Telegram Web
አሜሪካዊው ቦክሰኛ እስልምናን በነዚህ ምክንያቶች አከብራለሁ ይላል

" ከሴቶች ጋ ችግር ካለብህ ኢስላም ይፈታዋል። ሚስትህ የማትታዘዝህ ከሆነና ተያያዥ ችግሮች ካሉብህ ኢስላም በርግጥ ይፈታዋል። ኢስላም ባሎች በአሁን ጊዜ ለሚያጋጥመቸው የተለያዩ ችግሮች መፍትሔ ይሰጣል።
በዚህ ፕሮግራማችን ላይ የምንወያይባቸው ችግሮች አስመልክቶ ኢስላም ለሁሉም መፍትሔ አለው። ልክ ነኝ ? ይህ እስልምናን በተመለከተ የመጀመሪያው ነው ።
እኔ ሙስሊም አይደለሁም ነገር ግን እምነት መምረጥ ብፈልግ በክርስትያን ሀገር ስለምኖር ወደ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ። ለቤተክርስቲያን በየወሩ 20000 ዶላር እለግሳለሁ። ቤተክርስቲያኗ እዚህ ጠንካራ ናት። ከቤተክርስቲያን ጓደኞች እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ ።ለዚህም ስል ብዙ ገንዘብ እሰጣቸዋለሁ። ለዚህም እኔ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ እላለሁ። ነገር ግን በአንድ እምነት ላይ እንወራረድ ብትለኝ ለወደፊት በቡርሳ እንደማስይዘው ሁሉ በኢስላም አስይዝ ነበር። ምክንያቱም ሙስሊሞች ይቅር አይሉም!! ክብራቸውን ለመንካት አይደለም ይህን የምለው ምክንያቱም አንተ ሁሉንም ነገር በይቅርታ የምታልፍ ከሆነ አንተ አላማ ቢስ ነህ ማለት ነው:: በአሁን ጊዜ ክርስቲያኖች በጣም ልቅ ሆነዋል ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ትችላለህ ልጃገረዶች ቅዳሜ ማታ ይዘሙታሉ ከዛም እሁድ ጠዋት ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ ከዛም እሁድ ማታ ይዘሙታሉ በዚህም ምንም ችግር እንዳለ አይሰማቸውም:: ልክነኝ?
እኔ የማፈንገጥን መብትን ከሚቃወሙት አይደለሁም ነገር ግን መፅሃፍክ ላይ ያለውን ነገር የማትተገብር ከሆነ ስለዚህ ይህ ምንድነው?! አንተ አሁን በምንድነው የምታምነው?!! በሁሉም ነገር ላይ የምትለሳሰለስ ከሆነ የምትከላከልለት መርሆ የለህም ማለት ነው:: በለንደን ጎዳኖች ላይ "እየሱስ አፈንጋጭ ነው" የሚል አርማ ያለበት ሸሚዝ ለብሼ መሄድ እችላለሁ ምንም ነገር አይደርስብኝም :: በኢስላም መልዕክተኛ ላይ ተመሳሳይ ነገር ባደርግ መንገዱ መጨረሻ ላይ ሳልደርስ በፊት ሬሳ ነው የምሆነው:: ይህ ነው ክብር በመስጠት ያላቸው የእምነት ጥግ:: የሚያምኑበትን ነገር የሚከላከሉ ሰዎችን እኔ አከብራለሁ እኔ የማከብራቸው እውነተኛ አማኞች ስለሆኑ ነው ለሚያምኑበት ነገር ለመከላከል ዝግጁ ናቸው ብቸኛ ስለእምነታቸው የሚከላከሉት ሙስሊሞች ናቸው ስለሚያምኑበት ነገር ይከላከላሉ ማንም እንዲሳለቅባቸው አይፈቅዱም መዋረድን አይፈቅዱም ይህን ነገራቸውን አከብርላቸዋለሁ ይህ ነው በጣም የሚያስገርም ነገራቸው"::

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
Forwarded from [ IKRAM ISLAMIC CALLIGRAPHY ]
የውዱ ሰው የነብይነት ታሪክ በሂራእ ዋሻ ውስጥ በመልዕክተኛው ላይ በወረደችው <አንብብ> በተሰኘችው ቃል ይጀምራል ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዓለይ
< #አንብብ> በተሰኘችው ቃል ጅማሬ ታሪካችንን ክብራችንን ህይወታችንን በርግጥ ጀመርን
< #አንብብ> በተሰኘው ቃል መውረድ የተቀደሰው ጉዟችን ተጀመረ
የምድር ገጽታ የቀናትና የዓለም ገጾች ተቀየሩ
💡ያች አጋጣሚ ለኛ ሙስሊሞች በህይወትችን እጅግ አስደሳች በብርሃንና በጨለማ በኩፍርና በኢማን በድንቁርናና በእውቀት መካከል ልዩነትን የፈጠረች አጋጣሚ ነበረች
< #አንብብ> የተሰኘችው ቃል ከመዝገበ ቃላት ተርታ ከቋንቋ ሚስጥር መድብል ለይቶ መመረጥ መቻል እጅግ ድንቅ ስራ ነው ።
...ሙሃመድ ሆይ! ጥሪህን ከመጀመርህና ትእዛዞችህን ከመፈጸምህ በፊት
◍{አንብብ} {እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፤}◍
አል-ዓለቅ ፡ 1
#አንብብ የተሰኘችው ቃል በእርግጥም በትርጉም በይዘትና መልዕክት በማስተላለፍ ምንኛ ውብና ያማረች ቃል ነች

@Ikramislamiccalligraphy
Forwarded from [ IKRAM ISLAMIC CALLIGRAPHY ]
ከመተኛትህ በፊት አላህን አውጋው....
ከአላህ ጋር ተነጋገር
ዛሬ ልብህን ስለሰበረው ነገር ንገረው
እንደማትመለስበት ቃል ገብተህ ስለነበረውና
ደግመህ ስለ ስለሰራሀው ወንጀል ተናዘዝ
ልብህ መሰበሩን ንገረው
መጠገንም እንደሚያስፈልግህ
ጠጋኙም እርሱ ብቻ መሆኑን ዝቅ ባለ ድምፅ ንገረው
ወንጀልህንም ይምርህ ዘንድ አጥብቀህ ለምነው
ስለ ነገ ህልምህም አጫውተው እንዲያሳካልህም
ተማፀነው!

አውራው አዛኙ ጌታህን አውጋው !!

መልካም ተመስጦ 😊
አላህ መጨረሸችንን ያሳምርልን እኚህ ሰው በመስጂደል ሀረም በሱጁድ ላይ እንዳሉ ጌታቸውን ተገናኝተዋል

@Habibacalligraphy
ሱብሃነላህ ምን አይነት የቂን ነው ?!

@Habibacalligraphy
ነገ ሀሙስ ቀን መፆም የውዱ ነብያችን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ነው ከዛ በተጨማሪም ስራችን ወደ ሰማይ የሚወጣበት ቀን ነው የቻለ ይፁም ያልቻለም ለሌላው ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁን

@habibacalliraphy
በተከበሩት ዐስሩ የዙልሒጃ ቀናት ሁለተኛው ቀን ላይ ነን ኡድሒያ የማረድ ኒያ ያለን ሰዎች #ፀጉር#ጥፍራችንን እንዳንቆረጥ
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል " የሚያርደው ኡድሒያ ያለው ሰው የዙልሒጃ ወር ጨረቃ ከታየች ጀምሮ ኡድሒያን እስከሚያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን አይቁረጥ"
ሙስሊም ዘግበውታል

@Habibacalligraphy
#بالروح بالدم نفديك ياقدس

#Free-Palastine

🎨 @Habibacalligraphy
።።።።። የዝሙት መንገድ ።።።።


እህቴ__ሆይ! ጀነት አይገቡም ከተባሉት ውስጥ ነሽ ወይስ...???



ይህንን ፁሁፍ አንብበሽ ያለሽበትን ተመልከቺ!

አብዛኛው ቤት ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) የተነበዩት ትንቢት እየታየ ነው አላህ ካዘነላቸው ሲቀር!


ጉርድ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ከጉልበታቸው በታች እራቁታቸውን ናቸው፣

ሙሉ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን ከመወጣጠሩ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ሙሉ ለሙሉ ያሳያል፣

ሲላቸውም ደረታቸውና የወገባቸው ክፍል የማይሸፍንም ይለብሳሉ፣

ሻርፕ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን አስሬ የምትወርድ ወይም ለሳንፕል እዩልኝ በሚል መልኩ ይለብሳሉ።

ሌላም ሌላም ጉድ የሚሳኝ አይነት ምናልባትም ሙስሊም ያልሆኑት ከሚለብሱትና ከሚያስከፈ መልኩ ለብሰው እያየን ነው።


እኔ እምልሽ እህቴ! ምን ፍለጋ ነው ቅጥ ያጣ አለባበስ የምትለብሺው?


“ደስታ” እንዳትይኝ ሸሪዐዊ አለባበሳቸውን ጠብቀው ካንቺ በተሻለ ደስታን የሚጎናፀፉት ስንትና ስንት ናቸው!!


“ውበት” እንዳትይኝ ወወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ውበት ያለው ስርኣት ባለው ሸሪዓዊ አለባበስ ነው፡፡

እመኚኝ ይሄ ቅጥ ያጣ አለባበስሽ አያምርብሽም!! “አይኔን ግንባር ያርገው” ካልሽ አትጠራጠሪ የውስጥሽን መታወር ነው ገሀድ ያወጣሽው፡፡

ምናልባት “ውበት እንደተመልካቹ ነው” እያልሽ እራስሽን ትሸውጂ ይሆናል፡፡

አልተሳሳትሽም! ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ብልግናም ለባለጌዎች ያምራል!!

አዎን ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ጋጠ ወጥነትም ለጋጠ ወጦች ያምራል፡፡

ልክ ነሽ ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ርካሽነትም ለርካሾች ያምራል!!

ህሊናችን ሲገለበጥ አስተሳሰባችንም ምርጫችንም ይገለበጣል፡፡


እንዲህ የምለብሰው “የህይወት አጋር ፍለጋ” ነው እንዳትይኝ፤ በዚህ አለባበስሽ አይናቸውን የሚጥሉብሽ ያለጥርጥር ርካሽ ወንዶች ናቸው፡፡

የህይወትሽ አጋር፣ ውሃ አጣጪሽ እንዲሆን የምትፈልጊው ርካሽ ወንድ ነውን?አላሁልሙስተዓን!!

እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው፡፡

የወረደ አለባበስ የምትለብሽው የነቁ በሚመስሉሽ፣

“ስም” ያላቸው ዘፋኞች፣ ነጮች፣ ከሃዲዎች፣

ጋጠ ወጦችን ለመመሳሰል ነው ወይስ አይደለም?

ከሆነ ነገ አላህ ፊት ያለምንም አስተርጓሚ እርቃንሽን ለምርመራ ትቆሚያለሽ!!

ያኔ ምን ይውጥሻል???

በተለይ ደግሞ ጋጠ ወጦችን ተከትለሽ ከፈፀምሺው ጉዳዩ ምን ያክል አሳፋሪ ምን ያክል አሸማቃቂ እንደሚሆን ለአፍታም ቢሆን ከዚያ አስፈሪ ቦታ ላይ እራስሽን አቁሚና ታዘቢው፡፡

ነው ወይስ አንቺ ጀነትን አትፈልጊም? ታማኙና እውነተኛው፣

ከስሜታቸው የማይናገሩት ነብይ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)

እንዲህ አይነት ቅጥ ያጣ አለባበስ ላይ የወደቁ ሴቶችን ጀነትን ቀርቶ ሽታዋንም አያገኙም እያሉ ነው፡፡


"ሁለት ክፍሎች የእሳት ናቸው።

እነሱንም አላየኃቸውም።

አንዶቹ የከብት ጅራት የመሰለ አለንጋ ይዘው በዚያ የአላህን ባሮች የሚገርፉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የለባሽ እርዘኛ(ለብሳ ያለበሰች)፣

ተዝንባዩች እና አዘንባዩች እራሳቸው እንደ ከሳ ግመል ሻኛ የሆኑ በፍፁም ጀነት አይገቡም፤ አረ እንዳውም ሽታውንም አያገኙም።

የጀነት ሽታ ከዚያ ወደዚያ(ከረጅም ርቀት) የሚገኝ ሆኖ ሳለ።" (ሙስሊም 2128፣ አህመድ 440/2)

እኔ እምልሽ የኔ እህት! እጣ ፈንታሽ ይሄ እንዲሆን ትፈልጊያለሽን?! ለዲንሽ ዋጋ ስጪ!!

ወንድሜ ሆይ! ባለቤትህ ወርዳና ተዋርዳ ስትወጣ ዝም ማለት ያንተ ባልነት ምኑ ጋር ነው?

አባት ሆይ! ልጅህ የአደባባይ መነጋገሪያ እስክትሆን ያንተ ሚና ምን እንደሆነ ረሰሀውን?

አንተስ ወንድሜ እህትን መቆጣጠር ምንተሳነህ?

ስህተት/ጥፋት እያየን ዝም ካልን አላህ እንዴት ነስሩን ይስጠን?

የእስካዛሬው ይብቃ! ዛሬውኑ ቤታችንን በዲን እናስዉብ!


አላህ ያግራልን!



ሀሳብ አስተያየት
👉 @abu_hafsaa


Join 👉 @halal_zewj
كل عام
وأنتم لربكم طاءع
ولنبيكم تابع
ولمجتمعكم نافع
ولدينكم رافع
وللجنة طامع !
كل عام وأنتم بألف ألف خير


ውድ የሀቢባ ካሊግራፊ አባላት Eid mubarek
@Habibacalligraphy
"እንዲሰጣችሁ ብላችሁ አትገዙት ይልቁንስ እርሱን ለማስደሰት ስትሉ ተገዙት ...እርሱ በናንተ ደስተኛ ከሆነ ... በስጦታው ያስደምማቹሃል "

ሸይኽ አሽ ሸዕራዊ

@Habibacalligraphy
Forwarded from Hik promo
አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ የሀኒያ ካሊግራፊ ቤተሰቦች በያላችሁበት ሁሉ ሰላማችሁ ይብዛልን እያልኩ😍 የመጀመሪያ ዙር የካሊግራፊ ውድድር ሰሞኑን እንጀምራለን ኢንሻአላህ እስከዛው ድረስ ወዳጆቻችሁን ወደ ቻናሉ በመጋበዝ እንድትተባበሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን 😊

ውድድሩ የሚዳኘው
25 በ like
25 በ viuw
50 በዳኞች ይሆናል
ከ1-3 የወጡ ተወዳዳሪወች ሽልማት ይኖራል
1-25 ካርድ🎁
2-15 ካርድ🎁
3-10 ካርድ🎁

✔️ዋናው ነገር ችሎታችሁን ለማሳየት መጣራችሁ ነው እና

✔️የምትወዳደሩት ለማሸነፍ መሆን መቻል አለበት

ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ 👉 @hanana_calligraphy_bot
JOIN &SHARE 👉 @haniya_calligraphy
ጂን የማይጠጋቸውና ሸይጧን የሚሸሻቸው ሴቶች
1. ሀያዕ ያላት ሴት { ኢማኗ ጠንካራ ስለሆነና መገኘት የሌለባት ቦታ ስለማትገኝ }
2. ኢስቲግፋር የምታበዛ ሴት{ወደ አላህ ቅርብ ስለሆነች}
3. ግዴታ የሆኑ ድንጋጌዎችን በሰዐቱ የምትተገብር ሴት
4. ለይል የምትሰግድ ሴት { ይህን ስታደርግ ሸይጣን ማየት ስለማይፈልግ }
5. ለባሏ ብቻ የምትኳኳልና ሚስክ ቤቷን የምታውድ ሴት 👉 ለጌታዋ ታዛዥ ለመልዕክተኛው ዐለይሂ አፍደሉ ሰላቱ ወሰላም መንገድ እንዲሁም የነቢያችንን ሚስቶች ፈለግ የምትከተል ስለሆነ እርሷን የመተናኮል አቅም አይኖረውም :: አላህ ሆይ ሙስሊም ሴቶችን አንተው ጠብቅልና ሀያዕና ተቅዋንም ጨምርላቸው 🤲

🦋 @Habibacalligraphy
ከእስካሁኑ ስራዎቼ ውሰጥ part 1 እንካችሁ ብያለሁ ❤️

JOIN us 👇👇👇
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
https://www.facebook.com/groups/242067870787957/
Forwarded from Haniya Calligraphy🎨
ሀምሌ 20/11/2013

አሰላሙ አለይኩም ሀቢባቲ እንዴት ናችሁልኝ
የመጀመሪያው የካሊግራፊ መወዳደሪያ ይሄን ይመስላል ፅሁፍ ላይ ያሉትን ሁሉ በማሟላት መስራት አለባችሁ

ስማችሁን ቀን እና የምትኖሩበትን ቦታ መፅፍ አለባችሁ

በውድድሩ ፈፅሞ የማይቻልና ከውድድሩ ውጭ የሚያረግ ነገር
ፎቶ ኢፌክት አይቻልም
አስገድፎ መስራት አይቻልም
ከተሰጠው ሰአት ውጭ መላክ አይቻልም

ስራችሁን የምትልኩት በ👇👇 @hanan_calligraphy_bot
@hanan_calligraphy_bot
@hanan_calligraphy_bot

✔️ስራችሁን የምንቀበለው እስከ ሀሙስ 2:00 ድረስ ብቻ ነው

✔️like view ውጤት እስከሚለቀቅ ድረስ ማሰባሰብ ትችላላችሁ

✔️ውጤት ቅዳሜ 2:00 ይለቀቃል

እዚህ ጋር ማወቅ ያለባችሁ like and view ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ነው የውድድሩን 50% ይይዛሉ

ውድድሩ የሚቀርብበት @haniya_calligraphy
@haniya_calligraphy
@haniya_calligraphy

ወሰላሙ አሌይኩም መልካም እድል ❤️❤️😘
አላህ ሆይ እዝነትህን 🤲😥

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
Forwarded from [ IKRAM ISLAMIC CALLIGRAPHY ]
صلى على من علمنا الحب♥️

@ikramislamiccalligraphy
2024/09/11 10:12:10
Back to Top
HTML Embed Code: