ ምንድነው የደበቅሽው እስቲ አሣይኝ ቦርሣሽን አንሺው...>>
<<ይኸው አርበኢን ኪታቤ ነው እዚህ ስለማይፈቀድ ነው በቦርሣዬ ከልዬ የምሃፍዘው>>
<<እና እቤትሽ አታፍዢም ደግሞ ምን ይጠቅምሻል?>>
<<ማለት ምን ይጠቅምሻል? ዛሬ መድረሣ ፈተና ስላለን ነው የቸኮልኩት።>> ማሂ ግራ ተጋባ።
<<መድረሣ? የምን መድረሣ?>>
<<ሃሃ አታድርቀኝ ዞር በል ሰዐት አትሻማብኝ..>>
<<የምሬን ነው እኔ እኮ አላውቅም መድረሣ ምናምን>>
<<ውይ ማሂ በአላህ ዞር በል አልኩሃ>> ትኩረቴ ሁሉ መሸምደዱ ላይ ስለነበር እሱ ላለኝ ነገር ቦታ አልሰጠሁትም።
<<እእ እ..ሺ..>> ብሎ ከአጠገቤ ራቅ አለ። እንደምንም ሸምድጄ ጨረስኩ። የትምህርት ጊዜው እንዳበቃ፤ እነኢክሩ ቀድመውኝ ሸምድደው ስለ ነበር ከነሱ እየተጠያየቅን ወደ መድረሣ መንገዳችንን ጀመርን። አንዳንዴ ከረፈደ ወይንም ፈተና ከሆነ ከትምህርት ቤት በዛው ነው የምንገባው፤ ቅርብ ስለሆነ ቶሎ ደረስን። ብዙ ተማሪ ስላልነበረ እኛ የመጀመሪያዎቹ ተፈታኝ ነበርን። እንደ ፈራነው አልነበረም እኛ ከሸመደድነው ጥቂት ነበር ፈተናው ላይ የነበረው፤ ሰዐታችን ሲደርስ ወደ ቤት አመራን ።
*
ጊዜው ከምንም በላይ ይፈጥናል፤ ሰሞኑን ስለሚኒስትሪ ፈተና ነው ጭንቃችን። አስተማሪዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችን ያሰሩናል፤ በዛ ላይ ቅዳሜ ማጠናከሪያ ተብሎ መግባት ተጀምሯል።
አስተማሪዎቹ ከሌላ ትምህርት ቤት እየመጡ ነው የሚያስተምሩን በጣም ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው፤ ረባሹ ተማሪ ሣይቀር ነው በደንብ የሚከታተላቸው። ተማሪን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው በደንብ የገባቸው ይመስለኛል፤ ለዛም ነው የሚያስተምሩት ተማሪ የሚወዳቸውና የሚከታተላቸው።
.
ዛሬ ግን ከሌላው ቀን ትንሽ አቆይተውናል እኔ ደግሞ አዛን እስኪል እቤት መድረስ አለብኝ። ቅዳሜ ቅዳሜ አክስቴ ጋር ተሰብስበን እንሄዳለን፤ ዙሁር ሁሉም ቤተሰብ አክስቴ ጋር ነበር የሚሰግደው አሁን እኔ ስለማረፍድ ጥለውኝ ይሄዳሉ። ታላቅ ወንድሜ ይጠብቀኝና ከእሱ ጋር እሄዳለው፤ እሱም ግን አዛን ካለ አይጠብቀኝም... ስለዚህ አስፈቅጄ ለመውጣት አሰብኩ። አስተማሪው <<በፍላጎት መማር እንጂ ተገዶ መማር ጊዜ ማቃጠል ነው>> ይላል፤ ስለዚህ በፈለግነው ጊዜ መውጣት እንችላለን ማለት ነው። አስፈቅጄ እንደወጣሁ ማሂ ተከትሎኝ ወቶ አስቆመኝ።
<<እንዴ አንተም ወደ ቤት ልትሄድ ነው?>> እኔ ስለቸኮልኩ ላለመቆም እያልኩ...
<<አይ ኢብቲ ላናግርሽ ምፈልገው ነገር ስላለ ትንሽ ጊዜ ስጪኝ ..>>
<<ኧረ ማሂ አሁን አልችልም ሌላ ቀን አይሆንም..?>>
<<አሁን ነው መሆን ያለበት በናትሽ ኢብቲ አትሂጂ>> ድምፁ በሲቃ ታፍኗል።
<<ማሂ ምነው ችግር አለ?>> ደንግጫለው።
<<አዎ ኢብቲ ታስፈልጊኛለሽ ካንቺ ብዙ ነገር ማወቅ ና ማግኘት እፈልጋለው ተረጂኝና ሁሉንም ልንገርሽ>> አይኖቹ እንባ አቅርረዋል። ለተወሰነ ሰዐት ዝም እንዳልኩ ቆየሁ። ብዙ ሃሣብ ተመላለሰብኝ ግን እሱ እንዲነግረኝ እዚህ መቆየት አለብኝ፤ እሱ ደግሞ አይሆንም።
<<እ...ማሂ ሰኞ ትነግረኛለህ ቻው..>> ይሄን ቃል በደመነፍስ እንደተናገርኩት ጥዬው ሄድኩ ዞር ብዬ እንኳን አላየሁትም።
.
ወደ ቤቴ እየተቃረብኩ መጣሁ... መንገዴን ከጀመርኩ ጀምሮም ግን ምንም ላርፍ አልቻልኩም። ጭንቅ ብሎኛል፤ ምን ሊለኝ ነበር የሚለው ጥያቄ እረፍት ነስቶኛል፤ እንዲሁ ስወዛገብ ሰፈሬ ደረስኩ። መንገድ ላይ ወንድሜን አገኘሁት።
<<በመጨረሻ መጣሽ አፍጥኝው በቃ አዛን ስላለ መስጂድ ሰግደን እንሄዳለን ቤት ደርሰሽ ነው ወይንስ በዚሁ እንሂድ ?>> ድምፄ ሲጠፋበት ከእቅፉ አወጣኝ፤ <<ምነው አሞሻል እንዴ?>> ለካ እስካሁን እቅፉ ውስጥ ነበርኩ። ሁሉንም ሰምቼዋለሁ መልስ መስጠት ግን አልቻልኩም። ብዙ ጊዜ ራስ ምታት ሲይዘኝ ስለማልናገር ዝም ባልኩ ቁጥር አሞሻል እንዴ የሁል ጊዜ ጥያቄው ነው።
<<ትንሿ ምንድነው?>>
<<ኧረ ምንም>>
<<አሞሻል አይደል?>> ትኩር ብሎ እያየኝ።
<<እእ አዎ ትንሽ.. በቃ ሂድ እኔ ልተኛ ነው።>>
<<ኧረ አልሄድም አሞሽማ ብቻሽን>> ብሎ ድርቅ አለብኝ። ትንሽ ተጨቃጭቀን እሱ ሄደ እኔም ወደ ቤት ገባሁ።
.
እንዲሁ ሃሳብ አጨናንቆኝ እንጂ ደህና ነበርኩ። ወንድሜ እንደሄደ ሰግጄ ቁጭ አልኩ። ብዙም ሳይቆይ የጊቢው በር ተንኳኳ። <ኡፍፍ ምናለ ማንም ባይመጣ> እያልኩ ወደ በሩ አመራሁ። ስከፍት ግን ደነገጥኩ፤ ዩሲ ና ራቢ ነበሩ። መደንገጤ እንዴት እዚህ መጡ? ወይ እንዴት ቶሎ ወጡ? ይሁን.. ለራሴም አልገባኝም።
<<ምነው ምሳ የለም እንዴ ፈዘዝሽ እኮ አሣልፊኝ ባክሽ>> ዩሲ ገፍትራኝ ገባች። ለካ ግቡም አላልኳቸውም።
<<አንቺ እንደወጣሽ እኮ አስተማሪውም ሄደ። ለትንሽ ቀደምሽን አብረን ምንመጣውን>> ራቢ ግራ መጋባቴን ተመልክታ ከመጠየቄ በፊት ትመልስልኝ ጀመረች። <<ከዛ ደግሞ ጫፍ ጋር ወንድምሽ እቤት ናት ሲለን በዚሁ ከች አልንልሽ...ገባሻ ሃሃሃሃ ሣታስቢው ሰርፕራይዝ አደረግንሽ።>>
<<አቦ ርቦኛል የሚበላ እፈልጋለው!!>> ዩሲ።
<<እሺ በቃ ስገዱ ላቀራርብ>> እስኪሰግዱ ምሳ አቀረብኩ። እንዳጋጣሚ ዩሲ የምትወደው ምግብ ነበር እኛን አላስበላ እያለችን ትንሽ ከበላች ቡኃላ አንድ ላይ መብላት ጀመርን ። በዚህ መሃል ዩሲ <<ማሂ ምን ሆነው ይሁን?>> ስትል ደነገጥኩ።
<<ምን ሆነ?>>
<<ምን እንደሆነማ እኛም አላወቅንም ብቻ አልቅሶ አይኑ ቀላልልቶ ነበር። በዛ ላይ እነ ባቢንም አላናግር ብሏቸው ብቻውን ሄደ።>> እንዲህ ስትል ትን አለኝ ራቢ ጀርባዬን ስትደበድብ ዩሲ ውሃ ምናምን ስትል ለትንሽ ሰዐት ተዋከብን... ትንታው ለቀቀኝ። ስረጋጋ ሁሉንም ነገር ነገርኳቸው፤ በዚህ ጊዜ ነበር ራቢ ያልጠበቁት ነገር የተናገረችው።
<<በቃ እንደጠረጠርኩት...>>
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ዘጠኝ
(ሂባ ሁዳ)
.
.
<<በቃ እደጠረጠርኩት... ይወድሻል..>> ራቢ ነበረች።
<<አንቺ ደግሞ ሁሌ መጠርጠር.. እንደዛ እንኳን አይሆንም ዝም ብለሽ ነው።>> ምንም ልትሰማኝ አልቻለችም።
<<አንቺ እኮ ቆየ ይወዳታል ማለት ከጀመርሽ፤ አይደለም ይሄ ተጨምሮ>> ዩሲ የቀረውን ምግብ እየጎረሰች።
<<እሺ ካላመናችሁኝ የባለፈው ብቻ እኮ በቂ ማረጋገጫ ነበር እኮ እእ ምን ልትሉ>> ሁለታችንም ተያይተን <<የቱ?>> አልናት ለማስታወስ..
<<ባለፈው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ጊቢ ውስጥ ሲከበር ማሂር ስልኩን ክፍል ውስጥ ቻርጅ ላይ አድርጎ <ማንም እንዳይነካው!> ብሎ ወጣ። ቻርጅ አስቸግሮት አናዶት ነበር... አቤላ ላይ ሁላ <ለምን ነካኸው> ብሎ ጓ! ብሎ ነበር። እሱ ሲወጣ ኢብቲ ገባች። ስልኩ የማሂ እንደሆነ ስታውቅ ጋላሪ ላይ ገብታ ስትመሰጥ የሆነ ሰው ሄዶ ለማሂር ነገረው። ከውጪ ሲገባ በዛ አካሄዱ ላየውሟ የሌለ ያስፈራ ነበር፤ በሩን እንዴት ብርግድ እንዳደረገው ኢብቲም ደንግጣ ስልኩን ለቀቀችው፤ ማሂር ሄዶ እነሣውና <አንቺ ነሽ እንዴ የነካሽው? ደግሞ ተይው ግላሱ ነው አልተጎዳም> ቢላትስ፤ ከኋላ የነበረው ተማሪ እኮ ከአሁን አሁን አጋጫት እያለ... ሃሃሃሃ... አጅሬው ኢብቲ መሆኗን ሲያውቅ ምንም እንዳልተፈጠር <ስጨርሺ ቻርጅ ላይ አድርጊው ካስቸገረሽ ደግሞ ጥሪኝ> ብሎ ላሽ ቢልስ። እኔ ደግሞ ለኢብቲ ያለውን ቦታ ማየት ቻልኳ! እእ ምን ልትሉ ነው?>>
<<እኔ ግን ምንም እንዳዛ አላስብም ራቢ። ምን አልባት ሌላ ነገር ይሆናል እኮ ማን ያውቃል ..>> ሃሳቧ የሚያሳምን ነገር አለው፤ ግን ለመከላከል ሞከርኩ።
<<እኔም ኢብቲ እንዳለችው ነው። ራቢ እኛ በዚህ እድሜያችን እንዴት ይሄን እናስባለን? ማይሆን ነገር እኮ ነው።
እንርሣው ባይሆን የቅድሙን ጥያቄዎች እንስራቸው ምን ትላላችሁ?>> ዩሲ ጉዳዩን ለማስቀር ተባበረችኝ።
<<ካላችሁ ምን ይደረጋል ግን እኔ ያልኩት እውነት መሆኑን በቅርቡ ታረጋግጣላችሁ ጠብቁ ብቻ <ራቢ ብለሽ ነበርሽ> ስትሉ መስማቴ የማይቀር ነው>>
<<አንቺ ደግሞ አንዴ ነገር ከጀመርሽ ቡኃላ አትፋቺም ዩሲ እንጀምር በቃ!!>> ነገሩን ዘጋሁት።
*
ያን ቀን ከትምህርት ቤት መልስ ጥያቄዎችን ሰርተን ከተለያየን በኃላ ዛሬ መገናኘታችን ነው። እንደተለመደው ክፍል ገብተን መማር ከጀመርን ሰዐታት አልፈዋል። ምሳ ሰዕት ላይ ዩሲ ማሂን እንዳወራው አስታወሰችኝና የተቀመጠበት ሄድኩኝ።
<<ሰላም ማሂሬ>> ለማውራት እንዲመቸኝ ከጎኑ እየተቀመጥኩ።
<<እእ እንዴት ነሽ?>>
<<አልሃምዱሊላህ አለሁልህ.. ምነው አሞሃል እንዴ?>> ፊቱ ልክ አለመሰለኝም።
<<ብታመምስ...ማንም ለማከም ፍቃደኛ ካልሆነ..>>
<<ማለት እንዴት?>>
<<ካልገባሽ አንድ ቀን ይገባሻል...>>
ምንም ማሂ አልመስልሽ አለኝ። ቢያንስ የቅዳሜውን ባወራው በዛው ወሬ መቀየሻ ይሆነኛል ብዬ አሰብኩ።
<<እኔ ምልህ ማሂ..>>ምን ብዬ እንደምጀምርለት ሃሳብ ስፈልግ።
<<ምን ነው ችግር አለ?>> ከአይኔ ላይ ፍርሃቴን ያነበበው መሰለኝ።
<<ሣይሆን... ቅዳሜ በጣም ቸኩዬ ስለነበረ ነው የሄድኩት እሺ ..>>
<<እሺ>> እሱ በግድ ፈገግ ለማለት ይሞክራል፤ እኔ ደግሞ እያባበልኩት መሰለኝ። ትንሽ ዝም ካልን በኃላ
<<እና አሁን ንገረኛ ምንድነው ማሂ ...>>
<<ኧረ.. አሁንስ ጊዜ አለሽ ማለት ነው?>>
<<ያኔ እኮ...>>አላስጨረሰኝም
<<ነገርሽኝ እኮ በቃ!>>
<<እህህህ ማሂ አሁን ንገረኝ እያልኩሃ>> ንግግራችን ወደ ጭቅጭቅ መስመር መቀየር ጀመረ።
<<ምን እንድነግርሽ ነው የምትፈልጊው?>> ድምፁ ላይ ቁጣ ታክሎበታል። <<ልትነግረኝ የነበረውን ነዋ ቀስ ለማለት እየሞከርኩ ...>>
<<ተውኩት በቃ!>>
<<እህህህ ማሂር አታድርቀኝ እንግዲ...>>
<<ሁሉም ነገር ላንቺ ቀልድ ነዋ የሚመስልሽ..ለማንኛውም ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል!>> ሲቃ በተሞላበት ድምፅ። <<አመሰግናለሁ>> ብሎኝ እየፈጠነ ወደ ውጪ ወጣ። እኔም ምንም መናገር አልቻልኩም ነበር እዛው ቁጭ አልኩ። <ያ ኢላሂ ምን ጉድ ነው? ኡፍፍፍ ኢብቲሣም ምንድነው ያደረግሽው.. ቲሽሽሽ> በራሴ ተናደድኩ። ያኔ ጥዬው ባልሄድ ይሄ ሁሉ አይፈጠርም ነበር። ምናለ ባዳመጥኩት... በራሴ ተናድጃለው፤ ከፍቶኛልም። እዛው ወንበሩ ላይ ድፍት ብዬ ባለቅስ ደስ ይለኝ ነበር።
*
<<ምንሼ እስካሁን እእ? ስሚ አታዝጊ ተነሺና ተናገሪ...>> አንገቴን ቀና አድርጋ እስክነግራት ትጠብቀኛለች፤ ራቢ።
<<ምንም አላለኝም>>
<<ሃሃሃሃ ኧረ ባኪ እስካሁን አብራቹ ስትጫወቱ ነበራ ታዲያ ማን አሸነፈ? ሃሃሃ>> ራቢ የሚያበሽቅ ሳቋን ለቀቀችው። ምንም መናገር ስላልፈለኩ ዝም አልኳት። እሷ ግን ምንም ልትረዳኝ አልቻለችም።
<<ኧረ ይሄ ነገር ምንድነው እእ? ሚስጥር ነው እንዴ እህቴ..>> አላስጨረስኳትም
<<ኡፍፍፍ አንቺ ደግሞ ችግር አለብሽ አትፋቺም! ዞር በይ በናትሽ .. >>
<<እህህ ኢብቲ በአላህ ምን ሁነሽ ነው?>> ድምጿ ይሰማኛል ላዳምጣት ግን አልፈለኩም።
<<ውዴ ወዴት ነው ጥድፊያው?>>ዩሲ ነበረች።
<<መጣሁ። እንዳትከተይኝ!>> ፈርታኝ <እሺ> ብላ እዛው ቀረች።ብቻዬን አንድ ጥግ ስር ቁጭ ብዬ ደቂቃዎች አለፉ። ልቤ መረጋጋት አልቻለም፤ ላስብ ብሻም ራሴን መሰብሰብ ግን አልቻልኩም። ከራሴ ጋር ስወዛገብ ጊቢው ጭር አለ። እኔም ወደ ክፍል ሄድኩኝ፤ ብዙ አልፎኛል መሰለኝ አስተማሪው እያረመ ነበር። ስገባ አላየኝም... ሄጄ ተቀመጥኩ። ወደ ኃላ ስዞር ማሂን አየሁት፤ መልሼ ዞሬ ተቀመጥኩ። ራቢ ፈርታኝ ፊቷን አዙራ ተቀመጠች። የመውጫ ሰዐታችን ደርሶ እስክንለያይ ድረስ ምንም ሳንነጋገር ተለያየን።
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስር
(ሂባ ሁዳ)
.
.
የስምንተኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና መፈተኛ ጊዜ ደርሰ፤ እንደ አጋጣሚ ረመዳንም አብሮ ገባ። የፈተናችን ቀን የጀመረው በረመዳን የመጀመሪያ ቀን ነበር።
.
የጠዋቱን ከተፈተንን በኃላ ለዙሁር ሰላት ወደ መስጂድ አመራን፤ ድባቡ ልዩ ነበር። ግማሹ ጥግ ጥግ ይዞ ቁርዐኑን ይቀራል ሌላው ደግሞ ሱና ሰላቶችን ይሰግዳል። ሰግደን ወደ ምንፈተንበት ትምህርት ቤት አመራን መንገድ ላይ እነ አቤላን አግኝተን ስንተራረብ ት/ቤት ደረስን። ከማሂ ጋር እንደበፊቱ ባይሆንም እናወራለን። እሱ በጣም ሊቀርበኝ ቢፈልግም እኔ ግን ከላይ ከላይ ነው የማወራው፤ በአገኘሁት ጊዜ ያኔ እያውራሁት ጥሎኝ የሄደው ቀድሞ ይታወሰኛል። እስካሁን ተናድጄበታለሁ፤ እሱ ግን ረስቶት መሰለኝ ኩርፊያውን ትቶ ምንም እንዳልተፈጠረ ያወራኛል።
የመጀመሪያ ቀን ፈተናችንን ደስ በሚል ሁኔታ አጠናቀቅን። ብዙዎች ቀላል ነው ብለዋል፤ አቤላ ከዘጠና በላይ አመጣለው ብሎ ይፎክራል። ከእኔ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነው የምንፈተነው ሙሉ መልሳችን አንድ አይነት ሣይሆን አይቀርም። ማሂ፣ ዩሲና ራቢ ግን ሌላ ሌላ ክፍል ነው የሚፈተኑት።
ከምንፈተንበት ትምህርት ቤት እስከምንማርበት ትምህርት ቤት ርቀት ቢኖረውም እያወራን ስለነበረ ሳይታወቀን ደረስን። ሁሉም በየአቅጣጫው ተበታተነ እኛም ስለ ነገው ፈተና እያወራን ሰፈራችን ስንደርስ ተለያየን።
*
ዛሬ ፈተናው ትንሽ ከበድ ይል ነበር፤ ግን እንደምንም የጠዋቱን ጨርሰን ወጣን። ከአቤላ ጋር ውጪ ላይ ቁጭ ብለን ስንዛዛግ ማሂና ባቢ መጥተው ተቀላቀሉን። ፈተናውን ስላልሰሩ ተናደዋል።
<<እና ፈተና እንዴት ነበር?>> እንዳገኘኋቸው ያቀረብኩት ጥያቄ ነበር።
<<አቦ ተይን ቀናችን አይደለም የሆነ ገገማ ፈታኝ ነበር ምንም አላሰራንም>> ባቢ ብስጭት ብሎ መለሰ።
<<ማሂ አንተስ አልሰራህም?>>
<<ባክሽ ከኃላ ላሉት አስኮረጅክ ብሎኝ ቀማኝ ያውም ሣልጨርስ በቃ>>
<<የከሰዐቱን ትሰራላችሁ። እእ.. አይዟችሁ እሺ...>> ሁለቱም አሳዘኑኝ አቤላም እነሱ ስላልሰሩ ደበረው።
<<አቦ በቃ እዚው ዱቅ እንበል ሙዳችን ተከንቶማ ወዴት እንቀየሳለን>> አቤላ ከአንዱ ዛፍ ስር ሲቀመጥ አብረውት ቁጭ አሉ።
<<ኢብቲ ነያ ተቀመጪ>> ባቢ እንድቀመጥ ተጠጋልኝ።
<<ኧረ መስጂድ ልሄድ ነው ባቢ..>>
<<እንዴ ምን ልትሰሪ?>> ማሂ በመገረም እያየኝ።
<<ሃሃሃ አንተ ደግሞ ልጫወት ልበልህ..>> አጠያየቁ ገርሞኝ እያየሁት።
<<ጀለሶችሽ መጡ>> አቤላ ወደነ ዩሲ እየጠቆመኝ። <<ደግሞ እዳትቆዪ አብረን እንገባለን>>
<<እሺ በቃ ቻው..>> ተሰነባብተናቸው ተለያየን።
*
ከነ ዩሲ ጋር መስጂድ ደርሰን ተመለስን። የመጨረሻውን ፈተና ለመፈተን ሁሉም ጓጉቷል መፈተኛ ጊቢ ጋር ስንደርስ ተማሪው ጢቅ ብሏል። ጭራሽ የሚገባው በፍተሻ ነው፤ ሰልፉ ደግሞ ረዘም ያለ ነበር። መጨረሻ ላይ እኛ ነበርን አቤላ መጥቶ ጠራኝና ከፊት ሊያስገበኝ እነባቢ ወደ ተሰለፉበት መሄድ ጀመርን።
<<እኔ ምልሽ ኢብቲ>>
<<ወዬ አቤላ>>
<<ከዛሬ በኃላ በቃ አንገናኝም ማለት ነው?>>
<<ኧረ ለምን? ውጤት ሲወጣ እንገናኛለን እኮ..>>
<<እስከዛስ አንቺም ጀለሶችሽም ስልክ የላችሁ ..ከነ ማሂ ጋ እኮ እያወራን ነበር እሱም ደብሮታል ልንለያይ መሆኑ...>>
<<እህ አቤላ...ዘጠኝም አብረን እንመዘገባለን አያሣስብም ኮ....>>
<<እሱማ አዎ ግን ያው...>> የምናወራውን ሳንጨርስ እነ ባቢ ጋ ደረስን << እነዚያው እነባቢ.. ነይ በዚህ ጋ>> ባቢ የሃይላንድ ሚሪንዳ እየጠጣ ነበር። አቤላን ሲያየው ለማሂ አቀበለው።
<<ኧረ አልሰማቹም ብትጨርሱት>> አቤላ ፈጠን ብሎ ወደ ማሂ ሲንደረደር፤ ማሂ ለአቤላ ወይስ ለባቢ ሊያዳላ ነው ብዬ የሚሆነው ስጠብቅ... ያላስብኩት ነገር ተፈጠረ።
<<እንዴ ማሂ!!>> ሚሪንዳውን የሚጠጣውን ማሂን አይቼ ከድንጋጤ ጋር ስጮህ ሶስቱም ወደኔ ዞሩ። መደንገጤን ሲያዩ መጨቃጨቃቸውን አቆሙና ማሂ ላይ አፈጠጡበት። ማሂ ግራ ገብቶት <<እእ ምን ሁነሽ ነው አስደነገጥሽኝ እኮ>> የተደፋበትን ሚሪንዳ እየጠራረገ ከኔ ምላሽ ይጠብቃል።
<<እህ በረመዳኑ ትጠጣለህ እንዴ! ፆመኛ ነሃ ረስተኸው ነዋ...>> አይን አይኑን ሳየው አንገቱን ደፋ። እነ አቤላ ዝም ብለው ፊት ፊታችንን ያዩናል።
<<እናንተ ልጁን አሳሳታቹታ...ሃሃሃሃ ቀልበ_ቢስ ሁላ። ማሂ በል ተጉመጥመጥ>> ማሂ ካቀረቀረበት ሲነሳ አይኑ በእምባ ተሞልቶ ነበር።
<<እህ ማሂ ምን ሆነህ ነው?>> ጥያቄን ሳይመልስ ከመሮጥ ባልተናነሰ መልኩ ከአጠገቤ ራቅ ብሎ ሄደ።
<<ምንድነው ባቢ ንገረኝ?>> ግራ እብደገባኝ በሚያሳብቅ አስተያየት።
<<ኧረ ምንም አላውቅም..>> ፊቱን አዞሮ መለሰልኝ።
<<አቦ ተናገር በናትህ ምንም እየገባኝ አይደለም ችግር አለ እንዴ? ማሂ ለምንድነው እንዲህ የሚሆነው?>>
<<እሺ ለሱ አትናገሪውም እእ ብንግርሽ? ማይልኝ..>>
<<ኡፍ ባቢ አዎ ተናገር...>> እስክሰማው ጓጓቻለው። ምን ይሁን? ማሂ ምንድነው ያልነገረኝ? ለምንስ ይፈራኛል? የራሴ ጥያቄ ነው።
<<ምን መሰለሽ ኢብቲ...>> ባቢ ንግግሩን እንዲቀጥል በጭንቅላቴ ምልክት ሰጠሁት።
<<ማሂር እንዳንቺ አይደለም>>
<<ማለት?>> ምንም ለማለት እንደፈለገ
አልገባኝም።
<<ስልሽ አለ አይደል... ምንም አያውቅም>>
<<ባቢ በግልፅ ንገረኝ። እሱ ህጻን አይደለም እኮ ምንድነው የማያውቀው?>>
<<ማሂሮ ኮ አይሰግድም፣ አይፆምም በቃ ስለ እምነታቹ ምንም አያርፍም... እንዳንቺ ቁርዐን ቤት ምንናምን እሱ ጋ ወፍ የለም! አላ በቃ ማወቅ ይፈልጋል፤ ግን ደግሞ የሚረዳው ሰው አላገኘም። አንቺ ደግሞ በጣም ጎበዝ ነሽ እኔ ከማውቃቸው.. እሱም ደግሞ ለዛ ነው አንቺን መቅረብ የሚፈልገው። ብዙ እንደምትረጂውና እንደምትለውጪው አምኖ ነበር። ግን አንቺ ልታዳምጭው አልፈለግሽም፤ ስለሱ እኮ ምንም አታውቂም። ሊነግርሽ ቢፈልግም መንገዱን ትዘጊበታለሽ፤ በፊት ሙስሊም ጀለሶች ነበሩን እነሱ ከማሳወቅ ይልቅ ሙድ መያዣ አደረጉት። ለምን? ባለማወቁ ምክንያት! ምንአልባት አንቺ ታስተካኪዋለሽ ብለን ነበር፤ ግን ምን ያረጋል...በቃ ምንም ነው ልትረጂው ያልቻልሽው... ኢብቲ እንደነገርኩሽ ካወቀ ያልቅልኛል። የነገርኩሽም አንቺም ሳታውቂ እንዳሁኑ በሞራሉ ከምትጫወጪበትና እሱም ባንቺ ቅስሙ ከሚሰበር ብዬ ነው። በቃ ሁሉንም ባላየ እለፊው አታስጨንቂው፤ በናትሽ አሁንም በቃ እያለቀሰ ነው የሚሆነው እስቲ ልየው...>> ባቢ ከአይኔ እስኪጠፋ በሄደበት መስመር ፈዝዤ ቀረሁ። ምንድነው የሆነው? እኔስ ምንድነው ያደረኩት? ምንድነው የሰማሁት? ሁሉም ድንግርግር አለብኝ። ጭራሽ ያልጠበቁት ነገር በአንዴ መዐት የወረደብኝ ያህል ከበደኝ። ከየት መጣ ያላልኩት እምባ ሂጃቤ ድረስ አበስብሶኛል። መሬትና ሰማዩ እየተሽከረከረ መሰለኝ፤ አይኔ ብዥዥዥዥ አለብኝ። ምን ያህል ደቂቃ እዛው እንደነበርኩ አላውቅም ብቻ አቤላ መጥቶ ፊቴን እንዳስታጠበኝ ትዝ ይለኛል። ከዛም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ምን ሁና ነው ብለው ሲጠይቁትም ይሰማኝ ነበር። አጠገቤ ቁጭ ብሎ አይዞሽ ምናምንም ሲለኝም ነበር።
ከደቂቃዎች በኃላ ተረጋጋሁ፤ ወደራሴ ስመለስ የማጠቁርበት እርሳሴን መፈለግ ጀመርኩ።
.
<<አቦ አስቦክተሺኝ ነበር እኮ...ሆ... ወይ አትናገሪ ወይ ነቃ አትዪ.. በስማም የሌለ ክብድ ብሎኝ ነበር ኮ። ባለቀ ሰዐት ጉድ ልንሆን? ዘጠና ብዬ ስጎርር ዘጭ ልታስብዪኝ!? ፈጣሪ ሆይ ተመስገን>> ብሎ ብርክክ ሲል ክላሱ ሁላ በሳቅ አጥለቀለቀው።
<<ሃሃሃ...አንተ በቃ ፈታ አልክብኛ? ኧረ ግን አቤላ ተቀየምኩህ>> እንደማኩረፍ ብዬ እያየሁት።
<<ማሪያምን ኢብቲዬ ጭንቅ ብሎኝ ነበር.. >>
<<ኧረ ፈታኙ መጣ>>
<<ስድስት ስድስት>> ሲል ሁሉም ተስተካክሎ ቁጭ አለ፥ ፈታኙ።
*
<<የዛሬው ደግሞ ከስከዛሬው ሁሉ ቀላል ነበር ደስ ሲል አ አቤላ? ደግሞ በጣም ቀላል..>> ከመፈተኛ ክፍል ወደ ውጪ እየወጣን።
<<ኧረ ምን አውቄ.. ቀለሜዋ አንቺ ..ብቻ ላጥ ላጥ ስታረጊው እኔም ከስር ከስርሽ ኮፒ አደረኩልሽ>> ደስ እንዳለው ከፊቱ ላይ ይነበባል።
<<ደግሞ ማንም አልወጣም እኮ... አባቴ.. ቸኮልን መሰለኝ>> ዞር ዞር ስንል ከሁለታችን ውጪ ማንም አልነበረም።
<<እና የዛሬው ፈተና ኮ ያንቺ ስለሆነ ነው። ቲቸር ራሱ ባይሎጂን ከኢብቲሳም ገልብጡ አልነበር ያለው? አንቺና ባይሎጂ ኮ በቃ ቤተሰብ ሆናችሁዋል።>>
<<ሃሃ አንተ ደግሞ አታመሳስል እኮ.. ስማማ... ማሂ ና ባቢ ሰርተው ይሆን?>>
<<ኧረ እንጃ በናትሽ፤ ካልሰሩ የመጭ ነው ሚደብረኝ... ደግሞ ማሂሮ ሲገባ ከፍቶት ስለነበረ ተረጋግቶ የሚሰራም አይመስለኝም።>> እንዲሁ እየተነጋገርን የተወሰኑ ተማሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ከተማሪው መሃል ባቢ ወደኛ መጣ።
<<እእ እንዴት ነበር ተሰራ?>> አቤላ አይን አይኑን እያየ ይጥይቃል።
<<ባክህ ያው ነው ትንሽ ነው የሰራሁት..>>
<<እና ብራዘርስ እየሰራ ነው..?>>
<<ማ? ማሂሮ? እሱኮ ሄደ>>
<<ወዴት?>> ሁላታችንም ሳናስበው ጮክ ማለታችን አስደንግጦት
<<እህህ... ቀስ በሉ፤ እቸኩላለው ብሎ ላጥ አለ። ምንም አላናግር ብሎኝ ሄደ ወዲያው እንደወጣን...>>
<<በቃ ቻው እሺ>> ብዬ እኔም ትቻቸው ሄድኩ። አቤላ ቢጠራኝም እየፈጠንኩ በሌላ አቅጣጫ ሄድኩ። እነዩሲ ሲመጡ በነኢክሩ ሰፈር አድርገን ሄድን፤ ሁላችንም ደብሮናል። እንደ ሌላው ቀን ፈታ ብለን ማውራት አልቻልም። ያው ትምህርት ከተዘጋ ሁሌ ስለማንገናኝ አብረን ስለ ማንውል እንጂ መድረሳ ለአጭር ሰዐት እንገናኛለን፤ ግን እንደ ልብ የምናወራበት ሰዐት አናገኝም። እሱን እያስብን ለመለያየት በቆምንበት መንገድ ላይ ብዙ ከቆየን በኋላ እንደምንም ተቃቅፈን ተለያየን። እኔና ዩስ እሰከ ሰፈር አንድ ላይ ብንጓዝም በሃሳብ ግን ሁለታችንም ለየብቻ ነበርን።
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስራ አንድ
(ሂባ ሁዳ)
.
.
እነ ዩሲ በር ጋር ደርሰን ሁለታችንም ቆምን። እኔ ዝም ብያት ወደ ቤታቸው ስገባ ተከተለችኝ፤ ሳሎን በግማሽ በኩል በተነጠፈው መጅሊስ ላይ ዘፍ አልኩ። ዩስሪ ከደቂቃዎች ቡኃላ ልብሷን ቀያይራ አጠገቤ ቁጭ አለች፤ ዝም ብላ እኔ እስክነግራት ትጠብቃለች። ሁሌም በከፋኝ ሰዐት እነሱ ቤት ሄጄ ነው የሚወጣልኝ... ሁሉንም ዝርግፍግፍ አድርጌ እነግራታለሁ። ከኔ በላይ እሷ ትጨነቃለች፤ ዛሬ ግን ዝምታዬ በዛባት መሰለኝ ለማውራት ተገደደች።
<<ኢብቲዬ ሀቢብቲ ምንድነው የሆንሽው? ቅድም ጀምረሽ ልክ እንዳነበርሽ እኮ አውቃለሁ፤ ብቻችንን ስንሆን እናወራለን ብዬ ነው ዝም ያልኩት>> ምንም ሳልመልስላት ስቀር አላስቻላትም ድጋሚ ሌላ ቃላት ሰነ ዘረች... <<ማሂ ነው አይደል? እንዲ ያስከፋሽ.. እእ ኢብቲ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ በአላህ እያስጨነቅሽኝ ነው>>
<<ዩሲ እሱኮ ምንም አላደረገም እኔ ነኝ እንጂ የጎዳሁት። ልቡን ስብርብር ነው ኮ ያደረኩት ምን አይነት ልጅ ነኝ!? አመት ሙሉ አጠገቤ ከችግሩ ጋር ሲታገል የነበረን ሰው እንዴት እገፋዋለሁ?...ዩሲ ንገሪኝ እስቲ ምን አይነት ግዴለሽ ሰው እንደሆንኩ..>> በመሃል ትንፋሼ መቆራረጥ ጀመረ፤ ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልኩም። ዩሲ አቅፍኝ ማልቀስ ስትጀምር ይባሱኑ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ሰዐቱ ወደ መምሸት ሲጠጋጋ ፊቴን ታጥቤ ወደ ቤት ገባሁ። ወንድሜ ፈተና ያልሰራሁ መስሎት ቢጨነቅም ትንሽ እንደደከመኝ ተናግሬ ከኢፍጣር ቡኃላ ወደ መኝታዬ ሄጄ ከራሴ ጋር ብዙ ተጨቃጨቅኩ። ከረጅም የድካም ሰዐታት በኃላ እንቅልፍ አሸለበኝ።
*
*
ከሁለት ወራት ቡኃላ የሚንስትሪ ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተሰብስበናል። ከረጅም ጊዜ የናፍቆት ወሬ በኃላ ተማሪዎቹ ውጤት ለመቀበል ተሰለፉ፤ እኛ መጨረሻ ላይ እንቀበላለን ብለን ጥግ ላይ ቁጭ አልን። እነ አቤላ ተሰልፈዋል እሱ ዘጠና አመጣለሁ ብሎ አሲዟል፤ ባቢም ከኃላው ነበረ፤ ማሂን ግን አላየሁትም። ዛሬ ደግሞ በጣም እፈልገዋለሁ... ብዙ ነገር ላወራው ተዘጋጅቼበት ነው የመጣሁት፤ በዛ ላይ ናፍቆኛል። ባቢ ጋር ሄጄ ስጠይቀው እንደማይመጣ ነገረኝ። ለምን ምናምን ሣልል ቀጥ ብዬ ስሄድ ከኃላ ሂጃቤ ሲጎተት ለማስለቀቅ ዞር ስል በአየሁት ነገር ድንግጥ አልኩኝ <<ኢብቲዬ>> ብሎ እጁን ሲዘረጋ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ስጠጋው እቅፍ አደረገኝ፤ ምናልባት መተቃቀፋችን የመጀመሪያም የመጨረሻም መሰለኝ... ትንሽ እንደቆየን ድንግጥ ብዬ ከእቅፉ ወጣሁ።
<<እእ ይቅርታ ሳላስበው ነው...>> እንደመሳቀቅ ሲል አሳዘነኝ።
<<ኧረ ችግር የለውም ማሂ ...>>
<<እና ደህና ነሽ? እንዴት ነሽ ተጠፍፋን ኣ?>>
<<አለሁ አልሃምዱሊላህ አንተ እንዴት ነህ እእ ሁሉ ሰላም ነው?>>
<<አዎ ሰላም ነው። ደግሞ ረፍቱ ተስማምቶሻል እእ አምሮብሻል..>>
<<ሙድ አትያዝብኛ አንተ ነህ ያማረብህ እኮ...>>
<<ሃሃሃ ኧረ ባክሽ... ስገባ እኮ ሳይሽ ወዳንቺው መጣሁ፤ ጀለሶችን አላገኘዃቸውም ከመጣሽ ቆየሽ እንዴ?>>
<<ኧረ እዛ ጋር ተሰልፈዋል። አንተን ፈልጌ እኮ ባቢ አይመጣም ሲለኝ ወደዚህ ስመጣ ነው ያገኘሁህ አላወቁም መሰለኝ
እንደምትመጣ...>>
<<ኧረ ያውቃል ሊያዝግሽ ፈልጎ ነው ይሄ ዱዝ..እና ፈልገሽኝ ነው እእ?>> ፊቱ ላይ ፈገግታ ሞላ ሞላ ብሏል።
<<አዋ! ማሂ እፈልግሃለው ..እንዲ ቁመን አይደለም በቃ እንጨርስና እናወራለን።>>
<<ኧረ ደስ ይለኛል..በቃ እነ ባቢ ጋ ልሂድ እስኪ ..>> ፈጠን እያለ ወደ ተሰለፉት ልጆች አመራ። እሱ ወዳዛ ሲሄድ እነኢክሩ ወደኔ መጡ። ኢክራም ቸኩላ ሰለነበረ ካልተቀበልኩ ብላ ሄድን፤ እኔ ግን ፈራሁ። ውጪ ላይ ቆሜ እነሱ ገቡና እየሳቁ ወጡ እንደምታልፍ እርግጠኛ ነበርኩና ጥምጥም አልኩባት፤ ወዲያው ሸኝተናት ተመለስን።
*
እነ ባቢ ለመቀበል እየገቡ ነበር እኔን ሲያዩ ቆም አሉ፤ እኔም ወደነሱ ሄድኩ። <<ባቢ ምነው? እእ..>> ሶስቱም የተጨነቁ መሰለኝ።
<<ኢብቲ ሁላችንም እናልፋለና? ፈራን እኮ..>> አቤላ ቀጠለ
<<እኔ እኮ ምንም አልመሰለኝም ነበር ኡፍፍ አሁን ግን እነዚህ አንቦቆቦቁኝ>> አቤላ እንዲህ ማለቱ አስገርሞኛል።
<<አቦ ፈታ በሉ እናልፋለን። አሁን ግቡ በቃ..>>
<<ኢብቲ አንቺ ለምን አሁን አትቀበይም ነይ አብረን እንግባ እእ..>> ማሂ።
<<አይ ቀስ ብዬ እቀበላለው እስቲ የአቤላንም ልየው። ያው አንዳይነት ነገር ነው እኮ ውጤታችን የሚሆነው...>>
<<በናትሽ ነይ አብረሽኝ ..እንደውም የቅድሙን አሁን እናውራና በኃላ አብረን እንቀበላለን እእ..>>
<<ኧረ አያሣስብክ እሱ ይደርሳል ..>>
<<እኔ ግን አሁን ብናወራ ይሻለኝ ነበር..ደግሞ አሁንም ስልክ የለሽማ?>>
<<አዎ ምነው? ልትገዛልኝ ነው? ሃሃሃሃ>>
<<የኔን ውሰጂው እኔ ኮ ሌላም አለኝ እቤት ...ሲሙን ላውጣውና ስልኩን ይዘሽው ትሄጃለሽ በቃ እሺ..>>
<<አንተ ደግሞ አታምርራ .. እኔ እኮ ቀፎ ስለሌለኝ አይደለም እቤት አይፈቀድልኝም። ገና በስምንተኛ ክፍል ነው የምባለው..>>
<<እንዳዛ ከሆነ እሺ፤ ግን እኮ ቁጥሬ ራሱ የለሽማ? ነይ ልፃፍልሽ ..>>
<<በኃላ ትሰጠኛለህ ኧረ ግባ እነ ባቢ አስጠበካቸው እኮ..>> እሺ ብሎ ወደ በሩ አመራ። በሩ ጋር ሲደርስ ዞር ብሎ አየኝ፤ በጣም ፈርቷል። አስተያየቱ አሁንም አይኔ ላይ አለ። ርቆ እንደሚሄድ ሰው ፍዝዝ ብሎ ነበር፤ እንዲገባ በአይኔ ምልክት ስሰጠው ገባ።
*
ከነ ራቢ ጋር ባቢ ማሂ ና አቤላ ስንት እንደሚያመጡ እየገመትን፤ የሶስቱንም ግምት ያገኘ ሎሊፖፕ እንደሚገዛለት ተስማምተን እስኪወጡ ዛፍ ስር ቁጭ ብለን መጠበቅ ጀመርን። ከደቂቃዎች ነኃላ የሆነች ልጅ እያለቀሰች ስትወጣ ደንግጠን ወደ በሩ ሄድን። ወደ ዘጠነኛ ክፍል ስላላለፈች ወደ አንዱ ጥግ ሄዳ ማልቀሷን ቀጠለች። ፍርሃታችን ይባሱኑ ጨመረ፤ ራቢ እጄን ጭምድድ አድርጋ <<ኧረ ፈራሁ እኛስ እናልፋለን ወይይ?>> አለች።
<<እንጃ አላውቅም። ራቢ እነ ማሂ ለምን ቆዩ?>> ዩሲ ነበረች በር በሩን እያየች። ወዲያው ማሂ እየሮጠ ወጣ ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ በፍጥነት ወደሱ ስሄድ እነ አቤላም ከኃላው እየሮጡ መጡ። እሱ ጋር ከመድረሴ በፊት ወደ ጊቢው መውጫ እየፈጠነ መራመዱን ቀጠለ ከኃላ ባቢ ቢጠራውም ሊቆም አልቻለም።
እንደምንም ልደርስበፍት ሁለት እርምጃ ያህል ሲቀረኝ የጊቢውን በር በእግሩ ጠልዞ ወዲያው ወጣ። ተከትዬው ብወጣም እሱ ላይ መድረስ አልቻልኩም። ብጠራውም እጁን እያወናጨፈ ርቆ ሄደ። እኔም ባለሁበት ከአይኔ እስኪጠፋ ተከተልኩት። እነ ዩሲ መጥተው ወደ ውስጥ ገባን አቤላና ባቢ ተመልሰው መጡ።
<<በናትሽ ማሄሬ ኮ ወደቀ በአንድ ነጥብ ቲሽሽሽ ብሽቅ ነው ያኩት>> አቤላ ተናዶ ያወራል፤ ሌላው ዝም ብሎ ቁጭ ቁጭ ብሏል። ዛሬም ያልሆነ ስህተት ሰራሁ፤ ምን አለ መጀመሪያ ብናወራ እሱም እናውራ ሲለኝ እሺ ብለውስ? በቃ ሁሌ የራሴን ሃሳብ ብቻ ነው የምፈፅመው። ለዛሬ እንኳን እሱን ብሰማውስ እንዴት ከስህተቴ አልማርም? እሺ ካሁን ቡኃላ የት ነው የማገኘው? ጭራሽ ስልኩ ቁጥሩን ሲሰጠኝም አልተቀበልኩትም! ኧረ ኢብቲሣም ምንድነው ያደረግሽው? የነበረኝን አንድ እድል ባልሆነ መንገድ አጣሁ እኮ። ሁለት ወር ሙሉ ስጠብቀው የነበረው ቀን በአንዴ እንዲህ ምንም ሳላደርግ ሊያልፈኝ ነው እንዴ? እነዚያ የባከኑ ቀናቶችን በዛሬ አስተካክላው ብዬ ምንም ሳላደርግ እንዲሁ ባክነው ቀሩ ማለት ነው?
.
<<ኢብቲ ተማሪው እኮ ተቀበለ እኛ ብቻ ቀረን እእ እንቀበል በቃ ቁርጣችንን እንወቀው>> ራቢ ከገባሁበት ሃሳብ መለሰችኝ እሺ ተባብለን ለመቀበል ተስማምተን ወደ በሩ ጋ ስንደርስ አቤላ እየወጣ ተገጣጠምን የውጤቱን ካርድ ሳይ ልቤ ምቱን ጨመረብኝ።
<<እእ አቤላ እ.ን.ዴ.ት ነው..>>
<<አቦ ተይኝ እኔ ደግሞ አልፋለው ማለቴ ድሮም ካንቺ ሰርቼ>>
<<ማለት?>> ዩሲ ደንገጥ ብላ ወረቀቱን ለማየት ስትጠጋው።
<<ቲ! ያው ናችሁ። ምን የወደኩበትን ለማየት ምን አስቸኮለሽ ዞርበይ ከዚህ ሲያስጠሉ>> ሶስታችንንም ገልመጥ አድርጎ አየን።
<<በናትህ አቤላ ንገረኝ ወደቅን ነው የምትለኝ? ድምፄ ከፍ እያለ መጣ።>>
<<አቤላ አትበይኝ ዱዝ! አቤል ነው ስሜ። አው እንኳን ደስ አለሽ እኔ ወደኩኝ ከሌላው ብሰራስ አንቺን አምኜ ሙሉ ካንቺ መስራቴ..>> ከዚህ በላይ አልሰማሁትም፤ እየተቻኮልኩ ወደ ቢሮው ገባሁ
<<ይቅርታ የኔን ወረቀት ..>>
<<እንዴ ኢብቲሳም የት ጠፍተሽ ነው እስካሁን?>> ባይሎጂ አስተማሪያችን ስሜን እየፈለገ። <<እሲቲ ቁጭ በይ እስከዛው>> እንድቀመጥ ጋበዘኝ። ቢለኝም እዛው መቆምን መረጥኩ... እስኪያገኘው ጨነቀኝ። አንድ ወረቀት ነጥሎ እንደያዘ።
<<ምን ነክቶሽ ነው ግን ምን ሁነሽ ነበር?>>
<<ማለት ቲቸር? መቼ?>> ግራ እየተጋባሁ ጠየኩት ...
<<መቼ? ለፈተናው ነዋ። ጥሩ ጎበዝ ልጅ አልበርሽ እንዴ? በአንዴ ምንድነው እንደዚህ የቀየረሽ>> አስተማሪው አፈጠጠብኝ <ምነው ባልገባሁ> አልኩኝ በውስጤ።
<<ቲቸር ም.ን.ድ.ነው እ ውጤቴ?>> የሞት ሞቴን ጠየኩት።
<<እኛማ ብዙ ተስፋ የጣልንብሽ ልጅ ነበርሽ፤ የትምህርት ቤቱንም ስም ታስጠሪያለሽ ብለን ጠብቀን ነበር አዝናለሁ ኢብቲሳም። አሉኝ ከምላቸው ዋነኛዋ ተማሪ እንዲህ አልጠበኩም ነበር አፍሬብሻለው...>> አይኖቼ በዕንባ እየተሞሉ ልቤ ምቱን ላይ በላይ ሲደጋግመው በሰማሁት ነገር ልዘረር ምንም አልቀረኝም።
<<እና ወ.ድ.ቀ.ሻ.ል ነው..>>
<<በሚያሳዝን ሁኔታ አዎ>> በተቀመጠበት ወንበር ወደ ኃላ ለጠጥ ብሎ እየተቀመጠ የምሆነውን ያያል።
በምን ሃይል እንደሆነ ባይገባኝም ወረቀቴን ስጠኝ ብዬ ጮኽኩበት። በር አካባቢ የነበሩት ዩሲና ራቢ ገቡ። እሱ ከቦታው ሳይንቀሳቀስ..
<<ብሰጥሽስ ምን ያደርግልሻል>> ብሎ የሹፈት ፈገግ አለ። እነ ራቢ ደንግጠው እርስ በርሳቸው ይተያያሉ። ይባሱኑ ብሽቅ አልኩና <<ወረቀቴን ስጠኝ ብወድቅስ ምን አገባህ>> ብዬ ከእጁ ላይ መንትፌው ወደ ውጪ ወጣሁ። ራቢ ተከትላኝ ወረቀቱን ተቀበለችኝ፤ ራቢ ለዩሲ <<ነይ! ነይ!ቶሎ በይ>> ስትል ዩሲ ምንድነው ብላ ራቢ ጋር መጣች። እኔ መቆም አቅቶኝ ከዚህ ወደዚያ እሽከረከራለሁ፤ በመሃል ራቢ <<የስሥሥሥሥሥሥሥሥ>> ብላ ስትቀውጠው ከዩሲ ጋር ተቃቀፉ።
<<ኢብቲ ነይማ አፍጥኝው>> ብላ ወደኔ መጣች። እጇን ወረቀቱ ላይ እየጠቆመችኝ ትስቃለች፤ 96 ይላል ፁሁፉ።
<<እእ.. ደስ ይላል ራቢ። ያንቺ ነው የዩሲ?>> ብዬ ሁለቱንም አፍራርቄ ሳይ ይስቃሉ አብራቼው ፈገግ ለማለት ስሞክር
<<ኢብቲ እይማ>> ብላ ድጋማ ከወረቀቱ ላይ ሌላ ነገር አስነበበችኝ። <ኢብቲሳም ማህሙድ> ይላል።
<<ማለት?>> ሁለቱም ላይ አፈጠጥኩባቸው።
<<ያንቺ ኮ ነው 96 የኔ ውድ ነቀነቅሽው ኮ!>> ብላ ጥምጥም ስትልብኝ ደግሜ አየሁት ዩሲም ተጨመረች። በመሃል <ሰርፕራይዝ> ሚል ድምፅ ሰማን። ዞር ስል አቤላ እየሳቀ ነበር፤ እኔ አልፌ እሱ መውደቁ ትዝ ሲለኝ ወረቀቱን ለራቢ ሰጥቻት ወደሱ ሄድኩ፤ <አቤላ..> ስለው ምንም ሣይመልስልኝ ወረቀቱን ሰጠኝ የማየውን ማመን ስላቻልኩ እሱን አየሁት <<አዎ ነቀነቅነው 92>> ብሎ ሳቀ
<<ውይኔ ደስ ሲል>> ብዬ ስጮኽ <<ተጫወትንብሻ ከቲቸር ጋ!>> ብሎ ከት ብሎ ሳቀብኝ። ብሽቅ አልኩና ልመታው ማሯሯጥ ጀመርኩ።
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስራ ሁለት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
ከአቤላ ጋር ቁጭ ካልን በኃላ ..ምን አለ የማሂም እንዲሁ ቀልድ ነው ብላችሁኝ ደስታዬ ሙሉ ቢሆን እያልኩ አስባለሁ። እነ ዩሲም ምርጥ ውጤት ስላመጡ በጣም ደስ ብሏቸዋል። ሶስታችንም የትምህርት ቤቱ ሰቃይ ሆነናል። እኔ ግን ልቤ ላይ ሌላ ጭንቀት አለ እሱም ማሂር ነው። በቃ በአንድ አጋጣሚ ተገናኝተን በሌላ አጋጣሚ ተለያየን ማለት ነው? እኔ ግን እጣፈንታን ተቀየምኳት.. ራሷ አገናኝታን ራሷው አለያየችን። አሁን ማሂር ምን ይሁን የሚሆነው..
<<ኢብቲ ማሂ ስለወደቀ ከፋሽ አ? እኔም ደብሮኛል የሌለ አብሬው ብወድቅ ነው ያልኩት>> አቤላ እንዲህ ሲለኝ ስለ ማሂ እያሰብኩ ስለነበረ ደነገጥኩ።
<<አዎ አቤላ አሳዘነኝ.. ሁኔታውን አይተኸዋ። እኔ ምልህ እስቲ ስለ እሱ ንገረኝ... ፋሚሊዮቹ ምን አይነት ናቸው?>>
<<አይ ስለወደቀ እንኳን አይቆጡትም አያሣስብሽ..>> የጠየኩት ጥያቄ የገባው አልመሰለኝም።
<<ሣይሆን አላይደል እምነታቸው ላይ...>>
<<እእ እሱን ነበር እንዴ የጠየቅሽኝ... አንድም እኮ የጓዳው እሱ ነው። ለዛ ነው ቶሎ ሆድ የሚብሰው፤ ሰውም ብዙ የማይቀርበው እንዳያጣ ስለሚፈራ ነው። ኡፍፍ ብራዘር ምርጥ ልጅ ኮ ነበረ>>
<<ማለት አቤላ ቤተሰቦቹ ላይ ችግር አለ? ማለቴ አይስማሙ?>>
<<ሣይሆን እናቱ ከሞተች ቆየት ብሏል። ያኔ ጩጬ ነበር፤ ፈታ ብሎ ነበር የሚያድገው። እናቱ ከሞተች በኃላ ነገራቶች ተቀየሩ ፋዘሩም ሌላ ሚስት አገባና ከአዲሱ ሚስቱ ጋር እምነቱን ቀየረ፤ በፊት ኮ ምርጥ ሼኪ ነበር ይባላል። በቃ ማሂሬም ትምህርት ቤት ብቻ አስገብተው ላሽ አሉት፤ ግን ፋዙካው የሌለ ነው የሚወደው። እንዲከፋው ምናምን አይፈልጉም ግን የሚፈልገውን አላሟሉለትም። አለ አይደል ከመሰረታዊ ነገር ውጪ እሱ በጣም የሚያስጨንቀው እምነቱ ነበር። በፊት ብዙም አያርፍም ነበር ሲቆይ ሲቆይ ግን የሌለ ይሸምመው ጀመረ። አብሶ ሙስሊሞችን ሲያይ ሽምቅቅ ነው የሚለው፤ አንዳንዴ ምን እንደሚሉት አይገባውም። ከነርሱ ጋር እንደፈለገ ፈታ ብሎ አያወራም፤
ምክንያቱም እነሱ ከሚያውቁት ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ሲጠይቃቸው ደግሞ <እንዴት አታውቅም ለስሙ ሙስሊም ነህ> ብለው ሙድ መያዣ ያደርጉታል። ለዛም ነው ከኔና ከባቢ ጋር ብቻ የምታይው፤ እኛ ከድሮም አብረን ስለተማርን ሁሉንም ነገር እናውቃለን። ምንም አንደባበቅም.. በቃ እኔ ማሂሮ የመጭ ነው የሚያሳዝነኝ፤ የሌለ ምርጥ ልጅ እኮ ነው በናትሽ። አንድ ጥሩ ሰው ቢገጥመው እኮ የሌለ ደስተኛ መሆን ይችላል።>>
<<አቤላ እኔ ግን ምን አይነት ሰው ነኝ? እንዴት ምንም ማድረግ ያቅተኛል..>>
<<ኢብቲሣም ምንአልባት ከዛሬ ቡኃላ አንገናኝም ይሆናል ከመለያየታችን በፊት ግን ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ ...>> አቤላ እጁ ላይ ያለውን ክር እያሽከረከረ ንግግሩን ቀጠለ።
<<ኢብቲ በመጀመሪያ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም ልረሳው አልችልም። ለኔ ሁላችሁም ምርጥ ነበራችሁ፤ ትለዩብኛላችሁ። ሁሌ አብረን ብንሆን ምነኛ ደስ ባለኝ ግን መለያየት ልክ እንደመገናኘት ነው ፈልገሽ ሣይሆን መሆን ስላለበት ብቻ የሚሆን። እና ደግሞ ኢብቲ ሁላችንም እናከብርሽ ነበር ባቢም ማሂሮም ስለሌሉ እነሱንም ሁኜ ነው የምነግርሽ። በተለይ ለኔና ለባቢ በጣም ለውጠሽና፤ ብዙ ነገሮችን እንድናይ ረድተሽናል። የሰው ክብር ከምንም በላይ አሳውቀሽናል። ብቻ ብዙ ነገር.. ታዲያ ግን ይሄን ለኛ ባደረግሽ ጊዜ ካንቺ ሌላ ነገርን ጠብቀን ነበር። መጠበቅ ብቻ ሣይሆን ታደርጊዋለሽ ብለን ነበር..ግን ምን ያደርጋል፤ አንዳችን አርፍደናል አልያም ዘግይተናል። መቼስ ገብቶሻል አይደል? ስለ ማሂር ነው። በጣም እንድትቀራረቡ ከባቢ ጋር ብዙ ነገር ፈጣጥረን ነበር። እንድታወሩ ብዙ አጋጣሚ መሳይ ነገሮችን ስንፈጣጥር ነበር። የኛ ልፋት ውጤቱ ላይ ሳይደረስ ቀረ። ለምን? አንድም ማሂር ፈሪ ስለሆነ፤ ከዛሬ ነገ አወራታለሁ ሲል። ሌላው ደግሞ ያንቺ ትኩረት አለመስጠት ነው። እንዴ ኢብቲ ብዙ አጋጣሚዎች ላይ እኮ ማሂ ስለእምነቱ እንደማያውቅ ካንቺ መማር እንደሚፈልግ ነግሮሽ ነበር። ግን አንቺ ሁሌ ቀልድ እየመሰለሽ ታልፊዋለሽ። ከዛሬ ነገ ቀኑ እየሄደ ሲመጣ ማሂር ሁሉንም እንዲነግርሽ በግድ አሳምነን ላክነው። ግ'ና ምን ያደርጋል..እቸኩላለው ብለሽ ልታዳምጭው ፍቃደኛ አነበርሽም፤ ሌላ ስብራት ፈጠርሽበት። ትዝ ይልሻል አይደለ? ከቀናት በአንዱ ቅዳሜ ቀን ነበር። የዛኔ ያየሁትን የማሂን ተስፋ ማጣት ምንም ላይ ደግሜ የማየው አይመስለኝም። ሁላችንም ባንቺ እምነት ነበረን፤ ነገራቶችን ታስተካኪያለሽ ብለን... ደግሞ እኔ ወይ ባቢ ከምንነግርሽ ራሱ ቢነግርሽ እንደሚሻል አስበን ነው። ብቻ ኢብቲ አውቃለሁ፤ በጣም ጎበዝ ልጅ ነሽ፤ በትምህርትም በእምነታችሁም። እኔ በአስራ አራት አመቷ ወንድ አልጨብጥም የምትል ሴት ካንቺ ውጪ አላውቅም። በዛ ላይ በጣም ተግባቢም ልጅ ነሽ። ግን አንድ ነገር ይጎልሻል፤ ሰዎችን ማድመጥ፣ በዙሪያሽ ላሉት ትኩረት መስጠት.. ይሄን ባህሪሽ በናትሽ እንደምንም አስተካኪው። ድጋሚ የማሂን አይነት ሰው ትኩረት እንዳትነፍጊ። ኢብቲ የምር በጣም አመሰግናለሁ። ያው እኔ ከባቢ ና ማሂሮ ተለይቼ ያለፍኩት ካንቺ ስለሰራሁ ነው። የዛሬውን ቀን እንዲ አልጠበቅናትም ነበር። ከነ ማሂሮ ጋር ፈታ እንላለን ብለን ነበር አልሆነም። የስምንተኛ ክፍል ላይፍ ለኔ ከየትኛውም የትምህርት ቤት ላይፍ በላይ ነው። ፈጣሪ መልካሙን ያድርግልን፤ ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ እንገናኝ ይሆናል።>> ከተቀመጠበት ተነሳ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ አላውቅም... አቤላ እንዲህ ቁም ነገራቶችን ያወራል ብዬ አልጠበኩም ነበር። እኔም ተነሳሁ።
<<ቻው ኢብቲ በቃ>>
<<አቤላ..>>
<<ወዬ>> ፊቱን ሙሉ ለሙሉ ወደኔ አዞረ።
<<በጣም ይቅርታ ስለሁሉም..>> ታምቆ የተያዘው ዕንባዬ ቀደመኝ። እኔ ከዕንባዬ ጋር ስታገል አቤላ እየሮጠ ወደ በሩ ሸሸ። ከአቤላ መሸሽ ጋር የኔም ህልምና ተስፋ ላይመለስ አብሮ ሸሸ፤ ፀፀቱ እኔው ጋር ቀረ።
.
አንድ አመት ሙሉ ከኔው ጋር እየዋለ ለሚሄድ፤ በየቀኑ ከጎኔ ለማገኘው.... ተስፋውን በኔ ላይ ጥሎ መሰበሩን ለሚያሳየኝ ሰው.... መጠገን ትቼ ተስፋውን ገደል መክተቴ... ምን ያህል የባከኑ ቀኖች.... ከኔ ጋር እንደነበሩ አሁን ገባኝ ....ቢገባኝስ ምን ሊፈይድ... ከነስብራቱ ተስፋውን ጥሎ... ማሂሬ ሄደ እኮ!..
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን 💔 😥
በዘመኑ ፍጻሜ የኡለማዎች ሞት ይበዛል፤ ጅህልናም ይስፋፋል፡- “አላህ እውቀትን ከሰዎች ነጥቆ አይቀማም ነገር ግን ኡለማዎችን በመውሰድ ዕውቀት እንዲነሳ ያደርጋል።አንድም አሊም በማይተውበት ጊዜ ፣ ሰዎች አላዋቂ መሪዎችን ይወስዳሉ፣ ከዚያም ይጠየቃሉ ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፣ ተሳስተው፣ ያሳስታሉ።

ሼይኽ ሰዒድን ዛሬ ሸኝተናል 💔💔 ነገ ተራው የኛ ነው...አላህ በጀነቱል ፊርደውስ ይቀበላቸው 🤲

@Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስራ ሶስት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
(ከአምስት አመታት በኃላ)
*
*
<ምንም የምወደውም የምጠላውም ነገር የለኝም። የወደድኩትን ጠልቼ፣ የጠላሁትን ወዶጄ ተምታቶብኛል። ማንንም ስለማልወድ ሌሎች እኔን አይወዱኝም ብል፤ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ማለት ይቻለኛል?> የዛሬው የፌስቡክ ጥያቄዬ ነው።
.
ዛሬ ቀኑ ድብልቅልቅ ብሎብኛል፤ ምን እያሰብኩም ሆነ እየሰራሁ እንደሆነ ራሱ አልገባኝም። ለዛም ነው በደመ ነፍስ እንዲህ ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ የወጣሁት... ምን አልባት ሰሞኑን እቤት ስለዋልኩ ተጫጭኖኝ ይሆናል ብዬ ወጣ ለማለት ወሰንኩ። ከሰፈሬ ስወጣ ወደ ዊንጌት ታክሲ ለመያዝ አስፋልቱን ለመሻገር ከፊት የሚመጣ መኪና ለማየት ዞር ዞር ስል አንድ የማውቀው የሚመስል ሰው ፊት አየሁ። ከብዙ ሰው ጋ ተመሳሰለብኝ ወደ እሱ እየቀረብኩ ስመጣ ግን ልቤ ምቷን ከእርምጃዬ ጋር ጨመረች።
*
<<ይ..ቅር.ታ አ..ቤ..ላ..ማለቴ አቤል?>>
<<እንዴ እንቺ! በፈጣሪ ኢብቲሳም ነሻ>>
<<እእ አዎ ወዬኔ ግን እንዴት ነህ በአላህ?>>
<<አለሁልሽ... በስማም! በሂወት ግን አለሽ ኢብቲ? ተዐምር ነው የሆነብኝ..>>
<<በጣም ተቀይረሃል። ትልቅ ሰው መሰልክ እኮ ፂም ምናምን እየሞካከርክ ነው.. ሃሃሃሃሃ>> ፊቱ ላይ ጣል ጣል ያሉትን ፀጉሮች እያየሁ ሳኩበት።
<<እና አሁንማ ግብዲያ ሆነናል አንቺ ራሱ.. አይ ግን ለኔ ምንሽም አልተቀየረብኝም። ነይ እንግባ ቦታ አለ..>> ሁለታችንም ገቢና ገብተን ማውራታችንን ቀጠልን።
<<እና ከየት ወዴት ምናምን በናትሽ እስቲ አውሪኝ>>
<<እኔ ከሰፈር ወደ ጓደኛዬ ሰፈር እያሄድኩ ነው ..አንተስ..>>
<<ጓደኛ ስቲ.. እነዛ ሁለቱ ደህና ናቸው? በናትሽ ማን ነበር ስማቸው?..ያቺ እብዷ ..ራቢያ ነበረች መሰለኝ>> ፊቱን ጭምድድ እያረገ።
<<ሃሃሃሃ አሁንማ እብድ አደለችም። እእ ደህና ናቸው በአምስት አመት ውስጥ አለመርሳትህ ሲገርም..>>
<<ኧረ እንዴት ይረሳል ..ከማሂሮ ጋር እኮ በተገናኘን ቁጥር ነው የምናነሳው ያን ጊዜ..>> ማሂ ስሙ ሲጠራ የሆነ ንዝረት ነገር ተሰማኝ።
<<ማሂርን ታገኘዋለህ? ደህና ነው?>>
<<አዎ ብዙም ባይሆን ደህና ነው ኧረ እሱ ተመችቶታል..>>
<<ስታገኘው ሰላምታዬን አድርስልኝ እሺ በናትህ..>>
<<ኧረ አያሳስብሽ..አባ ወራጅ! አልፌው መጣሁ እኮ። ኢብቲ በቃ እናወራለን እሺ>> የገቢናውን በር ዘግቶ ከመኪናው ወደ ታች መራመድ ጀመረ።
.
<<አንድ ሰፈር አደላችሁም እንዴ?>> ሹፌሩ በጎን በኩል ሊያየኝ እየሞከረ።
<<አይ አይደለንም..>>
<<እና ትምህርት ቤት ነው የምትተዋወቁት? ከገባቹ ጀምሮ ኮ ስታወሩ በጣም ቅርብ መስላችሁኝ ሁኔታችሁ..>>
<<ሳይሆን ስምንተኛ ክፍል አብረን ነበር የምንማረው እና ዛሬ ተገናኘን ከአምስት አመት በኃላ>>
<<ዋው! ደስ ስትሉ አምስት አመት ረጅም ነው እኮ..>>
<<አዎ ረጅም ጊዜ ነበር>> ብዙ ነግራቶች እንደየጊዜው ተቀያይረዋል። አንዳንድ ሰዎች መጥተዋል፤ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሄደዋል። እኔ ጋር በራሱ ስንት ነገር ተቀያየረ... ራቢ ስራ ጀምራለች፤ ኢክሩም ስራ ና ክላስ አንድ ላይ እያጧጧፈች ነው፤ ዩሲ ደግሞ ዩንቨርስቲ ሄዳ የጊቢ ተማሪ ሆናለች። ነገራቶች ምን ያህል እንደተቀየሩ ለአፍታ ውልብ ውልብ አሉብኝ።
<<እና አምስት አመት ማለት አንቺ አሁን የጊቢ ተማሪ ነሽ ማለት ነዋ ምንድነው የምትማሪው?>>
<<አይ እዚሁ ኮሌጅ ነው የምማረው ፋርማሲስት..በዛው እዚህ ጋር ያዝልኝ..>>
<<ደረሽ እንዴ? በቃ ቆንጅዬ መልካም ቀን..>> እጁን አውሎብልቦልኝ ጉዞውን ቀጠለ።
*
ዊንጌት መናፈሻው ውስጥ ቁጭ እንዳልኩ አንድ ቴክስት ደረሰኝ
<<ኢብቲ በጣም ይቅርታ.. ክላስ አስቸኳይ ፈተና እንዳለብን ነግረውን ወደዛ እየሄድኩ ነው..>> ከሰፈር እሷን ለማግኘት ቢሆንም የመጣሁት እዛው ትንሽ ሰዐታት ለማሳለፍ ወሰንኩ። በመሃል አቤላ ትዝ አለኝ ኡፍፍፍ ለካ ስልክ ቁጥር አልተቀያየርንም ኦህ ሲያበሽቅ!! በቃ እንደውም ወደ ቤት ብመለስ ይሽለኛል። ሂጃቤን አስተካክዬ ከመናፈሻው ወጣሁ።
*
እቤት እንደደረስኩ ለአመታት ልቤን ሲያስጨንቀኝ የነበረው ነገር እንደ አዲስ ነገራቶችን ይመላለሱብኝ ጀምሯል። ማሂር ለመጨረሻ ጊዜ ሲያየኝ የነበረው ቅፅበት ታወሰኝ። ወደ ግንባሩ ድፍት ካለው ፀጉሩ ጋር ትላልቅ አይኖቹ ከነሽፍሽፍታቸው፣ ፈገግ ሲል ስርጉድ ከሚለው ዲንፕሉ ያ ውብ የሆነው ፈገግታው አሁንም አይኔ ላይ ይመላለሳል። አሁንም እንደዛ ይሁን ወይንስ ተቀይሮ? ማሂሬ በአንድ አጋጣሚ ለአፍታ ብቻ ባየው ብዬ ተመኘሁ። በተቀመጥኩበት ብዙ አሰብኩ ነገራቶችን አለመርሳቴ ለራሴ
አስገረመኝ። ዛሬ ከአቤላ ስልኩን እንዴት አልተቀበልኩም?..ግን ብቀበለውስ ደውዬ ምን ልለው ነበር? <ማነሽ? ምን ፈለግሽ?> ቢለኝስ?...እንደምንም ስለትናንት ይቅርታ መጠየቅ ብችል ና ልቤን ከፀፀት በገላገልኳት።
*
#ዕለተ_እሁድ_ከምሽቱ_3:30
*
<<ሃይ እንዴት ነሽ ሰላም ነዋ?>>
<<እኔ ደህና ነኝ>> ከማላውቀው አካውንት የተላከልኝን መልዕክት እየመለስኩ።
<<ኢብቲዬ ሰላምታሽ ደርሶኛል እ የኢሜል አካውንትሽን በግድ ነው ያገኘሁት በዚህ ስልክ ቁጥር በቴሌግራም ከተመቸሽ መልዕክትሽን ላኪልኝ እጠብቃለሁ። ማሂር ..>> የደረሰኝን መልዕክት ማመን አቃተኝ። ማለት ማሂር..? ማሂ.. እንዴት? ወይኔ ደስ ሲል... ቆይ ምንድነው ያለኝ? ደግሜ አነበብኩት። ልክ የዛሬ ስድስት ቀን አካባቢ ነበር አቤላን ያገኘሁት ሰሞኑን ስለ ማሂ ሳስብ ነበር፤ አሁን ደግሞ መልዕክት ደርሶኛል። ወድያውኑ በመልዕክት መለስኩለት።
<<ሰላም ማሂ ኧረ ቆይ ቲጂ መጣሁልህ...>> ጊዜ አልፈጀሁም ስልኩን መዘገብኩና ቴሌግራም ላይ አካውንቱን አመጣልኝ። ምን አልባት ያለበትን ሁኔታ ከገለፀልኝ ብዬ ፕሮፋዬሉን በረበርኩ ምንም የሚገልፅልኝ ነገር ሳጣ መበርበሬን ተውኩት።
ልቤ ፈራ ምን ልለው ነው?...ምንስ ሊለኝ ይሁን?..... ለአመታት ባገኘሁት ስል እንዳልነበር አሁን ግን አመነታሁ ....ልክ እንደ "ግራጫ ".... ግራጫ የራሱ የሆነ ቀለም እንደሌለው ሁሉ ....እኔም ውሳኔ የለኝም ...ግራጫ ልክ ሁለቱንም በአንድ አጣምሮ እንደያዘ.. የኔም ሃሳብ አንዱ ላይ አረጋም.... ግራጫ ለአንዱ እንደሚያዳላ ሁሉ ...የኔም ሃሳብ ላውራው አላውራው ብሎ ሁለቱንም ቢይዝም... እንደ ግራጫ ወደ አንዱ አዳልቶ አዘንብሏል።
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
■ እነዚህን አራት ነገሮች እንጠንቀቅ
● الافراط في العطاء يعلم الناس استغلالك
ከመጠን በላይ መስጠት ሰዎች ያለአግባቡ እንዲጠቀሙብህ ያስተምራል
● الافراط في التسامح يعلم الناس التهاون في حقك
ከልክ በላይ መቻቻል ሰዎች እንዲዳፈሩህና መብትህን እንዲጋፉ መንገድ ይከፍታል
● الافراط في الطيبة يجعلك تعتاد الانكسار
ከልክ በላይ ለሰዎች ደግ መሆን የልብ ስብራትን እንድትለምድ ያደርግሃል

● الافراط في الاهتمام بالاخرين يعلمهم الاتكالية
ለሌሎች ከልክ ያለፈ አሳቢነት ጥገኛ እንዲሆኑ ያስተምራል።

🎨 @Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስራ አራት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
ለማሂ በቴሌግራም መልዕክት ላኩለት <<ሰላም ማሂሬ...>>
<<ወዬ እንዴት ነሽልኝ ውድ አለሽልኝ?>>
<<አልሃምዱሊላህ አለሁልክ እ..አወቅከኝ? ኢብቲሳም ነኝ ..>>
<<ኧረ እንዴት ሆኖ አንቺን እረሳለው.. እየጠበቁሽ ነበር ትመጪያለሽ ብዬ የሚለውን ግጥም ታውቂዋለሽ ሃሃሃሃ>>
<<ሃሃሃ አላውቀውም.. እና እንዴት ነክ ሁሉ ሰላም?>>
<<የዋህ ምን ይሆናል ብለሽ ነው አለሁልሽ>>
<<መኖር ደግ ነው...እና ቤተሰብ ሰላም ነው ናቸው?>> ኡፍ ከምን ጀምሬ ማውራት እንዳለብኝ እንጃ...
<<እኔ እያለሁ ምን ሊሆኑ..አንቺ ጋርስ ?ሁሉ ሰላም ነው?...>>ስለ በፊቱ አንዳንድ ነግሮችን አንስተን ስንስቅ ትንሽ ቆየን።
<<በቃ ኢብቲ ደክሞኛል ልተኛ ነው ነገ እናወራለን...>>
<<እሺ ሰላም እደር ...>> ከኦን ላይን ወጥቼ ማሂን እንዴት ማውራት እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ መሽቶ ነበርና ከሃሳቤ ጋር በዛው አሸለብኩ።
*
ከሰኞ ጀምሮ በተከታታይ የፋይናል ፈተና ስለነበረኝ ኦንላይን ብዙም አልኖርም። ከማሂ ጋርም ሰፊ የማወራበት ሰዐት አላገኘሁም። እንደምንም እየገባሁ መልዕክት አስቀምጥለታለሁ። ግን ምላሹ ሁሉ ቀልድ ነው፤ አልያም ወሬ ይቀይራል። ነገራቶችን ሸፋፉኖ ማለፉ ምንም አልተዋጠልኝም፤ የሚጠቀማቸው ቃላት ጭራሽ የማላውቀው ሰው እያወራሁ ይመስለኛል። ፈተና ስጨርስ ሊያገኘን እንደሚችል ጠየቀኝ... ሳላመነታ ተስማማሁ።
ግን ሳገኘው ማሂር ወፍሮ ይሁን..ወይንስ ረዝሞ..ያ ፈገግታው ይኖር ይሁን...ወይስ...ኮስታራ ሆኖዋል..ማሂ የተሻለ ሂወት ውስጥ ይሁን...ወይስ መጥፎ ሂወት እየገፋ ይሁን..አሁን ደስተኛ ነው ...አልያም ብሶተኛ.. ማሂ ምን አይነት ህይወት ውስጥ ይሁን?
*
#ከሳምንት_ቡኃላ
#ዕለተ_ቅዳሜ_8:00 #ጦር_ሃይሎች
*
<<ሰላም ምን ልታዘዝ?>> ከወገቡ ጎንበስ እንደማለት እያለ አፈራርቆ ያየናል፤ አስተናጋጁ።
<<ኢብቲ ምን ይሁንልሽ ምሣ ምናምን ...?>>
<<አይ ማሂ በልቻለሁ ወተት ይሁንልኝ..>>
<<በቃ ለኔ ማኪያቶ..>>
<<ወተቱ በትልቁ በትንሹ ?>> አስተናጋጁ ደግሞ ጠየቀ።
<<በትልቁ አድርግላት ድመት ነገር ናት ..>>
<<ሳፊ ወይስ ...>>
<<ዉይ ኖርማል አድርግላት በቃ!>> አስተናጋጁ ፈጠን ፈጠን እያለ
ተራመደ።
<<በፈጣሪ ካልዲስ ደግሞ አያዝጉ። ትልቅ፤ ትንሽ...ሳፊ ምናምን ከዛ ደግሞ ከአንድ ሰዐት በኃላ ይዘው ይመጣሉ..>> <<ያው እያወራህ ከሆነ ችግር የለውም ከቸኮልክ ነው የሚያበሳጨው...>>
<<ኧረ ኢብቲ እኔ ትግስት የለኝም መጠበቅ ምናምን ኡፍፍፍ። አንቺ ፀሃይዋ አንቺ ልከሻት ነው በረታችብኝ እኮ>> ከላይ የለበሰው ውሃ ሰማያዊ ጃኬት አውልቆ ወንበሩ ላይ አንጠለጠለው።
<<ምነው?>> አይኔ ወዳረፈበት እጁ ግራ በመጋባት ተመለከተ።
<<ኦውውው ይሄን አይተሽ ነው እንዴ>> እጁ ላይ ወደ ተሳለው ታቶ እያመላከተኝ <<አያምርም እንዴ?>>
<<አይ ገርሞኝ ነው...>>ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ እየተጋባሁ..
<<አንዴ መጣሁ ..>> ወደ ውጪ መራመድ ሲጀምር በደንብ ለማየት ሞከርኩ። ፀጉሩ ተንጨባሯል፤ ሰውነቱ ከስቷል፤ እስካሁን ምንም አልነገረኝም ምን ውስጥ ሊሆን ይችላል? ብዙ ነገራቶች ለአፍታ ተፈራረቁብኝ..
.
<<ኢብቲ ወዴት ሄድሽ?>>
<<ኧረ አለሁ ከመቼው ተመለሰክ ..>>
<<አይ ስገባ አይቼ ነበር ቀድመሽኝ እንዳትገቢ ስቸኩል አልፌው መጣሁ። አሁንም እንደምትወጂ እርግጠኛ ነኝ..>> ሎሊፖፕ አቀበለኝ።
<<እውነት ነው በሎሊፖፕማ አልጨክንም አንተ ደግሞ አትረሳም ሃይ ጎበዝ ነህ...>>
<<አይ ኢብቲ እንዴት ይረሳል>> ሌላ ሃሳብ ውስጥ ሲገባ አትኩሬ ተመለከትኩት። በፊት በኩል ጥቁር ፀጉሩ አሁን በሌላ ቀለም ተቀይሯል፤ ድቅድቅ ብሎ የተሳሰረ የሚመስለው ቅንድቡ በአንዱ በኩል ተቆርጦ መሃል ላይ ክፍተት ተፈጥሯል፤ ከንፈሩ አካባቢ በልዟል... ከዛ በላይ መመልከት አልቻልኩም ማሂ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንደገባ አሰብኩ። እኔ ማስበው እንዳይሆን ፈራሁ..
<<ማሂ?>>
<<ወዬ...ተመሰጥኳ? ታውቂያለሽ ኢብቲ ያ ጊዜ ደስ ይል ነበርኮ..>>
<<ማሂ አሁን እንዴት ነህ በአላህ? ደህና ነህ?>>
<<ደህና አልመስልማ? ምነው አስፈራሁሽ እንዴ?..ባይሆን ጠጪ እስቲ>>
<<ማሂ የተገናኘነው ሻይ ቡና ለማለት አይደለም...እንድናወራ ነው። ...እስቲ አውራኝ እንዴት ነህ..>>
<<ለምን ስለኔ ትጨነቂያለሽ? ትወጂኛለሽ እንዴ?..>> ማሂ አይን አይኔን ሲያየኝ ይባስኑ አጨናነቀኝ።
<<እንዴ ማሂ ለምን እጠላሃለው? ለምን አሎድህም?>>
<<እንደሱ ነው እንዴ>> ከልብ በማይመስል ፈገግታ መለሰልኝ።
<<ማሂ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ። ማውቄ እኔን ጎድቶኛል ምክንያቱም ያኔ ምንም ላደርግልህ አልቻልኩም ነበር። አሁን ግን...>>
<<አሁን ምን? እስቲ ምን ታውቂያለሽ? ሃሃሃ... ምን ታውቂያለሽ ከስሜ ውጪ..?>>
<<እሺ አንተ ንገረኝ ማላውቅ ከሆነ..>> <<ከምን እስከ ምን ኢብቲ? ብታውቂስ ቆይ ምን የምትለውጪው ነገር አለ? ሰምተሽ አይዞህ ልትዪኝ ነው? አመሰግናለሁ..>> ማኪያቶውን በሁለት ትንፋሽ ጨለጠው፤ ፊቱ መቀያየር ጀመረ። ዛሬ ምንም ቢፈጠር ለመቀበል ዝግጁ ሁኜ ነው የመጣሁት ብቻ
በትዕግስት ማሂን መቆጣጠር አለብኝ።
.
<<ማሂ ስላንተ ባቢ እና አቤላ ሁሉንም ነገር ነግረውኛል። ወላሂ ማሂሬ ያን ጊዜ አንተን ማግኘት አልቻልኩም። በርግጥ እስኪነግሩኝ መጠበቅ አልነበረብኝም፤ አንተ በተግባር ብዙ ልታሳየኝ ጥረህ ነበር። ግን እኔ አልገባኝም አለ አይደል.. ወተት ነጭ ነው እስክባል ድረስ። ማሂ አውቃለሁ በኔ ላይ ተስፋ ነበረህ፤ ያን ተስፋ አጨለምኩብህ አይደል? ማሂ ከተለያየን በኃላ እኮ ብዙ ፈልጌህ ነበር፤ ግን አላገኘሁክም። አውቃለሁ ሳንለያይ በፊት ቁጥርህን ስትሰጠኝ አልተቀበልኩህም። እኔ ይሄ ሁሉ ይፈጠራል ብዬ አላስብኩም ነበር። ማሂ እኔ ስላንተ በማሰብ ራሴን ተወቃሽ አድርጌ ላለፉት አመታት በፀፀት ውስጥ አለሁ። እባክህን ማሂ አንድ ነገር እንኳን እንዳደርግ ፍቀድልኝ...ቢያንስ አሁን ያለህበትን ሁኔታ ንገረኝ።>> አይኑን ከኔ ላይ አነሳና ወደ ጠረዼዛው አጎነበሰ።
<<ኢብቲ ታውቂያለሽ? እንደ አሁን ሰዐት በራሴ ተስፋ የቆረጥኩበት ጊዜ የለም። ያኔ እኮ በቃ መሉ ለሙሉ የምፈልገውን ህይወት የማገኝ መስሎኝ ነበር። ቆይ ኢብቲ አንድ ሰው ወዶ አላዋቂ ይሆናል እንዴ? እኔ እኮ እምነቴን ለማወቅ ብዙ ቦታዎች ሄጄ ነበር። ለካ ለማወቅም ትንሽ ማወቅ አለብሽ። <ገና ጀማሪ ነህ..እንዴት ትንሽ እንኳን አታውቅም? ምናምን.. እስቲ ስገድ> እህህ! ስርአቱን አውቄ ለመስገድ አይደል እንዴ እነሱ ጋር መሄድ የፈለጉት? ቆይ ሌሎችስ ስለ እምነቴ አላውቅም አስተምሩኝ ማለት የሌሎች መሳለቂያ ሙድ መያዣ ማድረግ ምን ይጠቅማል? ኢብቲ በናትሽ ስለተውኩት ነገር አታስወሪኝ። ..ብቻ ያኔ ካንቺ ብዙ ጠብቄ ነበር፤ በቃ አልሆነም ደግሞ እንደማገኝሽ እርግጠኛ ነበርኩ። ግን እንዲ ከረፈደ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ይሄን አንብቢው እስቲ ከዋሌቱ ላይ ከሁለት ወረቀት አንዱን አውጥቶ ሰጠኝ ወረቀቱ እጥፍጥፍ ብሏል በዛ ላይ የቆየ ይመስላል። ተቀብዬ ከፈትኩት
#ትዝታ
.
.
ትዝታ እኮ ሳቅ ነው ቢኖረውም ትካዜ፤
ትዝታ ታሪክ ነው የማይረሱት ጊዜ፤
እኔም ኑሪያለሁኝ በትዝታ አለም፤
ስለአንች በማሰብ ስለአንቺ በማለም።
መኖር ከተባለ እኔም ኑሪያለሁኝ፤
በዝምታ አለም ሁሌ እየፈራሁኝ፤
በአይናፋር አንደበት ዝምታን መርጬ፤
ከመናገር ይልቅ በሀሳብ ቀጭጬ፤
ራሴን በመደበቅ ማውራትን ፈርቼ፤
በስቃይ ኑሪያለሁ ግራ ተጋብቼ።
.
ራሴን በመውቀስ ራሴን በመስደብ፤
በዚች አስቸጋሪ በዚች ፈታኝ አለም፤
በተመስጦ ታሪክ በሚመስል የህልም፤
እውነት ኑሪያለሁኝ 'ኔነቴን በማሰብ።
.
<<ግጥም እንደምትፅፍ አላውቅም ነበር።>> ግጥሙን አንብቤ ቀና እያልኩ።
<<ምንም አታውቂም አልኩሽ ኮ ..ብዙ ፅፌ ነበር ግን የሆነ ቦታ ቁጭ ስል እንዲበሩ እለቃቸዋለሁ እስካሁን ምንም አላገኘሽም እንዴ...>> ፈገግ ለማለት ይሞክራል።
<<እሺ ማሂ ያለፈውን ታሪክ አወራን፤ እሱ እንደግጥምህ ነው.. ትዝታ ልንለው እንችላለን። አሁንስ እሺ ማሂ አትደብቀኝ እባክህን..>>
<<ኢብቲ ላንቺ ምንም አይጠቅምሽም አውቃለሁ። ነገራቶችን ለማስተክልከል ትፈልጊያለሽ ግን የማይስተካከል ህይወት አለ>>
<<ማሂ በናትህ ህመሜን ቀንስልኝ...>> ንግግሬን አላስጨረሰኝም
<<እናቴ ብትኖር እዚህ ነገር ውስጥ የምገባ ይመስልሻል? ተያ ኢብቲ... በቃ አንቺ እንደምታስቢኝ አይነት ማሂር አይደለሁም፤ ልሆንም አልችልም። መጥፎ ሰው ነኝ፤ አሁን ምንም አላማ የለኝም። እውነቱን ልንገርሽ? ያኔ በረመዳን ሚሪንዳ ስጠጣ እንደዛ ለደነገጥሽው ለምነግርሽ ነገር ምን ልትሆኚ እንደምትቺ ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር። ስለኔ ከአሁን በኃላ እንድትጨነቂ አልፈልግም ኢብቲ። እኔ ማሂ በአሁኑ ሰዐት አልንገርሽ ያኔ በምታውቂኝ ማሂ ኑሪበት..>> አይኖቹ እንባ አቀረሩ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ ልናገረው አልችልም፤ ብቻ እንደምንም ራሴን ለመቆጣጠር እታገላለሁ።
<<በመጀመሪያ ኢብቲ እወቂ.. በጣም እንደምወድሽ። እንዲህ ስልሽ ግን ባልሆነ መንገድ እንዳትረጂኝ ምን አልባት እህት ስለሌለኝም ይሆናል። እናቴን በልጅነቴ ማጣቴም ይሆናል። እነሱን የምትተኪልኝ ይመስለኝ ነበር፤ ከአንቺ ጋር እህትና ወንድም ሁነን እንዴት እንደምንሆን እንደምናድግ ብዙ ጊዜ አስበው ነበር። አለ አይደል የራሳችን ላይፍ ኖሮን ሁላ እንደ ፍሚሊ ልንኖር.. ብቻ ብዙ ብዙ ሃሳብ ሆኖ ቀረ እንጂ፤ እስካለፉት ሶስት አመታት ድረስ..>> አይኑን ማየት አልቻልኩም አንገቴን ከመሰብር ውጪ። ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ።
<<ማሂ እሺ አሁንስ?>>
.
.
የመጨረሻው ክፍል...
ነገ ይቀጥላል...
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አስራ አምስት
(የመጨረሻው ክፍል)
(ሂባ ሁዳ)
.
.
ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ።
<<ማሂ እሺ አሁንስ?>>
<<አሁንማ... አሁንማ ኢብቲ...ተስፋ የቆረጠ ሰው አታውቂም?...ራሱን የጠላ ሰው?... መኖር የሰለቸው? ....እየኖረ የሞተ?.... ህልሙን ቅዠት የሆነበት?... ከራሱ ርቆ በሌሎች የተደበቀ.... ልቡን ላለማድመጥ ጩኸት የሚፈጥር?... ከኑሮ ለመሸሽ በጪስ የተወሸቀ?...ኢብቲ ከፊትሽ ያለው ለሴቶች ክብር ብሎ የሚጣላው ማሂር እኮ አይደለም። የሴቶችን ክብር የሚወስድ እንጂ..>> ድምፁ በሲቃ ታፈነ አይኖቹ መሸከም ያልቻሉትን ዕንባዎች ሲለቋቸው ቁልቁል ፈሰሱ። ከዚህ በላይ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም። ድንዝዝ ያሉት እጆቼ ዕንባዬን መጥረግ ተሳናቸው። ምንም ቃል መናገር አልቻልኩም የማሂ ዕንባ እያይሁ ከማንባት ውጪ።
እንደምንም ራሱን አረጋግቶ ግንባሩን በሁለት እጆቹ ደጋፍ አደረገ
<<ኢ.ብ..ቲ>> ድምፁ መቆራረጥ ጀመረ። <<አ.ል.ች.ል.ም እንዲህ መኖር አህ.ህ.ህ>> እጆቹ እንደመንቀጥቀጥ አደረጋቸው።
<<ማሂሬ ደና ነህ?>> በጣም ደንግጫለው አይኑን ይጨፍናል መልሶ ይገልጣል ..
<<ማሂ ማሂሬ?>>ድምፁ ጠፋብኝ
<<ትንሽ ደቂቃ ብቻ... ይ.ተ.ወ.ኛ.ል ..>>
.
<<ኢብቲ አየሽ አይደል እዚህ ድረስ ነኝ.. በሰዐቱ ካልተጠቀምኩ እንዲህ ነው የሚያደርገኝ መውጣት ማልችለው ሱስ ውስጥ ወድቄያለሁ። ኢብቲ ከዚህ ቡኃላ የኔ የምለው ምንም አይነት ነገር የለኝም፤ የኔ ቀርቶ እኔም አልኖርም። እኔ እኮ አሁን አንቺን ማግኘቴ ደስ ብሎኛል። ቢያንስ እንደኔ ሌላ ሰው ሰው በማጣት የህልሙ ብርሃን ጭላንጭል ሲሆን... ጭላንጭሉን ወደ ብርሃን እንዲቀየር እንደምታግዥው ለራሴ ቃል ትገቢልኛለሽ። ከአሁን በኃላ ሰሚ ላጡ አባሽ ለሚፈልጉ ዕንባዎች እንደ አሁኑ አብረሻቸው ከማልቀስ ይልቅ መፍትሄ እንደምታመጪላቸው እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ። ኢብቲ ያለፈው ፀፅቶሻል? ጎድቶሻል አይደል? በሌሌች አስተካኪው። ከመስማት ማድመጥን ልመጂ። ማየት ብቻ ሣይሆን በመመልከት አስተውዪ ...>>
<<ማሂሬ እንዴት ልቻለው? ይሄን ሁሉ ከመሆኑ በፊት እኮ..ማሂ ይሄ ሁሉ በኔ እኮ ነው! ራሴን ምን ብዬ ላሳምነው?>> ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልኩም ስቅስቅ ብዬ ከማልቀስ ውጪ።
<<ኢብቲ ነገርኩሽ እኮ... በቃ ያለፈ ታሪክ ነው። ያገኘሁሽ ሁላ በኔ ምክንያት መጨነቅሽን ትተሽ ሰላምሽን እንድታገኚ ነው።>>
<<ማሂ ለዚህ ሁሉ ስህተት ምንድነው ይቅርታው?>>
<<ኢብቲዬ ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል። በኔ ህይወት አንቺ አልዘገየሽም፤ እኔ ቸኮልኩ እንጂ.. እኔን እርሺኝ ከአሁን በኃላ የሚመጡትን ማሂሮችን እርጂያቸው። ከዚህ በላይ ስታለቅሺ የማየት አቅሙ የለኝም። ማንም አንቺን ባያስከፋሽ ምኞቴ ነው። በኔ ምክንያት እንድታለቅሺ ከቶ አይቻለኝም። ቃል እንድትሰጭኝ ፈልጋለሁ ማሂን በድዬዋለሁ ብለሽ እንደማታለቅሽ..>>
<<ማሂ ጭራሽ ከአዕምሮዬ በላይ ሆንክብኝ እኮ። ያልከኝን ሁሉ አደርጋለሁ ግን በጣም ይ.ቅ.ር.ታ...ስለሁሉም>> ድምፄ ታፈነ ማውራት እየፈለኩ ግን አንደበቴ ተሳሰረ። ከሚቆራረጠው ትንፋሼ በቀር ..
<<ማ.ማማ..ሂ.እኔ... >> ወደኔ ተጠጋ ሊያባብለኝ ሞከረ፤ ግን አልሆነለትም። ዕንባዎቹ እየተሽቀዳደሙ መሰለኝ። ለመጥረግ ብሞክርም እንደ አዲስ የሚፈሱት እጄን አረጠቡት። እንደ ትኩስ ውሃ ቢያቃጥለኝ፤ ልቤ ከሚለበልበው ህመሜ በላይ የሱ ሲቃ ገዘፈብኝ። እጄን ከፊቱ ላይ አወረዳቸው ወደ ጆሮዬ ተጠጋ።
<<ኢብቲ እኔ ከአሁን በኃላ የለሁም። ስለኔ ብለሽ ሌሎች ማሂሮችን እርጂያቸው ስለኔ ስታለቅሺ ከዚህ በላይ ማየት አልችልም>> ለመጨረሻ ጊዜ ከማሂ የወጡ ቃላት ነበሩ። ማሂ እያየሁት በምን ፍጥነት በር ጋር እንደ ደረሰ እኔንጃ ብቻ በር ጋር ሲደርስ አንዴ ዞር ብሎ አይቶኝ ከአይኔ ሸሸ።
.
ከደቂቃዎች ቡኃላ ተረጋጋሁና አካባቢዬን አስተዋልኩ፤ ጠረዼዛው ላይ ማሂ ሂሳብ አስቀምጧል በኩባያ ሙሉ ወተት አለ። ማሂ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ውሃ ሰማያዊ ጂንስ ጃኬት አለ አንስቼ ያዝኩት፤ የማሂሬ ነበር። ለትናንቱ ህመሜ ዛሬ ማስታገሻ አጊቻለሁ...ትናንት ላይ የባከኑት ቀናት ዛሬ ላይ ዋጋ አስከፍለውኛል ያውም በማሂሬ!
.
ሁላችንም ውስጥ ትላንት አለ፤ ትናንታችን ውስጥ ደግሞ ስህተቶች አሉ፡፡ ምናልባት የኛ ምናልባትም ደግሞ በህይወታችን ዉስጥ የገባ የሌላ ሰው ስህተት አለ፡፡ ከትላንት ስህተታችን ለመታረም መቁረጥ አለብን፡፡ እኛ ህይወት ውስጥ ስህተት የሚፈጠረው በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በእኛ ምክንያት ነው፡፡ ባለማወቅ ሰዎችን ብዙ ጎድተና፤ እንዲያዝኑ አድርገናል፤ በእርግጥ ሰዎችን ከልክ በላይ የሆነ ቦታ እንዲሰጡን የሚያደርጉ ነገሮች አሉ፡፡ ግና ትክክል ነው ብለው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የነሱን የህይወት ፈተና ማለፊያ ያደርጉናል... አልያም እናደርጋቸዋለን፡፡ ይሁና.......! ሁሉም በየራሱ መንገድ ትክክል ነው፡፡ በቃ...አሁን ዛሬ ላይ ነን። ምናልባት ነገ ብለን ትናንት ተስፋ ያደረግነው ነገር ዛሬ ላይ ፀፀት ሆኖ ይሆናል፤ ግን አልፎዋል አራት ነጥብ፡፡ ያ ሁሉ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እምነት፣ ስህተት ....በቃ ሁሉም ትላንት ነው፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው! አዲስ ከስህተት ተምረን የምንለወጥበት ባለፉ ስህተቶች ድጋሚ የማናልፍበት። ሌላ ከኖርነው እድሜ ላይ የተጨመረችልን ልዩ ቀን። ያለፈው ይሁና.......! ይሄን ሁሉ አልፈን እንድንቆም ለረዳን አላህ ምስጋና አቅርበን ነጋችንን የምንስልባት ባለ ፀሀይ ቀን፡፡ እርግጠኛ ነኝ ነገ ከትላንት ይሻላል፡፡ የሄደው ነገር ሁሉ ለመልካም ነው፡፡ ዛሬዬን ያዘጋጀልኝ ጌታዬ ነገዬን የተሻለ እንደሚያደርግልኝ አምናለው፡፡ ምናልባት አልሄድንም ይሆናል ፤ አልመጣንም ይሆናል ፤ ግን ፈቀቅ ብለናል ፡፡
ቅድም ማሂ በሰጠኝ ወረቀት ጀርባ መሞነጫጨር ጀመርኩ... ምን አልባትም ለማሂ የፃፍኩት የመጨረሻ ቃላቶቼ ናቸው።

#ግራጫ_ቀናቶች
~~~~
ጣዕም የለሽ ህይወት
ትርጉም አልባ ኑሮ ፤
ቀንም ሆነ ምሽት
የሳግ እንጉርጉሮ ፡፡
በጥቁር ደመና
እንባን ያቀረሩ ፤
በሳቅ በትወና
ባዷቸውን የቀሩ ፤
ወይ ከነጭ አልሆኑ
ወይ ደግሞ ከጥቁሩ ፤
ብዙ ቀኖች አሉኝ
በመሃል የቀሩ ፡፡

የፃፍኩትን ወረቀት ሳጣጥፍ ከጀርባው ሌላ ፁሁፍ በትናንሹ ተፅፎ አይሁ ለማንበብ ወረቀቱን ዘረጋሁትና ማሂ እንዳለኝ በአትኩሮት ለማንበብ ራሴን አብሰብ አደረኩ።
❝ግን በመሄድና በመምጣት የጊዜ ርዝማኔ ውስጥ የተስፋ ስብራቶች፣የልብ ቁስሎች ፣ የአእምሮ መላሸቆች ስንት ይሆኑ...? ባለመኖር እውነታ ውስጥ ስንት የመኖር ህልም ይሞት ይሆን.....? በትናንት ህመም ውስጥ ስንት ዛሬዎች ባከኑ፤ የነገ ህልሞች ደቀቁ............❞
አንብቤ ስጨርስ እንደ ጀት ቅርፅ ሰራሁበት ከካፌው እንደወጣሁ ወደ ሰማዩ ለቀኩት..በአንዱ መስመር ሲሄድ እኔ በሌላኛው መስመር ሄድኩ ....

ተፈፀመ
••••••
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
2024/07/07 06:57:51
Back to Top
HTML Embed Code: