Telegram Web
ብዘሀ -ቋንቋ : የአንጎል ጤና እና የመርሳት ህመም

ቋንቋ ለሰው ልጅ የተሰጠ የሒወት ብርሐን ነው። ያለ ቋንቋ ሰው ከሰው ምንም አይነት መስተጋብር አይኖረውም ፤ ቋንቋ አልባ አኗኗር ጨለማ ውስጥ ከመቀመጥ በላይ የሒወት ጨለማነት ያዘለ ነው።

ብዙ ቋንቋ መቻል በአንጎል ጤና ላይ የሚኖረው ሐይል ከፍ ያለ ነው። ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ የሚችሉ ሰዎች በአንጎል ቋት አቅማቸው (cognitive capacity ) አንድ ቋንቋ ከሚችሉት በላይ ናቸው። ቋንቋ ለሰው ልጅ አንጎል-ቋት እና የአንጎል ልኬት (Intelligenc Quotient ) መዳበርና መበልፀግ ሁነኛ መሳሪያ ነው።

ቋንቋ ለአንጎል ምግብ እና ውሐ ሆኖ ያገለግላል። ሁለት እና ከዚያ በላይ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው የማስታወስ ችሎቸው የዳበረ ነው ። ቋንቋ ማሰላለሰልን ይገነባል። ማሰትታወስ ለመማርና ለእውቀት ቅድመ ሁኔታ ነው። ማስታወስ የማይችል ሊማር አይችልም። መማር የማይችል የሰው ሰው ሆኖ ሊቀጥል አይችልም።

መማር ሲባል ሀ.ሁ..ሂ...እያሉ መቁጠር ብቻ ሳይሆን ካለፈ ልምድ መማር፣ ከተፈጥሮ መማር፣ ከሌሎች መማር፣ ከድርጊት መማር መቻልን ጭምር ነው። ፊደል ሳይቆጥር መማር የሚችል ፍጡር ነው የሰው ልጅ።

አዳዲስ ሐሳቦችን አፍልቆ ለችግሮች መፍትሔ መስጠት መቻል ሰዎችን ከሰዎች ሊለያይ የሚችል ነው። የመፍትሔ ሐሳብ አፍላቂነት በብዘሀ-ቋንቋ ይበለፅጋል። ብዙ ቋንቋ የሚችሉ ችግር ከመፍጠር ይልቅ ለተፈጠረ ችግር መፍትሔ ማመንጨት የሚችል አንጎል ባለቤት ናቸው።

ውሳኔ ሰጪነት በብዘሐ ቋንቋ ይጨምራል። አንድን ጉዳይ ተረድቶ በማገናዘብ አጥጋቢ መልስ መስጠት የሚያስችል ምጡቅ አእምሮ ያሻል። ለዚህ ሁነኛውና ተፈጥሯዊው መንገድ ሰዎች ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ እንዲያቁ ማድረግ ነው።

የመጃጀት ህመም(Dementia ) ዋነኛ ምክነያት የሆነውን Alzheimer ችግር መቀነስ የሚያስችል ነው ብዘሐ ቋንቋ ። ብዙሐ ቋንቋን የተላበሱ ሰዎች በሗለኛው ዘመናቸው የሚገጥማቸውን ትልቅ የአንጎል ህመም ማስቀረት ይችላሉ። የመጃጀት ህመም በቀላሉ በቋንቋ መከላከያ መሳሪያ መግታት የሚቻል ነው።

በሀገራችን ብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ልጆችን ሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ከማጠናከር አልፎ የልጆችን የአእምሮና የአንጎል ጤና መጠበቅና ማጎልበት የሚችሉበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው። ቋንቋን ማወቅ ተፈጥሯዊ ችሎታ ነው። ቋንቋዎች ሁሉ ለሰው ልጅ አኗኗር ማቅለያነትና የሒወት ማሳለጫነት የሚውሉ መግባቢያዎች ናቸው። በቋንቋ ይበልፅጉ የአንጎል ጤናዎን ያስጠብቁ!!

References

1) Menon AJ, Malo PK, Jain S, Gandhi S, Sundarakumar JS, Rai P, Issac TG. Association between multilingualism and cognitive performance among older adults in rural southern India. J Neurosci Rural Pract. 2024 Jan-Mar;15(1):81-85. doi: 10.25259/JNRP_376_2023. Epub 2023 Oct 30. PMID: 38476421; PMCID: PMC10927057.

2)Dolas, F., Jessner, U. and Cedden, G. (2022) ‘Cognitive Advantages of Multilingual Learning on Metalinguistic Awareness, Working Memory and L1 Lexicon Size: Reconceptualization of Linguistic Giftedness from a DMM Perspective’, <i>Journal of Cognition</i>, 5(1), p. 10. Available at: https://doi.org/10.5334/joc.201.

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ : የአንጎል ፣ ህብረ-ሰረሰርና ነርቭ-ዘንግ እና ጡንቻ ህክምና እስፔሻሊስት ፤ ረ/ፕሮፌሰር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስና ሐኪም ግዛው ሆስፒታል

@HakimEthio
11👍9
Vacancy announcement | September 16, 2025

Hayat Hospital Medical College is the pioneer private hospital providing comprehensive health care services. Our Hospital wants to recruit competent health professionals in vacant positions listed below in the hospital.

The detail of the vacancies and requirements are as follows;

1.  Clinical Nurse
Qualification – BSC in Clinical Nursing
Number – 02
Experience – 1 year and above 

2. Pharmacist
Qualification – Bachelor of clinical pharmacy (B.Pharm)
Number – 03
Experience – 1 year and above  

3.  ICU Nurse
Qualification – BSC in critical care  or BSC in Clinical Nursing
Number – 02
Experience – 1 year and above 

4. Receptionist
Qualifications: Diploma and above in information technology or management related fields.
Number: 03
Experience: 1 year and above in hospitality

5. Secretary

Qualifications: Diploma and above in Secretariat science or related fields.
Number : 02
Experience: 1 year and above in secretary, hospital experience is preferable.

Duration of vacancy: 5 Working days for all positions from the day of advertisement.

Salary:  negotiable for all positions.

Submit your CV to Hayat Hospital Administration during working hours from 8:30am – 5:00pm.
 
Hayat Hospital Medical College PLC

@HakimEthio
14👍1
🧠💉 Depo-Provera Linked to Meningioma Risk: What Clinicians and Patients Need to Know (JAMA Neurology, Sept 2025)

A U.S. study in JAMA Neurology (Xiao et al., 2025) uncovers a link between Depot Medroxyprogesterone Acetate (DMPA, Depo-Provera) and meningioma risk, guiding clinical practice and patient counseling.

🔍 Study Overview

- Design: Retrospective cohort study of 61 million women (TriNetX database).

- Goal: Assess meningioma risk with DMPA and other contraceptives.

- Outcome: Meningioma diagnosis.

📊 Key Findings

👉 DMPA: Relative Risk (RR) = 2.43 (95% CI, 1.77–3.33); Number Needed to Harm (NNH) = 1152.

👉Highest Risk in:

🩵 Women using DMPA for >4 years.

🩵Women starting DMPA after age 31

👉💊 Oral MPA: RR = 1.18 (95% CI, 1.10–1.27); NNH = 3020.

Other Contraceptives: No risk increase for Combined Oral Contraceptives, Levonorgestrel IUDs, Progestin-Only Pills, or Subdermal Implants.

🌍 Context

👉Aligns with European studies (2018–2023) showing 2–7× meningioma risk with high-dose progestins, with tumor regression possible after discontinuation.

👉 Europe’s response included warnings and lawsuits, signaling U.S. medico-legal risks.

🩺 Clinical Takeaways

1. 🗣️ Counsel Clearly: DMPA doubles meningioma risk (1 extra case per ~1150 women). Highlight low absolute risk.

2. 🧑‍⚕️ Personalize Care: Reconsider long-term DMPA (>4 years) in women over 30 or with meningioma history, NF2, or cranial irradiation.

3. 🔄 Safer Options: Suggest LNG-IUD, progestin implants, or COCPs, which show no meningioma risk.

4. 👀 Stay Alert: Investigate neurological symptoms (e.g., headaches, vision changes) with exams or MRI; consider stopping DMPA if meningioma is found.

⚖️ Medico-Legal Note

France’s lawsuits against progestin manufacturers stress documenting informed consent. U.S. providers should discuss risks and alternatives to reduce liability.

🎯 Bottom Line

👉DMPA’s meningioma risk is small but notable for long-term users or those over 30.

👉Counsel precisely, screen high-risk patients, offer alternatives, and document discussions.

👉DMPA remains valuable with informed choices.

📚 Source: Xiao et al., JAMA Neurology, September 2025

Dr.Abera Etana / Internal Medicine Resident

#MedEd #OBGYN #Neurology #FamilyMedicine #WomensHealth #Contraception #Meningioma #DMPA #PatientSafety #SharedDecisionMaking #ABE

@HakimEthio
40👍10
ሃይድሮሴፋለስ | Hydrocephalus

ሃይድሮሴፋለስ (በአማርኛ አቻ ትርጉም አላገኘሁለትም): የአንጎል አና ህብለሰረሰር ፈሳሽ ኡደት መዛባት ተከትሎ የሚመጣ የፈሳሽ መከማቸት ሲሆን ይህም በአንጎል ላይ ግፊት አና ጫና በማምጣት በዙዎችን ለሞት የዳረገ ህመም ነው::

በህፃናት አና በ አዋቂዎች አመጣጡ አና የሚያሳየው ባህሪ ይለያያል:: የህፃናት የራስ ቅል በቶሎ ስለማይገጥም ግፊቱ ሲጨምር በማደግ ትልቅ ጭንቅላት ይኖራቸዋል::

የፈሳሹ መከማቸት አንጎሉን ከራስ ቅል ጋር ስለሚጫነው አድገታቸው ዘገምተኛ ይሆናል:: ይህም ማለት ራሳቸዉን ችለው መቀመጥ በሚገባቸው ሰዓት ያንን ማድረግ ያዳግታቸዋል:: መናገር የሚገባቸዉን ያክል መናገር ይቸገራሉ:: ቀስበቀስ እይታቸው ሊጠፋ ይችላል:: አለፍ ሲል ደግሞ ለሞት ይዳርጋል ::

የራስ ቅል ከገጠመ በሁዋላ (በመሃል አናት ትር ትር የሚለው ሲጠፋ) የፈሳሹ ግፊት በቶሎ ስለሚጨምር በጣም ድንገተኛ እና ካልታከመ ለሞት ይዳርጋል::

በአብዛኛው በህፃናት የሚከሰትበት ምክንያት በተፈጥሮ ሲሆን ተያያዥ የነርቭ ዘንግ ከፍተት ችግር ሊኖራቸው ይችላል:: የጨቅላ ሕፃን እንፈክሽን ተከትሎ ሊመጣ ይችላል:: ሌላኛው አና በቶሎ መታከም የሚገባው የህፃናት አንጎል እጥኢ(Brain tumor) ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ነው::

ሕክምናዉም የ ፈሳሹን መስመር ማስተካከል ሲሆን

1: በቱቦ (shunt catheter )ከ አንጎል ወደ ሆድ (Peritoneal space)ወይም ወደ ሌላ ክፍል (pleura or atrium) እንዲፈስ ይደረጋል:: ቱቦው ከቆዳ ስር የሚያልፍ ሲሆን በዙዉን ጊዜ አድሜ ሙሉ የሚቆይ ነው::

2: በ ኢንዶስኮፕ (Endoscopic ventriculostomy) የፈሳሹን መስመር መክፈት

3: መስመሩን የዘጋዉን ዕጢ በ ቀዶ ጥገና ማስወገድ

4: ግዜያዊ ማስተገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም

5: አንዳንዴ ፈሳሹ ወደ ዉጭ በተዘጋጀለት ማጠራቀሚያ እንዲፈስ ማድረግ እና ሌሎችም::

ይህ መታከም የሚቺል ችግር የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ እና የአእምሮ አድገት ዘገም አንዲል ያደርጋል:: ሁላችንም ይመለከታልና የበኩላችን እንወጣ::

References

1. Mulugeta B, Seyoum G, Mekonnen A, Ketema E. Assessment of the prevalence and associated risk factors of pediatric hydrocephalus in diagnostic centers in Addis Ababa, Ethiopia. BMC Pediatr. 2022 Mar 18;22(1):145. doi: 10.1186/s12887-022-03212-6. PMID: 35303805; PMCID: PMC8932009.

2. Hochstetler, A., Raskin, J. & Blazer-Yost, B.L. Hydrocephalus: historical analysis and considerations for treatment. Eur J Med Res 27, 168 (2022). https://doi.org/10.1186/s40001-022-00798-6

September is hydrocephalus awareness month.
ዶ/ር ሱራፌል መኮንን: የአንጎል ህብለሰረሰር ቀዶ ጥገና ስፔሺያሊስት: Pediatric Neurosurgery Fellow)
Istanbul, Turkey

@HakimEthio
30👍4
Dear MOE/MOH

The expansion of postgraduate medical education in Ethiopia is a commendable step toward addressing the severe shortage of specialists. However, the rapid establishment of programs in newly opened universities without adequate infrastructure presents serious challenges to training quality.

For example, in Internal Medicine and Pediatrics residency programs, many trainees from new institutions are required to spend nearly half of their training period at established centers such as St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) or Addis Ababa University (AAU).

While these attachments are vital for their exposure, they also highlight the inadequacy of the home institutions to independently provide comprehensive specialist training.

This dependency undermines the credibility of the newer programs and raises concerns about the competency of their graduates.

Furthermore, learning in a fragmented, “block” or “detachment” format significantly impairs educational continuity, weakens the mentor–mentee relationship, and limits the holistic development that residency training demands.

Medical education, particularly at the postgraduate level, requires consistency, depth of supervision, and long-term patient follow-up—elements that are compromised by this arrangement.

Unless urgent measures are taken, there is a risk of producing specialists who are underprepared for independent practice. This not only endangers patient safety but also dilutes the credibility of our postgraduate training system.

To address this, expansion of programs must be aligned with readiness: minimum infrastructure, adequate faculty, and stable clinical exposure must be guaranteed before approval. New institutions should initially partner with well-established ones under a structured mentorship framework until they are capable of independent training.

In parallel, accreditation processes must be strengthened to enforce quality benchmarks, and investments made in faculty development and training resources.

The ultimate goal should not merely be increasing numbers of specialists, but ensuring that every graduate is competent, confident, and capable of delivering high-quality care. Without prioritizing quality alongside expansion, we risk undermining the very healthcare system we aim to strengthen.

Dr. Mubarek Zeynu: Consultant Internist

@HakimEthio
46👍4
🔎 የስራ ቅጥር ማስታወቂያ🔎
ድርጅታችን ኦንኮ የፓቶሎጂ ምርመራ ማዕከል ከዚህ  በታች ለተገለፀው ክፍት የስራ መደብ  ብቁ የሆኑ አመልካቾችን በማወዳደር መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ክፍት የስራ መደብ መጠሪያ:
-  ላብራቶሪ  ቴክንሺያን

የስራ ቦታ: አዲስ አበባ

የተፈለገው ባለሙያ ብዛት፡  1

ደሞዝ፧ በስምምነት

  መስፈርቶችን የምታሟሉ  አመልካቾች  ዋናውን የትምህርት ማስረጃችሁንና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን   ተመላሽ ከማይደረግ  ኮፒ ጋር  በመያዝ  በአካል በመምጣት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ በአካል መምጣት የማትችሉ በቴሌግራም ወይም በኢ.ሜል  አድራሻችን  መረጃችሁን በመላክ መመዝገብ ይቻላል፡፡

1.የምዝገባ ጊዜ  08/01/2018ዓ.ም-15/01/2018በስራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ፤
2.የመመዝገቢያ ቦታ ፡- የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም /በቴሌግራም እና በኢሜል በመላክ መመዝገብ ይቻላል፤
3.የፈተና ቀን ፡-በድርጅቱ  ቴሌግራም የሚገለፅ ይሆናል፡፡

የቴሌግራም ቁጥር -0901085242
ኢሜል [email protected]
አድራሻ፡-
ኦንኮ የፓቶሎጂ  ምርመራ  ማዕከል  አድራሻ  አ.አ እንቁላል  ፋብሪካ  ኖክ ነዳጅ ማደያ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0901085242
6
👉ያለመውለድ ችግር (መካንነት) 10 ዋና ዋና ምክንያቶች👇

ጥንዶች ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍቸው የሚጠብቁት ነገር ልጅ መውለድ ነው። አንድ ሴት ምንም የመውለድ ችግር ሳይኖርባት እና የወሊድ መከላከያ ሳትጠቀም በአንድ ወር ውስጥ የማርገዝ እድሏ 20% ሲሆን 6 ወር ውስጥ 60% እንዲሁም በ1 ዓመት 85% ነው። ለሁለት አመት ቢሞክሩ ደግሞ 95% የማርገዝ እድል አላቸው።

15% የሚሆኑ ጥንዶት በአንድ አመት ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙ ቋሚ የግብረስጋ ግንኙነት እያደረጉ የማርገዝ ችግር ያጋጥማቸዋል። ይህም መካንነት ወይም ያለመውለድ ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሎ ህክምና ይጀመርላቸዋል።

የሴቷ እድሜ ከ35 አመት በላይ ከሆነ ለ6ወር ሙከራ አድርጋ እርግዝና ካልተፈጠረ የመካንነት ህክምና መጀመር አለባት።

መውለድ ያለመቻል እጅግ በርካታ ምክንያቶች ሲኖሩት አንዳንዶቹ ወደ 20% የሚሆኑት ይህ ነው የሚባል ምክንያት የላቸውም።

ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ዋናዋናዎቹ ምክንያቶች እነሆ

1. ከወንድ በኩል የሚኖር መካንነት (male factor infertility)

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 20% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ከወንድ በኩል የሚኖር ነው።ይህም በጭንቅላት ውስጥ የሚመረት ሆርምሞን ማነስ, በዘር ፍሬ ላይ የሚያጋጥም ሰፐርም የማምረት ችግር (primary testicular defect in spermatogenesis), የወንድ የዘር ትቦ መዘጋት, እንዲሁም ምክንያቱ የማይታወቅ የወንድ መካንነት (idiopathic male infertility) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከ70-80% የሚሆነው በወንዶች በኩል የሚያጋጥም መካንነት በዘር ፍሬ (testes) በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ያለማምረት ችግር የሚመጣ ነው። ይህም በዘር (genetics) ፣ በኢንፌክሽን ፣ በአደጋ፣ ጨረር መጋለጥ፣ ለሙቀት መጋለጥ እንዲሁም የሆርሞን ማነስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

2.በሴቶች ላይ እንቁላል የመለቀቅ ችግር (ovulatory dysfunction)

25% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ምክንያት የእንቁላል ያለመለቀቅ ችግር ነው። አንዲት ሴት ስትወለድ ከ1-2 ሚሊየን የሚጠጉ እንቁላሎች በኦቫሪ ውስጥ ይኖራሉ። አነዚህ እንቁላሎች እድሜዋ አየጨመረ ሲሄድ እየቀነሱ ይመጣሉ። እርግዝና እንዲፈጠር እንቁላል ከኦቫሪ ወደ ማህፀን ግድግዳ መለቀቅ አለበት ይህ የመለቀቅ ሂደት በተለያየ ሆርሞኖች ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው። የእነዚህ ሆርሞኖች መዛባት እንቁላል እንዳይለቀቅ ሊያደርጉ ይችላሉ።
PCOS ፣ ከአንጎል የሚመነጭ ሆርሞን ማነስ፣የፕሮላክቲን መብዛት ፣ የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ/መብዛት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

3.የማህፀን ቱቦ መዘጋት

በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ እንቁላል አስተላላፊ ትቦዎች በተለያየ ምክንያት ሊዘጉ ይችላሉ። በሰርጀሪ፣ በኢንፌክሽን፣ ከማህፀን ውጭ በሚያጋጥም እርግዝና እንዲሁም በሆድ እቃ ውስጥ በሚያጋጥም ጠባሳና መጣበቅ ሊዘጋ ይችላል።

4.በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚያድግ እጢ

በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚፈጠር እጢ እንቁላልና ስፐርም ሴል እንዳይገናኙ እንዲሁም እርግዝና ከተፈጠረ በኋላም ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ሊያደርጉ ይችላሉ።

5.የማህፀን አፈጣጠር ችግር

በተፈጥሮ ለሁለት የተከፈለ ማህፀን (septated uterus) ተደጋጋሚ ውርጃ እንዲኖር እንዲሁም ምንም ማህፀን ያለመፈጠር ችግር የመካንነት ችግር ሊያመጡ ይችላሉ።

6.ኢንዶሜትሪዮሲስ (endometriosis)

ጠባሳና መጣበቅን በመፍጠር የማህፀን ትቦ እንዲዘጋ እንዲሁም በኦቫሪ ውስጥ እጢ (endometrioma) በመፈጠር የእንቁላል ማምረት ሂደትን በማወክ መካንነትን ሊያመጣ ይችላል።

7.የዘረ መል (chromosome) ችግር
Turner syndrome, down syndrome, Kallman syndrome, የተባሉ የዘረመል ችግሮች ያለመውለድ ችግር ያመጣሉ።

8.ምክንያቱ የማይታወቅ (unexplained infertility)

ብዙ ምርመራዎች ተደርገውም ምንም ምክንያት ላይገኝ ይችላል።ይህም 20% የሚሆኑት ያለመውለድ ችግር ያለባቸው ጥንዶች ላይ ያጋጥማል።

9.የግብረ ስጋ ግንኙነት አደራረግ ችግር
እርግዝና እንዲፈጠር እርግዝና የሚፈጠርበትን የወር አበባ ኡደት ጊዜ ጠብቆ የማድረግ ችግር፣ ማለስለሻ ጄሎችን መጠቀም ያለማርገዝ እድልን ይጨምራሉ። እንቁላል የሚለቀቅበትን ወቅት ጠብቆ (Fertile period) ተደጋጋሚ ግንኙነት ማድረግ የማርገዝ እድልን ይጨምራል።

10.እድሜና የአኗኗር ሁኔታ
የሴቶች እድሜ ሲጨምር የእንቁላል መጠን እየቀነሰ ይሄዳል። በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ፣ለተለያዪ ኬሚካሎች መጋለጥ፣ ለጨረር መጋለጥ፣ የክብደት መጨመር፣ ጭንቀት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መውሰድ ለመካንነት ያጋልጣል።

ዶ/ር በላይ አለሙ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
ለማማከር ☎️ +251977297156 ይደውሉ።

ቴሌግራም ይቀላቀሉ: www.tgoop.com/Wellwoman2

Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

@HakimEthio
23👍1
ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ |Did you know that Sante Medical College is:

👉Listed in the World Directory of Medical Schools
👉Accepted in the General Medical Council of UK
👉Recognized by MOE as one of the TOP 9 Universities/Colleges in the country by passing EXIT EXAM
👉Selected as the Only national Piloting OSCE Center for Dental Medicine by MOH

Which means our graduates are eligible:
👉To be International Medical Graduates (IMGs)
👉To apply for USMLE starting from year III, required for practicing in the USA
👉To take licensing examinations like the PLAB, required for practicing in the UK

Now; we are OPEN FOR REGISTRATION for Programs:

Undergraduate
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Science

Post graduate
👉MPH in General Public Health
👉MPH in reproductive health
👉MPH in Public Health Nutrition

Contact Address:
👉Telegram: https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone: +251-944-36-80-87
👉Email: [email protected]
👉https://www.santemedicalcollege.edu.et


======
https://www.tgoop.com/MedNotev
8👍2
10 ቁልፍ የህፃናት ጤናማ እንቅልፍ መሰረታዊ መርሆች | Dudhaalee Bu’uuraa  Kurnan Hirriba Gaarii  Daa’immaniif

👍1. ለልጅዎ ቋሚ የእንቅልፍ ሰዓት ያዘጋጁ።

👍2. የመኝታ እና የንቃት ሰዓት በትምህርት ቤት  እና ከትምህርት ቤት ውጭ ባሉ ምሽቶች አንድ አይነት መሆን አለበት። ከአንድ ቀን ወደ ሌላ ከ 1 ሰዓት በላይ ልዩነት ሊኖር አይገባም.

👍3. ከመተኛቱ በፊት መኝታ ቦታ ምቹ ያድርጉ።  እንደ ቴሌቪዥን መመልከት ወይም የኮምፒውተር ጨዋታዎችን መጫወትን የመሳሰሉ አነቃቂ እንቅስቃሴዎችን ከመተኛቱ በፊት ያስወግዱ።

👍4. ልጅዎን በረሃብ እንዲተኛ አያደርጉት. ከመተኛቱ በፊት ቀላል ምግብ (ለምሳሌ ወተት እና ኩኪስ) ጥሩ ነው. ከመተኛቱ በፊት በ1 ወይም 2 ሰዓት  ውስጥ ብዙ ምግብ መመገብ ግን እንቅልፍን ሊያስተጓጉል ይችላል።

👍 5. ማታ ከመተኛቱ በፊት ቢያንስ ለተወሰነ ሰዓታት ካፌይን (Caffeine) ያላቸውን ምርቶች ያስወግዱ። እነዚህም ለስላሳ መጠጥ፣ ቡና፣ ሻይ እና ቸኮሌት ያካትታሉ።

👍6. ልጅዎ በተቻለ መጠን በየቀኑ ከቤት ውጭ ጊዜ እንደሚያሳልፍ እና በመደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሳተፉን ያረጋግጡ።

👍7. የልጅዎን መኝታ ክፍል ጸጥ እና ጨለማ / ዝቅተኛ ደረጃ ያለው የምሽት ብርሃን /ያድርጉ

👍8. የልጅዎን መኝታ ክፍል በምሽት ምቹ በሆነ የሙቀት መጠን ያስቀምጡ (<24°C [75°F])።

👍9. የልጅዎን መኝታ ክፍል ለእረፍት ጊዜ ወይም ለቅጣት አይጠቀሙ💀.

👍 10. ቴሌቪዥኑን  መኝታ ክፍል ውስጥ አያስቀምጡት።

ለሁሉም ወላጆች 👨‍👩‍👧‍👦 ይህ 👁️‍🗨️ መረጃ ይደርስ ዘንድ share ያድርጉት።

Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

👍 1. Daa’imman keessaniif yeroo ciisichaa murtaa’e  qabaadhaa.

👍 2. Yeroon ciisichaa fi hirribaa ka'uu   mana barumsaa fi sanaa alatti  sa’aatii walfakkaataa ta’uu qaba. Guyyaa tokko irraa gara guyyaa biraatti garaagarummaan gara sa’aatii 1 ol jiraachuu hin qabu.

👍 3. Sa'aatii ciisichaa duraa yeroo tasgabbaa'aa taasisuu. Sochiiwwan humna guddaa qaban kan akka tapha garaa garaa fi sochiiwwan kaka’umsa qaban kan akka televijiinii ilaaluu ykn tapha kompiitaraa taphachuu  irraa fagaachuu.

👍 4. Daa'ima  keessan osoo  beela qabuu   hin raffisinaa. Ciisicha dura nyaata salphaa (fkn, aannan) nyaachuun gaariidha. Nyaanni ulfaataan yeroo ciisan sa’aatii 1 ykn 2 keessatti nyaachuun garuu hirriba gaarii akkan arganne godhuu danda’a.

# 5. Oomishaalee kaafeeniin of keessaa qaban yoo xiqqaate sa'aatii murasaaf ,osoo hin ciisin dura ,irraa fagaachuu. Isaanis  dhugaatii laallaafaa  , buna, shaayii fi chokoleetii ni dabalata.

👍 6. Daa'imni  keessan guyyaa hunda, yeroo danda’ametti  alatti dabarsuu fi sochii qaamaa akka godhuu mirkaneessaa

👍 7. Kutaa ciisichaa daa’ima keessanii callisaa fi dukkanaa’aa taasisuu.

👍 8. Kutaa ciisichaa daa’ima keessanii halkan ho’a mijataa (<24°C [75°F]) qabaachuu qaba

👍 9. Kutaa ciisichaa daa’ima keessanii  adabbiidhaaf hin fayyadaminaa.

👍10. Televijiinii kutaa ciisichaa daa’ima keessanii keessa akka hin Goone Mirkaneessaa.

👨‍👩‍👧‍👦; By Dr SAMUEL SHUMELIS : የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት : ድሬ ዳዋ

@HakimEthio
30👍6
2025/09/18 16:08:12
Back to Top
HTML Embed Code: