እንኳን ለ2018 ዓ/ም አዲስ ዓመት (እንቁጣጣሽ) በሠላም አደረሳችሁ !
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መልካም ዓዲስ አመት።
ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ | You are invited to Visit our College.
Now; we are OPEN FOR REGISTRATION for Programs:
Undergraduate
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Science
Post graduate
👉MPH in General Public Health
👉MPH in reproductive health
👉MPH in Public Health Nutrition
Contact Address:
👉Telegram: https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone: +251-944-36-80-87
👉Email: [email protected]
👉https://www.santemedicalcollege.edu.et
ዕውቀትን ለህይወት እንሰጣለን!
Bringing KNOWLEDGE to LIFE!

❤14👏1
ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም ፤ ትኩሳት እና ኦቲዝም:
<<ፓራሲታሞል ልጆችን ለኦቲዝም እየዳረገ ነው>> የሚለው ሰሞንኛ የጥናት ውጤት ሐተታና
ፓራሲታሞልን አንዲት ነፍሰጡር እናት በምን ምክነያት ልትወስድ ትችላለች? የሚለውን መረጃ ልስጥ። በእርግዝና ወቅት እናቶች በጀርም መወረር (Infection) ሲጠቁ የሰውነት ሙቀት መጨመር ያጋጥማቸዋል። የሙቀት መጨመር በፓራሲታሞል ይታከማል። ሌላው የራስ ምታት ህመም ሲገጥማቸው ፓራሲታሞልን ይወስዳሉ።
ከፓራሲታሞል ውጪ ለእርጉዝ ሴት ጥሩ የሆነ የህመም እና የሚቀት መጨመር ማከሚያ መ'ዳኒት የለም። አማራጭ የሌለውን መ'ዳኒት እንዳይወስዱ ያደርግ ይሆን?
አሁን ፓራሲታሞልም መዘዝ ይዞ መጥቷል የሚል ጥናት ይፋ ተደረገ በሚል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። የጥናቱን ዝርዝር ግኝትና ምክረ ሐሳብ ለአንባቢያን ላካፍል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ርዕሶችን አንባቢያን በጥልቀት እንዲያዩና እንዲያነቡ እጋብዛለሁ። ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም ፤ ትኩሳትና ኦቲዝም የሚሉትን ተረድተው ሲጨርሱ በፓራሲታሞል ዙሪያ ያለውን ውዝግብ መልስ ይሰጥዎታል።
ጥናቱ በዚሁ ወርሐ ነሐሴ ይፋ የሆነ ነው። ያለፉ ጥናቶችን ሰብሰብ አድርጎ የሚደረግ የጥናት አይነትን መሰረት አድርጎ የተጠና ነው ። ጥናቱ 46 የቀደሙ ጥናቶችን አቅፏል። ከነዚህ መካከል በ6 ጥናቶች ውስጥ ፓራሲታሞል ለኦቲዝም አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ሲያሳዩ ፤ በ20 ጥናቶች ውስጥ ደግሞ የትኩረት ማጣትና መቅቀዝበዝ ችግር (ADHD)፤ በተቀሩት 18 ጥናቶች ላይ ሌሎች የአዳጊ አንጎል እድገት ችግሮች እንዳሉ ተስተውሎባቸዋል።
ጠቅለል ሲደረግ Neurodevelopmental Disorders /የአዳጊ አንጎል ችግሮች / ፓራሲታሞልን በእርግዝና ወቀት በወሰዱ እናቶች ላይ ካልወሰዱት ከፍ ባለ መጠን ተከስቷል የሚል ነው። በዚህ ጥናት ላይ ፓራሲታሞልን ባልወሰዱ እናቶች ላይም ኦቲዝም እና ሌሎች የአዳጊ አንጎል ችግሮች መከሰታቸውን ያሳያል። ከዚህ የምንረዳው ፓራሲታሞል ብቸኛው የኦቲዝም መነሻ አለመሆኑን እና ፓራሲታሞልን አለመውሰድም ከዚህ ችግር ነፃ እንዳማያደርግ ነው። ልዩነቱ የቁጥር ነው።
በተጨማሪም ፓራሲታሞል መንስኤ ነው ሳይሆን የተባለው ፓራሲታሞል በወሰዱት ላይ መጠኑ ጨምሯል ነው ያለው። ይኸ ማለት የcause and effect ግንኙነት ይኑረው አይኑረው በሚለው ዙሪያ በዚህ ጥናት አልተዳሰሰም። በጥናቱ ማጠቃለያ ላይ ፓራሲታሞል አትውሰዱ የሚል መልእክት ሳይሆን አግባብነት ያለው አወሳሰድ ይኑር ነው የሚለው። መጠኑ የተመጠነ፣ ለአጭር ግዜና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ መወሰድ እንዳለበት ምክረ ሐሳብ አጥኚዎቹ አስቀምጠዋል። ለዚህ ደግሞ የሚከተለው ሌላኛው ጥናት(2) የፓራሲታሞልን አስፈላጊነት ይተነትናል።
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የሰውነት ትኩሳት (ሙቀት መጨመር) ካልታከመ የኦቲዝም የመከሰት እድልን በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። የሙቀት መጨመር በተለይ ከሶስት እስከ ስድስተኛው የእርግዝና ወራት ሲኖር ኦቲዝም የመከሰት እድሉን በብዙ እጥፍ ያሳድገዋል። ይኸን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት ትኩሳት በአፋጣኝ መታከም አለበት። ለዚህ ደግሞ ያለን አማራጭ ፓራሲታሞል ነው። ከፓራሲታሞል ውጪ ያሉ የሙቀት ማከሚያ መድሐኒቶች ለእርጉዝ እናት አደገኛ ናቸው።
ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም በሁለት መንገድ ይያያዛሉ። የመጀመሪናው ፓራሲታሞልን በወሰዱ እናቶች ላይ ኦቲዝም ከፍ ባለ መጠን እንዲታይ ሲያደርግ በሌላ መንገድ ደግሞ በፓራሲታሞል የታከመ ትኩሳት የኦቲዝምን መከሰትን ሲቀንስ ያሳያል። እንግዴህ ማመዛዘንና የትኛው የተሻለ ውጤት አለው? የሚለውን ገምግሞና ተወያይቶ ማስኬድ እንደሚገባ ጥናቶቹ ያሳዩናል።
<<ፓራሲታሞል ብወስድ ወይስ ባልወስድ ነው >>? የሚሻለኝ የሚለውን ጥያቄ በአፅኖት መመልከት ተገቢ ነው። አሁን ባለው የጥናት መረጃ መሰረት መውሰድ ካለመውሰድ የተሻለ ነው። ነገር ግን አወሳሰዳችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። የሚወሰደውን መጠን መመጠን (ሁለት ክኒን ከመውሰድ አንድ ኪኒን ማድረግ)፤ ለብዙ ቀናት ከማዘዝ ለአጭር ቀናት ማዘዝ፤ ለሙቀት መጨመር መንስኤ የሆነውን በፍጥነት ለይቶ አስፈላጊውን ህክምና መስጠት ... በትኩሳት የሚጨምረውን የኦቲዝም መጠን ቀንሶ በፓራሲታሞል መውሰድ የሚፈጠረውን ጭማሬ መቀነስ የሚያስችለን ተመራጭ እርምጃ ነው። በቀጣይ በሚደረግ ጥናት አዲስ ምክረ-ሐሳብ እስኪመጣ ማድረግ ያለብን ከላይ የጠቀስኩትን ብቻ ነው።
ልብ ይበሉ ! ፓራሲታሞል የሚሹ ሁነቶችን አለማከም የበለጠ አደገኛ እንደሆነ ጥናቶች አሳይተዋል። አግባብነት ያለው የፓራሲታሞል አወሳሰድን ተግባራዊ እናድርግ የሚለው የህክምና መርህ አሁንም መተግበር እንዳለበት ጥናቱ አስቀምጧል። ከዚህ ውጪ ፓራሲታሞልን በጭራሽ አትውሰዱ ለሚሉት ትኩሳትና ኦቲዝም የሚለውን ሁለተኛውን ጥናት ገብተው ያንብቡ። ትኩሳት ከፓራሲታሞል ከፍ ባለ መጠን ከኦቲዝም ጋር የተያያዘ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው።
References
1) Prada, D., Ritz, B., Bauer, A.Z. et al. Evaluation of the evidence on acetaminophen use and neurodevelopmental disorders using the Navigation Guide methodology. Environ Health 24, 56 (2025). https://doi.org/10.1186/s12940-025-01208-0
2 ) Croen LA, Qian Y, Ashwood P, Zerbo O, Schendel D, Pinto-Martin J, Daniele Fallin M, Levy S, Schieve LA, Yeargin-Allsopp M, Sabourin KR, Ames JL. Infection and Fever in Pregnancy and Autism Spectrum Disorders: Findings from the Study to Explore Early Development. Autism Res. 2019 Oct;12(10):1551-1561. doi: 10.1002/aur.2175. Epub 2019 Jul 17. PMID: 31317667; PMCID: PMC7784630.
ዶ/ር መስፍን በኃይሉ : የአንጎል ፣ ህብረ-ሰረሰርና ነርቭ-ዘንግ እና ጡንቻ ህክምና እስፔሻሊስት ፤ ረ/ፕሮፌሰር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስና ሐኪም ግዛው ሆስፒታል
@HakimEthio

❤75👍10👏3
🌼 ኦንኮ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ሴንተር የ2018 ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ህፃናት ህክመና ክፍል በመገኘት ለታካሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ እና በዓሉን ከሀኪሞች፣ ነርሶች፣ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በማሳለፉ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።
አዲሱ አመት የሰላም የደስታ እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን!
🌼 መልካም በዓል! 🌼
📍አዳማ 04 ቀበሌ ወደ ገንደ ጋራ በሚወስደዉ መንገድ ላይ
📞 0949000086 | 0949000066

❤9👍1
ዳህራይ ፍርምባ እንቅርት (Retrosternal Goiter): የማህበረሰባችን የተደበቀ ስጋት!
🦋 ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የታይሮይድ በሽታዎች አሁንም ጉልህ ነገር ግን ብዙም ያልታወቁ የህዝብ ጤና ስጋት ናቸው። ከነዚህም መካከል፣ ዳህራይ ፍርምባ እንቅርት ወይም “retrosternal goiter” ተብሎ የሚጠራው የበለጠ ግንዛቤ የሚያስፍልገው ሁኔታ ነው።
🦋 በአጠቃላይ እንቅርት የሚያመለክተው የታይሮይድ እጢ መጠን መጨመርን ሲሆን፣ የታይሮይድ እጢ ደግሞ በአንገት ስር የሚገኝ የቢራቢሮ 🦋 ቅርጽ ያለው አካል ነው።
ብዙ እንቅርቶች በአንገት ላይ የሚታዩ ወይም የሚዳሰሱ ሲሆኑ፣ ዳህራይ ፍርምባ እንቅርት ወደ ደረት ዉስጥ፣ ከፍርምባ (የጡት አጥንት) ጀርባ ወደ ታች ያድጋል። በዚህ የተደበቀ ቦታ ምክንያት, ከባድ ችግሮች እስኪያመጣ ድረስ ሳይታወቅ ሊቆይ ይችላል.
ለምን ዳህራይ ፍርምባ እንቅርት አሳሳቢ ሆነ?
🇪🇹 ብዙ ኢትዮጵያውያን ከሚያውቁት የእንቅርት በሽታ በተለየ የዳህራይ ፍርምባ እንቅርት በሽታ በጊዜ ለመለየት በጣም ከባድ ነው። 🌰 በደረት ውስጥ የሚገኙትን የንፋስ ቧንቧዎች (ትራኪ)🌬, የምግብ ቧንቧ 🍽 እና ዋና ዋና የደም🩸 ቧንቧዎችን መጨፍለቅ🗜 ይችላል.
ይህ ወደሚከተለው ሊያመራ ይችላል-
🦋በተለይ በሚተኛበት ጊዜ የመተንፈስ ችግር።
🦋በመተንፈሻ ቱቦ መጥበብ ምክንያት የሚመጣ ማንኮራፋት ወይም ሲር ሲር የሚል ጩኸት።
🦋ጠጣር ምግቦችን ለመዋጥ መቸገር።
🦋በአንገት ወይም ፊት ላይ የደም ሥር ማበጥ፣ በደም ሥሮች ላይ በሚፈጠር ግፊት ምክንያት የሚከሰት።
🦋ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች፣ ለሕይወት አስጊ የሆነ ድንገተኛ የአየር መተላለፊያ መዘጋት ሊያጋጥም ይችላል።
🇪🇹 በሀገራችን ኢትዮጵያ የአዮዲን እጥረት በስፋት ተስፋፍቶ ስለነበር የታይሮይድ እጢ መጨመር የተለመደ ነው። የጨው አዮዲን መጨመር ሁኔታውን ቢያሻሽልም፣ ለዓመታት የቆዩ ትልልቅ ጎይተሮችን ያዳበሩ ሰዎች አሁንም እንደገና ለዳህራይ ፍርምባ እንቅርት ሊጋለጡ ይችላሉ።
በምርመራ ወቅት ያሉ ተግዳሮቶች
አንዱ ትልቁ ፈተና የዳህራይ ፍርምባ እንቅርት ሁልጊዜ ከውጭ የሚታይ አለመሆኑ ነው። ብዙ ሕመምተኞች አደጋውን ሳይገነዘቡ ለብዙ ዓመታት አብረው ይኖራሉ, ምልክቶቹ ከባድ እስኪሆኑ ድረስ። ለምርመራው ብዙ ጊዜ እንደ የደረት ኤክስሬይ፣ አልትራሳውንድ ወይም ሲቲ ስካን ያሉ ምስሎችን ይፈልጋል፣ በኢትዮጵያ አካባቢዎች በቀላሉ የማይገኙ ምርመራዎች።
ሕክምናው ምን መሆን አልበት?
😷 ለዳህራይ ፍርምባ እንቅርት ዋናው ሕክምና የጨመረው የታይሮይድ እባጭ ለማስወገድ ቀዶ ጥገና ነው. ይህ እንቅርት ወደ ደረት ስለሚዘልቅ እና አስፈላጊ የሆኑ መዋቅሮችን ሊጨምቅ ስለሚችል የተካኑ የቀዶ ጥገና ቡድኖችን የሚፈልግ ቀዶ ጥገና ነው።
❎ በአንዳንድ ሁኔታዎች, እንደ የደረት አጥንት መክፈት የመሳሰሉ ልዩ ኦፕራሲዎኖችን ሊያስፈልግ ይችላል። እንደ እድል ሆኖ, በጊዜ ከተሰራ ቀዶ ጥገና ምልክቶችን ለማስታገስ ብቻ ሳይሆን ሕይወትን አስጊ ከሆኑ ችግሮች ለመታደግ ይጠቅማል🤷🏿♂️🤷♂️።
🙏🏻አመሰግንለሁ ዶ/ር አለምነህ ምትኩ: የቀዶ ህክምና ሀኪም
ለመሰል ምክር ይከታተሉ https://www.tiktok.com/@dr_alemneh_surgeon?_t=ZS-8zf4hX7refI
0930005416

❤27👍2
🙋 አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ!
የካንሰር ስፔሻሊስት ዶክተር በመሆኔ አልፎ አልፎ የሚፈትነኝ የሞያ አጋጣሚ አለ። እሱም የታካሚው የቅርብ ሰዎች በተቻለ መጠን ሁሉንም የታካሚውን የህክምና መረጃ ከታካሚው እንድደብቅላቸው የሚጠይቁበት አካሄድ ነው።
መነሻው ለታካሚው ከማሰብ እና በሀሳብ/በጭንቀት እንዳይጎዳባቸው ከመመኘት እንደሆነ እገምታለውኝ። ቢሆንም ይህንን ማድረግ ታካሚዎች ስለ ህክምናቸው የማወቅ መብታቸው እንደተጨፈለቀ እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ይህም በህክምና ሂደቱ ላይ እምነት እንዲያጡ እንዲሁም ህክምናቸውንም እንዲያቋርጡ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
በሀገራችን በዚህ ጉዳይ ላይ የተወሰኑ ጥሩ ምርምሮች የተደረጉ ሲሆን ሁለቱን በጥቂቱ እንድናያቸው ወደድኩኝ። የመጀመሪያው ጥናት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ታካሚዎች ላይ የተደረገ ሲሆን፥ ድምዳሜው ይህንን ይመስላል።
"ታካሚዎች ቤተሰቦቻቸው ከሚጠብቁት (ከሚፈቅዱላቸው) በላይ ስለ ህክምናቸው በቂ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ።"
ሁለተኛው ጥናት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የተደረገ ነው። ይህ ጥናት ለየት ያለ እና የሚያስገርም ውጤት ነበር ያሳየው። ይህም -
"84% የሚሆኑ የታካሚ ቤተሰቦች (ቢቻል) ለታካሚው ስለ ህመሙ ዓይነት ምንም ባይነገረው ይፈልጋሉ። ነገር ግን እነዚህ የታካሚው የቅርብ ሰዎች የካንሰር ህመም ቢገኝባቸው ግን ምንም ዓይነት መረጃ እንዲደበቅባቸው አይፈልጉም።"
ከራሴ የህክምና ልምድ እና እነዚህን ምሰል ጥናቶችን ከግምት ውስጥ አስገብቼ አንድ ነገር በግልጽ መነገር እንዳለበት ነው የተረዳውት። እሱም -
የታካሚዎች በህክምና ሂደት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማክበር የሁላችንም ሀላፊነት ነው።
⁉️ እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Dr. Abraham Adamu: Assistant Professor of Clinical Oncology

❤34👍12