tgoop.com/Hulaadiss/38742
Last Update:
አማራ ክልል በትራፊክ አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት አለፈ!
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ዐሳወቀ!።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፦ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደገለፁት ተሽከርካሪው ትናንት ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሠዎችንና እህል ጭኖ ሲጓዝ ከረፋዱ 3፡30 አካባቢ በደባርቅ ወረዳ ልዩ ሥሙ «አበርጊና» በተባለ ቦታ ላይ ሲደርስ ተገልብጦ 14 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል ።
ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ቢሆንም፤ ለመኪናው መገልበጥ ምክንያት ነው ያሉትን ኃላፊው ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል ። «ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሲመጣ የነበረ በተለምዶ ‘ካሶኒ’ እየተባለ የሚጠራ መኪና ነው፥ በየዳ አድሮ እህል ጭኖ እየመጣ ከበየዳ ወጣ እንዳለ አበርጊና ከተባለች ጎጥ ሲደርስ ተገልብጧል» ብለዋል ።
የአደጋው መንሳኤ አንዱ ከመጠን በላይ መጫን መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፦ የመኪናው አቅም ከሚችለው እህል ጭነት በላይ 50 ሠዎችን አሳፍሮ ነበር ብለዋል። ሌላው ለአደጋው መንሳኤ ተብሎ የሚገመተው አሽከርካሪው ለመስመሩ አዲስ በመሆኑ የመንገዱን ባሕርይ ዐለማወቅ ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል ። በአድጋው 12 ሠዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ፤ ሌሎች ሁለት ደግሞ ዛሬ ጠዋት ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል ። ቀሪ 37ቱ ደግሞ በተለያዩ የሕክምና ቦታዎች ሕክምና እየወሰዱ እንደሆነና 27ቱ በከባዱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።
BY Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Hulaadiss/38742