በጥምቀት በዓል መዳረሻ በርካታ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየታፈሱ መሆኑ ታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ስፍራዎች በተለይ በደማቁ የጥምቀት በአል ወቅት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ታውቋል።
እንደ ሽሮ ሜዳ፣ ፈረንሳይ፣ ካዛንችስ፣ ሳሪስ፣ አዋሬ ወዘተ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ወጣቶች በብዛት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።
ሽሮ ሜዳ አካባቢ ትናንት ማታ ከ30 በላይ ወጣቶችን የሽሮ ሜዳ ፖሊስ አፍሶ እንደወሰዳቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ የቤተክርስቲያን ጥምቀት አስተባባሪዎች እና ምንጣፍ የሚሸከሙ ልጆች መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በዛሬው እለት ሳሪስ አዲስ ሰፈር እና ብሄረ ፅጌ አካባቢ ለጥምቀት በአል የተሰቀሉ ማስዋቢያዎችን ፖሊስ በሀይል ያነሳ ሲሆን ሰቅላችኋል የተባሉ አንዳንድ ወጣቶችም እንደታሰሩ ታውቋል።
ከዚህ በፊት በየመንገዱ የሚሰቀሉ እና የኦርቶዶክስ አርማ ያለበት ባንዲራ ጭምር በፖሊስ በበርካታ ስፍራዎች እንዲወርድ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል።
ማምሻውን ከፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ፎቶ: ፋይል
መሠረት ሚዲያ

የጣርያና ግድግዳ ግብር ሕገ ወጥ ነው ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር ሕገ ወጥ ነው በሚል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱን አስታዉሶ ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ወስኖልኛል ሲል እናት ፓርቲ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል::
#ዳጉ_ጆርናል

ራሱን አግቶ ከቤተሰቦቹ ገንዘብ የጠየቀው በቁጥጥር ስር ዋለ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ጋና ዮሀንስ ቀበሌ ለቤተሰቦቹ ታግቻለሁ በማለት ብር እንዲከፈል ተጠይቆ ቤተሰቦቹ ብሩን ለመስጠት አይከል ከተማ ድረስ ተጉዘው ብሩን በተጠየቁበት አግባብ ሊሰጡ ሲል በፖሊስ በተደረገ ክትትል ሊቀበል ሲወጣ እጅ ከፍንጅ ሲያዝ ታግቻለሁ ያለው እራሱ ሆኖ ተገኝቷል።

በኢትዮጵያ ታዳጊ ሴቶች የመጀመሪያ የግብረ ስጋ ግንኙነት በ17 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ እንደሚፈፅሙ ተነገረ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የግብረ ስጋ ግንኙነት አማካይ እድሜ ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም በአሁኑ ሰአት በ17 አመት እድሜ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የመጀመሪያ የግብረ ስጋ ግንኙነትን እንደሚፈፅሙ ተነግሯል።
በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የስኩል ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ መምህር አቶ አሰፋ ስሜ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጉዳዮን አስመልክቶ በፈረንጆቹ አቅጣጠር 2021 ላይ በፒ.ኤም.ኤ ኢትዮጵያ አማካኝነት የዳሰሳ ጥናት ተደርጓል።
ጥናቱ በገጠርና በከተማ መካሄዱን የገለፁት አቶ አሰፋ ከ25 እስከ 29 ፣ ከ30 እስከ 34 እንዲሁም ከ35 እስከ 39 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ተጠንቷል ብለዋል።
በጥናቱ መሰረት ከከተማ ይልቅ የገጠር ሴቶች የመጀመሪያ ወሲብ የመፈፀሚያ እድሜ እንደሚቀንስ የተገለፀ ሲሆን እድሜያቸው ከ35 እስከ 39 ያሉ እናቶች ቀደም ብለው የመጀመሪያ የወሲብ ግንኙነትን ስለመፈፀማቸው ተገልጻል።የግዳጅ ጋብቻ መኖር በገጠር የሚኖሩ ሴቶች ቀድመው የመጀመሪያ ወሲብን እንዲፈፅሙ ያደረገ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት የነበሩ እናቶች በ16 አመት እድሜ ላይ እያሉ ይህንን ተግባራዊ ያደርጉ እንደነበር አቶ አሰፋ የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በ17 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የመጀመሪያ ጊዜ የወሲብ ግንኙነትን ይፈፅማሉ ብለዋል።
ይህም የመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ መዘግየትን ያሳያል በማለት ተናግረው፤ ሴቶች በበሰለ እድሜ ላይ ሆነው ከጋብቻና ከልጆች ፍላጎት ጋር በተገናኘ መወሰን እንዲችሉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
የቤተሰብ እቅድ ምጣኔን አስመልክቶ እድሜዋ ከ35 እስከ 39 ያለች አንዲት የገጠር ሴት በ 26 አመት እድሜ እያለች ትጠቀም እንደነበር በማስታወስ አሁን ላይ በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝ ተጠቅሷል።ይህም ለውጥ የመጣው በሴቶች ዘንድ ያለው ግንዛቤ በማደጉ እና የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት በመሻሻሉ ነው ተብሏል።
በቅድስት ደጀኔ

ትራምፕ ለጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ባይደን ምስጋና መዉሰዳቸዉን ተገቢ ያልሆነ ሲሉ ተናገሩ
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት በእርሳቸውና በመጪው አስተዳደራቸው ግፊት ባይደረግ ኖሮ ፈጽሞ ሊደረስ እንደማይችል በመግለጽ ሙሉ እውቅና ሰጥተዋል።"በዚህ ስምምነት ውስጥ ባንሳተፍ ኖሮ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በጭራሽ አይደረስም ነበር" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል ሲል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
"መንገዱን ቀይረነዋል፣ እናም በፍጥነት ቀይረነዋል፣ እውነቱን ለመናገር፣ እኔ ስልጣን ላይ ከመሆኔ በፊት ቢደረግ ይሻላል" ብለዋል።ትራምፕ በቴሌቭዥን ቀርበው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ባይደን "ምንም አላደረጉም!" ሲሉ ተናግረዋል።"ይህን ባላደርግ ኖሮ ታጋቾቹ በጭራሽ አይወጡም ነበር" ሲሉም አክለዋል። በሌላ በኩል የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱን አረጋግጧል፡፡
የቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን ስምምነቱ መጠናቀቁን አረጋግጧል።የሀገሪቱ የደህንነት ካቢኔ እና ከዚያም መንግስት ስምምነቱን ለማፅደቅ ስብሰባ ይቀመጣል፡፡ስምምነቱን የሚቃወሙት ሁለት የቀኝ ክንፍ ሚኒስትሮች ኢታማር ቤን ጊቪር እና ቤዛሌል ስሞትሪች በተቃውሞ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ተናግረዋል።
የተኩስ አቁም እና የታጋቾች የመልቀቅ ድርድር ምዕራፍ አንድ ሲያበቃ፣ መንግስትን ለማውረድ ተቃዉሞ ኃይሉን እንደማይቀላቀሉ ጠቁመዋል።የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ብሊንከን የመጀመሪያዎቹን ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾች በመልቀቅ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በታቀደው መሰረት እሁድ ይጀመራል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፤ ከምክር ቤቱ አሰራርና መመሪያ ውጪ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ መመዝበሩ በኦዲት ግኝት ተረጋገጠ
የንግድ ምክር ቤቱ በ78 ዓመታት ታሪኩ አንድም ጊዜ #የፋይናንስ_ሪፖርት አቅርቦ እንደማያውቅ የንግድ ምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሃፊና የኢኖቬሽንና የሪሶርስ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ለሜሳ ጉደታ ነግረውናል፡፡
በተቋሙ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የህግና መመሪያ ጥሰትና የሃብት ምዝበራ በተጨባጭ ማረጋገጥ በማስፈለጉ ከ2015 ዓ.ም አጋማሽ እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ያለውን በመውሰድ፤ በተሰራው ልዩ የኦዲት ምርመራ በተለያዩ ጊዜያት ከአሰራር ውጪ የወጣና የት እንደገባ የማይታወቅ ገንዘብ መኖሩ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ለአብነትም በተሰራው የኦዲት ምርመራ ምዝበራዎቹ በ321 ማስረጃዎች እንደተደገፉ የሚያስረዱት ምክትል ዋና ፀሃፊው አቶ ለሜሳ፣ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ያለ መመሪያ መከፈሉ ተረጋግጧል፤ ላልተሰጠ ስልጠና ከ223 ሚሊዮን ብር በላይ ለአባላቱ ተከፍሏል፡፡
ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ባለቤትነቱ የማህበር አባላቱ የሆነ #መኪና ያለ አግባብ ለግለሰብ በሽልማትነት መሰጠቱ ከኦዲት ግኝቱ መካከል ናቸው እነዚህ እንኳን ሲደመሩ የተመዘበረውን ገንዘብ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ያደርሰዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከካዝናው በሚሊዮኖች የሚቆጠር #ገንዘብ እየወጣ አንድ ሰው በዓመት ውስጥ 57 ጊዜ ያለ አግባብ የውጭ ጉዞ ማድረጉን የኦዲት ግኝቱ አሳይቷል፡፡
ምንም አይነት አሰራር ሳይኖር ለግለሰቦች ሽልማት እየተባለ ቅጣ ያጣ የሃብት ማድፋፋት መፈፀሙንም አቶ ለሜሳ ያነሳሉ፡፡
በዚህ ምዝበራ ውስጥ እጃቸው አለበት በሚል የቻምበሩ 4 የስራ ሃላፊዎች ከስራ እስከ ማሰናበት የደረሰ የዲሲፕሊን እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
እነዚህን ችግሮች ተመልክተን ቻምበሩ #ሪፎርም እንደሚያስፈልገው በመግባባት በተደረገው ሪፎርም የአሰራር ማሻሻያ ተደርጓልም ብለዋል፡፡
የቦርድ አባላት ለውጥ በማድረግ ትናንት ሃሙስ ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም አዳዲሶቹን የቦርድ አባላት በመረጠበት 18ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ወ/ሮ ዛህራ መሃመድን በወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ምትክ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል፡፡
11 የቦርድ አባላት ባሉት ስብስብ ኢንጂነር አበበ ጉርሜሳ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
አዳዲሶቹ ተመራጮች በገንዘብ ምዝበራ ተጠርጥረው የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደባቸው 4ቱ የቻምበሩ የስራ ሃላፊዎች በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡
ShegerFMRadio102_1
ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎቱ ተቋረጠ
ቲክቶክ ከደቂቃዎች በፊት በአሜሪካ መስራት አቁሟል።
ከቻይና መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው በአሜሪካ መንግስት ክስ የቀረበበት የቲክቶክ ዋና ድርጅት ባይት ዳንስ ማስተካከያ እንዲያደርግ ወይም የድርጅቱን የአሜሪካ ቅርንጫፍ ለአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሸጥ ተጠይቆ ነበር።
ቲክቶክ አገልግሎቱ ለ175 ሚልዮን አሜሪካውያን ዛሬ ቢቋረጥም ሰኞ እለት ወደ ስልጣን የሚመጡት ዶናልድ ትራምፕ እገዳውን እንደሚያስቆሙት ይጠበቃል።

በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል መምህራንን የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ማስገደዱ ተገለጸ
በአማራ ክልል ከመስከረም እስከ ታሕሳስ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የጉልበት ሥራ ለመስራት ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታወቀ፡፡
በክልሉ ያሉ መምህራን ለተማሪዎቻቸው ሲሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው እየሰሩ ነበር ያለው ማህበሩ፤ "አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ ካቅማቸው በላይ እየሆነ ነው" ብሏል፡፡
"ለወራት ደመወዝ ያልተከፈሉ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ ባለመቻላቸው የጉልበት ሥራ የሚሰሩ አሉ" ያሉት፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ ናቸው፡፡
"በዚህም ቀጣዩ የመምህራኑ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት የትምህርት ሥራውንም ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሄደው ለመማር ሲሞክሩ በተፈጠረ የቦታ ጥበት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲቀመጡ አስገድዷል ነው የተባለው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ መምህራንን የተመለከቱ ችግሮች በሁሉም አካባቢ አይነት እና መጠናቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡
(አሐዱ)

"በህወሓት አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - አቡነ ማትያስ
በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ።
“ሁኔታዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል ሊያጠፋ ወደሚችል ሁኔታ እያመራ ይገኛል፤ ይህንን እያየን ዝምታን መምረጥ በሰውና በፈጣሪ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ይህንን የምክር ደብዳቤ ለመጻፍ ተገድጃለሁ” ብለዋል።ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
“በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል።“በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

‹‹አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም›› ሲሉ የክለቡ አሰልጣኝ ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ የነበረው አቡበከር ናስር የዛሬ ሶስት አመት ከኢትዮጵያ ቡና ወደደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ መዘዋወሩ ይታወሳል፡፡
ይህ የሀያ አራት አመቱ ተጨዋች ለአዲሱ ክለቡ አስራ ዘጠኝ ጊዜ ከተሰለፈና አራት ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ ባጋጠመው ጉዳት የተነሳ ለበርካታ ጊዜያት ተቀያሪ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡ ይሁንና ከወራት በፊት ሰንዳውንስ በዚያው ደቡብ አፍሪካ ለሚገኝ ክለብ ለአንድ አመት በውሰት ሰጥቶት ነበር፡፡
አቡበከር ናስርም ሱፐርስፖርትስ ለተሰኘው ክለብ ለመጫወት በጥቅምት ወር የፈረመ ሲሆን በጉዳቱ በማገገሙ ለአዲሱ ክለቡ ጥሩ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተስፋ ተጥሎበት እንደነበር ጎል ዶት ኮም ገልጿል፡፡ ይሁንና ተጨዋቹ አሁን በክለቡ ውስጥ ሲሰለፍ አለመታየቱን ተከትሎ ጎል ዶት ኮም አሰልጣኙን ጠይቋል፡፡
የሱፐር ስፖርት አሰልጣኝ የሆኑት ጋቪን ሀንት ሲመልሱም ‹‹አቡበከር አሁን የት እንዳለ አላውቅም፡፡ ላለፉት ሁለት ሳምንታት አይቼው አላውቅም›› ካሉ በኋላ የልምምድ ቦታ ላይ መገኘት ማቆሙን አስረድተዋል፡፡ ተጨዋቹ ክለቡን በተቀላቀለባቸው አራት ወራት ውስጥ ያለፈቃድ ጥሎ እየጠፋ በተደጋጋሚ እንዳስቸገራቸውም ገልፀዋል፡፡ እንደጎል ዶት ኮም ዘገባ አሰልጣኙ በዚህ የተነሳ አቡበከርን ወደቀድሞ ክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመመለስ ሀሳብ አላቸው፡፡
አቡበከር በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።

በነቀምት ከተማ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ እና በቪዲዮ ቀርፆ ለማህበራዊ ሚድያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በነቀምት ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ውስጥ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀም በቪዲዮ ቀርፀው ለማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች እና ደፋሪው ግለሰብ በፍጥነት ተከታትሎ ለህግ በማቅረብ ውሳኔ ማሰጠቱን የነቀምት ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የነቀምት ከተማ አስተዳር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጥቄሳ እንደገለፁት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የተባለው ግለሰብ በነቀምት ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ የ17 ዓመቷን ታዳጊ ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች እያለ መንገድ ላይ ጠብቆ ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር አስገድዶ ወደ ጫካ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተገልጿል። አንደኛው ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ17 ዓመቷን ልጅ በዱላ እየደበደበ የለበሰችውን ልብስ ሲያወልቅ እና የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምባት ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር እና ሶስተኛ ተከሳሽ ፍራኦል ታሪኩ የተባሉት ግለሰቦች በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ ከባህል እና ወግ ውጪ አስነዋሪ ተግባሩን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።
በተጨማሪም አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ከሁለቱ ግብረአበሮቹ ጋር በመቀናጀት የ15 አመቷን ታዳጊ ጠልፈው አንደኛ ተከሳሽ የተከራየበት በመውሰድ አንደኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምበት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃቱን በእጅ ስልካቸው በመቅረፅ ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ15 ዓመቷን ታዳጊ ከነቀምት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጠልፎ በመውሰድ ከግብረአበሮቹ ጋር በማስገባት በዱላ በመደብደብ ልብሷን እንድታወልቅ በማድረግ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀምባት ሁለቱ ግብረአበሮቹ በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ አስነዋሪ ድርጊቱን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን የነቀምት ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎቹን ያስቆጣ እንደነበረ ዋና ኢኒስፔክተር ፍሮምሳ ገልፀዋል።
ፖሊስም ይህንን ከማህብረተሰቡ ባህል እና ወግ ውጪ የሆነን ድርጊት በመከታተል በጥቂት ቀናት ውስጥ የድርጊቱ ፈፃሚዎች እና ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የዚህ ድርጊት ዋነኛ ፈፃሚ እና ተባባሪዎች ላይ ምርመራ መዝገቡን በስፋት በማጣራት በሆስፒታል በተገኘ የምርመራ ውጤት እና በተጎጂዎች ቃል እንዲሁም ተከሳሾች የሰጡት የእምነት ቃል በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለአቃቤ ህግ የላከ መሆኑን ተገልፆል። አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ አንቀፅ 620 ንዕስ አንቀፅ 2 እና ንዑስ አንቀፅ 4 በመጥቀስ በጭካኔ በማሰቃየት የመድፈር ጥቃት በመፈፀም እጅግ አስነዋሪ እና የማህበረሰቡን መልካም ስነምግባር እና ፀባይ በተፃረረ መልኩ የተፈፀመ ድርጊት ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸው ክስ የተመሠረተባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በአቃቤ ህግ የቀረበውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ 12 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርፆ በማሰራጨት እና ተጎጂዋን በመጥለፍ ተባባሪ በመሆኑ በ 4 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሶስተኛ ተከሳሽ በድርጊቱ ያለው ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ በአንድ ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጢቄሳ ጨምረው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ከ 400 ሺህ በላይ ህሙማን የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም በተከሰተው የዋጋ ንረት ሳቢያ በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ተነገረ
የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ቢሆን ድጋፍ የሚያደርገው ሰዉ በጣም እየቀነሰ በመሆኑ ህሙማኑ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን የኩላሊት ህክምና እጥበት በጎ አድራጎት ማኅበር አስታውቋል ።
ማህበሩ እንዳለው አሁን ላይ ከ 400 ሺህ በላይ ሰዎች የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ የመድኃኒት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመናሩ ስቃያቸው በየዕለቱ እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል ።

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጸሙ
********
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የሀገራት መሪዎች፣ ባለሐብቶች፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት ባለቤቶች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው ቃለ መሐላ የፈጸሙት፡፡
በዋሺንግተን ዲሱ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው የቃለ መሐላ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የአሁን እና የቀድሞ መሪዎች እንዲሁም ከ500 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ከእንግዶቹ መካከል የአማዞን እና የአፕል የቴክኖሎጂ ካምፓኒ መሥራቾች ጄፍ ቤዞስ እና ቲም ኩክ፣ የሜታ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፣ የጎግል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱንዳር ፒቻይ እንዲሁም ለፕሬዚዳንቱ የምርጫ ዘመቻ ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ያዋጡት የኤክስ ባለቤት ኢሎን ማስክ እንደሚጠቀሱ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ኅዳር ወር ነበር የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ያሸነፉት፡፡

በሂጃብ ጉዳይ ነገ መቐለ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሄድ አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ፥ የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ መደረጋቸውና ከትምህርት ገበታ መራቃቸው መግለጹ ይታወሳል።
በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሦሥት ጊዜ ደብዳቤ የፃፈው እንዲሁም የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበልም በማለታቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መገደዱን ገልጿል።
በዚህም ነገ ጥዋት 1 ሰዓት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።
ሁሉም ፍትህ ፈላጊ የሰልፉ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል።
ሰልፉ ከቀናት ዓርብ ጥር 9 ሊደረግ የነበረ ቢሆንም የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ነው ለነገ የተዘዋወረው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከሂጃብ ጋር ተያይዞ የተነሳ ውዝግብ የሚመለከቱ ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ፤ ነገ ጥር 13/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ የሚካሄደው ስልፍም ተከታትሎ ያቀርባል።

በመቐለ ከተማ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል!
ፍርድቤት የትምህርተ ቤቱ በሂጃብ የተሸፈኑ ሴት ተማሪዎችን አላስተናግድም ማለቱነ በማገድ ለፈተና እንዲመዘገቡ ቢያዝም ትዕዛዙን በመተላለፍ እስካሁነ ተማሪዎቹ አልተመዘገቡም።