Telegram Web
LCH article.pdf
2.8 MB
Unifocal scalp langerhans cell histiocytosis in an adolescent child: A case report

Sisay Abush Mulisa: Tsion Haile Woldemariam: Birhanu Kassie Reta: 
Robel Tibebu Kasaye: Asonya Abera Akuma: Adem Reshid Abdella: Fadil Nuredin Abrar: Hidaya Yahya Mohammed: Yemane Leake Gebremichael

https://doi.org/10.1016/j.hmedic.2025.100362

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
3
s44250-025-00274-y (1).pdf
1.6 MB
Practice of preoperative care among nurses in southern Ethiopia: a multi center cross- sectional study

Deginat Tesfaye Lonsako, Biftu Geda, Tesfaye Gobena, Temesgen Kechine, Yisehak Wolde, and Sintayehu Samuel

Link: https://rdcu.be/eGl7x

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
2
World_j_surg_2025_Hsu_Current_Landscape_of_Children_s_Surgery_in.pdf
1.1 MB
Current Landscape of Children's Surgery in Africa: A Multicenter Analysis of 16,000 Cases

Phillip J. Hsu | Madeleine Carroll | Alan Zambeli‐Ljepovic | Bolusefe Tijesuni Olatunji‐Banire| Pawan Mathew |Jason Axt| Thierno Diallo | Mekonen Eshete | Bertille Ki | Joseph Macharia | George Ngock| Absalat Serawit |Emma Bryce | Doruk Ozgediz | Maija Cheung

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
1
ድንገተኛ የህፃናት ተደጋጋሚ የሆድ ቁርጠት መንስኤ❗️

✔️ የአንጀት ውስጥ እርስ በእርስ መደራረብ አብዛኛውን ጊዜ ህፃናት ላይ የሚስተዋል የጤና እክል ሲሆን የሚከሰተውም የላይኛው የአንጀት ክፍል ልክ እንደ ቴሌስኮፕ የታችኛው የአንጀት ክፍል ውስጥ በተለያየ ምክንያት እንዲሁም ያለምንም ምክንያት እርስበርስ ተደራርቦ እና ተቀርቅሮ ሲቀር ነው። ይህም ችግር በህክመናው Intussusception በመባል ይታወቃል።

✔️ ታድያ ይህ ክስተት በጊዜ ካልታከመ የአንጀት የደም ዝውውርን በማቋረጥ የአንጀት መሞትን እንዲሁም ከባሰ የአንጀት መበስበስ እና መበሳት ከዛም በጤናማው መንገድ መወገድ ያለበት የአንጀት ውስጥ ቆሻሻ የሆድ እቃ ውስጥ በመፍሰስ እና የሆድ እቃ ግድግዳ ብግነትን በማስከተል የልጆችን ሂወት በአጭር ጊዜ ውስጥ አደጋ ላይ ይጥላል።

✔️ ይሄ የጤና እክል በብዛት እድሜያቸው ከ 6 ወር እስከ 3 አመት ያሉ ህፃናት ላይ በተለይ ከቫይረስ ጋር በተያያዘ የጉንፋን ወይም የተቅማጥ ህመም ከተከሰተተ በኋላ ሲከሰት ይስተዋላል።

✔️ በዋነኝነት የሚታዩት ምልክቶች

👉 ለጥቂት ደቂቃዎች የሚቆይ ሁለት እግራቸውን ወደ ሆዳቸው የሚያሳጥፍ ሀይለኛ የሆድ ቁርጠት መኖር እንዲሁም ከህመሙ በኋላ በመሀል ደግሞ ደህና መሆን እና ያለ ምንም የህመም ምልክት ወደ ጨዋታቸው መመለስ እና ከዛም ከትንሽ እረፍት በኋላ ተመሳሳይ የሆነ የሆድ ህመም እየደጋገመ መከሰት

👉 ከህመሙ ጋር ተያይዞ የበሉትን ማስመለስ እና ላብ ማላብ እንዲሁም ከመጠን በላይ ማልቀስና መወራጨት

👉 የሰገራ ደም መቀላቀል ወይም የተዝለገለገ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ እንዲሁም አንዳንዴ ከባሰ አንጀት በፊንጢጣ በኩል መውጣት

👉 የሰገራ መውጣትን መከልከል

👉 የሆድ መንፋት ወይም እብጠት መኖር ናቸው ።

✔️ ታዲያ ወላጆች እነዚህን የጠቀስኳቸውን ምልክቶች ካስተዋላቹ የልጅዎ ሂወት አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት በጊዜ ወደ ጤና ተቋም ልጅዎን መውሰድ ያስፈልጋል።

✔️ በጤና ተቋም የመላው እና የሆድ አካላዊ ምርመራ፣ የደም ምርመራ እና የሆድ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ችግሩ መኖር አለመኖሩ መታየት ያስፈልገዋል።

👉 የሚሰጠው ህክምና እንደተገኘው ውጤት እና ልጁ እንዳለበት የጤና ሁኔታ ይለያያል። ማለትም

1️⃣ ያለምንም ህክምና በቀጠሮ በክትትል በማድረግ

2️⃣ ያለቀዶ ህክምና በፊንጢጣ በኩል በለስላሳ ቀጭን ቱቦ በሚሰጥ ፈሳሽ ወይም አየር የተደራረበውን የአንጀት ክፍል ወደ ጤናማው ቦታው እንዲመለስ በማድረግ እንዲሁም ደግሞ

3️⃣ እንደ አስፈላጊነቱ በቀዶ ህክምና እንዲታከም ይደረጋል።

👉 በዋነኝነት የቀዶ ህክምና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታዎች

✔️ ህፃኑ በጊዜ ወደጤና ተቋም ሳይሄድ ወይም በተገቢው ምርመራ ችግሩ ሳይታወቅለት ቀርቶ ችግሩ የተከሰተበት የአንጀት ክፍል የተጎዳ ከሆነ እና የሆድ እቃ ግድግዳ ብግነት ከተከሰተ

✔️ በአልትራሳውንድ ምርመራ ሲታይ መንስኤ የሆነው ችግር ከታየ

✔️ በፈሳሹ ወይም በአየሩ ህክምና የአንጀት መደራረቡ ወደ ጤናማ ቦታው የመመለስ ተስፋ ከሌለው ወይም ተያይዞ የአንጀት መበሳት ከተከሰተ ነው።

👉 ታዲያ በቀዶ ህክምና ጊዜ የተደራሪበው አንጀት ክፍል ሲላቀቅ የአንጀቱ ክፍል የበሰበሰ ወይም የተበሳ ከሆነ የተበላሸውን ክፍል ቆርጦ ማውጣት እና የቀረውን የአንጀት ክፍል በመቀጣጠል መስፋት ያስፈልጋል።

👉 ነገርግን የተበላሸው የአንጀት ክፍል ከወጣ በኋላ የቀረው የአንጀት ክፍል የበገነ ወይም ያበጠ ከሆነ እንዲሁም ህፃኑ ላይ ተፈጠረበት ኢንፌክሽን ደረጃው ከፍ ያለ ከሆነ አንጀቱን እርስ በእርስ ለመስፋት ወይም አንጀቱን ለመቀጣጠል ስለማይቻል ለጊዜው ሰገራ ማውጫ በጎን ሆድ እቃ ግድግዳ በኩል ማውጣት ያስፈልጋል ።

👉 ከዛም አንጀቱ ወደ ጤንነቱ ሲመለስ እና የልጁ ጤንነት እንዲሁም ሰውነቱ ከህመሙ እና ከቀዶ ህክምናው ሲያገግም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አንጀቱን ወደ ቦታው መልሶ እንዲሰፋ እና ወደ ጤናማ ስራው እንዲመለስ ይደረጋል።

ስለዚህ በአጠቃላይ ለወላጆች የምመክረው ልጃቹ ላይ ተደጋጋሚ የሆነ የሆድ ቁርጠት መኖር እና ከህመሙ ጋር ተያይዞ የበሉትን ማስመለስ ካለ እንዲሁም ደም የቀላቀለ ካካ ካስተዋላቹ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የሆድ አልትራሳውን ምርመራ ልጅዎን ማስመርመር እና ችግሩ በዋነኝነት የአንጀት እርስበርስ መደራረብ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋቹሀል ማለት ነው።

ማጣቀሻ - Coran Pediatric Surgery 7th Edition

ዶ/ር ዮናታን ከተማ: በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሀኪም

ሰላምና ጤና በያላችሁበት ይሁን!

ለበለጠ ማብራሪያ 👇👇👇 መጎብኘት ይችላሉ።
YouTube - https://youtube.com/@kedmialetenawo?si=4k6s0RROG_lVCA3u

@HakimEthio
19👍2
On September 5, 2025, Addis Ababa University College of Health Sciences, Department of Surgery has successfully conducted a breast cancer surgery campaign, through the generous support of Gilando Biomedical Solutions, providing timely surgical care to patients and working toward our goal of maintaining a zero backlog.

A heartfelt thank you to Gilando Biomedical Solutions for standing with us in the fight against breast cancer and for helping us move closer to equitable access to surgical care. 💙

@HakimEthio
👍6👏32
ምዝገባ ጀምረናል | ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ :-
=============


Programs we offers:

Undergraduate programs
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Since

Post graduate programs
👉MPH in General Public Health
👉MPH in reproductive health


Contact Address:
👉Bisrate Gebreal, Doba Building, Addis Abeba , Ethiopia
.👉Telegram: https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone: +251-944-36-80-87
👉Email: [email protected]
👉https://www.santemedicalcollege.edu.et

====================
7
የቆዳ ሸንተረር (Striae Marks)
በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት

👉 የቆዳ ሸንተረር ከ52 እስከ 90% በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት በቆዳ ላይ የሚወጡ ሸንተረሮች ሲሆኑ እነኚህም የተለያዩ አይነት ከለሮች - ቀላ ያሉ፣ ወደ ወይንጠጅ የሚሄዱ፣ ነጣ ያሉ ወይም ጠቆር ያለ ከለር የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ።

👉 የቆዳ ሸንተረሮች በእርግዝና ላይ በሁሉም አይነት የቆዳ ከለር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚከሰቱ የቆዳ ለውጦች ሲሆኑ፤ በመጀመሪያ ልጅ እርግዝና ላይ ገዝፈው የሚታዩ ሲሆን በተለይ ሶስተኛው መንፈቅ ላይ (ከ 7ወር በውሀላ) በይበልጥ እይታቸው ይጨምራል።

👉 ብዙን ጊዜ እነኚህ ምልክቶች በሆድ ላይ ገዝፈው ይታዩ እንጂ በጭን፣ መቀመጫ እና በጡት ቆዳ ላይም ይወጣሉ።

💥ለምንድን ነው የቆዳ ሸንተረር የሚከሰተው?

የቆዳ ሸንተረር የሚከሰትባቸው ምክንያቶች ይህ ነው የሚባል ትክክለኛ ምክንያት ባይኖርም የብዙ ምክንያቶች ውጤት ነው ተብሎ ግን ይታሰባል። እነኚህም:-

       👉 የሆድ ቆዳ ለውጥ - ፅንሱ ባደገ ቁጥር የሆድ ቆዳሽን እየወጠረው እና እየለጠጠው ስለሚሄድ በተጨማሪም ያንቺም የሰውነት ኪሎ መጨመር የራሱ የሆነ አስተዋፅዎ ይኖረዋል

      👉 በውጥረቱም ምክንያት ቆዳ እንዲለጠጥ የሚጠቅሙ collagen(ኮላጅን) እና elastin(ኢላስቲን) የተሰኙ ንጥረ ነገሮች ስራቸውን በትክክል አለመስራት እና መቆራረጥ ወይም መሰባበር ፤ ይህም ሲድኑ የቆዳ ሸንተረር ማምጣት

     👉 በእርግዝና ጊዜ በሚኖሩ ወይም በብዛት በሚለቀቁ ንጥረ ፈሳሾች ምክንያት አንዱ የሸንተረሮቹ መንስኤ ሆኖ ይጠቀሳል

    👉 ጥቂቶቹ ደግሞ በዘረመል ችግር (genetic alteration in connective tissues) ምክንያት ሊከሰቱ ይችላል።

💥 ለቆዳ ሸንተረር የሚያጋልጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?💥

     👉 ለቆዳ ሸንተረር የሚያጋልጡ ነገሮች የተወሰኑት ያለንን ሁናቴ በማስተካከል መቅረፍ የሚቻሉ ሲሆኑ ፤ የተወሰኑት ደግሞ መቅረፍ የማይቻሉ አይነት ሊሆኑ ይችላሉ።

    👉 ባብዛኛው ለቆዳ ሸንተረር እንዳጋላጭ ሁኔታ የሚጠቀሱት:-

         📌 በእርግዝና ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ኪሎ መጨመር እና
         📌 ፅንሱ ከፍተኛ ወይም ትልቅ ኪሎ ከሆነ ነው

    👉 ሌላ ተጠቃሽ አጋላጭ ምክንያቶች ተብለው የሚጠቀሱት ደግሞ:- የቀደመ እርግዝና ላይ ሸንተረሩ ተፈጥሮ ከነበረ ፣ በቤተሰብ ከነበረ እና እርግዝና በልጅነት የተፈጠረ ከነበረ ናቸው።

💥 ምልክቶች

          👉 ብዙን ጊዜ በግራ እና በቀኝ በኩል እኩል የሚከሰቱ ሲሆን

          👉 ስፋታቸው ከ ትንሽ ሚ.ሜትር እስከ ሴ.ሜትር ሊሆኑ ይችላሉ

💥 ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዋች ላይ

         👉 በመጀመሪያ ላይ ወደ ቀይ እና ሀምራዊ ቀለም ያላቸው የቆዳ ሸንተረሮች መታየት ይጀምራሉ

         👉 ጊዜው በሄደ ቁጥር ከለራቸው ወደ ነጣ ያለ የቆዳ ሸንተረር ይቀየራል


💥 ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዋች ላይ

         👉 ሸንተረሩ ጠቆር ያለ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ሰማያዊ ከለር ሊይዝ ይችላል


💥 ህክምናው ምን ይመስላል?

         👉 የቆዳ ሸንተረር በህይወት ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት የሆነ አስጊ ሂኔታ የለም ፤ በዚህም ምክንያት ሁሉም በቆዳ ላይ የሚከሰት ሸንተረር ህክምና አያስፈልገውም።

        👉 ህክምናው ሙሉ በሙሉ ሸንተረሩን ማጥፋት አይችልም፤ ነገር ግን የሸንተረሩን ከለር መቀነስ እና አካባቢው ካለው የቆዳ ሁኔታ ጋር ለማመሳሰል መሞከር ይሆናል።

        👉 የተለያዩ የህክምና ዘዴ አይነቶች ሲኖሩ ከነኚህም ውስጥ ቆዳ ላይ የሚቀቡ ቅባቶች , እንደ Tretinoin እና Hyaluronic acid ንጥረ ነገር የያዙ መድሀኒቶች እና የጨረር ወይም የሌዘር ህክምና አይነቶች ተጠቃሾች ናቸው።

        👉 መድሀኒቶቹ (የሚቀቡትም ሆኑ የጨረር ህክምናዎቹ) በእርግዝና ወቅት በፍፁም መጠቀም አይፈቀዱም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ለፅንሱ ካላቸው ጉዳት ነው።


💥 ቀድሞ መከላከል ይቻል ይሆን?

       👉 🧴🧴በአለም ላይ ብዙ አይነት የኮስሞቲክ ውጤቶች እንደ ክሬም፣ ሎሽን፣ ቅባቶች እንደ ኮኮናት(cocoa butter) ፣ ኦሊቭ  (Olive oil)፣ ቫይታሚን E የያዙ መድሀኒቶች እና የመሳሰሉት ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝና ላይ የቆዳ ሸንተረር ይጠቅማሉ ተብለው የተሞከሩ ቢሆንም ከውጤት አንፃር ግን ምንም አይነት አመርቂ ውጤት አላመጡም።

ማድረግ የሚጠበቅብሽ ነገር

👌 ኪሎሽን መቀነስ
👌 ፈሳሽ በደንብ መውሰድ
👌 የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
👌 የቆዳ ላይ ሸንተረሮች ገና እንደታዩ ጊዜ ሳይሰጡ የቆዳ ሀኪም ማማከር :- ይህ ሸንተረሮቹ በእንጭጭነታቸው ስለሚገኙ በቀላሉ ባሉት መድሀኒቶች ማከም ስለሚቻል።
___

ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜ
ሻሊስት -  0911138054
Join the following telegram channel for more https://www.tgoop.com/DrDawitMOBGYN

@HakimEthio
9👍2
We're proud to have Dr. Mesale Solomon, an experienced and highly skilled General &  Colorectal Surgeon, as part of our team at ICMC General Hospital.

With years of surgical training and a strong commitment to patient-centered care, Dr. Mesale Solomon is dedicated to diagnosing, treating, and managing a wide range of colon, rectal, and anal conditions.

With a compassionate approach and advanced surgical expertise, we are specializes in:
🔹 Colon & rectal cancer treatment
🔹 Hemorrhoids, fistulas & fissures
🔹 Inflammatory bowel disease (IBD)
🔹 Colonoscopy & cancer screenings

Whether you're seeking answers for ongoing digestive issues or need specialized surgical care, you're in excellent hands.

⭐️ ICMC General Hospital  ⭐️
     "we care for your health"

For more information and appointment
☎️
0116678646 / 0949020202
or free call 📞 9207

Telegram  https://www.tgoop.com/icmcgeneralhospital
facebook  https://web.facebook.com/icmcgeneralhospital
tiktok         https://www.tiktok.com/@icmc_general_hospital?_t=ZM-8ti59Ze8ylJ&_r=1

📍Around CMC square behind Tsehay Real Estate


@HakimEthio
6
ብዘሀ -ቋንቋ : የአንጎል ጤና እና የመርሳት ህመም

ቋንቋ ለሰው ልጅ የተሰጠ የሒወት ብርሐን ነው። ያለ ቋንቋ ሰው ከሰው ምንም አይነት መስተጋብር አይኖረውም ፤ ቋንቋ አልባ አኗኗር ጨለማ ውስጥ ከመቀመጥ በላይ የሒወት ጨለማነት ያዘለ ነው።

ብዙ ቋንቋ መቻል በአንጎል ጤና ላይ የሚኖረው ሐይል ከፍ ያለ ነው። ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ የሚችሉ ሰዎች በአንጎል ቋት አቅማቸው (cognitive capacity ) አንድ ቋንቋ ከሚችሉት በላይ ናቸው። ቋንቋ ለሰው ልጅ አንጎል-ቋት እና የአንጎል ልኬት (Intelligenc Quotient ) መዳበርና መበልፀግ ሁነኛ መሳሪያ ነው።

ቋንቋ ለአንጎል ምግብ እና ውሐ ሆኖ ያገለግላል። ሁለት እና ከዚያ በላይ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው የማስታወስ ችሎቸው የዳበረ ነው ። ቋንቋ ማሰላለሰልን ይገነባል። ማሰትታወስ ለመማርና ለእውቀት ቅድመ ሁኔታ ነው። ማስታወስ የማይችል ሊማር አይችልም። መማር የማይችል የሰው ሰው ሆኖ ሊቀጥል አይችልም።

መማር ሲባል ሀ.ሁ..ሂ...እያሉ መቁጠር ብቻ ሳይሆን ካለፈ ልምድ መማር፣ ከተፈጥሮ መማር፣ ከሌሎች መማር፣ ከድርጊት መማር መቻልን ጭምር ነው። ፊደል ሳይቆጥር መማር የሚችል ፍጡር ነው የሰው ልጅ።

አዳዲስ ሐሳቦችን አፍልቆ ለችግሮች መፍትሔ መስጠት መቻል ሰዎችን ከሰዎች ሊለያይ የሚችል ነው። የመፍትሔ ሐሳብ አፍላቂነት በብዘሀ-ቋንቋ ይበለፅጋል። ብዙ ቋንቋ የሚችሉ ችግር ከመፍጠር ይልቅ ለተፈጠረ ችግር መፍትሔ ማመንጨት የሚችል አንጎል ባለቤት ናቸው።

ውሳኔ ሰጪነት በብዘሐ ቋንቋ ይጨምራል። አንድን ጉዳይ ተረድቶ በማገናዘብ አጥጋቢ መልስ መስጠት የሚያስችል ምጡቅ አእምሮ ያሻል። ለዚህ ሁነኛውና ተፈጥሯዊው መንገድ ሰዎች ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ እንዲያቁ ማድረግ ነው።

የመጃጀት ህመም(Dementia ) ዋነኛ ምክነያት የሆነውን Alzheimer ችግር መቀነስ የሚያስችል ነው ብዘሐ ቋንቋ ። ብዙሐ ቋንቋን የተላበሱ ሰዎች በሗለኛው ዘመናቸው የሚገጥማቸውን ትልቅ የአንጎል ህመም ማስቀረት ይችላሉ። የመጃጀት ህመም በቀላሉ በቋንቋ መከላከያ መሳሪያ መግታት የሚቻል ነው።

በሀገራችን ብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ልጆችን ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ከማጠናከር አልፎ የልጆችን የአእምሮና የአንጎል ጤና መጠበቅና ማጎልበት የሚችሉበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው። ቋንቋን ማወቅ ተፈጥሯዊ ችሎታ ነው። ቋንቋዎች ሁሉ ለሰው ልጅ አኗኗር ማቅለያነትና የሒወት ማሳለጫነት የሚውሉ መግባቢያዎች ናቸው። በቋንቋ ይበልፅጉ የአንጎል ጤናዎን ያስጠብቁ!!

References

1) Menon AJ, Malo PK, Jain S, Gandhi S, Sundarakumar JS, Rai P, Issac TG. Association between multilingualism and cognitive performance among older adults in rural southern India. J Neurosci Rural Pract. 2024 Jan-Mar;15(1):81-85. doi: 10.25259/JNRP_376_2023. Epub 2023 Oct 30. PMID: 38476421; PMCID: PMC10927057.

2)Dolas, F., Jessner, U. and Cedden, G. (2022) ‘Cognitive Advantages of Multilingual Learning on Metalinguistic Awareness, Working Memory and L1 Lexicon Size: Reconceptualization of Linguistic Giftedness from a DMM Perspective’, <i>Journal of Cognition</i>, 5(1), p. 10. Available at: https://doi.org/10.5334/joc.201.

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ : የአንጎል ፣ ህብረ-ሰረሰርና ነርቭ-ዘንግ እና ጡንቻ ህክምና እስፔሻሊስት ፤ ረ/ፕሮፌሰር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስና ሐኪም ግዛው ሆስፒታል

@HakimEthio
👍98
2025/09/17 08:48:03
Back to Top
HTML Embed Code: