Telegram Web
Forwarded from በዝሙት አንዘምን 🚫 (Last name)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👆
ተመልከት ይሄን ጉድ አጂብ ሰው ውሸት ይዞ ለሃይማኖቱ እንደዛ እየለፉ እኛ ግን ሀቅ ይዘን ተኝተናል ጥቅማችንን ብቻ እያሳደድን ነው፣ በዱንያ ላይ ለውጥ ካላመጣን እንቅልፍ እናጣለን በአኼራችን ጉደሰይ ግን ለውጥ አለማምጣታችን አያሳስበንም፣ ቁጭ ብለን አንተ ውሃብይ አንተ ሱፍይ በመባባል ስንጨቃጨቅ እንውላለን! ወንድም እህቶቻችን ግን የሚበሉት አጠው ሳይፈልጉት ሃይማኖታቸውን እየቀየሩ ይገኛሉ።

ሰው በማጣት ወይ በጅህልና ሲከፍር ያሳዝናል ከሆነ ቡሀላ ከማዘን ይህንን ያሳስበኛል የሚል በአቅሙ ችላ ሳይል ያግዘ፤ 1ብርም ቢሆን ከብዙ ሰው ሲሆን ዋጋ አለው። እነሱ ለማክፈር ማያረጉት ጥረት የለም መስጂድ መሄጃችን መንገድ ላይ ስብከት ነው ፣ ታክሲ ውስጥ ስብከት ነው፣ ግቢ ላይብረሪ ጥቅስ ነው። እነሱ እውነት ሳይዙ እንዲ እውነት ለማስመሰል እታየገሉ የኛ መተኛት ያናዳል።  

እና አሁን ለጊዜያዊ ለረመዳን ማፍጠሪያ ለመስጠት አስበን ነበር። አምና አፍጥር ሰአት ግቢ እየመጡ ይለምኑን ነበር የሚል መልእክት ተላልፏል ኢንሻ አላህ የምንረዳበትን መንገድ አድራሻ አስቀምጣለሁ ሁላችንም የምንችለውን እናድርግ!

  ሼር እናድርገው! ሚዲያን ተጠቅምን ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን። አንተኛ በገንዘብ ማገዝ ካልቻልን በዱዓና መልእክቱን በማስራጨት እናግዝ። ምክንያቱም ብዙ አሉ ማገዝ እየፈለጉ በምን አይነት መንገድ ላግዝ ብለው የሚያስቡ። ስለዚህ በምንችለው እናስራቸው

CBE 1000382062888
holder Fedlu Kadir,
ስልክ 093 724 0724

Munira bargieho & samira kori
CBE 1000547610184

        ባረከላሁ ፊኩም

👉 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር 👍
ገራሚ ታሪክ
==========
(በተለይ ወላጆች ይህን ሸይኽ ፕሮፌሰር ዐብዱ-ር'ረዛቅ አል-በድር የሚነግሩንን ታሪክ በደንብ አዳምጡት!)
||
ከሆነ ሃገር ለዑምራ የመጣ አንድ ሰው ጠዋፉን ጨርሶ በካዕባ ዙሪያ ሐጀረ-ል-አስወድ አካባቢ ዱዓእ እያደረገ ነበር። አስተውላችሁ ከሆነ ሐጀረ-ል-አስወድ ጋር ከፍተኛ የህዝብ መገፋፋት ስላለ እጃቸውን በሆነ መያዣ ላይ አስደግፈው የሚቆሙ ወታደሮች አሉ። በዚያ አጋጣሚ እዛ ጋ ቆሞ የነበረው ወታደር ገጠመኙን እንዲህ ይተርከዋል። "በጣም ለቅሶው የበረታ ሰው ድምፅ ሰማሁ። ምንድን ነው ብዬ ዘወር ሲል አንድ ሰው ከባድ ለቅሶ እያለቀሰ አላህን ይለምናል። ለቅሶው ስለሳበኝ ምን እያለ ይሆን ብዬ ሳዳምጠው በዱዓቅ መሃል «ያ ረብ! (ጌታዬ ሆይ!) ሰዎች ልጆች አሏቸው። እኔ ልጅ የለኝም!» ይህን ቃል እየደጋገመ በጣም በብርቱው ያለቅሳል። ሲደጋግመው ስለነበር በጆሮዬ ይህንን ድምፁን ሸምደጀዋለሁ።

ከዚያም ከ18 ወይም 20 አመታት በኋላ በዚሁ በሐጀረ-ል-አስወድ ቦታ ሳለሁ፤ ራሱኑ ያኔ የሰማሁትን ድምፅ ሰማሁ። ግለሰቡን አስታወስኩና ፊቱን ለመመልከት ዞርኩ። ራሱ የያኔው ሰውዬ ነበር። ልክ እንደዛው በብርቱው እያለቀሰ አላህን ይለምናል። ምንድን ይሆን የሚለምነው ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ። "ያ ረቢ! (ጌታዬ ሆይ!) ይህንን ልጅ አጥፋልኝ!" ይላል። እዛ ዱዓእ ማድረጊያው ዘንድ ሆኖ ልጄን አጥፋልኝ እያለ አላህን ይማፀናል። ከቆምኩበት ቦታ ወረድኩና ከዚያ ከካዕባው ዙሪያ ይዠው ወደ ውጭ (ወደ ዳር) ወጣን። እንዲህም አልኩት፦ «ከዛሬ 18 አመታት በፊት በዚሁ ቦታ አላህ ልጅ እንዲሰጥህ ስትለምን የነበርከው ሰው አይደለህምን?»
«አዎ!» አለኝ። እኔም «አንተ በዚህ ቦታ ልጅህን ሁለት ጊዜ በድለኸዋል። የመጀመሪያው በደልህ፤ እኔ ያኔ ሰምቸሃለሁ፣ ዱዓህን ሐፍዤዋለሁ፣ ዝም ብለህ "ልጅ ስጠኝ!" ነበር እንጂ ስትል የነበረው "መልካም ልጅ ስጠኝ!" አልነበረም ያልከው። አሁን ደግሞ ሁለተኛው በደልህ ራሱ ቦታ መጥተህ አላህ እንዲያጠፋው ትለምናለህ። በመጀመሪያውም በመጨረሻውም አላሳመርክለትም። አሁንም ወደዛው ቦታ ተመለስና አላህ እንዲመራው ዱዓእ አድርግለት። ልክ እንደበፊቱ ራሱኑ ለቅሶ እያለቀስክ ቀልቡን እንዲመራለት ዱዓእ አድርግለት። ይህን አስረዳሁትና ይዤው መልሼ ወደዛው ቦታ ወሰድኩት።  ከዚያም ለቅሶውን ጀመረና ለልጁ ሂዳያ እንዲሰጠው አላህን መለመን ጀመረ።

ከዚያም ከአንድ አመት በኋላ ከልጁ ጋር መጣ። ሰላምታ አቀረቡልኝና ለልጁ ታሪክህን ንገረው አለው። ከዚያም ልጁ መሃላ እየማለ፤ ያኔ አባቴ በዚያ ቦታ እያለቀሰ አላህ ሂዳያ እንዲሰጠኝ በሚማፀንበት ሰዓት ተነስቼ ውዱእ አድርጌ ሶላት ጀመርኩ። ከዚያም በኋላ ሁኔታዬ ተስተካከለ።
በብዙ መልኩ ወላጆቹን አዛ የሚያደርግና በሐራም ነገሮች ላይ ሲያሳልፍ የነበረ ልጅ ነው።»

ከዚህ የምንማረው፤ ወላጆች አላህ ልጅ እንዲሰጣችሁ ስትፈልጉ፣ ልጅ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ነገር ስትጠይቁት መልካሙን (ሷሊሑን) ጠይቁት። አንዳንዱ ፊትና ይሆናል። አይበለውና መጥፎ ካጋጠማችሁ ለውሳኔ ቸኩላችሁ በንደት አትራገሙ፤ በምትራገሙበት ምትክ አላህ እንዲያስተካክለው ዱዓእ ብታደርጉበት የበለጠ ነው። አላህ መልካምን ሁሉ ይወፍቀን።

||
Copy
የሴት ፊትና
Daru tewhud
በተለይ ወደ ዳዕዋ የቀረባችሁ ወንድሞች ክፉ ምሳሌ እንዳትሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላሀ

        www.tgoop.com/Darutewhide
የዱንያ ፈተና
Daru tewhid
ዱንያን እንደ አህያ ተጠቀማት እንጂ እንደ አህያ አትጠቀምህ።

 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላሀ

          www.tgoop.com/Darutewhide
ወዳጆቼ

ወንጀል እና አመፅ
ሁላችንም የገባንበት በር ነው!
ሁላችንም የዋኘንበት ባህር ነው! አላህ ከመረጣቸው እና ከመለመላቸው ከአንቢያዎች እና ከመልዕክተኞች በቀር የተጠበቁት ካልሆኑ በስተቀር ከሱ አይድኑም!
እኔ አንቺ አንተ ሁላችንም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉን ነን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል"የአዳም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው ከስህተኞቹ መሀከል በላጮቹ ተፀፃቾቹ ናቸው"
ቅጣት እና ጥፋት በወንጀል ላይ መዘውተር ነው! ያ ደካማ ነፍሶች ያስዋቡት ቆሻሻ ሸይጣኖችም። ኡመር እና አብዱልዐዚዝ ረሂመሁሙላህ እንዲህ አሉ እናንተ ሰዎች ሆይ! ወንጀል የሰራ አላህን መሀርታ ይጠይቅ እና ይቶብት
ከጥፍት ሁሉ ጥፍት እዛው ወንጀል ላይ መዘውተር ነው በወንጀል ምክንያት መፀፀት እና ማልቀስ ግድ ይላል ወዲያውንም ከሱ መቆጠብ ወደ ሀቅ መመለስ ስህተት ውስጥ ከመስመጥ የተሻለ ነው! ወደ አላህ በመመለስ ዲንን በመያዝ ካልሆነ በስተቀር ህይወት አትስተካከልም!!
ብዙዎች ወላዋዮች ናቸው!
ብዙዎች ወንጀሎቻችን ብዙ ናቸው! የሚሉ ናቸው
ብዙዎች ወንጀላችን የጠለቀ ነው "አላህ ይምረናልን??" ይላሉ "አዎ" አላህ ይምራችኋል!! ከቶበታችሁ ከተፀፀታችሁ እና ከተመለሳችሁ እንደውም በተውበታችሁ እና በመመለሳችሁ አላህ (ሱ.ወ) ይደሰትባቸኋል
አላህ ተውበተኞችን ተጥራሪዎችን ይወዳል! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:- "ከወንጀል የተመለስ ወንጀል እንደሌለበት ነው!" ወደ ተውበት እና ወደ ፀፀት እንቻኮል "ጌታዬ ወደ ምድር መልሱኝ" እያልን ከመጮሀችን በፊት ወደ አላህ እንመለስ

https://www.tgoop.com/Ibnalisunnahchannel/3777
👆👆👆join share
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እርዳታ ለሚሹ ሰዎች ለመድረስ ምን ያክል ፍላጎት አሎት?

ከላይ እንደተገለጸው እርዳታ ሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ማገዝ/መርዳት ለምፈለጉ ሰዎች ይህ ድርጅት ለናንተ ትክክለኛው ቦታ ነው።
ከኛ ጋር ለመስራት የሚያስፈልገው የናንተ ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ብቻ ሲሆን ለመቀላቅል ያሰባቹ ሰዎች ይህን ፎርም🗒 በመሙላት መግባት የመትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

⚫️ይህን በጎ አድራጎት ድርጅት ለመቀላቀል መስፈርቶች
-ይህን ድርጅት ለመቀላቀል ፈቃደኛ መሆን።
-16-22 እድሜ ክልል ውስጥ ባሉት።
-የመመዝገቢያ ገንዘብ💵 እና ፎቶ ማሟላት።
-የወር ተቀማጭ መክፈል ።
-አስፈላጊ ቦታዎች ላይ በሰአቱ🕐 መገኘት።

መመዝገቢያ፡ https://forms.gle/FF8c58eREJoJ2LWN6

https://www.tgoop.com/Ibnalisunnahchannel/3780
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እዚህ ተቀምጠን በምኞት ብዙ አመት እንደምንኖር እናስባለን ይህን ተስፋ ምንድነው ሚሰጣቹ???
ያልሞትኩት ስላልታመምኩ ነው ብለህ ታስባለህ! የሞቱት ደግሞ የሆነ ችግር ስላለባቸው ነው/በዶክተሮች ስህተት ነው ብለህ ታስባለህ 😔😔
አላህ የቀደረብህ ቀን መች እንደሆነ አታውቅም አሁንም እኮ ልትሞት ትችላለህ በተኛንበትም እኮ በዛው ልንቀር እንችላለን

ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ ምናልባት ዛሬ ወደ አላህ ለመመለስ የተሰጠን የመጨረሻ ቀን ሊሆን ይችላልና በተውበት እናሳልፈው

ያአላህ መጨረሻችንን አሳምርልን

https://www.tgoop.com/Ibnalisunnahchannel
join and share
🪴‏"أكبر ما يُمكن أن يقدمه أبٌ لأطفاله هو أن يحبَّ أمهم"

🪴"አባት ለልጆቹ ሊያደርግ የሚችለው ትልቁ ነገር እናታቸውን መውደድ ነው
2024/06/30 12:41:41
Back to Top
HTML Embed Code: