Telegram Web
Bethel Medical College white coat ceremony, 2025

@HakimEthio
38
Amente_et_al-2025-BMC_Pediatrics.pdf
1.3 MB
Social-demographic and behavioral predictors of core indicators of complementary feeding practices among mothers of children aged 6–23 months: baseline results from a cluster-randomized trial in rural Ethiopia

Tadele Amente, Yohannes Kebede and Tefera Belachew

https://rdcu.be/euze3

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
3
የቤት ውስጥ ጥቃት ወይም የቅርብ ጓደኛ ጥቃት (Intimate partner violence - IPV)

✍️የቤት ውስጥ ጥቃት ወይም የቅርብ ጓደኛ ጥቃት (Intimate partner violence-IPV) የምንለው በgynecology ዲፓርትመንት ውስጥ ብዙ ግዜ የሚያጋጥመን ነገር ነው።

👉በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ ከ15-70% ፆታዊ ግንኙነቶች ውስጥ ሊከሰት ይችላል። እንደየሀገራቱ ይለያያል።በኢትዮጵያ የEDHS 2016 ሪፖርት 34% ቢልም ሌሎች ጥናቶች ከ50% በላይ እንደሆነ ያስቀምጣሉ።

✍️ከቤት ውስጥ ጥቃቶች ውስጥ የቅርብ ጓደኛ ጥቃት የበለጠ በብዛት ይገኛል። በወንዶችም ላይ የመከሰት እድሉ አለ መጠኑ ከሴቶች ቢያንስም (~15%)።

👉የቅርብ ጓደኛ ጥቃት (Intimate Partner Violence) ፆታዊ ትንኮሳ (እስከ መድፈር)፣ አካላዊ ጥቃት (መምታትን ጨምሮ)፣ ማስፈራራት፣ ከልክ በላይ መቆጣጠር። ብዙ ጊዜ አካላዊ ጥቃት ከሌሎች በኋላ ነው ሚመጣው። ተያያዥ ናቸው። አካላዊ ጥቃት የሚደርስባት ፆታዊ ጥቃት አብሮ ሊደርስባት ይችላል።

✍️አጋላጭ ምክንያቶች

ሴት መሆን በራሱ አጋላጭ ሲሆን አለመማር… ሥራ አጥ መሆን፣ በጓደኛቸው የኢኮኖሚ ተደጋፊ ሲሆኑ፣ ድባቴ ውስጥ መሆን፣ አጥቂው በኢኮኖሚም ሆነ በሌላ የበለጠ የበላይ ሲሆን፣ አጥቂው ቅናታዊ ተቆጣጣሪ ባህሪ ሲኖረው፣ እንዲሁም የገቢና የትምህርት ልዩነት መኖር የበለጠ አጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም አጥቂው የልጅነት ጉዳት (childhood trauma) ካለበት፣ የሥራ ና የኑሮ አለመረጋጋት ካለበት፣ እንዲሁም እፅ ተጠቃሚ ከሆነ የማጥቃት ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል።

👉በማህበረሰብ ደረጃ ደግሞ ድህነት፣ የሴቶችን መብት የሚጠብቁ ተቋማት ጠንካራ አለመሆን፣ ድርጊቱ ሲፈፀም የሚወሰነው ቅጣት አነስተኛ መሆንና ሴቶች በማህበረሰቡ ያላቸው ወግ (ቤት ውስጥ መሆን አለባቸው፣ መጨቆን አለባቸው … የሚባል ከሆነ) ለሴቶች ጥቃት በር ይከፍታል።

✍️ብዙ ጊዜ ራስ ምታት፣ የወገብ ህመም፣ የደረት ህመም፣ የማህፀን ህመም፣ የአባለዘር በሽታ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖች የመሳሰሉት በተደጋጋሚ የሚያማቸው ሰዎች (ሴቶች) ቤት ውስጥ የቅርብ ጓደኛ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ሊሆን ይችላል።

👉 በቅርብ ጓደኛ ጥቃት ምክንያት ለሥነልቦና ችግር (ድባቴ፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ ችግር፣ ከጉዳት በኋላ የአእምሮ ህመም፣ ራስን ማጥፋት (Suicide)….)፣ ለአካላዊ ጉዳት፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ የልጆች ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

✍️ የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባት ሴት ህክምና ቦታ ብትሄድ ምን ሊደረግላት ይችላል?

ደህንነቷን ለማስጠበቅና የራሷን ውሳኔ መወሰን እንድትችል ይሞከራል። ይህም ምን ያህል ለተጨማሪ ጥቃት ተጋለጭ እንደሆነች በመገምገም እና የሥነልቦና ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም በዚህ ጉዳይ የሚሰሩ ድርጅቶችን በማሳታፍ ነው።

👉የሥነልቦና ድጋፍ:— ይህ የመጀመሪያው ሊደረግላት የሚገባው ነገር ሲሆን በዚህም የሥነልቦና ድጋፍ በማድረግ መረዳት እና ማበርታት ማለት ነው። ይህም ርህራሄ (Empathy) በማሳየት የደረሰባት ነገር በሷ ጥፋት እንዳልሆነ እና በአጥቂው ያልተገራ ባህሪ እንደሆነ አስረግጦ በመንገር፣ ግላዊ ምስጢሯን በመጠበቅ ባለመፍረድ እና ባለመጫን መረዳት እና እገዛን ማድረግ ያስፈልጋል።

✍️እገዛ ስንል ርህራሄ (empathy) በማሳየት በከባድ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች በመረዳት ይህ እንደማይገባት በአፅንዖት መግለፅ ያስፈጋል።

👉የጥቃቱን አደገኝነት እና መጠን ምን ያህል እንደሆነም በደንብ መለየት መመዘን ያስፈልጋል። ለህይወት የሚያሰጋ ለሞት የሚያደርስ ሊሆን ስለሚችል በተቀመጡ የተለያዩ መለኪያዎች (Assessment Tools) በመጠቀም መለየት ያስፈልጋል። ከሚሰጠው እገዛ በተጨማሪ ከህግ አካላት ጋር ለማገናኘትና እርዳታ እንድታገኝም ለማገዝ ይጠቅማል።

✍️ አጥቂው ከቤቱ ውጪም አስቸጋሪ ከሆነ፣ ለልጆች ለጓደኛ አስቸጋሪ አይነት ከሆነ፣ የሚያስፈራራት ከሆነ፣ ተቆጣጣሪ አይነት ባህሮ ካለው፣ እፅ ተጠቃሚ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት ጉዳት አድርሶ የሚያውቅ ከሆነ፣ እና የጦር መሣርያ የሚይዝ ከሆነ ወደፊትም አደጋ የማድረስ እድሉ ከፍ ያለ ይሆናል።

👉በአጠቃላይ:—— የደረሰባትን ጉዳት ከማከም በተጨማሪ
-የሥነ ልቦና ድጋፍ
-የደረሰባትን ጉዳት በደንብ መሰነድ (ለህግ ክፍል ሊያስፈልግ ስለሚችል)
-በዚህ ጉዳይ የሚሰሩ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ጋር እንድትገናኝ መርዳት
-ህጋዊ እርዳታ እንድታገኝ ማመቻቸት
ያስፈልጋል።

References
1. William 4th edition
2. UpToDate 2025
3. EDHS 2016
4. Chernet, A.G., Cherie, K.T. Prevalence of intimate partner violence against women and associated factors in Ethiopia. BMC Women's Health 20, 22 (2020).

#gynecology #intimatepartnerviolence #sexualabuse #share

ዶ/ር ዘላለም ግርማ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት

@HakimEthio
42👍8
⭐️ የአርትሮስኮፒ ህክምና!

ይህ ዘመን አፈራሽ ህክምና መገጣጠሚያ ውስጥ የሚከሠቱ ህመሞችን እና ጉዳቶችን ለማከም የሚረዳ ሲሆን፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አነስተኛ ቀዳዳዎችን በመገጣጠሚያው ዙሪያ በመፍጠር በአንዱ ቀዳዳ ከ1.7 እስከ 7 ሚሊ ሜትር መጠን ያላቸውን አነስተኛ ካሜራዎችን በማስገባት፣ በሌላኛው ቀዳዳ ደግሞ በካሜራው እገዛ የሚከናወነውን ቀዶ ህክምና ለማከናወን የሚረዱ አነስተኛ ይዘት ያላቸውን መሳሪያዎችን በማስገባት የታመመውን ወይም የተጎዳውን የመገጣጠሚያ ክፍል ማከም ያስችላል።

ህክምናው በሠብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ስልጠና በወሰዱ የአጥንት ስፔሻሊስቶች የሚሠጥ ሲሆን፣ ከተለመደው ህክምና አንፃር የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል:

👉 ቆዳ እምብዛም ሳይከፈት የሚከናወን በመሆኑ ታካሚው ከቀዶ ህክምና በኋላ በፍጥነት እንዲያገግም ያስችላል።

👉 ቁስሉ ሲድን እጅግ በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው እና ገፅታን የማያበላሹ ጠባሳዎችን ብቻ ትቶ ያልፋል።

👉 በተለመደው የቀዶ ህክምና አሠራር (open surgery) በቀላሉ ሊደረስባቸው የማይችሉ አስቸጋሪ ቦታዎችን በካሜራ እገዛ በጥሩ እይታ ጭምር እንዲደረስባቸው ያስችላል።

👉 ከቀዶ ህክምና በኋላ በሚኖረው የማገገም ሂደት ውስጥ ቀድሞ ወደነበሩበት የብቃት ደረጃ ለመመለስ የሚያስፈልጉ ድጋፎች እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መጠን እንዲቀል ያደርጋል።

👉 ከቀዶ ህክምና በኋላ ሊከሠት የሚችልን የመገጣጠሚያ መድረቅ ይከላከላል / የመከሠት ዕድሉን ይቀንሳል።

እነኚህን እና ሌሎች ጥቅሞችን የሚያስገኘው የአርትሮስኮፒ ህክምና የተለያዩ አይነት ጅማት ጉዳቶችን፤ እንደ እግር ኳስ እና ሩጫ ባሉ ስፖርቶች ወቅት የሚከሠቱ ጉዳቶችን፤ የመገጣጠሚያ ካርትሌጅ መላላጥ ህመሞችን እና ጉዳቶችን፤ የመገጣጠሚያ መድረቅ ችግሮችን ፤ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽኖችን፤ ተደጋጋሚ የመገጣጠሚያ መውለቅ ችግሮችን፣ በመገጣጠሚያ ዙሪያ የሚከሠቱ ስብራቶችን፤ በዳሌ፣ ትከሻ ወይም ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያዎች መጥበብ ምክንያት የሚከሠቱ (impingement) ህመሞችን እንዲሁም ምክኒያታቸው በውል ያልታወቀ የመገጣጠሚያ ህመሞችን ለመለየት (diagnostic arthroscopy) እና ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል።

🔹ዶ/ር ማህደር እሸቴ : - ሲንየር ሜዲካል ስፔሻሊስት ( ኦርቶፔዲክስ ሰርጀሪ፣ ስፖርት ሜድስን እና አርትሮስኮፕ)


⭐️አይ.ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ⭐️
             ለጤናዎ እንተጋለን!!!    
    
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ     
☎️ 0116678646/ 0949020202    
ወይም በነፃ የስልክ መስመራችን    
📞 9207    

ቴሌግራም ✔️   https://www.tgoop.com/icmcgeneralhospital
ፌስቡክ
    ✔️    https://web.facebook.com/icmcgeneralhospital
ቲክቶክ      ✔️    https://www.tiktok.com/@icmc_general_hospital?_t=ZM-8ti59Ze8ylJ&_r=1
📍ሲ.ኤም.ሲ አደባባይ ከፀሀይ ሪል ስቴት ጀርባ

@HakimEthio
6
Salale University Comprehensive specialized Hospital night view

📷 Dr. Tekle Nigusu

@HakimEthio
👏3417
በኢትዮጵያ ለአእምሮ ጤና የሚመለከተው ማነው?

የአእምሮ ጤና በኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ከተነፈጋቸው እና ችላ ከተባሉ ዘርፎች አንዱ ነው።

የአእምሮ ጤና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና አጀንዳ አካል እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል፤ ነገር ግን በተጨባጭ በአመራር ደረጃ ለጉዳዩ ኃላፊነት የወሰደው አካል ማን እንደሆነ ለማየት ያስቸግራል።

በዘርፉ የምንሠራ በርካታ ባለሙያዎች የምንጠይቀው ጥያቄ አለን!!

በጤና ሚኒስቴር ውስጥ ለአእምሮ ጤና ጉዳይ በቁምነገር የሚሠራ አካል አለ ወይ? ለአእምሮ ጤና ብቻ የተቋቋመ መምሪያ ወይም የአመራር ቡድን አለ ወይ?

ምክንያቱም በተጨባጭ የምናያቸው ነገሮች በጣም አሳሳቢ ናቸው::

1. የአእምሮ ጤና ክፍል የሌላቸው ጤና ጣቢያዎች መኖራቸው

2. ግልጽ የአእምሮ ጤና አመራር የሌላቸው ሆስፒታሎች መኖራቸው

3. ወጥ የሆነ የመድሃኒት አቅርቦት አለመኖር

4. የተማሩ ነገር ግን ሥራ ላይ ያልዋሉ የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች መኖራቸው

5. በዘርፉ የተቀናጀ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አለመኖሩ

6. ራሱ የቻለ የአዕምሮ ጤና ዲፓርትመንት አለመኖሩ

7. ህክምና ያላገኙ ወይም የተዘነጉ የአእምሮ ህመምተኞች መኖራቸው

ይህ ሁኔታ በጤና ሚኒስቴር ውስጥ የኢትዮጵያን የአእምሮ ጤና ችግር በንቃት የሚከታተል እና ለተግባራዊነቱ የሚሰራ አካል/ተቋም፣ መምሪያ ወይም ቡድን መኖሩን እንድንጠራጠር ያደርገናል።

በወረቀት ደረጃ የአእምሮ ጤና መምሪያ ቢኖርም እንኳን በሚፈለገው ደረጃ ለማኅበረሰቡ ተገቢው አገልግሎት ከመስጠት አንፃር እንቅስቃሴ-አልባ ይመስላል። ምንም አይነት ግልጽ ሥራ፣ ግንኙነትም ሆነ የተቀናጀ እርምጃ አይታይም።

ጠንካራ አመራር እና ግልጽ ኃላፊነት ከሌለ

•ፖሊሲዎች/መመሪያዎች/ በወረቀት ላይ ብቻ ይቀራሉ።

•ክትትል፣ ተጠያቂነት እና የበጀት ድጋፍ አይኖርም።

•የአእምሮ ጤና ወደ ጎን መገፋቱ ይቀጥላል።

አስቸኳይ ምላሽ እና እርምጃ ያስፈልገናል!!

እንደ ሀገር የአእምሮ ጤናን እየመራ ያለው ማነው?

ለድጋፍ፣ ለቅንጅት ወይም ለትብብር የምናነጋግረው ማንን ነው?

እንደ ሀገር የአዕምሮ ጤና ዳይሬክቶሬት/ቋሚ ተጠሪ መ/ቤት/የት ነው የሚገኘው?

ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ ጤና በእውነት የምታስብ ከሆነ፣ የአእምሮ ጤና ጉዳይ በባለቤትነት ሊያዝ እና በግልጽ ሊመራ ይገባል ጉዳይ ነው። በምንም አይነት ሁኔታ ትኩረት ሊነፈግ ወይም ሊረሳ አይገባም።

አሁንም በድጋሜ እንጠይቃለን ለአእምሮ ጤና ኃላፊው ማነው?

Yordanos Yihun: Psychiatry Professional, Founder, Ethio Psychiatry

@HakimEthio
👍159👏3
Delayed Presentation of Foreign body ingestion.pdf
739.7 KB
Delayed presentation of foreign body ingestion in resource-limited setting managed with endoscopy: Case report and literature review

Wudassie Melak Asmare, Ageru  Zeleke Endalew, Addisu Assfaw Ayen,  Zelalem Mulu Lashitie, Bekalu Gashaw Teshome, Gebeyaw Addis Bezie*

Link: https://doi.org/10.1016/j.ijscr.2025.111620

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
6👍5
Transcatheter Aortic Valve Replacement (TAVR) successfully performed at Tikur Anbessa Specialized Hospital

TAVR is a life-saving, minimally invasive procedure for patients with severe aortic stenosis. For the first time, this advanced intervention has been performed inside the country by a collaborative team of international experts and committed Ethiopian professionals.

Team members
- Dr. Tesfaye Telila and Dr. Obsinet Merid, CEOs of HeartAttackEthiopia
- RN Mary McFarland
- Dr. Nish Patel
- Dr. Clifford Kavinsky
- Dr. Jim Kauten
- RCIS Sandra and Josh
- The exceptional local Ethiopian team, whose dedication, preparation, and teamwork brought this vision to life

@HakimEthio
64👍2
Radial access LAD stent (PCI) done for double vessel CAD - STEMI  at ICMC General Hospital

📌 Patient overview
A 50 years old male presented with anterior squeezing chest pain of 4 hours duration not relieved by ibuprofen associated with nausea, vomiting of ingested mater and easy fatigability.

He has No hx of HTN, or smoking.
He is a knonw DM patient on treatment not adherent to his medication

📌Physical exam
GA- Comfortable
VS- All are in normal range
PE- Unremarkable exam

📌Investigation
ECG- Inferior wall MI

ECHO- IHD with preserved LV systolic dysfunction
Angiography -Double vessel coronary artery disease (CAD) - STEMI - The left anterior descending artery (LAD) & Right Coronary Artery (RCA)

📌Diagnosis
Inferior wall STEMI + Poorly controlled T2DM

📌Procedure
Radial access LAD stent (PCI) done for double vessel CAD - STEMI

📌Post op
The patient has smooth & Fast recovery course.
ECHO - Normal Echocardiography

Radial access PCI (Percutaneous Coronary Intervention) and femoral access PCI are both techniques used to perform coronary angiography and interventions like stent placement. But Radial artery access offers many benefits to patients over femoral access, including

- Lower Risk of Complications: Radial access tends to have fewer complications related to bleeding, hematomas, and arterial dissection compared to femoral access.

- Quicker Recovery: Patients can often ambulate and sit up immediately after the procedure, leading to a quicker discharge.

- Reduced Risk of Limb Ischemia: Since the radial artery is a smaller vessel, there is a lower risk of causing ischemia (lack of blood supply) to the limb.

- More Comfortable for Patients: Since the access is at the wrist, patients can usually move around and are generally more comfortable post-procedure.

- Lower Mortality Rate: Radial access is associated with lower mortality in high-risk patients, including those with acute coronary syndrome (ACS) and those who are elderly or have comorbidity (e.g., diabetes, chronic kidney disease, etc.). This is partly due to the reduced risk of major bleeding and vascular complications (e.g., hematomas, large groin puncture) that can increase morbidity and mortality in patients.

Several studies have shown that the lower complication rates with radial access are linked to better short- and long-term outcomes, potentially contributing to a lower risk of mortality.

⭐️ ICMC General Hospital  ⭐️
"we care for your health"

⭐️አይ.ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ⭐️
             ለጤናዎ እንተጋለን!!!    
    
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ     
☎️ 0116678646 / 0949020202    
ወይም በነፃ የስልክ መስመራችን    

📞 9207    
ቴሌግራም ✔️   https://www.tgoop.com/icmcgeneralhospital
ፌስቡክ
    ✔️    https://web.facebook.com/icmcgeneralhospital
ቲክቶክ      ✔️    https://www.tiktok.com/@icmc_general_hospital?_t=ZM-8ti59Ze8ylJ&_r=1

📍ሲ.ኤም.ሲ አደባባይ ከፀሀይ ሪል ስቴት ጀርባ

@HakimEthio
10
💡ሳርኮማ እንደ አጥንት፣ ጡንቻ፣ ካርቲሌጅ፣ የደም ሥሮች ወይም ስብ ከመሳሰሉት የሰውነታችን አገናኝ ሕብረ ሕዋሳት የሚመነጭ የካንሰር አይነት ነው።

የሳርኮማ ምልክቶች ፦

🔻አብዛኛውን ጊዜ በክንድ ፣ በእግር ወይም በወገብ ውስጥ ያለ ሕመም ወይም እብጠት
🔻በጊዜ ሂደት የሚያድግ እባጭ
🔻እባጩ እንደ ቦታው ሕመም፣ መደንዘዝ ወይም የተገደበ እንቅስቃሴ ሊያስከትል ይችላል
🔻የአጥንት ሳርኮማ የአጥንት ህመም፣ እብጠትና ስብራት ሊያስከትል ይችላል
🔻የሕብረ ሕዋስ ሳርኮማ ዕጢው በጣም ትልቅ እስኪሆን ድረስ የሕመም ምልክት ላያመጣ ይችላል

የሳርኮማ መንስኤዎች :-

🔻አብዛኛውን ጊዜ ትክክለኛው መንስኤ ባይታወቅም በዘር የሚተላለፉ የክሮሞዞም መዛባቶች ሚና እንደሚጫወቱ ይታስባል
🔻በተጨማሪም ለጨረር እና ለአንዳንድ ኬሚካሎች መጋለጥ ከሳርኮማ በሽታ ጋር የተያያዘ ነው

የሳርኮማ ሕክምና፦

- ዕጢውን ለማስወገድ የሚደረግ ቀዶ ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ዋነኛው መንገድ ነው
- ከቀዶ ሕክምና በፊት ወይም በኋላ የቀሩትን የካንሰር ሴሎች ለመግደል የጨረር ሕክምና መጠቀም ይቻላል
- ከቀዶ ሕክምና በፊት ዕጢውን ለመቀነስ ወይም የቀሩትን የካንሰር ሴሎች ለመግደል ኬሞቴራፒ ለከፍተኛ ደረጃ፣ ለትልቅ ወይም ለተራቀቀ ሰርኮማ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል


🥼በኦንኮ አድቫንስድ ድያግኖስቲክ ሴንተር ከባዮፕሲ አገልግሎት ባሻገር ከ 10 በላይ የሳርኮማ የኢሚዩኖሂስቶኬሚስትሪ ምርመራዎች አሉን::

📍ቁጥር 1. እንቁላል ፋብሪካ ከ ኖክ ማደያ አጠገብ

📍ቁጥር 2. አለርት ሆስፒታል አቅራቢያ ፥አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት

  📞0945606969| 0949065555| 0949045555

#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours #HealthcareExcellence
9
Call for application

@HakimEthio
4
2025/07/12 04:53:32
Back to Top
HTML Embed Code: