አሁንም ሂድ፥ ይህንም ሕዝብ ወደ ነገርሁህ ምራ፤ እነሆ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ አለው።
ኦሪት ዘጸአት 32:34
@Hiwotegziabher
ኦሪት ዘጸአት 32:34
@Hiwotegziabher
እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።
ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
@Hiwotegziabher
ኦሪት ዘፍጥረት 28:15
@Hiwotegziabher
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት።
የያዕቆብ መልእክት 1:2, 3
@Hiwotegziabher
የያዕቆብ መልእክት 1:2, 3
@Hiwotegziabher
ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
@Hiwotegziabher
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
@Hiwotegziabher
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:3
@Hiwotegziabher
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:3
@Hiwotegziabher
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:8,9
@Hiwotegziabher
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:8,9
@Hiwotegziabher
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።
የሉቃስ ወንጌል 10:19
@Hiwotegziabher
የሉቃስ ወንጌል 10:19
@Hiwotegziabher
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:27-29
@Hiwotegziabher
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:27-29
@Hiwotegziabher
እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:15,1
@Hiwotegziabher
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:15,1
@Hiwotegziabher
ሃሌ ሉያ። 1 እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
መዝሙረ ዳዊት 116:1,2
@Hiwotegziabher
መዝሙረ ዳዊት 116:1,2
@Hiwotegziabher
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
የዮሐንስ ራእይ 3:20
@Hiwotegziabher
የዮሐንስ ራእይ 3:20
@Hiwotegziabher
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን። ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉትንም፥ ጌጠኛ ልብስም ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ። ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ተመቱ።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ። 20:21,22
@Hiwotegziabher
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ። 20:21,22
@Hiwotegziabher
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
🌻🌻🌻✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝✝✝
‹‹‹ እንኳን አደረሳችሁ ›››
✝ #መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
=>ይህች ዕለት እጅግ ክብርትና ልዕልት ናት:: አዲስ ዓመት: አዲስ ሕይወት: አዲስ ተስፋ: አዲስ በረከትን እናገኝ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ከዚህች ዕለት አድርሶናልና:: ለእርሱ ምን ይከፈለዋል? "ተመስገን" ከማለት በቀር::
=>ይህቺ ዕለት ብዙ ስያሜዎች ቢኖሯትም እነዚህን እንጠቅሳለን:-
1.ቅዱስ ዮሐንስ (መጥምቁ ዮሐንስ ርዕሰ ቅዱሳን ስለሆነ በእርሱ ተሰይማለች)
2.ርዕሰ ዐውደ ዓመት (የዐውደ ዓመቶች ራስ)
3.እንቁጣጣሽ (ንግስተ ሳባንና ንጉሥ ሰሎሞንን አንድ ያደረገች ዕለት)
4.ዕለተ ማዕዶት (መሸጋገሪያ)
5.ጥንተ ዕለታት (የዕለታት መጀመሪያ)
6.ዕለተ ብርሃን (የአዲሱን ዓመት ብርሃን የምናይባት)
=>ከምንም በላይ ግን ይህች ዕለት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት:: አሮጌው ዓመት የዚህ ዓለም ምሳሌ ሲሆን አዲሱ ደግሞ የሰማያዊው ሕይወት ምሳሌ ነው:: ዻጉሜን ደግሞ የዘመነ ምጽዓት ምሳሌ ናት:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዕለቷ ክብርት ናት::
*" ምንተ ንግበር / ምን እናድርግ? "*
+እግዚአብሔር ከእኛ ብዙና ከባድ ነገሮችን አይፈልግም:: ደግሞም አይጠብቅም:: እርሱ ቸር ነውና በአዲሱ ዓመት ከእኛ:-
1.እንፋቀር ዘንድ
2.ንስሃ እንገባ ዘንድ እና
3.የቀናውን ጐዳና እንድንመርጥ ብቻ ይፈልጋል::
*በተሠማራንበት ሥራ ሁሉ: ባለንበትም ሃገር ሁሉ እግዚአብሔርን እናክብር: ድንግል እመቤታችንን እናፍቅር: ቅዱሳንን እናስብ ዘንድ ልንተጋ ይገባል:: ለዚህም ደግሞ የሥላሴ ቸርነት: የእመ ብርሃን አማላጅነት: የቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከት ይደርብን::
✝ ዘመኑን የፍቅር: የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: ✝
+*" ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ "*+
✝ ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው:: (ማቴ. 10:3) ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም:: ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል:: በትውፊት ትምሕርት መሠረት 'በርተሎሜዎስ' የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው::
*ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል:: በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ: የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል::
*ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል:: ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው:: የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::
*ከቅዱስ ዼጥሮስ: ከቅዱስ እንድርያስ: ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል:: ሙታንን አስነስቶ: ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን አውጥቶ: ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል:: የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው: አብበው ያፈሩ ነበር::
*ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል:: በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ: ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ: አሸዋ ሞልቶ: ባሕር ውስጥ ጥሎታል:: በዚያውም ዐርፏል::
+*" ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ "*+
✝ይህቺ ሃገረ ቁልዝም ግብጽ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን ብዙ ቅዱሳንን አፍርታለች:: በተለይ የአባ እንጦንስና የልጆቹ ማረፊያ ከመሆኗ ባሻገር ቅዱስ አባ ሚልኪም ወጥቶባታል:: ቅዱሱ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ: የስለት ልጅም ነው:: ጥሩ ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ እጅግ ባለጸጐችም ነበሩ::
*በስለት መንታ ልጆችን (ሚልኪና ስፍናን) ወልደው: በሥርዓት አሳድገዋል:: ቅዱስ ሚልኪ በሕጻንነት ወራቱ ስቆና ከሕጻናት ጋር ተጫውቶ አያውቅም:: ብሉያትና ሐዲሳትን ጠንቆቆ ካጠና በኋላ እድሜው 19 ሲደርስ ወላጆቹ "እንዳርህ" አሉት:: የልቡን እያወቀ "እሺ" አላቸው::
*ቀጥሎም "ባልንጀሮቼን ልጋብዝበት" ብሎ: 1,000 ወቄት ወርቅ ተቀብሎ: በፈረስ ተቀምጦ ሔደ:: መንገድ ላይ መቶውን ለተከተሉት: 9 መቶውን ወቄት ለነዳያን: ፈረሱን ደግሞ ለአንድ ደሃ ሰጥቶ: ጡር (ጢር) ወደ ሚባል በርሃ ገሰገሰ::
*መጥፋቱ በቤተሰብ ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: እናቱም ዐይኗ ተሰወረ:: እርሱ ግን አባ አውጊን ከሚባል ባሕታዊ ሒዶ ደቀ መዝሙሩ ሆነ:: ለ3 ዓመታትም ተፈትኖ መነኮሰ::
*ከዚያም በጠባቡ ጐዳና ገብቶ በጾም: በጸሎት: በትሩፋት ከፍ ከፍ አለ:: ከቅድስናው ብዛት የተነሳ አጋንንት ገና ከርቀት ሲያዩት ይሸሹት ነበር:: የነካቸውም ሁሉ ይፈወሱለት ነበር:: በእርሱ ጸሎትም በፋርስና በሮም ሰላም ሆነ::
*አንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ሲሔድ የአገረ ገዥውን ልጅ ዘንዶ በልቶት ሲለቀስ ደረሰ:: ጸሎት አድርጐ ዘንዶውን ጠራውና "እንደ ነበረ አድርገህ ትፋው" ሲል አዘዘው:: ዘንዶውም ተፋው: ሰይጣኑም ሸሽቶ አመለጠ::
*ሃገረ ገዥው ደስ ቢለው 300 ቤቶች ያሉት ገዳም ለማር ቅዱስ ሚልኪ አነጸለት:: በዚያም 300 መነኮሳት ተሰብስበው ትልቅ ገዳም ሆነ:: ማር ሚልኪ ሁሉን ካሰናዳ በኋላ "ከዚህ አልወጣም" ብሎ በዓቱን ዘጋ:: ሰይጣን ግን "አስወጣሃለሁ" ብሎ ፎክሮ ሒዶ በንጉሡ ልጅ አደረባትና አሳበዳት::
*"ከሚልኪ በቀር የሚያሰወጣኝ የለም" አለ:: ንጉሡ ወታደሮቹን ጠርቶ "ሒዳችሁ: አባ ሚልኪን ይዛችሁ ብትመጡ ሽልማት: ካልሆነ ግን ሞት ይጠብቃችሁአል" አላቸው:: እነርሱም በጭንቅ አግኝተው "እንሒድ" አሉት:: "በሮም ከተማ በር ላይ እንገናኝ" አላቸው::
*ልክ በዓመቱ እነርሱ ሮም ሲደርሱ ማር ሚልኪ ደመና ጠቅሶ ከተፍ አለ:: ልጅቱንም አቅርቦ ሰይጣንን "እየታየህ ውጣ" አለው:: ወደል ጐረምሳ ሆኖ ወጣ:: ወስዶም አሰረው:: ከቀናት በኋላ ሕዝቡና ንጉሡ እያዩ ማር ሚልኪ ደመና ላይ ተቀምጦ: ሰይጣኑን የድንጋይ ገንዳ አሸክሞ እየነዳ ወሰደው::
*ሕዝቡም ደስ ብሏቸው በታላቅ ዝማሬና እልልታ ሸኙት:: ሰይጣኑንም ለዘለዓለም አሰረው:: ቅዱስ ሚልኪ በገዳሙ ለዓመታት ከተጋደለ በኋላ በዚህች ቀን ቅዱሳን አባ እንጦንስ: መቃርስ: ሲኖዳና ሌሎችም መጥተው: በክብር ተቀብለውት ዐርፏል:: አበው 'ትሩፈ ምግባር' ይሉታል::
+" ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት "+
✝ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በብርሃናት ላይ ተሹሟል:: ለሃገራችን ልዩ ፍቅር ያለው መልአኩ ከሔኖክ ጀምሮ የብዙ ቅዱሳን ረዳት ነው:: ዛሬ በዓለ ሲመቱ ነው::
+" ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ "+
✝ታላቁ ጻድቅ: የትእግስትም አባቷ ቅዱስ ኢዮብ በጭንቅ ደዌ ለብዙ ዘመናት በመከራ ከኖረ በኋላ በዚህች ቀን በፈሳሽ ውሃ (በዮርዳኖስ) ታጥቦ ሰውነቱ ታድሷል:: ክብርም ተመልሶለታል:: በፈሳሽ ውሃ የምንጠመቅበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::
+የበርተሎሜዎስ አምላክ ፍቅሩን: የሚልኪ አምላክ ትሩፋቱን: የራጉኤል አምላክ ረድኤቱን: የኢዮብ አምላክ ትእግስቱን ያሳድርብን::
+መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ርዕሰ ዓውደ ዓመት
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ /ማር/ ሚልኪ (ትሩፈ ምግባር)
4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅዱስ ኢዮብ ተአጋሲ
6. ሜልዮስ ሊቀ ዻዻሳት

🌼 የምወድህ ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ🥰
ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።
ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ
ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።
ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።
በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን
🌻 መልካም አዲስ ዓመት ይሁን ለኹላችን | ሠናይ ሐዲስ ዓመት ይኲን ለኲልነ
🙏🏾ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏🏾
🥰ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!🥰