ጥሩ የሙያ ስነምግባር ያላቸውን ትሁት የጤና ባለሙያዎችን እናመስግን
ሐሙስ ማታ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም ከትዳር አጋሬ ጋር ለወሊድ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተገኘሁ::
ጳውሎስ ቴርሽየሪ ሪፈራል ሆስፒታል በመሆኑ ታካሚ ይበዛል:: በዕለቱ አዳር ሽፍት የነበሩ ዶክተሮች እና ሚድዋይቭስ በግልፅ የሚታየውን የሥራ ጫና ተቋቁመዉ ደስ በሚል ሁኔታ አስተናግደዉ ማዋለጃ ክፍል ላኩን:: ማዋለጃ የነበሩ ዶክተሮች እና ሚድዋይቭስ እንዲሁ ርህራሄ በተሞላበት መንገድ ተቀበሉን::
በምጥ ሰዓት ባለቤቴ ጋር እንድሆን እኝህ የርህራሄ ባለቤቶች ፈቀዱልኝ:: ሌሊቱንም ያለ እረፍት አነጉት:: በመጨረሻም በባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት እና ፈጣሪም ረድቶን በሰላም ተገላግላ ቤታችን ገባን::
እንዳከበራችሁን ፈጣሪ ክብሩን ያድላችሁ:: ዘመናችሁ ሁሉ ይባረክ::
ዶ/ር ስዩም, ዶ/ር ታምራት, ዶ/ር ሳሙኤል (Gynecology and Obstetrics final year resident) and others whom I miss to mention.
Midwives- እሸቱ መኮንን (ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ ያገዘን), ትዕግስት ትልቅሰው, ምስር, አስፋ አባተ (labour ward coordinator) and others whom I miss to mention.
Neonatal Advanced life support specialist/NALS- ዓለም
Anesthesia team- ዶ/ር ዮሐንስ (Anesthesiologist), ዶ/ር ሀያት (final year anesthesiology resident), አምደ (Anesthetist).
Nurse- ብርሃኑ and others whom I miss to mention.
Pharmacist- ሙሉጌታ, ሸዋ
- Gessesse Demissie (Anesthesia Lecturer)
@HakimEthio

❤48
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦንኮ አድቫንስድ የምርመራ ማእከል አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ከሙሉ ምርመራ ጥቅላችን ላይ
የ 30% ቅናሽ አድርጎ እየጠበቃችሁ ይገኛል።
ቅናሹ ለአንድ ወር ብቻ ስለሚቆይ ፈጥነው ቀጠሮ በማስያዝ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።
📞0945606969| 0949065555| 0949045555
🌻🌻🌻መልካም አዲስ አመት።🌻🌻🌻
💢መደበኛ የጤና ምርመራ ማድረግ ጤናችንን ለመጠበቅ እና ህመሞች ከመባባሳቸው በፊት ህክምና ለመጀመር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
ኦንኮ አድቫንስድ ድያግኖስቲክ ሴንተር
📍ቁጥር 1. እንቁላል ፋብሪካ ከ ኖክ ማደያ አጠገብ
📍ቁጥር 2. አለርት ሆስፒታል አቅራቢያ ፥አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
📍ቁጥር 3. አዳማ 04 ቀበሌ, ወደ ገንደ ጋራ በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን
📢 Join our Telegram Channel:
👉🏻https://www.tgoop.com/oncopathologydiagnosticcenter
#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours
#Oncopathology# healthcheckup
#wellnesspackage

❤7👏2
Missed duodenal injury after BAT.pdf
2.2 MB
Isolated retroperitoneal duodenal perforation after blunt abdominal trauma, an often-missed injury: A case report
Halid Melkamu, Kirubel Abebe, Fekadu Negash, Binyam Yohannes, Hilmneh Yirdaw, Mekdes Meseret
Link: https://doi.org/10.1016/j.ijscr.2025.111889
To send your papers use @HakimAds

❤10👍9
የፅንስ ፆታ ማወቅ የሚያስደስት ወይስ የሚያስጨንቅ⁉️🤔
👉🏽 ጥንዶች የእርግዝና ጊዜ ከ18 ሳምንት እስከ 22 ሳምንት በደረሰ ጊዜ የልጃቸውን ፆታ ማወቅ ይችላሉ። በተሻለ አልትራሳውንድ ደግሞ ከ12 ሳምንት ጀምሮ የሚታወቅበት ጊዜ አለ።
👉🏽 ነገር ግን ረቀቅ ባሉ የዘረመል ምርመራዎች (genetic analysis) የፅንስ ፆታ ከ9 ሳምንት ጀምሮ ማወቅ ይቻላል።
👉🏽 በIVF (In Vitro Fertilization) እርዳታ የሚወልዱ ጥንዶች ደግሞ ገና ከመጀመሪያው ውጭ ላይ የተዳቀለው የወንድ ዘር (sperm cell) እና የሴት እንቁላል(egg) የፈጠረውን ፆታ ማህፀኗ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ማወቅ ይቻላል።
👉🏽 የፅንስን ፆታ ቀድሞ ማወቅ ይጠቅማል የሚሉ ጥንዶች እንዳሉ ሁላ፤ ማወቁ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላል የሚሉም በርካታ ናቸው።
⚡️⚡️ የፅንስን ፆታ ቀድሞ ማወቅ ብዙ ጥቅም አለው የሚሉ ጥንዶች የተወሰኑት ምክንያቶችን ይዘረዝራሉ:-
✍️ስሜታዊ ዝግጅት:- ይህም በርግዝና ወቅት ከልጃቸው ጋር እንዲቀራረቡ ይረዳል ይላሉ
✍️ተግባራዊ ዝግጅት :- ስም እንደማውጣት፣ የልጅን ክፍል እንደማስጌጥ፣ ልብስ መግዛትን እና የመጨረሻ ሰዓት ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጭንቀቶችን ይቀንስልናል ይላሉ
✍️የመጓጓት ስሜትን መቀነስ :- ይህ ፆታን የማወቅ ጉጉት ጥርጣሬን ሊፈጥር ስለሚችል፤ ሌሎች እርግዝና ነክ የሆኑ ጉዳዬች ላይ ላያተኩሩ ስለሚችሉ ፥ ማወቃቸው ጉጉታቸውን ሊያረካ እንደሚችል እና እቅዶችን ማውጣት ላይ ጠንካራ እንደሚሆኑ ይናገራሉ
✍️ታላላቅ ወንድም ወይም እህት ካሉ ቀድመው ማወቃቸው የቅናት ስሜትን በተወሰነ መልኩ ሊቀንስላቸው እና እራሳቸውን በተወሰነ መልኩ እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል ተብሎ መታሰብ
✍️ከፆታ ጋር የተያያዙ የዘር ውርስ በሽታዎች ለምሳሌ እንደ ሄሞፊሊያ ለመሳሰሉት ወላጆች ለሚገጥሟቸው ችግሮች ቀድመው ዝግጅት እንዲያደርጉ መርዳት
⚡️⚡️ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆነው ፥ በተቃራኒው ደግሞ ያሉ ጥንዶች ፆታን አስቀድሞ ማወቅ የተወሰኑ ችግሮች አሉት ብለው ያስባሉ:- እነኚህም
✍️አንዲት እናት ወይም አባት ሴት ልጅ እንዲኖራቸው "ቢመኙም" ነገር ግን ወንድ ልጅ ሊወልዱ እንደሆነ አስቀድመው ቢረዱ ይህ ለወሊድ የሚሰማቸውን ደስታ እና ጉጉት ሊቀንስ ይችላል። ባልና ሚስቱ በሕፃኑ ጾታ ቢደሰቱም፣ የቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ቅር መሰኘታቸውን ሊገልጹ ይችላሉ፣ ይህ ደግሞ በጣም አስጨናቂ እና በእውነት የሚያበሳጭ ሊሆን ይችላል!
✍️የመገረም ስሜት - ብዙ ጥንዶች ህፃናቸውን በሚጠብቁበት የመጨረሻይቱ ደቂቃ ፆታውን ማወቅ የግርምት፣ ልዩ እና አስደሳች ተሞክሮ እንደሆነ ያምናሉ
✍️የፆታ አመለካከትን መቀነስ - ጾታውን አለማወቅ ወላጆች ስለ ልብስ፣ መጫወቻዎች ወይም የሕፃናት ክፍል ማስጌጫዎች አስቀድሞ ግምቶችን ከመፍጠር ወይም ባህላዊ የፆታ-ተኮር የሚጠበቁ ነገሮችን ከመግዛት እንዲቆጠቡ ሊረዳቸው ይችላል።
✍️ሁሉን ያካተተ ዝግጅት፡ ወላጆች በፆታ ላይ በተመሰረቱ የሚጠበቁ ነገሮች ከመገደብ ይልቅ የሕፃኑን መምጣት በአካታች እና በሚስማማ መንገድ ለማዘጋጀት ማተኮር ይችላሉ።
⚡️⚡️ በመጨረሻም ፆታን የማወቅ ሁኔታን ለጥንዶቹ ልተውና ፤ የሕፃኑን ጾታ ከመወለዱ በፊት ማወቅ ትክክል ወይም ስህተት የሚባል ነገር የለውም - ይህ ለባልና ሚስት ፍጹም የሆነ የግል እና ሚስጥራዊ ውሳኔ ይሆናል። ዋናው እና ጠቃሚው ነጥብ ፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ጤናማ እርግዝና እና ጤናማ ህፃን መውለድ ስለሆነ።
ለደረሳችሁ ነፍሰ ጡሮች - የአጥር ወፍ አትስማሽ እያልኩ መልካም ጊዜን ተመኘሁ።
ዶ/ር ዳዊት መስፍን
የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት
https://www.tgoop.com/DrDawitMOBGYN
https://www.facebook.com/share/15QEEDkmoB/?mibextid=wwXIfr

❤23👏6
የወር አበባ ህመም | Dysmenorrhea
✅የወር አበባ ህመም (Dysmenorrhea) ማለት የወር አበባ የሚመጣበት ወቅት የሚሰማ ህመም ነዉ። የህመሙ ደረጃ ብለያይም ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ከ1-2ቀን በየወሩ የዚህ ችግር ተጠቂ ናቸዉ።
ለአንዳንዶች ትንሽ የወገብ አካባቢ ህመም ይሰማቸዋል፤ ለሌሎቹ ግን ከበድ ያለ የህመም ስሜት እና ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ራስ ምታትና መሰል ችግሮች ልኖሩ ይችላሉ።
✅የወር አበባ ህመም ዓይነቶች👇
👉1, የመጀመሪያ (primary dysmenorrhea): ይህ ዓይነቱ የመጀመሪያዉ ወር አበባ የሚታይበት እድመ ጀምሮ የሚከሰት ነዉ። ህመሙም ጊዜዉን ጠብቆ ከሚመረተዉ Prostaglandin ከሚባል ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር ጋር የተያያዘ ነዉ። ዕድሜ ገፋ ስል እና ስወልዱ ይህ ዓይነቱ የወር አበባ ህመም እየቀነሰ ይሄዳል።
👉2, ሁለተኛዉ ዓይነት የወር አበባ ህመም (Secondary dysmenorrhea) :ይህ ዓይነቱ የወር አበባ ህመም ከመኃል የሚጀምር እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ የሚሄድ ነዉ። ይህንን የሚያስከትሉ ሌላ ችግሮች ይኖሩታል።
ለምሳሌ፦ የማህጸን ሞኝ እጢ (Myoma), Endometriosis, Adenomyosis... ያሉ ናቸዉ። ስለዚህም የትኛዉ ነዉ ምክኒያቱ የምለዉን ለማወቅና ለይቶ ለማከም በሐኪም መታየት እንዳለበት ይመከራል።
✅ህክምና
👉1, የህመም ማስታገሻ በተለይም NSIAD ቡድን የሚመደቡ እነ Ibuprofen ጠቃሚ ናቸዉ።
👉2, ለወሊድ መከላከያ የሚንጠቀማቸዉ በዉስጣቸዉ Estrogen እና progestin የተባሉ ንጥረ ነገሮችን የያዙ እንዲሁም Progestin ንጥረ ነገር ብቻ የያዙም ለወር አበባ ህመም ለማከም ይጠቅማሉ።
ከመድኃኒት ህክምና ባሻገር የወር አበባ በሚመጣበት ወቅት ሙቅ ሻዉር መዉሰድ ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሰ ማድረግ ህመሙን ይቀንሳሉ።
👉ሚታየንን እሾህ እያነሳን ጉዟችን እንቀጥል!
👉ዶ/ር ጌታሁን ወዳሎ: የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም

👍30❤27
Fellows Of the College of Ophthalmology of Eastern, Central and Southern Africa (COECSA), 2025
@HakimEthio
@HakimEthio
❤15👏7