☞ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው አስሩ ነገሮች፡
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራትና ስሜታቸውን በመቆጣጠር ይታወቃሉ ፡፡ በአዕምሯዊ #ብስለትና በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች አያደርጉም ፡፡
➊. ፍርሃት የለባቸውም
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች #ምክንያታዊ አስተሳሰብን ስለሚያጎለብቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ወደፊት ሊገጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች አስቀድመው ስጋት ውስጥ ለሚጥል ጭንቀት አይዳረጉም ፡፡
➋. በሌሎች ስዎች ስኬታማነት አይቀኑም
አዕምሯቸው ሚዛናዊነትን ያጉለበተ ሰዎች ስኬትን ከተቀዳጁ ሌሎች ሰዎች ትምህርትን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆኑ ይነገራል ፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች በሌሎች ሰዎች ድክመትና ስኬትማነት ላይ ማተኮር የራስን እቅድ ያሳጣል ይላሉ ፡፡
➌. ባለፈ ነገር አይፀፀቱም
ስላለፈው ጉዳይ መጨነቅና በፀፀት ጊዜን ማሳለፍ ለወደፊቱም እቅድን እንዳይነድፉ መሰናክል ይሆናል ፤ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ካለፈው ችግራቸው ወይም ውድቀታቸው ትምህርት በመውሰድ አሁን ያለውን የተሻለ በማድረግ ለነገ ስኬታማነታቸው በጥረት ይሰራሉ ፡፡
➍. ራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም ፤ አይሸነፉም
ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አካላቸው እንኳ ቢደክም በአስተሳሰብና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይዘው ለስኬት ይበቃሉ ፡፡ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡
➎. ለውጥን አይፈሩም
እነዚህ ሰዎች ነገሮችን አመዛዝነው የሚተነብዩ በመሆናቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ለሚመጣው ውጤት ዝግጁ ናቸው ፡፡
➏. ከአቅማቸው በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜያቸውን አያባክኑም
በአዕምሯዊ ብስለታቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ሁሉም ነገር እነሱ ባቀዱት ልክ እንደማይሆንና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ስለሚያስቡ አይጨነቁም ፡፡ ከአቅማቸው በላይ ሆነው ለጭንቀት የሚዳርጉ ነገሮችን በአግባቡ በማስተናገድም ካልተገባ ውጥረት ራሳቸውን ያድናሉ ፡፡ በዚህም ሰኬታማነታቸውን ያጎለብታሉ ፡፡
➐. ተመሳሳይ ስህተት አይሰሩም
ብዙ ጊዜ ስህተት በድጋሚ ሊከሰት የሚችለው ያለፈውን ካለማገናዘብና እንዳይደገም ካለመዘጋጀት እንደሆነ የስነ ልቦና ምሁራን ናገራሉ ፡፡ ጥሩ የአዕምሮ ብስለት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለሚሰሩት ስህተት ኃላፊነትን በመውሰድ በቀጣይ እንዳይደገም መፍትሔ አስቀምጠው ይሰራሉ ፡፡
➑. በመጀመሪያው ውድቀታቸው አይሸነፉም
አዕምሯዊ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች በመጀመሪያው ውድቀታቸው መሸነፍን አያውጁም ፤ ከውድቀታቸው ትምህርትን በመውሰድ የተሻለ ውጤትን ለማምጣትም በትጋት ይሰራሉ ፡፡
➒. ቅፅበታዊ ውጤትን አይጠብቁም
አስተሳሰባቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት ስራ ወዲያውኑ ውጤት እንደሚያስገኝላቸው በማሰብ አይጓጉም ፡፡ ከዚህ ይልቅ ሁሉ ስራ የራሱ ጊዜ እንዳለውና የስኬቱም ምንጭ የተቀመጠለት ጊዜ ፣ የሚደረግለት ተግባራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በእቅዳቸው አስቀምጠው ጉዞ ወደ ፊት ይላሉ ፡፡ ይህ ደግሞ ምክንያታዊ ወይም እውናዊ የስኬት ምንጭ በአንድ ሌሊት እንደማይመጣ መረዳትን ያሳያል ነው ያሉት ባለሙያዎቹ ፡፡
➓. ዓለም ሁሉንም ነገር እንድታበረክትላቸው አይፈልጉም
ዓለማችን ብዙ ተቃርኖዎች ስኬትና ውድቀት ፣ ሀብትና ድህነት ፣ ሀዘንና ደስታ ወዘተ የተጣመሩባት እንደመሆኗ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ ከዓለም እንዲያገኙ አይፈልጉም ፡፡ ከዚህ ይልቅ በዓለም ላይ ደስታም ሆነ ሀዘን ፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት የሚያጋጥመው በራስ ጥረትና ጥንቃቄ ልክ ነው ብለው ያምናሉ ።
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
በዓሉ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣ የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
🏑🎄መልካም ገና🎄🏑
🎄 የስብዕና ልህቀት🎄

"ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል፡፡"
አርስቶትል
በህልውናችን ውስጥ ያለምክንያት የሚፈጠር ነገር የለም፡፡ ከእያንዳንዱ ፍጥረት በስተጀርባ አላማ አለ፡፡ ህይወትም ሆነ ሞት የተፈጠሩት በምክንያት ነው፡፡ ተፈጥሮ ማንኛውንም ነገር በከንቱ አትፈጥርም
ሰዎችም እንዲሁ የራሳቸው ተፈጥሯዊ አላማ፣ ግብና አቅጣጫ አላቸው፡፡ የአላማቸውና የተልእኳቸው ስኬት ውበት፣ እርካታና ደስታን ይፈጥራል፡፡ አምላክ ሰውን የፈጠረው በምክንያት፣ በአላማ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል፡፡ በአንጻሩ የተፈጠረበትን ምክንያት ተገንዝቦ ተልእኮውን ማሳካት ሲችል የአእምሮ ሰላምና የመንፈስ እርካታን ያገኛል፡፡
በብዙሀኑ ዘንድ ( Self - Realizationism) በመባል ፣ የሚጠራው የአርስቶትል የስነ ምግባር ፍልስፍና መልካም ህይወት ወይም ደስተኝነት ባህሪን፣ ሰብእናንና እምቅ ሀይልን ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ ከማዋል ይመነጫል የሚለውን እሳቤ መሰረት ያደረገ ነው፡፡
አንድ ህጻን እንደተወለደ ሰው አይባልም ሰው የመሆን እምቅ ሀይል ያለው ግን ሰው ለመባል ያልደረሰ ፍጡር ነው፡፡ እውነተኛ ሰው ለመሆን እምቅ ሀይሉ እውን ሆኖ መታየት አለበት፡፡
አንድ ሰው ከቤትሆቨን ያልተናነሰ ዜማዊ ተሰጥኦ ተችሮት ተሰጥኦውን ማወቅ ከተሳነው ወይም እያወቀ መጠቀም ካቃተው ከቶውኑ አርቲስት ሊሰኝ አይችልም፡፡ ታላቅ አርቲስት ለመሆን የሚያበቃ እምቅ ሀይል ቢኖረውም ሀይሉንና ተሰጥኦውን ጥቅም ላይ እስካላዋለው ድረስ የአርቲስትነት ተሰጥኦ ስላለው ብቻ አርቲስት አይባልም፡፡
እንደ አርስቶትል እሳቤ የሰው ልጅ ተቀዳሚ አላማ ተፈጥሮውና ተሰጥኦው እስከፈቀደለት አጥናፍ ተለጥጦ እምቅ ሀይሉን እውን ማድረግና ምሉእነትን መጎናጸፍ ነው፡፡ ይህን ማድረግ የቻለ ሰው ተልእኮውን ከመወጣት ስሜት የሚመነጭ የተሟላ እርካታና ደስታ ያገኛል፡፡
አንድ የአበባ ዘር ሊያብብ፣ ሊፈካና ሊያፈራ የሚችለው የእድገት ኡደቱን አጠናቆ ውበቱንና ሙሉነቱን አሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ሰው በርካታ ውስብስብ ባህሪያትን ይዞ ቢፈጠርም ተልእኮውን መወጣት ከቻለ ስኬታማ የሆነ ውብ፣ ደስተኛና ምሉእ ፍጡር ይሆናል፡፡
የስብዕና ልህቀት
https://www.tgoop.com/+Rn0O-d8bj50OUCcP

እስቲ ጠይቂለት
ይሄ ጭንቅላቴ
“ዓለም የሚለውጥ፣
ብልህ የሚያታልል፣
ሁሉ የሚመኘው-ሃሣብ አለኝ!” ብሎ -
ኩራት ኩራት ካለው
አትጠራጠሪ!
የሃሣቡ አስኳል አንቺ ነሽ ማለት ነው።
ይሄ ድህነቴ!
“ከዕንቁ የተወደደ፣
ከገበያ የሌለ፣
ገንዘብ የማይገዛው – ንብረት አለኝ!” ብሎ
ኩራት ኩራት ካለው፤
አትጠራጠሪ
ብቸኛ ንብረቱ አንቺ ነሽ ማለት ነው᎓᎓
ይህ ምንም እኔነት!!
ራሱን ፍለጋ ወደነፍሱ ዘምቶ፤
በእርካታ ቢጠመቅ የፈካ ገጽ አይቶ፡፡
ከዚያ
“ራሴን አገኘሁ፣
ስኬቴን ጨበጥኩት፣
አቅሜን መዘንኩት!” በተሰኘ ዜማ -
ፎክር ፎክር ካለው፤
አትጠራጠሪ
የተገኘው ምስል ያንቺ ነው ማለት ነው።
እኔ የምልሽ ግን?
ይሄ ፈጣሪያችን ፣
አካል ነፍስያዬን፣
ክብደቴን፣ ቁመቴን፣
ስፋቴን፣ ጥልቀቴን፣
መለያ ቀለሜን፣
የምናብ ዓለሜን፣
አንስቶ ያስረከበሽ ሕልምና ዕውኔን፤
እስቲ ጠይቂልኝ የት ጥሎኝ ነው እኔን?
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
ገጣሚ በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!
ይሄ ጭንቅላቴ
“ዓለም የሚለውጥ፣
ብልህ የሚያታልል፣
ሁሉ የሚመኘው-ሃሣብ አለኝ!” ብሎ -
ኩራት ኩራት ካለው
አትጠራጠሪ!
የሃሣቡ አስኳል አንቺ ነሽ ማለት ነው።
ይሄ ድህነቴ!
“ከዕንቁ የተወደደ፣
ከገበያ የሌለ፣
ገንዘብ የማይገዛው – ንብረት አለኝ!” ብሎ
ኩራት ኩራት ካለው፤
አትጠራጠሪ
ብቸኛ ንብረቱ አንቺ ነሽ ማለት ነው᎓᎓
ይህ ምንም እኔነት!!
ራሱን ፍለጋ ወደነፍሱ ዘምቶ፤
በእርካታ ቢጠመቅ የፈካ ገጽ አይቶ፡፡
ከዚያ
“ራሴን አገኘሁ፣
ስኬቴን ጨበጥኩት፣
አቅሜን መዘንኩት!” በተሰኘ ዜማ -
ፎክር ፎክር ካለው፤
አትጠራጠሪ
የተገኘው ምስል ያንቺ ነው ማለት ነው።
እኔ የምልሽ ግን?
ይሄ ፈጣሪያችን ፣
አካል ነፍስያዬን፣
ክብደቴን፣ ቁመቴን፣
ስፋቴን፣ ጥልቀቴን፣
መለያ ቀለሜን፣
የምናብ ዓለሜን፣
አንስቶ ያስረከበሽ ሕልምና ዕውኔን፤
እስቲ ጠይቂልኝ የት ጥሎኝ ነው እኔን?
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
ገጣሚ በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!
ስልጣን የሌለው አንድም ሰው
የለም!
ስልጣን እንደሚያባልግ በሎርድ አክተን የተነገረውን ዝነኛ አባባል ሳትሰሙ አትቀሩም፡፡ አባባሉ እውነት አይደለም፡፡ በተወሰነ መልኩ ሰውየው የታዘቡት ነገር ትክክል ቢሆንም እውነት አይደለም። ስልጣን በፍፁም ማንንም ሰው አያባልግም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሎርድ አክተን ትክክል ናቸው - ምክንያቱም ሁልጊዜም ሰዎች በስልጣን ሲባልጉ እናያለን፡፡ ስልጣን እንዴት ሰዎችን ሊያባልግ ይችላል?
በሌላ መልኩ ካየነው እንዲያውም የባለጉ ሰዎች ስልጣንን ማግኘት ይሻሉ፡፡ በእርግጥ ስልጣን በሌላቸው ጊዜ ብልግናቸውን በይፋ መግለፅ አይችሉም፡፡ ስልጣን ካላቸው ግን ነፃ ናቸው፡፡ የዚያን ጊዜ ከስልጣናቸው ጋር ስለሚንቀሳቀሱ አይጨነቁም፡፡ የዚያን ጊዜ እውነተኛ ማንነታቸው ፀሃይ ይሞቃል፤ እውነተኛ ገፅታቸውንም ያሳያሉ፡፡
ስልጣን በፍፁም ማንንም ሰው አያባልግም፡፡ ነገር ግን ባለጌ ሰዎች ወደ ስልጣን ይሳባሉ፡፡ እናም ስልጣን ሲኖራቸው ስልጣናቸውን በእርግጥም ፍላጐቶቻቸውን እና ጥልቅ ስሜቶቻቸውን ለማሟላት ይጠቀሙበታል፡፡
የዚህ አይነቱ ነገር ያለ ነው፡፡ አንድ ሰው በጣም ትሁት ሊሆን ይችላል የፖለቲካ ስልጣን ለማግኘት ሲፈልግ በጣም ትሁት ሊሆን ይችላል ታውቁትም ይሆናል - በመላው የህይወት ዘመኑ በጣም ጥሩና ትሁት ሰው እንደነበር ታውቁ ይሆናል፤ እናም ትመርጡታላችሁ፡፡ ስልጣን የያዘ ጊዜ ግን ለውጥ ይኖራል፤ ከዚያ በኋላ የድሮው አይነት ሰው አይደለም፡፡ በዚህ ለውጥ ሰዎች በጣም ይገረማሉ- እንዴት ስልጣን ያባልጋል?
በእርግጥ የሰውየው ትህትና የውሽት፣ የማሳሳቻ ነበር፡፡ ትሁት የነበረው ደካማ ስለነበረ ነው፤ ትሁት የነበረው ስልጣን ስላልነበረው ነው፤ በሌሎች ሀይለኛ ስዎች እንዳይደፈጠጥ ስጋት ስለነበረበት ነው ትሁት የነበረው፡፡ ትህትናው የፖለቲካ መሳሪያው ፖሊሲው ነበር። አሁን ግን መስጋት አያስፈልገውም፤ አሁን ማንም ሊደፈጥጠው ስለማይችል መፍራት አያስፈልገውም፡፡ ስለሆነም አሁን ወደ እውነተኛ ተፈጥሮው መምጣት አለበት፣ አሁን እውነተኛውን የገዛ ራሱን ማንነት መግለፅ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የባለገ መስሎ ይታያል።
በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ስልጣናቸውን በአግባቡ መጠቀም ይቸግራቸዋል፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣናቸውን አላግባብ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች ብቻ ናቸው ስልጣን ላይ ዝንባሌ የሚያድርባቸው፡፡ ትንሽ ስልጣን ካላችሁ እራሳችሁን ታዘቡ፡፡ አሁን መንገድ ዳር የምትቆሙ ተራ ደንብ አስከባሪዎች ልትሆኑ ትችላላችሁ። ነገር ግን አጋጣሚውን ካገኛችሁ ስልጣናችሁን አላግባብ ትጠቀሙበታላችሁ፤ ማንነታችሁን ታሳያላችሁ፡፡
ሙሳ ናስረዲን ደንብ አስከባሪ ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ እናም አንዲትን ሴት መኪና እየነዳች አያለ ይይዛታል፡፡ በእርግጥ በወቅቱ ሴትና መኪና በፍፁም አብረው አይሄዱም የሚል ሀሳብ ነበረ፡፡ ሴትየዋም ታዲያ ስህተት ፈፅማ ነበር፡፡ ሙላ ማስታወሻ ደብተሩን አወጣና መፃፍ ሲጀምር፣ ሴቲቱ «ቆይ! ጠቅላይ ሚኒስትሩን ስለማውቃቸው አትጨነቅ» አለችው፡፡ ሙላ ግን መፃፉን ቀጠለ፡፡ ምንም አይነት ከበሬታ አላሳያትም፡፡ «ሀገረ ገዢውንም ጭምር እንደማውቃቸው ታውቃለህ ወይ?» አለችው ሴቲቱ፡፡ ሙላ ግን አሁንም መፃፉን ቀጠለ፡፡
«ስማ ምን እያደረግህ ነው? ፕሬዝዳንቱንም እኮ አውቃቸዋስሁ!» አለችው ሴትየዋ፡፡
በዚህ ጊዜ ሙላ «የኔ እመቤት ትሰሚያለሽ? ሙላ ናስረዲንንስ ታውቂዋለሽ?» ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹ኧረ በፍፁም ስለ እሱ ሰምቼ አላውቅም፡፡»
«አንግዲያውስ ሙላ ናስረዲንን ካላወቅሽ ችግር ላይ ነሽ፡፡»
ስልጣን ሲኖራችሁ ... ነገሮች ቀላል አይሆኑም - አይደለም እንዴ? ዙሪያ ገባውን መታዘብ ትችላላችሁ፡፡ በአንድ የባቡር ጣቢያ ትኬት መሸጫ መስኮት ፊት ለፊት ቆማችሁ ሳለ፣ ትኬት ቆራጩ አንድ የሆነ ነገር ማድረጉን ይቀጥላል
ምንም የሚሰራው ነገር እንደሌለ
ብታውቁም፣ እሱ ግን ወረቀት ከወዲያ ወዲህ ማገላበጥ ይይዛል፡፡ ሊያዘገያችሁ ይፈልጋል፤ አሁን ስልጣን እንዳለው ሊያሳያችሁ ይፈልጋል፡፡ «ቆይ!» ይላችኋል፡፡ እናንተን እምቢ ለማለት ይህን
አጋጣሚ መጠቀም አለበት፡፡
ይህንን ነገር በገዛ ራሳችሁ ውስጥም አስተውሉት፡፡ ልጃችሁ ይመጣና «አባዬ ውጪ ወጥቼ ከነ አቡሽ ጋር ኳስ መጫወት «እችላለሁ ወይ?» ብሎ ይጠይቃል፡፡ «አይሆንም!› ትሉታላችሁ፡፡ ልጃችሁም ሆነ እናንተ የኋላ፣ ኋላ እንደምትፈቅዱለት ታውቃላችሁ፡፡ ከዚያ ልጁ መበጥበጥ፣ መዝለል፣ መጮህ ይጀምራል፡፡ «ሄጄ መጫወት እፈልጋለሁ» እያለ ይነተርካችኋል፡፡ በመጨረሻ «እሺ በቃ ሂድ» ትሉታላችሁ፡፡ ይህንን አስቀድማችሁ በደንብ ታውቁታላችሁ፤ ከዚህ በፊት የዚህ አይነቱ ነገር አጋጥሟችኋል፡፡ ደግሞም ውጪ ወጥቶ ኳስ መጫወት ችግር እንደሌለበት ታውቃላችሁ፡፡ ታዲያ ለምን እምቢ ትሉታላችሁ?
ስልጣን ካላችሁ ስልጣናችሁን ለማሳየት ትፈልጋላችሁ፡፡ ልጃችሁም የራሱ ስልጣን ስላለው መዝለል ይጀምራል፤ ሁከት ይፈጥራል ምክንያቱም ረብሻ እንደሚፈጥር እና ጐረቤቶቻችሁም ሰምተው በመጥፎ ሁኔታ እናንተን ሊያዩዋችሁ እንደማትፈልጉ ያውቃል፡፡ ስለዚህ <እሺ> ትሉታላችሁ፡፡
በሁሉም የሰው ልጅ ገጠመኝ ውስጥ ይሄ ነገር በተደጋጋሚ ሲፈጠር ታያላችሁ ሰዎች በየቦታው ስልጣናቸውን እያሳዩ ነው፤ ሰዎችን ያበሻቅጣሉ፣ ወይም በሌሎች ይበሻቀጣሉ፡፡ አንድ ሰው ካበሻቀጣችሁ እናንተም ወዲያውኑ የሆነ ቦታ ላይ የደረሰባችሁን በደል ለመበቀል ደካማ ሰዎችን ታገኙና በተራችሁ ታበሻቅጣላችሁ::
በመስሪያ ቤታችሁ ውስጥ አለቃችሁ ካበሻቀጣችሁ ቤታችሁ መጥታችሁ ሚስታችሁን ታበሻቅጣላችሁ፤ ሚስታችሁም የሴቶች መብት ታጋይ ካልሆነች ልጇ ከትምህርት ቤት እስኪመጣ ድረስ ጠብቃ ታበሻቅጠዋለች፡፡ ልጇም ቢሆን ዘመናዊ ከሆነ፣ አሜሪካዊ ከሆነ መኝታ ክፍሉ ይሄድና መጫወቻዎቹን ይሰባብራል ምክንያቱም እሱ ማበሻቀጥ የሚችለው መጫወቻዎቹን ብቻ ነው፡፡ እሱም ስልጣኑን መጫወቻዎች ላይ መግለፅ ይችላል፡፡ ሁኔታው በዚህ መልኩ ይቀጥላል። እንግዲህ ጨዋታው ይህንን ይመስላል፡፡ እውነተኛው ፖለቲካም ይኸው ነው...
ደግሞም ሁሉም ሰው ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ስልጣን አለው᎓᎓ ስልጣን የሌለው አንድም ሰው አታገኙም፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ብትሄዱ ስልጣን የሌለው ሰው ማግኘት አትችሉም፡፡ አንድ ሰው አንድ የሆነ ስልጣን ይኖረዋል፤ ቢያንስ ውሻውን በእርግጫ ነርቶ ስልጣኑን ይገልፃል፡፡ ሁሉም ሰው አንድ የሆነ ቦታ ላይ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው ፖለቲካ ውስጥ ይኖራል፡፡ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አትሆኑ ይሆናል፤ ይሄ ማለት ግን ፖለቲካዊ አይደላችሁም እንደማለት ተደርጉ አይታይም፡፡ ስልጣናችሁን በአግባቡ ካልተጠቀማችሁ ፖለቲከኞች ናችሁ፡፡ ስልጣናችሁን በአግባቡ የምትጠቀሙ ከሆናችሁ ግን ፖለቲከኛ አይደላችሁም፡፡
ስልጣናችሁን አላግባብ አለመጠቀማችሁን እወቁ፡፡ ይህን ከተገነዘባችሁ ይህንን በማድረጋችሁ አዲስ ብርሃን ታያላችሁ፤ እንዴት እንደምትንቀሳቀሱም ታያላችሁ - የዚያኔ በጣም እርጋታ የተላበሳችሁ እና አስተዋዮች ትሆናላችሁ፡፡ የአእምሮ ሰላምና ፀጥታን ታገኛላችሁ።
ምንጭ ፦ ህያውነት ፫ (ኦሾ)

ያልተፈተሹ ባህሪያት
“ትዕግስት ስጠኝ ብለን ስንጠይቅ፤ የሚሰጠን እረጅም ሰልፍ ነው” ትላለች ጸሀፊ ትሬሲ ማክሚላን። ትዕግስትን ስንጠይቅ የሚሰጠን ትዕግስትን የምንለማመድበት መድረክና ትዕግስትን የምናዳብርባቸው ሁኔታዎች እንጂ ትዕግስት ልክ እንደተሰጥዎ ከላይ አይቸረንም። ለዛሬ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው።
አንዳንዴ እራሳችንን ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ እናገኘውና ከራሳችን የማንጠብቀው ባህሪ ሲንጸባረቅብን እንደነግጣለን። ለወትሮ እኮ እንዲህ አልነበርኩም በማለት ግራ ይገባናል። ተሳድበን የማናውቅ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሌላውን ሰው ስናጥረገርገው፤ ትዕግስተኛ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ቀጠሮዋችን እረፈደ ብለን የታክሲውን ሹፌር ስናመናጨቀው፤ ቂመኛ አይደለሁም ስንል የከረምን ሰዎች የወደድነው ሲከዳን ለበቀል ስናደባ፤ በደላችንን ይቅር በለን እያልን ጠዋት ማታ እየጸለይን የበደሉንን ሰዎች ይቅር ማለት ሲከብደን፤የሌሎች ሰዎች ማግኘት ያስደስተናል የምንል ሰዎች እኛ የተመኘነውን ሌላው ሰው ላይ ስናየውና ሲከፋን፤ ፈራጅ አይደለንም ስንል ከርመን የእኛ ህልውና ሲነካ የፍርድ ወንበር ላይ ቁጢጥ ስንል፤ ባህሪያችን ለገዛ እራሳችን እጅግ ግራ ያጋባል።
ማንነታችን የሚገለጸው እኛ ስለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም ሌሎች ሰዎች ስለኛ ባላቸው አመለካከት ሳይሆን፤ እኛ ለሁኔታዎች በምንሰጠው ምላሽ ነው። ሰው እንቃለው የሚል ሰው ባያጋጥምም ፤ ሰው እጠላለሁ የሚል ሰው ስምተን ባናውቅም ሰው የሚንንቅና የምንጠላ ሰዎች ግን አንጠፋም። ከእኔ ከእራሴ ጭምር በውስጣችን መጥፎ ስሜት ያድራል ብለን ማሰቡ ይከብደናል፤ ይከብደናል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም አንፈልግም። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። “እኔ” ብለን የምንጠራው ማንነት በአብዛኛው የተገነባው ባልተፈተሹ ባህሪያቶቻችን ነው። ስለራሳችን ስናወራ በአብዛኛው የምናወራው በሀሳብ ስለገነባነው ማንነት እንጂ፤ በተግባር ስለምነተገብረው ባህሪዎቻችን አይደለም።
እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ በድፍረት መናገሩ ከባድ የሚሆነውም ለዚህ ነው፤ ሁላችንም ያልተፈተኑ ባህሪያቶችን አጭቀን ስለምንቀሳቀስ። አብዛኛው ባህሪያቶቻችንና አስተሳሰቦቻችን በቲዎሪ ደረጃ እንጂ በሙከራ የተረጋገጡ አይደሉም። መልካምነታችን፤ ትዕግስተኛነታችን፤ ፍትሃዊነታችን፤ ሰው አክባሪነታችን፤ እውነተኛነታችን ተገቢውን ፈተና አላለፉም። ፈተና ስል እውነተኛ ባህሪዎቻችንን እንድናጸባርቅ የሚያስገድዱን ሁኔታዎችን ነው። ጊዜ ስለተረፈን ከኋላችን ያለውን ተሰላፊ ከፊታችን ስላስቀደምነው ትዕግስተኛ ልንባል እንችላለን? በፍጹም!!! የማንኛችንም መልካምነትና ጥንካሬ በመልካም አጋጣሚዎች ሊረጋገጥልን አይችልም። በፈተናዎችና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምናሳያቸው ባህሪያቶች ይበልጥ እኛን ይገልጹናል።
ለዚህ ነው አንዳንዴ ውሳኔዎቻችንና ድርጊቶቻችን የሚያስደነግጡን። ተፈትነን ያገኘናቸው ባህሪዋቻችን ስላልሆኑ ልንጠቀምባቸው በሚገባን ቦታ ይጠፉብናል። ይህንን ማወቁ ምን ይጠቅምናል? ለሁለት ነገር ይጠቅመናል ብዬ አስባለው። አንደኛው ከውሸተኛ ማንነት ቀስ እያለ ያላቅቀናል፤ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ለሰው ልጅ ቢከብድም። የሚሰማንን ስሜት በካድን ቁጥርና “እኔ እኮ እንዲህ አይደለሁም” በማለት እራሳችንን በተከላከልን ቁጥር ባህሪያችንን ማሻሻል አስቸጋሪ ይሆንብናል። ከእራሳችን ጋር እየተቆራረጥን በቅዠት አለም ውስጥ መኖሩን እንለምደዋለን።በሌላ በኩል ማንነትና ባህሪያችንን ለሁኔታዎች ከምንሰጠው ምላሽ ተነስተን መዳኘት ከቻልን፤ ከእውነተኛ ምንነታችን ጋር እንቀራረባለን። የትኛው ባህሪያችን ላይ ይበልጥ ማሻሻል እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ስለራሳችን ባህሪ እርግጠኛ ሆኖ መናገሩ የሚያስከፍለው ዋጋ አለ፤ እሱም ወደ እውነት የሚወስደውን ጎዳና ያጠብብናል።እውንተኛ ማንነታችንን ለማወቅ ከፈለግን ስለራሳችን የምናስበውን ሳይሆን፤ ለሁኔታዎችና ለአጋጣሚዎች የምንሰጠውን ምላሽ ልናስተውል ግድ ይለናል። ሁለተኛው ጥቅም “እኔ ብሆን ኖሮ” በሚለው የፍርድ ዱላ እርስ በራሳችን ከመፈነካከት ያድነናል።
“ የሰው ባህሪያት በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች አይፈጠርም፤ በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች ይጋለጣል እንጂ”- ዚግ ዚግለር

7⃣ ዐይን-ገላጭ የጃፓኖች የሕይወት ጭብጥ!
1⃣ IKIGAI
፨ በሕይወት ውስጥ ዓላማህን ድረስበት።
፨ ሰርክ ማለዳ የመንቃትህን ምክንያት እወቅ።
፨ አስፈላጊነትህን (ለዓለም)፣ ጥንካሬህን፣ ዝንባሌህን የተወዳጀ የሆነ ነገር አስስ። ይሄ ነው ለሕይወትህ ትርጉም የሚሰጣት።
2⃣ SHIKITA GA NAI
፨ መለወጥ የማይቻልህን ነገር ተወው፣ ልቀቀው።
፨ ካንተ ቁጥጥር ውጪ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን እና ያም ያለ መሆኑን ተረዳ። ሂድ እና መቀየር በምትችለው ነገር ላይ ትኩረት አድርግ።
3⃣ WABI-SABI
፨ በጎዶሎነት ውስጥ ሠላምን አግኝ።
፨ ራስህ እና ሌሎችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ ምንም ነገር ፍፁም አለመሆኑን ተገንዘብ።
፨ ለእንከን-የለሽነት ከመትጋት ይልቅ ሕይወትን ልዩ በሚያደርጋት ጎዶሎነት ውስጥ ደስታን አጣጥም።
4⃣ GAMAN
፨ በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ።
፨ ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት-ብስለትህን እና ራስ-ገዝነትህን አሳይ።
፨ ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።
5⃣ OUBAITIORI
፨ ራስህን ከማንም ጋር እንዳታወዳድር።
፨ ሁሉም የተለየ ጊዜ-ቤት እና ልዩ ጎዳና አለው።
፨ ራስህን በሌላው ለመለካት ከመሞከር ይልቅ በራስህ መሻሻሎች ብቻ ማተኮርህ አስፈላጊ ነው።
6⃣ KAIZEN
፨ ሰርክ በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ውስጥ መሻሻሎችን ፈልግ!
፨ ጥቃቅን ለውጦች እንኳ መጠራቀም ችለው በጊዜ ሂደት ውስጥ ግዙፍ ለውጥ ያመጣሉ።
7⃣ SHU-HA-RI
"ተማሪዎቹ ሲዘጋጁ መምህሩ ይገኛል።"
―Teo Te Ching
👉 (እንዴት) ስለመማር እና በዘዴው ስለመጠበብ ማወቂያ መንገድ ነው። ከዕውቀቱ ለመድረስ ሶስት ደረጃዎች አሉት።
፨ SHU: የአንዱን አዋቂ (master) ትምህርት በመከታተል መሰረቶቹን መቅሰም!
፨ HA: ከአዋቂው የተቀሰመውን ትምህርት ከሙክረት በማዋሃድ የተግባር ልምምድ መጀመር።
፨ RI: ይሄ ደረጃ የሚያጠነጥነው ፈጠራዎች ላይ እና ትምህርቶቹን በተለያዩ መስኮች የመተግበር ችሎታ ላይ ነው።

ልብና መስታወት
አንዳችም ሳይጨምር፣ አንዳችም ሳይቀንስ፣
በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፣
ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት ፤
መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት::
ልብ ግን አቃተው!
በመጣው ሲደሰት፣ በሄደው ሲከፋ፣
ውለታ ሲደምር፣ ቅያሜ ሲያጣፋ፣
ከሚስጥር ሆድ ዕቃው ነገር ሲያመሰኳ
ቀለም አልባ ሆነ ይቅርታችን መልኳ።
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!!
አንዳችም ሳይጨምር፣ አንዳችም ሳይቀንስ፣
በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፣
ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት ፤
መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት::
ልብ ግን አቃተው!
በመጣው ሲደሰት፣ በሄደው ሲከፋ፣
ውለታ ሲደምር፣ ቅያሜ ሲያጣፋ፣
ከሚስጥር ሆድ ዕቃው ነገር ሲያመሰኳ
ቀለም አልባ ሆነ ይቅርታችን መልኳ።
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!!
#ጤነኛው_ድሀ_እና_በሽተኛው_ሀብታም
ጤናው የተጓደለ ሀብታምና ጤናው የተሟላ ድሀ ነበሩ፡፡ ሁለቱም እርስ በርስ ይቀናናሉ፡፡ ሀብታሙ ሰው ለጤናው ሲል ሀብቱን አሳልፎ ቢሰጥ ይወዳል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ድሀው ለገንዘብ ሲል ጤናውን ቢሰጥ ይመርጣል፡፡
ፈላጊና ተፈላጊን የሚያገናኝ በዓለም ታዋቂ የሆነ የቀዶ ጥገና ሐኪም የአንድን ሰው አእምሮ ለሌላ ሰው የመተካት ጥበብን ማግኘቱ ተሰማ፡፡ ድሀውና ሀብታሙም ሰው በሐኪሙ አማካይነት ድሀው ጤናውን ለሐብታሙ አሳልፎ ሊሰጥ፣ ሀብታሙም ለጤና ሲል ሀብቱን በሙሉ ለድሀው ሊሰጥ ተስማምተው ተዋዋሉ፡፡ ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሀብታሙ ሰው ከጥሩ ጤና ጋር ድሀ ሲሆን፣ ድሀው ደግሞ ጤናውን አጥቶ ሀብታም ሆነ፡፡
ቅይይሩ ስኬታማ ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ የተፈጠረውን ታሪክ እንመልከት፡-
በፊት ሀብታም የነበረው ሰው ሁልጊዜም የስኬታማነት አስተሳሰብ ስለነበረው ሌላ ሀብት መሰብሰብ ቻለ፡፡ ምንም እንኳን የስኬት አመለካከት ቢኖረውም፣ ስለጤናው ግን ዘንግቶ አያውቅም፡፡ ሁልጊዜ ያመኛል ብሎ ፍርሃት ያድርበታል፡፡ ትንሽ ህመም ሲሰማውም አጋኖ ነው የሚመለከተው። ይህ አመለካከቱ ቀልጣፋ የነበረውን አካል እያደከመው መጣ፡፡ በሌላ አገላለፅ ሀብታም፣ ግን በሽተኛ ሆነ፡፡
ወደ አዲሱ ሀብታም ግለሰብ ደግሞ እንሂድ፡፡ ይህ ሰው ሁልጊዜም የነበረው አመለካከት የድህነት ነው፡፡ ባገኘው ሀብት የተመጣጠነ አዲስ የሕይወት ደረጃ ከመመስረት ይልቅ ገንዘቡን የማይረባ ቦታ ላይ ይበትነው ገባ፡፡ ሞኝና ገንዘብ አይጣጣሙም የሚለው የድሮ አባባል በዚህ ሰው ላይ ሰራ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንዘቡ ሁሉ አለቀና ወደ ድህነቱ ተመለሰ፡፡ ሰውነቱስ? የህመም ስሜት ተሰምቶት አያውቅም፡፡ ራሱን ጤነኛ አድርጎ ይመለከታልና አእምሮው የተቀየረ ቢሆንም እንኳን ጤንነቱ ግን ትቶት አልሄደም፡፡ ተረቱ ሁለቱም ሰዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው መመለሳቸውን አውስቶ ያበቃል፡፡ ከዚህ ተረት ምን ትማር ይሆን? “አንተነትህ በአስተሳሰብህ ይለካል!” ወይም “የምታስበውን ትሆናለህ!”

በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ባህሪህን ይወስናል
ባህሪይህን ተመልከተውና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት በግለጽ ይጠቁምሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ስትሆን የምትገልጠው ባህሪይ በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ብቻህን ስትሆን፣ ስለራስህ ስታስብ፣ ራስህን በመስታወት ስትመለከተው ስለራስህ የምታስበውን ትክክለኛውን ሃሳብ አግኘውና ከሰዎች ጋር ስትሆን የምታንጸባርቀውን የባህሪህን ፍቺ ይነግርሃል፡፡
ለምሳሌ፣ ጤናማ የሆነ በራስ መተማመን አመለካከት ያለው ሰው የሚገልጠው ባህሪይና የዝቅተኝነት ስሜት ያለው የሚገልጠው ባህሪይ አንድ አይደለም፡፡
እንደተገፋና እንደተናቀ፣ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ማንም ሳይነካው ሰውን የሚነካና የሚተናኮስ ባህሪይ ያዳብራል፡፡ ማንም ገፋው አልገፋው ምንም ለውጥ እንደማያመጣበት የሚያስብ ሰው የተረጋጋና አላማው ላይ የሚያተኩር ባህሪይ ይታይበታል፡፡
ለምንም ነገር ያለመመጠን ስሜት ያለበት ሰው የፍርሃትና የአይን አፋርነት ባህሪ ይወርሰዋል፡፡ የሚመጥን ማንነትና አመለካከት እንዳለው የሚያስብ ሰው ደፋርነትና ተግባቢነት ይኖረዋል፡፡
ሰዎች አይፈልጉኝም የሚል ስሜት ያለበት ሰው ለሁሉም ሰውና ለሁሉም ነገር እሺ ባይነት ያጠቃዋል፡፡ ተፈለገም አልተፈለገም ተረጋግቶ የሚኖር ሰው ያመነበትንና ያላመነበትን በመለየት ሃሳቡን መግለጽ ችግር የለበትም፡፡
ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንደማይበቃ የሚያስብ ሰው አታላይና አጭበርባሪ ባህሪይን ያዳብራል፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ራሱን አሰልጥኖ መወዳደር እንደሚችል የሚያምን ሰው ደግሞ ቀጥተኛና እውነተኛ ይሆናል፡፡
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ጤናማ ሲሆን ማሕበራዊ ግንኙነትህም እንደዚያው ጤናማ ይሆናል፡፡
ስለዚህ ማሕበራዊ ሕይወትህ እንዲስተካከል ከፈለክ በቅድሚያ በራስህ ላይ ያለህን ምልከታ አስተካክለው፡፡
ዶክተር ኢዮብ ማሞ

አንዳንዴ . . . ያለ ነው!
አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!
አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!
አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!
አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!
አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!
አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!
አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!
አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!
አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!
አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

የማንሰን የመሸሽ ህግ
"ሰዎች በአብዛኛው ስኬትን የሚፈሩት ውድቀትን በሚፈሩበት ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡"
ማርክ ማንሶን
የማንሰን ህግ እንዲህ ይላል የሆነ ነገር ማንነትህን በበለጠ ስጋት ላይ በጣለው መጠን፣ በበለጠ ትሸሸዋለህ፡፡
ይህ ማለት ራስህን የምታይበትን መንገድ እንዳትለውጥ ስጋት ላይ የጣለ የሆነ ነገር በኖረ መጠን ራስህን ስኬታማ ወይም ስኬታማ ያልሆነ አድርጎ ለማየት ያለህን እምነት፣ እንዲሁም ራስህን በእሴቶችህ መሰረት የምትኖር አድርገህ የምታይ መሆኑን ለማሳየት በዚያ ነገር ዙሪያ የመገኘትህን ነገር የበለጠ ትሸሻለህ፡፡
በዚህ ዓለም ውስጥ እንዴት ተስማሚ እንደሆንክ ከማወቅ ጋር የሆነ ምቾት አብሮ ይመጣል፡፡ እና ያንን ምቾትህን የሚያነቃንቅ ነገር ሲመጣ፣ ሕይወትህን የተሻለ ሊያደርግ የሚችል እንኳን ቢሆን አስፈሪ ይሆንብሀል፡፡
የማንሰን ህግ በህይወታችን ውስጥ ላሉ ጥሩና መጥፎ ለሆኑ ነገሮች ሁሉ ይሰራል፡፡ ሚሊየን ዶላር ማግኘት ማንነትህን ስጋት ላይ ሊጥለው እንደሚችለው ሁሉ፣ ገንዘብህን ሙሉ በሙሉ ማጣትም ልክ የዚያኑ ያህል አስፈሪ ነው፡፡ ዝነኛ መሆን ልክ ስራህን የማጣት ያህል ማንነትህን ስጋት ላይ ይጥለዋል፡፡ ሰዎች በአብዛኛው ስኬትን የሚፈሩት ውድቀትን በሚፈሩበት ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ ያም ነን ብለው የሚያምኑትን ማንነታቸውን እና ልማዳቸውን ስጋት ላይ ይጥላል፡፡
ሁልጊዜ የምታልመውን ያንን የፊልም ፅሁፍ መፃፍ የምትሸሸው ያንን ማድረግህ የኢንሹራንስ ሰራተኛ የመሆንህን ማንነት ወደ ጥያቄ የሚያመጣ ስለሆነ ነው፡፡ ባለቤትሽ መኝታ ላይ ምን እንዲሆንልሽ እንደምትፈልጊ መናገር የምትሸሺው ያ ጥያቄ ጨዋ ሚስት የመሆን ማንነትሽ ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ብለሽ ነው፡፡ ጓደኛህን ሁለተኛ ልታየው እንደማትፈልግ የማትነግረው ጓደኝነታችሁን ማቋረጥ ከአንተ ጥሩና ይቅር ባይ ማንነት ጋር ስለሚጋጭ ነው፡፡
እነዚህ ራሳችንን እንዴት እንደምናይና ስለ ራሳችን ምን እንደሚሰማን ያለንን ማንነት ይለውጣሉ ብለን ስለምንፈራ በተደጋጋሚ የምናልፋቸው ጥሩና በጣም አስፈላጊ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡
ለረጅም ጊዜ የአርት ስራዎችን ኦንላይን ላይ አስቀምጦ ፕሮፌሽናል አርቲስት ስለመሆን የሚያወራ አንድ ወዳጅ ነበረኝ፡፡ ለአመታት ስለዚህ ነገር ሲያወራ፣ ገንዘብ ሲያጠራቅም፣ ስራዎቹን የሚያሳይባቸው ጥቂት የተለያዩ ድረገፆች ሳይቀር ሰርቶ ነበር፡፡ነገር ግን ስራዎቹን አላወጣቸውም፡፡ ያንን ላለማድረጉ ሁልጊዜም የሚሰጠው ተመሳሳይ ምክንያት ነው፡፡ የሰራው ስራ በበቂ ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ ወይም ሌላ የተሻለ ስዕል እየሳለ ነው፡፡ ወይም ለዚህ ጉዳይ በቂ ጊዜ ለመስጠት ገና አልተዘጋጀም፡፡አመታት አለፉ፡፡ የሚሰራውን ስራ ግን አሁንም አልተወም፡፡ ለምን? ምክንያቱም በስዕል ስራ ለመኖር ቢያልምም ማንም የማይወደው አርቲስት ከመሆን ይልቅ ማንም ስለ እርሱ ሰምቶ የማያውቅ አርቲስት ሆኖ መቅረት የበለጠ አስፈሪ ስለሆነ ነው፡፡ ቢያንስ ማንም ስለ እርሱ ሰምቶ የማያውቀው አርቲስት መሆኑ ተመችቶታል፡፡
መጨፈር የሚወድ ሁልጊዜ ለመጠጣትና ሴት ለማሳደድ የሚወጣ ሌላ ጓደኛ ነበረኝ፡ ለአመታት የሀብታም አኗኗር ከኖረ በኋላ ራሱን በጣም ብቸኛ፣ ሀዘንተኛና ጤና ያጣ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህ የዚህ የጭፈራ የአኗኗር ዘይቤውን መተው ፈለገ፡፡ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ በገባነውና ከእርሱ በተሻለ በተረጋጋነው በእኛ ቅናት አደረበት፡፡ ግን አልተለወጠም፡፡ ለአመታት ከባዶ ምሽት ወደ ባዶ ምሽት፣ ከጠርሙስ ወደ ጠርሙስ እያለ በዚህ አይነት ሕይወት ቀጠለ። ሁልጊዜ ሰበብ አያጣም፡፡ ሁልጊዜ መረጋጋት የማይችልበት ምክንያት ነበረው፡፡ያንን የአኗኗር ዘይቤ መተው ማንነቱን በእጅጉ ስጋት ላይ የሚጥል ነበር፡፡ መሆን የሚችለው ጭፈራ የሚወድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ ያንን መተው ና ትዳር መመስረት ስነልቦናዊ ክብርን የሚነካ ፤ነፃነትን የሚያሳጣ ና በራስ ላይ ግድያ እንደመፈፀም ነው፡፡
ሁላችንም የየራሳችን እሴቶች እና ልማዶች አሉን፡፡ እነዚህን እሴቶች እንጠብቃቸዋለን፡፡ በእነርሱ መሰረት እንኖራለን። እንከላከልላቸዋለን፡፡ እንንከባከባቸዋለን፡፡ ያንን ለማድረግ ብለን ባይሆንም እንኳን አእምሯችን የተሰራው እንደዚያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደተገለፀው አስቀድመን በምናውቀው ነገርና እርግጠኛ ነን ብለን በምናምንበት ጉዳይ ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ አድሏዊ ነን፡፡ እኔ ጥሩ ሰው ነኝ ብዬ የማምን ከሆነ ያንን እምነቴን ለመቃረን አቅም ያለው ሁኔታ ሲያጋጥመኝ ያንን ሁኔታ እሸሻለሁ፡፡በጣም ጎበዝ ምግብ አብሳይ እንደሆንኩ የማምን ከሆነ፣ ያንን ለራሴ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ደግሜ ደጋግሜ እፈልጋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ማመኑ አስቀድሞ ይመጣል፡፡ ራሳችንን የምናይበትን እይታ ምን እንደሆንን ወይም እንዳልሆንን የምናምነውን እስክንለውጥ ድረስ ሽሽታችንንና ጭንቀታችንን ማሸነፍ አንችልም፡፡
ደራሲ ማርክ ማንሶን

መፈጸም ያሉብንን ነገሮች እያስተላለፍን ከማስረፈድ ልማድ የምነወጣበት 11 መንገዶች።
ዴድላይንዎ ደርሷል። ቢሆንም ስራዎን እንደመፈጸም የማይረቡ ነገሮች እያደረጉ ነው። ፌስቡክ ይከፍታሉ፣ ፊልም ያያሉ፣ ኢንተርኔት ውስጥ ይዞራሉ ፣ ቲቪ ያያሉ ወዘተ። መስራት ወይም ማድረግ
የሚገባንን ነገር ስናዘገይ ነጻ ግዜአችንን በከንቱ እናጠፋለን፣ መፈጸም ያሉብንን ነገሮች እስኪረፍድ እንተዋለን። ከረፈድ በኋላ ደግሞ ጭንቀት ውስጥ እንገባለን። አስቀድመን ለምን አልጀመርንም እያልን እራሳችንን እንወቅሳለን። ይህ ችግር በከፍተኛ ደረጃ የተጠናወታቸው ለአመታት ይህን ልማድ እንደሱስ ሲደጋግሙ ይቆያሉ። ነገሮችን የሚያስረፍድ፣ መከናወን ያለበትን የሚያቆይ፣ ሰነፍ፣ ከስራ የሚደበቅ ሁሉ መገለጫችን ይሆናሉ። ይህ ችግር ውስጣችንን እየበላ በህይወታችን ማሳካት ከሚገቡን ነገሮች አርቆ ያስቀምጠናል።
ይህ ልማድ እድሜዎን እስኪጨርስ አይጠብቁ። በዚህ ጽሁፍ ከዚህ ጎጂ ልማዳችን የምንወጣባቸውን መንገዶችን እናያለን።
1) ስራዎን በትንንሹ ይከፋፍሉ
ነገሮችን ይምናዘገይበት አንዱ ምክንያት ጉዳዩን ለመፈጸም በጣም ከባድ መስሎ ስለሚታየን ነው። በዚህ ግዜ የመጀምርያው ክንውናችን መሆን ያለበት ስራውን በትንሹ መከፋፈል ነው። ከዛም በአንድ ግዜ አንዱን ብቻ መፈጸም ነው ያለብን። አሁንም እራስዎ ሲሰንፍ ካገኙት የሰሩትን ክፍፍል ይበልጥ ያስፉት። ስራዎቹ በጣም ሲያንሱ ለራስዎ “ኢች ብቻ ናት የቀረችኝ” ብለው ማሰብ ይጀምራሉ።
2) በአካባቢዎ ያለውን ነገር ይቀይሩ
የተለያዩ ቦታ እና ሁኔታዎች በምርታማነትዎ ላይ ተጽእኖ ያደርጋሉ። የስራ ገበታዎን እና ክፍልዎን አጢነው ይመልከቱ። ስራ እንዲሰሩ ይገፋፍዎታል ወይስ ጠቅልለው ተኙ ነው የሚሉዎት? ለስራ ካልጋበዘዎት የስራ አካባቢዎን መቀየር ይረዳዎታል። ከዚህ በፊት ይመችዎት የነበረው የስራ ገበታ ከግዜ በኋላ ሊሰለችዎት ስለሚችል ቢሮዎትን መለዋወጥ ይረዳዎታል።
3) ምን መቼ ማለቅ እንዳለበት እቅድ ያውጡ
እንደ ዴድላይን ለሟሟላት መጣር ለእራስዎ የስንፍና ፈቃድ የመስጠት ያህል ነው። ምክንያቱም ግዜ ያለን ይመስለንና ግዜውን ዝም ብሎ ለማሳለፍ ምክንያት ይሆነናል። መስራት ያለብዎትን ፕሮጀክት ከከፋፈሉ በኋላ ለእያንዳንዱ ዴድላይን ያዘጋጁ። ግዜ አከፋፈልዎን አጢነው ያውጡ። አንዱን አለማሳካት ማለት የሌላኛውን እቅድ የሚያስተጓጉል እንዲሆን አድርገው። የዛኔ የግዜ ግምትዎ ስራዎ ከሚያስፈልገው ግዜ ጋር እንዲጣጣም አደረጉ ማለት ነው። በፍጥነት ስራ እንዲጀምሩ ይረዳዎታል። ከቻሉ ወርሃዊ፣ ሳምንታዊ እና ቀናዊ የስራ ክፍፍል አውጥተው ቢቀንሳቀሱ ይበልጥ ይረዳዎታል።
4) የስንፍና ማቆሚያዎችዎን ያጥፉ
ስንፍና ከተጠናወትዎት አንዱ ምክንያት ለመስነፍ ስለቀለልዎት ነው። ስልክዎ ላይ የሚያዘናጉ አፕሊኬሽኖች ካሉ አጥፏቸው። በተደጋጋሚ የሚያዩት ቪድዩ ካለ ጨክነው አጥፉት። ቻት ማድረግ ከሆነ ችግርዎ መልእክት በደረስዎት ቁጥር እንዳይጮህ አድርጉ። በአካባቢዎ ያሉ መዘናጊያዎችን ያስወግዱ። የማህበራዊ ሚድያ የሚከፍቱበት የተወሰነ ሰአት አዘጋጁ። ከዛ ሰአት ውጪ አይክፈቱ።
5) ስራ እንዲሰሩ ከሚገፋፉ ሰዎች ጋር ለመዋል ሞክሩ
ለ10 ደቂቃ ብቻ ቢል ጌትስ ወይም ኢለን መስክን ቢያነጋግሩ የስራ መነቃቃትዎ ይጨምራል። አብረናቸው ግዜ የምናሳልፋቸው ሰዎች ባህሪያችን ላይ ተጽእኖ አላቸው። እነ ቢል ጌትስን አግኝቶ ማውራት የሚቻል ባይሆንም በአቅራቢያችን ለስራ ከፍተኛ መነቃቃት ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ። ከነሱ ጋር አብሮ መዋል የነሱን ባህሪ እንድንላበስ ይረዳናል።
6) እቅድ ያለው ጓደኛ ይኑርዎ
የራሱ እቅድ ያለው ጓደኛ ቢኖርዎ እቅዳችሁን ለማሳካት ሁለታችሁም ትተጋገዛላቹህ። አንዱ ሲሰንፍ ሌላኛው በመናገር እንዲቆጣጠር በማድረግ ሁለታችሁም እቅዳችሁን ለማሳካት አብራቹህ ትጥራላቹ። ሁለታችሁም ተመሳሳይ እቅድ ሊኖራቹህ አይገባም። ተመሳሳይ ቢሆን ይበልጥ ልትረዳዱ ትችላላቹህ። ከስህተቶቻችሁ ይበልጥ ትማራላቹ። ባይሆንም ግን በየግዜው ስለ አላማዎ እና ስራዎ በግልጽ የሚያወሩት ሰው ማግኘት በጣም ጠቃሚ ነው።
7) ስለ እቅድዎ ለሌላ ሰው ይንገሩ
ስለ እቅድዎ ለሚያቁት ሰው ሁሉ መናገር ተጠያቂነት ስሜት ያሳድርብዎታል። የቅርብ ዘመዶች እና ጓደኛዎች “እንዴት ሆነልህ/ሽ” ብለው መጠየቃቸው ስለማይቀር ላለመሸማቀቅ ሲሉም ቢሆን የተወሰነ ክንውን ለመፈጸም ይበረታታሉ። በፌስቡክ ገጽዎ ላይ ስለ እቅድዎ ለጓደኞችዎ በሙሉ መግለጽ እቅድዎን ለማከናዎን ይበልጥ ይገፋዎታል።
8) እቅድዎን ያሳካ ሰው ፈልጉ
ምንድን ነው ማሳካት የሚፈልጉት? እሱን ያሳኩ ሰዎች እነማን ናችው? ፈልገው ያግኟቸው። ግንኙነት ይፍጠሩ። የእቅድዎን ስኬት ፍሬ የሚያጣጥሙ ሰዎች ማወቅ ለራስዎ ከፍተኛ መነቃቃት ይሰጥዎታል።
9) እቅድዎን በየግዜው ያሻሽሉ
አንዳንድ ግዜ የስንፍና መንሻው እቅድ ሲያወጡ የፈጠሩት ስህተት ነው። እቅድዎን ለማሳካት መፈጸም አለብኝ ብለው ያስቀመጡት ክንውን እቅድዎን ለማሳካት ላይረዳዎት ይችላል። እሱን ሲረዱ ክንውኑን ለመቀየር እንዳይፈሩ። የመጨረሻ እቅድዎን በተለያየ ምክንያት መቀየር ከፈለጉ ግዜ ሰተው ያስቡ። ከግዜ በኋላ በሃሳብዎ ከጸኑ እንዲሁም ለእቅድዎ መቀየር አሳማኝ ምክንያት ካለዎት በፍጥነት ቀይረው አዲሱን እቅድ ለማሳካት በፍጥነት ይንቀሳቀሱ። አዲሱ እቅድዎን ለማሳካት የሚያስፈልግዎትን ክንውኖች አውጥተው ይንቀሳቀሱ።
10) ነገሮችን አያወሳስቡ
እቅድዎን ለማሳካት ትክክለኛውን ግዜ እየጠበቁ ነው? በዚህም በዛም ምክንያት ጥሩ ግዜ አይደለም ብለው ያስባሉ? ከሆነ ይህንን ሃሳብ በፍጥነት ይጣሉ። ሁሌም ወደ እቅድዎ ላለማምራት የሆነ ምክንያት ይኖራል። ትክክለኛው ግዜ እስኪመጣ ብለው የሚጠብቁ ከሆነ እቅድዎን መቼም አያሳኩትም። አንድን ነገር ችግር በሌለበት ግዜ እፈጽማለሁ ብሎ ማሰብ እንዲሁም የምፈጽመው ነገር ችግር ሊኖረው አይገባም ብሎ ማሰብ ቀንደኛ ላለመጀመር ይምንጠቀምባቸው ምክንያቶች ናቸው።
11) ዝም ብለው ያከናውኑት
መጨረሻ ላይ ዝም ብለው መስራት ያስፈልግዎታል። ምንም ያህል እቅድ ቢያወጡ፣ ቢያስቡ፣ ቢያወጡ ቢያወርዱ ከስራው ይሚታደግዎ ነገር የለም። ምንም ክንውን ማፈጸም ካልጀመሩ ወደ እቅድዎ አንድ እርምጃም አይንቀሳቀሱም። ምንም አይፈጠርም። ሁሌ ሰዎች በሁኔታቸው ይማረራሉ። ግን በዛውም ልክ ምንም ወደ እቅዳቸው የሚወስዳቸው ስራ ሲሰሩ አይታዩም። በስንፍና ወደ ስኬት መሄድ እንደማይቻል ህይወት ትነግረናለች። ምንም ሆነ ምን መፈጸም ይሚፈልጉት ነገር ተነስቶ ማድረግ መጀመር ነው።
ሌላውን ለማስተማር #ሼር ያድርጉት

Forwarded from Tesfaab Teshome
"ክፉ ቀኖች ያልፋሉ ፥ ፅኑ ሰዎች ያልፉታል"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ሀ፥ በህወሓት እና በኦነግ መካከል ያለው የፖለቲካ ሽኩቻ የመስዋዕት በግ ፈለገ። ሁለቱ እንዲሸናነፉ ያለ ሀጢያቱ የሚታረድ ሚስክን ተፈለጎ ተገኘ። ያ ምስክን በሀረርጌ ገጠራማ አከባቢ የተከበረ አባት ነው።ሰውዬው እንደዋዛ "ኦነግ ገደ*ለው" ተብሎ ተገ*ድሎ ተጣለ። የሰውዬው ሞት ቤተሰባዊ ምስቅልቅል ወለደ።
ጥላዬ ታደሰ የተባለ ሰቃይ ተማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበር። የአባቱን ሞት የሰማ ቀን ሰማይ ተደፋበት። ተስፋው ጨለመ፥ የመኖር ፍላጎቱ ትቶት ተሰደደ።
ጥላዬ ታደሰ ከአባቱ ሞት በኋላ ሌላ ሰው ሆነ። ሙሉ ለሙሉ ሱስ ውስጥ ተዘፈቀ። ጫት ፥ ሲጃራ እና አረቄ መደበቂያው ሆኑ። ሀዘኑን በአረቄ ሸሸገው።
ጥላዬ ሱሰኛ ሆነ ሲባል ዝም ብሎ ሱሰኛ አይደለም የሆነው። አንድ እሁድ እለት እስኪሰክር ጠጥቶ ተኛ። ከስካር ወለድ እንቅልፉ የነቃው ሰኞ ሳይሆን ማክሰኞ ነው። ከእሁድ እስከ ማክሰኞ በእንቅልፍ አሳለፈ። ሰኞ እለት ሳይኖርባት አለፈች። ጥላዬ ታደሰ ሲሰክር እዚህ ድረስ ነው።
የአባት ሞት ፥ ተስፋ መቁረጥ ፥ ሱሰኝነት ፥ ብተኝነት እየተፈራረቁ የደቁሱት ዶክተር ጥላዬ "ጥላዬ ቀደምኩት" የሚል ህይወቱን የሚናገር ግሩም መፅሐፍ አለው። "ይህ ሰው ማነው?" የሚል ጠያቂ ካለ ዶክተር ጥላዬ ዛሬ የተከበረ የናሳ ሳይንቲስት ነው። አዎን የናሳ ሳይቲስት!
ህይወቱ ከሱስ እስከ ናሳ በአስገራሚ ክስተቶች የተሞላ ነው። የዶክተር ጥላዬ ህይወት የሚነግረን ግሩም መልእክት አለ! ያም መልእክት "ክፉ ቀኖች ያልፋሉ፥ ፅኑ ሰዎች ያልፉታል" የሚል ነው።
ለ፥ ፓስተር ታምራት ሀይሌ "አባት" ብለን ብንጠራቸው ከማያሳፍሩን ጥቂት የሃይማኖት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ እጅግ የከበረ ስም ካላቸው ግንባር ቀደም ሰዎች መካከል አንዱ ፓስተር ታምራት ሀይሌ ነው።
የፓስተር ታምራት የትላንት ህይወቱ በብዙ ፈተና እና ውጣ ውረድ የታጨቀ ነበር።
አባቱ ታዋቂ ባለ ውቃቢ ነበር። ያ ብቻ ሳይሆን የአባቱ ውቃቢ እንዲያርፍበት ታምራት ተመረጠ። ከዚህ በኋላ ህይወቱ የሰቀቀን ሆነ። ገና በልጅነቱ ከእኩዮቹ ጋር በነፃነት መንቀሳቀስ የማይችል ሆነ። መናፍስት እየተገለፁለት ያሰቃዩት ነበር።
ቤተሰቦቹ ለሊት ለሊት ወንዝ ዳር እየወሰዱት የአምልኮ ስርኣት ፈፅመውበታል። ሰውነቱን እስኪቆስል በአሸዋ ከፈተጉት በኋላ በውሃ ይነከራል። የልጅ ሰውነቱ ላይ የተፈጠረው ቁስል ውሃ ሲያገኘው ስቃይ ቢፈጥርበትም ለውቃቢው ሲባል ደጋግሞ አድርጎታል።
ታምራት ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ በሰው ቤት ተቆጥሮ ሲሰራ ከሰው በታች ሆኖ ተዋርዷል፥ ስድብ እና ዱላን እንደዋዛ ተቀብሏል። ራሱን ስለማጥፋት አስቦም ያውቃል።
ዛሬ ላይ ፓስተር ታምራት የተከበረ ሰው ነው። "የታምራት አምላክ ተአምረኛ" የሚል የህይወት ታሪኩን የሚያወሳ መፅሐፍ አለው።
የታምራት ህይወት ምን ይነግረናል? "ክፉ ቀኖች ያልፋሉ!"
ሐ፥ ኢትዮጵያ ከምትኮራባቸው ጥቂት የላቁ አእምሮዎች መካከል አንዱ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው በቀላሉ የማይደገሙ ሊቅ ናቸው። ብቻቸውን ብዙ ሰው!
ጌታቸው ገና ጨቅላ ሳለ የፋሽስት ወረራ ቤተሰባዊ ምስቅልቅልን ወለደ። ከዛ በኋላ ብዙ አስቸጋሪ ወቅቶችን አሳልፏል።
አባቱ ለትምህርት ካላቸው ፍቅር የተነሳ ልጃቸው እንዲማር ዘመድ ዘንድ ሰደዱት። ውጤቱ ግን የተገላቢጦሾ ሆነ። ህፃኑ ጌታቸው መማር አልቻለም። እረኝነት እጣ ፈንታው ሆነ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የመማር መብቱን የተነፈገው ህፃን ሰብአዊ ክብሩንም ተቀማ። ሰውነቱ በእከክ ሲወረር አዛኝ አጣ። ሰውነቱ እስኪቆስል ድረስ ማከክ ግዴታው ሆነ።
ወደ አባቱ ሲመለስ የተከበረ ኑሮ አልጠበቀውም። ከአባቱ ጋር በመቃብር ቤት እየኖረ መማር እጣ ፋንታው ሆነ።
ጌታቸው ሀይሌ የእናቱን ፍቅር ሳይጠግብ ገና ጨቅላ ሳለ እናቱ ተለይታው ሄደለች። የእናት ናፍቆቱን የሚወጣበት በቂ እድል አልነበረውም።
አባቱ የጤና እክል ገጥሞት ከአልጋ መዋል ግዴታው ሲሆን ብቻውን ለአባቱ ቂጣ እየጋገረ ይኖር ነበር። እንደ እኩዮቹ መጫወት ሳያምረው አባቱን እያስታመመ እና ለአባቱ ምግብ እያበሰለ ልጅነቱን አሳልፏል።
ትዳር ከመሰረተ በኋላ ሐገር ለማገልገል በሚጥርበት ዘመን የደርግ ሰዎች ሊይዙት ቤቱ ድረስ ከመጡ በኋላ ተታኩሰው ጉዳት አድርሰውበታል። ፕሮፌሱሩ ለረጅም ዘመን በዊልቸር እንዲቀመጥ ያስገደደውን መዘዝ ያመጣው ያ ጉዳት ነበር።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ባለ ግርማ ሊቅ ሆነዋል። የስኬት ጫፍ ላይ ተገኝተዋል። ህይወታቸውን "አንዳፍታ ላውጋችሁ" በሚል መፅሐፍ ከትበውታል።
ህይወታቸው ምን ይነግረናል? ክፉ ቀኖች ያልፋሉ!
ሁላችንም በአንዳች አይነት መከራ እያለፍን ይሆናል። እጅ የማይሰጥ ፅኑ መሆን እንዳለብን የብዙዎች ህይወት ይነግረናል!
በእርግጥ ክፉ ቀኖች ያልፋሉ!
Nb፥ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለው "ክፉ ቀኖች ያልፋሉ ፥ ፅኑ ሰዎች ያልፉታል" የሚል የትርጉም መፅሐፍ አንብቤ ነበር። የመፅሐፉ ደራሲ ሮበርት ሹርለ ይመስለኛል።
@Tfanos

Forwarded from ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
አሁንን የመኖር ሀይል
በመጀመሪያ አሁን የጊዜ አካል አይደለም። ጊዜ እንዲኖር ያለፈው ወይም የወደፊቱ መኖር አለበት። አሁን የጊዜ አካል ሳይሆን ዘላለማዊ (eternal) ነው። ልብ ብላቹ ካሰባችሁት ጊዜ ያለው አእምሮአችን ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም ምናስባቸው ሀሳቦች በጊዜ ውስጥ ማለትም በባለፈው እና በወደፊቱ ጊዜ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እስኪ ምታስቧቸው ሀሳቦች ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ለማተኮር ሞክሩ፤ ከዚያ አእምሮአችሁ በባለፈው(past) እና በወደፊቱ(future) ላይ ተጠምዶ ታገኙታላቹ።
ስለ አሁን(present) ማሰብ አትችሉም። አሁን ላይ ማሰብ ሳይሆን መኖር (አእምሮ አልባ መሆን) ነው ምትችሉት። እስኪ ስለአሁን ለማሰብ ሞክሩ ምን ሀሳብ ወደ አእምሮአችሁ መጣ? በርግጠኝነት ምንም ማሰብ አልቻላችሁም፤ ስለዚህ ሀሳብ የሚያርፍበት ጊዜ ይፈልጋል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ምንም የማያስብ ስራፈት ትሆናላችሁ ማለት አይደለም። አሁን ላይ መኖር ስትጀምሩ ከአእምሮአችሁ በላይ መሆን ትጀምራላችሁ። ስለዚህ አእምሮአችሁን ምን ማሰብ እንዳለበት የምትወስኑት እናንተ መሆን ትጀምራላችሁ ማለት ነዉ። ነገር ግን አእምሮ ካለናንተ ፍቃድ በራሱ ማሰብ ያቆማል። አእምሮአችሁ እናንተ ሳትፈልጉ በሀሳብ የሚጠመድ ከሆነ ግን አሁን ላይ እየኖራችሁ አይደለም ማለት ነው።
አሁን ላይ ለመኖር ተደጋጋሚ የተመስጦ (meditation) ልምምድ ያስፈልጋችኃል፤ ምክንያቱም ከአእምሮአችሁ ካልተላቀቃችሁ አሁንን መኖር አትችሉም። ተመስጦ (meditation) ማለት ደግሞ ምንም ሳይሆን እራሳችንን ከአእምሮ ቁጥጥር የምናላቅቅበት መንገድ ማለት ነው። ከአእምሮአችሁ ስትላቀቁ ህይወትን ከዳር ቆማችሁ እንደ ተመልካች መታዘብ ትችላላችሁ።
ህይወትን በሙላት መኖር ከፈለጋችሁ ከኢጎ (ከአእምሮ ቁጥጥር) መላቀቅ ይኖርባችኃል። ኢጎ ከሌሎች የተሻላችሁ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ እና ሌሎችን እንድትጨቁኑ ይነግራችኃል። አለማችን ላይ የምናየው ጦርነት፣ ክፉት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ፅንፍ የወጣ ሀይማኖትን ተገን ያደረገ የሰዎች ጭፍጨፋ በሙሉ የኢጎ ውጤቶች ናቸው። ሁላችንም ውስጥ አይነቱ ይለያይ እንጂ የሆነ አይነት ኢጎ አለ። ኢጎ አሁንን እንዳንኖር የሚገዳደረን ቀንደኛ ጠላታችን ነው።
ሁላችንም ኢጎን አሽቀንጥረን መጣል ይኖርብናል። አለበለዚያ ሰዎች በሰላም የሚኖሩባት የተዋበች ምድር ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን ከኢጎ መላቀቅ እንደምናስበው ቀላል አይደለም። ከህፃንነታችን ጀምሮ የሆነ የኢጎ ማንነት ስንገነባ ኖረናል። ኢጎአችን ትክክለኛ ማንነታችን እስኪመስለን ድረስ ከስብዕናችን ጋር ተጣብቋል። አንዳዶቻችን የብሔር ማንነትን፣ ሀይማኖትን፣ ግለሰባዊ አስተሳሰብን፣ የበላይነት ስሜትን፣ የቆዳ ቀለምን እና የመሳሰሉትን እንደ ተፈጥሮአዊ ማንነት በመቁጠር ከሌሎች ጋር እስከ መጋጨት እና መተላለቅ የሚያደርሱን የኢጎ ገፅታዎች አሉን። እነዚህ ኢጎዎች ከፍ ሲሉ በሀገራት ደረጃ አሁን የምናየውን ጎራ ለይቶ መጠፋፋት ያስከትላል።
አእምሮአችን ህይወትን ውስብስብ አድርጎብናል። ህይወት ግን በጣም ቀላል ናት። አእምሮአችን ማፍቀር አይችልም፤ አእምሮአችን የሚችለው ማስላት ነው። ህይወት አሁን ናት። ከአሁን ወጪ ማድረግ ምትችሉት ነገር አለ? መኖርስ? ያለፈው እና የወደፊቱ ጊዜ ቅዠት ብቻ ናቸው። ያለፈ የምንለው ጊዜ ስንኖርበት አሁን ነበር፤ የወደፊቱም አሁንን ሆኖ ነው ሚመጣዉ። አሁን ላይ መኖር ስትችሉ ከሁለንተና ጋር ትዋሀዳላችሁ።
ብዙ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ለምሳሌ፦ ተራራ መውጣት፣ ከፍተኛ ህመም፣ ከባድ የህይወት ፈተና ሲያጋጥማቸው አሁን ላይ የመገኘትን አጋጣሚ አግኝተዋል። ነገር ግን አሁን ላይ ለመገኘት የግድ እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎች መጠበቅ የለባችሁም። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ አሁን ላይ መገኘት ትችላላችሁ።
@zephilosophy

የጅምላ ኢጎ
✍️ኤካህርት ቶሌ
ኢጎ በግላዊ ማንነቱ አለመርካቱን ለማመልከት ከሚያደርጋቸው ሙከራዎች አንዱ ከቡድን ጋር አንድ በመሆን የማንነት ስሜቱን ማስፋፋት እና ማጠናከር ነው። እነዚህ ቡድኖች ሃገር፣ብሄር፣ የፓለቲካ ፓርቲ፣ ማህበራት፣ ተቋማት፣ ሴክተሮት፣ ክለብ፣ አደገኛ ቦዘኔዎች ፣ የእግር ኳስ ቡድኖች እና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ።
አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሠው እኔነቱን ትቶ ለጅምላው መልካም ነገር ሲል ምንም ዓይነት የግል ጥቅም፣ ችሮታ ወይም ክብር ሳይፈልግ፣ ህይወቱን እስከመሰዋት ድረስ ሲሰራ ግላዊ ኢጎው የከሰመ ሊመስል ይችላል። የቡድኑ ያህል ዋጋ ቢከፍሉም፣ደስተኝነት ሙሉነት ይሰማቸዋል። ከኢጎ ባሻገር የሄዱ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን ከኢጎ ነፃ ወጥተው ሳይሆን ኢጎ ከግላዊ ወደ ጅምላዊ ተሸጋግሮ ነው።
የጅምላ ኢጎ ልክ እንደ ግል ኢጎ ግጭትንና ጠላትን የመፈለግ፣ በተሳሳቱ ሌሎች ላይ ትክክል መሆንን መፈለግ እና የመሳሰሉት ተመሳሳይ ባህሪያት አሉት። ፈጠነም ዘገየም፣ ቡድኑ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ አይቀርም፤ ምክንያቱም ግጭትንና የራሱን ክልል ለመወሰን ብሎም ማንነቱን ለማግኘት ተቃውሞን ሳያውቅ ይፈልግ ነበር።አባሎቹም ማንኛውም ከኢጎ ተነሳሽነት የሚፈጠረውን ተግባር ጋር ተከትሎ የሚመጣውን ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ። በዚህም ጊዜ የነበሩበት ቡድን ጠንካራ የጥፋት ተልዕኮ እንደነበረው ሊነቁና ሊገነዘቡ ይችላሉ።
የነበርክበት እና እራስህንም ያዛመድክበት ብሎም ስትሰራለት የነበረው ቡድን፣ በርግጥ የጥፋት መሆኑን በድንገት ስትረዳ በመጀመሪያ የሚያም ይሆናል፡በዚያ ጊዜ አንዳንዶች የበለጠ ክፉና መራር ይሆናሉ። ይህም ማለት የቀድሞው ሃሳብ፣ውዥንብር እና የወደቀ መሆኑን ሲረዱ ወዲያውኑ የሌላ አይነት ዕምነት ስርዓት ይቀበላሉ ማለት ነው። የኢጎአቸውን ሞት ከመቀበል ይልቅ፣ ከዚያ በማምለጥ በሌላ አዲስ ኢጎ ዳግም ይወለዳሉ።
የጅምላ ኢጎ ጅምላውን ከፈጠሩት ግለሰቦች ኢጎ በላይ ማስተዋል የለሽ ነው። ለምሳሌ ሰልፈኞች (ጊዜያዊ የጅምላ ኢጎ ስብስቦች) ግለሰቦቹ ከሰልፈኞቹ ውጪ ቢሆኑ ኖሮ የማይፈፅሙትን አይነት ከፍተኛ ጥፋት የመፈፀም አቅም አላቸው። በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ኖሮ ዕብደት ተደርጎ የሚወሰድን ተግባር፣ አገሮች ግን በተደጋጋሚ ሲፈፅሙት ይታያል።
የሰዎች፣ የብሄሮችና የሐይማኖት ተቋማት የጅምላ ኢጎ ፣ “እኛ ቅዱሶች፣ ሌሎች እርኩሶች” የሚል ጠንካራ የፓሪኖያ ችግር አለበት። የስፔናውያን ስቃይ፣ አፈንጋጮችንና “ጠንቋዮች”ን ማንገላታት እንዲሁም ማቃጠልና፣ እስከ ኣንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ የደረሰው የሐገራት ግንኙነት፣ አጠቃላይ የኮሚዩኒዝም ታሪክ፣የመስቀል ጦርነት ፣ጀሀድ፣ ቀዝቃዛው ጦርነት፣ በ1990ዎቹ በአሜሪካ የነበረው ማካርቲዝም፣ እስካሁን የዘለቀው የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፣ ሁሉም በሰው ልጆች ውስጥ በእጅጉ አሰቃቂ እና በፅንፈኛ ጅምላዊ የኢጎ በሽታ የተሞሉ የታሪክ ክፍሎች ናቸው።
ግለሰቦች፣ ቡድኖች አገሮች እስተዋይ ባልሆኑ ቁጥር፣ይሄ ኢጎአዊ በሽታ ወደ አካላዊ ጥቃት መሸጋገሩ አይቀሬ ነው። አካላዊ ጥቃት ኋላቀርነት ይሁን እንጂ
አሁንም ድረስ የተንሰራፋ ተግባር ነው። ምክንያቱም ኢጎ የእራሱን አሸናፊነት መጠበቅ፣ እራሱን ትክክል ሌሎች ስህተት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲል ይጠቀምበታል። ማስተዋል የለሽ በሆኑ ሠዎች መካከል ትንንሽ ክርክሮች ወደ አካላዊ ጥቃት በቀላሉ ያመራሉ። ክርክር ምንድን ነው? ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሠዎች የየራሳቸውን ምልከታ ይገልፃሉ፤ እነዛም ምልከታዎች ይለያያሉ። እያንዳንዱ ሠው ምልከታው ከፈጠረለት ሃሳብ ጋር አንድ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሃሳቦቹ ጠንክረው የማንነትና የሃሳብ ስሜት ላይ የዋሉ አዕምሮአዊ እቋም ይሆናሉ። በሌላ አባባል ማንነትና ሃሳብ ይቀላቀላሉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ለአመለካከቴ ስከራከር ወይም ስቆም ፣ ልክ እራሴን እንደምከላከል ይሰማኛል፤ እተውናለሁም። ሳላስተውለው ልክ ለህልወናዬ እንደምዋጋ እሆናለሁ፤
ስሜቶቼም የዚህን ማስተዋል የለሽ እምነት ያንፀባርቃሉ። እበሳጫለሁ፣ እናደዳለሁ፣እከላከላለሁ ወይም ኃይለኛ እሆናለሁ። እንዳልጠፋ በሚል ስጋት፣ ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል
ማሸነፍ አለብኝ።ውዥንብሩ ያ ነው። ኢጎ እራሱ የማትመለከተው አዕምሮ በመሆኑ ምክንያት አዕምሮም ሆነ ሀሳባዊ አቋሙ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አያውቅም።