የቻይናው ዲፕሲክ የሳይበር ጥቃት ደረሰበት
በተለቀቀ በቀናት ውስጥ በዓለም ላይ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው የቻይናው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጋዥ መተግበሪያ (DeepSeek) የሳይበር ጥቃት እንደደረሰበት ተዘግቧል::
ዲፕሲክ የአሜሪካውን ቻትጂፒት (ChatGPT) የሚፎካከር እና ተፈላጊነቱም እያደገ መሆኑ በተዘገበ በቀናት ውስጥ ነው ከፍተኛ የተባለ የሳይበር ጥቃት የደረሰበት::
ይህን ተከትሎም ዲፕሲክ በጊዜያዊነት አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል ከማቆሙ በስተቀር ሌሎች ተጠቃሚዎች መጠቀማቸውን እንደማያስተጏጉል አስታውቋል::
በአሜሪካ አፕ ስቶር እና ጎግል ስቶር ላይ በነጻ ከሚገኙ መተግበሪያዎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘ ሆኗል::
ይህን ተፈላጊነቱን ተከትሎም ሀገራት መተግበሪያውን መጠቀም አለመጠቀም ላይ የተለያዩ ምክረሃሳቦችን እየሰጡ ነው::
በዚህ ወቅት ዲፕሲክ የደረሰበት የሳይበር ጥቃት ከማን እንደሆነ በግልፅ ባይታወቅም ከተፎካካሪዎቹ ሊሆን እንደሚችል ዘጋርዲያን ዘግቧል::

በጌታቸው ረዳ ላይ የሚደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ልንለው እንችል ይሆን ?
በዛሬው እለት የታጠቁ ግለሰቦች መቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው ነበር ተባለ
በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መሀል እየተካረረ የመጣውን ውዝግብ ተከትሎ በዛሬው እለት የታጠቁ ግለሰቦች የመቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው እንደነበር ታውቋል።
ሙከራው የተካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ቡድን አባላት መሆኑን ምንጮቻችን ጠቅሰው ሙከራው ግን ያልተሳካ ነበር ብለውታል።
"ታጣቂዎቹን ወደ ሬድዮ ጣቢያው ይዞ የገባው በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የተሾመ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የተባለ ግለሰብ ነው" ያሉት ምንጫችን ድርጊቱ ሲከሽፍ የኤፍኤም ሬድዮ ጣቢያውን ማህተም ይዘው ሲወጡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።
ምን ያህል ታጣቂዎች ወደ ሬድዮ ጣብያው እንደገቡ እንዲሁም አላማቸው ምን እንደነበር እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።
Via (መሠረት ሚድያ)-

ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወሰነ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
በዚህም ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።
በዚህ መልኩ የቀረበውን ዝርዝር ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።
ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር።
ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቶ ነበር።
ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት በሐሰተኛ ሰነድ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ በአንደኛውን ክስ ላይ መገለጹን ተከትሎ በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው በተደራራቢነት የቀረቡና ተጠቃልለው ሊያስቀጡ የሚችሉ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ፍርድ ቤቱ አብራርቶ ሁለተኛውን ክስ ውድቅ በማድረግ በአንደኛው ክስ ብቻ በከባድ አታላይነት ሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
ሆኖም ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸው ተጠቅሷል።
በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።
የሀሳብ ልዩነት ያቀረቡት አንደኛው ዳኛ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የባንክ ሂሳባቸው በመገለጹ ብቻ የወንጀል ተግባሩ በስምምነት ተፈጽሟል ለማለት አያስችልም የሚል የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጠቅሰው ልዩነታቸውን አሳይተዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ዐቃቤ ሕግ ወንጀሉ የተፈጸመው በትብብር መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ይዟል።
በዚህም1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን ያቀረቡትን አራት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 21 መሰረት በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ደግሞ እያንዳንዳቸው አራት፣ አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በዕርከን 17 መሰረት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
በፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የተወሰነውን የጽኑ እስራት ውሳኔን የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እጃቸው ከተያዘ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።
በታሪክ አዱኛ

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ ይካተታል ተባለ!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡"መከላከያና መምህር የዚህ ሀገር ምሶሶዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ ሰዎች ሙያውን ወደውት እና ዩኒቨርሲቲውን መርጠው እንዲገቡ የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።
አክለውም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲም እንደ አንድ አማራጭ እንደሚካተት ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ለሚገኙ የለውጥ ሥራዎች ድጋፍ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሣ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመጥን በቂ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Via AS

Capital News: ዩኤስኤይድ እርዳታ መቆም ያመጣዉ ጫና | የመንግስት የዉጪ ጉድለት ምን ታሰበ?
https://youtube.com/watch?v=iSLZahEICEQ&feature=shared

YouTube
Capital News: ዩኤስኤይድ እርዳታ መቆም ያመጣዉ ጫና | የመንግስት የዉጪ ጉድለት ምን ታሰበ?
The paper that promotes free enterprise Established in 1998, Capital is your Ethiopian weekly business newspaper published and distributed by Crown Publishing Plc.
Contact us: Email: [email protected]
Phone No: +251-11 618 3253 | 11 661 0976
Mobile:…

በደቡብ ሱዳን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 20 መድረሱን ፕሬዚዳንቱ አስታወቁ
ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በሰጡት መግለጫ "ይህ ልብ የሚነካ ክስተት የ 20 ንፁሃን ሰዎች ሕይወትን ቀጥፏል፣ አንድ ሰው ተርፏል" ብለዋል።
ረቡዕ ዕለት 21 ተሳፋሪዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል ከሚገኘው የአንድነት የነዳጅ ማደያ ሲነሳ የመከስከስ አደጋ አጋጥሞታል።
ፕሬዝዳንቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ሁሉም የሚመለከታቸው ባለስልጣናት የአደጋውን መንስኤ ለመለየት ጥልቅ እና ፈጣን ምርመራ እንዲያካሂዱ መመሪያ መስጠታቸውን መግለጫው አመልክቷል።

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር በቀጣዩ ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ!
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ የካቲት 1 እና 2 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡በጉብኝታቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ እ.ኤ.አ በ2019 የተቋሙ ኀላፊ ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሳጣቸው ፖሊሲዎች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ዳይሬክተሯ በጉብኝታቸው ወቅት ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ ሁኔታ እና በኢኮኖሚ እድሎች ዙሪያ ውይይት የሚያካሂዱ ከመሆኑም በተጨማሪ በሀገሪቱ በማህበራዊ ልማት የተሰሩ ስራዎችን እነደሚጎበኙ ታውቋል፡፡

የሐኪሞች የስራ አጥነት ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ በተጨማሪ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ነዉ ተባለ፡፡
በህክምና የተመረቁ ስራ አጥ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስታዉቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሐኪሞች ተገቢውን ሕክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የሕይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ማህበሩ ሀኪሞች ብዙ ጫናዎችን ተቋቁመው ስራ እየሰሩ ቢሆንም የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይከፈላቸዉ የሚቆዩባቸዉ ክልሎች መኖራቸዉን አንስቷል፡፡
ክፍያ የሚጠይቁ ሐኪሞችም ለእስር የሚዳረጉበት ሁኔታዎች የታዩበት ዓመት ነበር ሲል ማህበሩ ገልጿል፡፡
እንደሕክምና ማህበር ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ለማድረግ ቢሞከርም፤ አሁንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ለብዙዎች ችግር ምላሽ መስጠት አልተቻለም ነዉ ያለዉ፡፡
ከዚህ ቀደም ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተግባር ይግዛዉ ፤ በአገራችን ያሉ የሀኪሞች ቁጥር ወደ 17ሺህ ነዉ ያሉን ሲሆን፤ ከዚህ መሃል ወደ 40 በመቶ የሚሆነዉ ወይም 1ሶስተኛዉ ብቻ የማህበሩ አባል መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሙያ ማህበር መቅጠር አይችልም ፤ማድረግ የሚችለዉ ጉዳዩን ማሳወቅ ነዉ ያሉት ዶ/ር ተግባር፤ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸዉን በወቅቱ አንስተዉ ነበር፡፡
ዘንድሮ 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 – 15/2017ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱንም ማህበሩ አስታዉቋል፡፡
በጉባዔዉ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱም ለማወቅ ችለናል፡፡
ማህበሩ ከተመሰረተበት 1940 ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
#EthioFM

ትራምፕ 30,000 ሰነድ አልባ ስደተኞችን በጓንታናሞ ቤይ ለማሰር ማቀዳቸውን ገለፁ
*****
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን በጓንታናሞ ቤይ ለማሰር ማቀዳቸውን ገልፀዋል።
ትራምፕ ስለ ዕቅዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገሩት በስርቆት ወንጀሎች የተከሰሱ እና ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች እንዲታሰሩ የሚደነግገውን የላርኪን ሪሌይ አክትን ሲፈርሙ ነው።
በጓንታናሞ ቤይ ውስጥ እስከ 30,000 የሚደርሱ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን እንደሚያስሩ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ በሕገ-ወጥ ስደት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
ይህ ዕቅድ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው በሕገ-ወጥ ስደት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የገቡትን ቃል እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ትራምፕ ስለ ዕቅዳቸው ሲናገሩ "ለአሜሪካ ህዝብ ስጋት የሆኑ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ለማቆየት በጓንታናሞ 30,000 አልጋዎች አሉን፤ ይህም ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን የመያዝ አቅማችንን በእጥፍ ያሳድጋል" ብለዋል።

የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሞክረዋል የተባሉ ክስ እንደቀረበባቸው ተገለጸ!
ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸውን የጣቢያው ጊዜያዊ ሥራ አስከያጅ ገለጹ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰብ ላይም ጣቢያው ክስ መመስረቱን ተናገሩ።
ጣቢያውን ሊቆጣጠሩ ነበር በሚል ወቀሳ ከቀረበባቸው ፣ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ምላሽ ለማግኘት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ደውለን ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለገለፁን ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።
ጉዳዩ ኣስመልክቶ ከመቐለ ፖሊስ አዘዥ ኮማንደር አንድነት ነገሰ ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፌስቡክ ገጹ በአወጣው መረጃ፣ ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ኤፍኤም 104.4 “የተሾመኩት እኔ ነኝ” በሚል የተነሳ፣ ጊዜያዊ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበርና ፖሊሰ ሁኔታው ለማረጋጋት በቦታው ተገኝቶ እንደነበር አስታውቋል።
Via VoA

የቱርክ አየር መንገድ በአስመራ በኩል አድርጎ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው፡፡ አየር መንገዱ እንደገለፀው ከፊታችን ማርች 31 አንስቶ ከኢስታንቡል ወደደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ያደርግ የነበረውን በረራ አቅጣጫ ይለውጣል፡፡
በዚህ መሰረት ከኢስታንቡል ወደ ጁባ የነበረውን ቀጥታ በረራ ወደሶስትዮሽ በመቀየር አስመራ ላይ እንዲያርፍ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ከኢስታንቡል የተነሳው አውሮፕላን በመጀመሪያ አስመራ ያርፍና እንደገና ተነስቶ ወደጁባ የሚያመራ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ይህንን ለውጥ ያደረገው በምስራቅ አፍሪካ ላይ ተደራሽነቱን ለማስፋት መሆኑን አስታውቋል፡፡
የፊታችን ማርች ሰላሳ አንድ የሚጀመረው ይህ አዲስ የበረራ ለውጥ በሳምነንት ሁለት ጊዜ የሚከናውን ሲሆን አየር መንገዱ እንደገለፀው ለዚህ በረራ የሚጠቀመው ደግሞ ቦይንግ 737 ማክስ 8 የተሰኘውን አውሮፕላን ይሆናል፡፡

ፑንትላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ያዘች
በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወደ ሀገራቸው እንደሚመልሱም አስታውቀዋል።
እርምጃው ሰነድ አልባ የውጪ ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣት ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። የተያዙት ስደተኞች በመኪና ተጭነው ከከማዋ ውጪ ተወስደዋል። ይህም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።
እርምጃው የተወሰደው ፑንትላንድ በአይሲስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ባልችበት ወቅት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ በአይሲስ አባልነት የተጠረጠረን ግለሰብ የፀጥታ ኅይሎች ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ ነው።
የተያዙት ስደተኞች ከሽብር እንቅስቃሴ ጋራ ግንኙነት ይኖራቸው ባለሥልጣናት ማስረጃ አላቀረቡም።
Via:- VOA

አብን በቀጣዩ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም-አባላቱ
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 300 የሚደርሱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በሥራ ላይ ባለመኾናቸው በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም ሲሉ አንዳንድ አባላቶቹ ለዋዜማ ተናግረዋል።
ከፓርቲው አባላት የተወሰኑት መንግሥትን ለመግልበጥ ሙከራ አያደረጋችኋል ተብለው ለ6 ወራት ከታሠሩ በኋላ፣ ባለፈው ሳምንት እንደተፈቱም በዘገባው ተመላክቷል።
አብን መጋቢት 11 ቀን፣ 2014 ዓ፣ም በባሕርዳር ከተማ ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ጉባኤው በድጋሚ እንዲካሄድ ቦርዱ ቢያዝም፣ እስካኹን ድረስ ፓርቲው ጉባኤውን ማካሄድ አልቻለም።
የፓርቲው አመራሮች ከምርጫ ቦርድ ጋር ያላቸው ንግግር በግልጽ የማይታወቅ መኾኑ፣ የፓርቲውን ሕልውና አሳሳቢ እንዳደረገው አባላቱ ገልጸዋል።
የአብን አባላት በፓርቲው ወቅታዊ ቁመና ዙሪያ ላነሱት ቅሬታ፣ የፓርቲው አመራሮች ምላሽ እንዲሠጡ ዋዜማ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካም አስታውቋል።

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ
👉🏽ይህ አለት በከተማ ላይ ካረፈ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚል ተሰግቷል
👉🏽የጠፈር አለቱ አሜሪካ በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ 500 እጥፍ ሀይል አለውም ተብሏል
*
የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡
የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ኤኤፍፒ የጠፈር ሳይንስ ባለሙያው ብሩስ ቤትስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የጠፈር አለቱ እንዲሰባበር እና ጉዳት ወደ ማያደርስ ቦታ ለማሳረፍ ጥረቶች በመደረግ ላይ ነው፡፡
ዓለም አቀፉ የጠፈር አለት ማስጠንቀቂያ ማዕከል በበኩሉ ወደ ምድር እየመጣ ያለውን የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ናሳ እንደተነበየው ከሆነ ይህ የጠፈር ዓለት አሁን ባለበት ፍጥነት መሰረት ወደ ምድር በፈረንጆቹ 2032 ላይ ወደ መሬት ይደርሳል፡፡
እስካሁን ባለው የጠፈር አለት ታሪክ ከ66 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የተከሰተው ከፍተኛ ውድመት እንዳደረሰ የተገለጸ ሲሆን 75 በመቶ በምድር ላይ የነበሩ ስነ ህይወቶችን አጥፍቷልም ተብሏል፡፡
ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ነበረው የተባለው ይህ የጠፈር ዓለት ባረፈበት ስፍራ ዳይኖሰሮችን ጨምሮ በርካታ ዝርያዎችን እንዳጠፋም ይታመናል፡፡
በቅርቡ ተከስቷል የተባለው የጠፈር አለት በ1908 በሳይቤሪያ የረፈ ሲሆን እስከ 2 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ዛፎችን እንዳቃጠለ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ወደ ምድር እየመጣ ነው የተባለው ይህ ግዙፍ ዓለት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ካይነቲክ ኢመፓክተር የተሰኘ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጉዳት ወደማያደርስ መልኩ መቀየር እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ይሁንና ይህንን ቴክኖሎጂ ለመተግበር ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የበለጸጉ ሀገራት ወጪውን የሚሸፍኑት በአለቱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ከተገነዘቡ ብቻ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
መረጃው የአል አይን ነው።

በሜታ ወልቂጤ በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል።
“በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ” የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በታዳጊ ልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል ፍትህ እንሻለለን ብለዋል።
ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የስምንት (8) ዓመት ታዳጊ ህጻን ናት፡፡ የአንደኛ ክፍል ተማሪ፡፡ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል ፡፡
በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡
ሮጣ ያልጠገበች ታዳጊዋ ለአዕምሮም በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ “እንዳትናገር በሚል” ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
ታዳጊዋ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ “ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው” ብለዋል።
በወረዳው የኤላ ከተማ በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።
የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ ቀጥለው፤ “የታዳጊዋ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወታው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡ ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት” ያሉን አስተያየት ሰጪው፤ 2009 ዓ.ም. የተወለደችው ታዳጊዋ ሲምቦ ገና በ8 ዓመቷ ለዚህ ለአሰቃቂው ድርጊት ሰለባ መሆኗን በቁጪት ተናግረዋል፡፡
“ባለሙያዎች በሰውነቷ ላይ የታየውን ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ እያደረጉ ነው” ያሉን የቤተሰብ አባል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ተኩል የተገኘው የታዳጊዋ አስክሬን በትናንትናው እለት ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙ ተገልጿል ።
ዶቼ ቬለ