ቅዱስ ላሊበላ ከዳቪንቺ የላቀው ጠቢብ
የፀሎተ ሐሙስ ምስል
አፍሮ አይገባ
The Last Supper
በያሬድ ሹመቴ እንደተፃፈው
*ሊዮላርዶ ዳቪንቺ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1495 እስከ 1498 ባለው ጊዜ በጣሊያኗ የሚላን ከተማ በቅድስት ማርያም (Santa Maria delle Grazie) ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደሳለው የሚነገረው ዝነኛው የመጨረሻው እራት (The last supper) ሲል ከሰየመው የጥበብ ውጤት አስቀድሞ ቅዱስ ላሊበላ ከዳንቪንቺ ከ300 ዓመታት አስቀድሞ የፀሎተ ሐሙስን የጌታ ራት በመስቀል ላይ ቀርጾ ከትውልድ ትውልድ አስተላልፎልናል።
*ምን አልባትም ከዳቪንቺ 30 እና 40 አመታት አስቀድሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው አልቫሬጽ የተባለው ሚስዮናዊ ለዚህ ጥበብ ምንጭ ሊሆን ይችላል።
*አልቫሬጽ ስለ ቅዱስ ላሊበላና ስለ ኢትዮጵያ ባሳተመው መጽሐፍ እማኝነት አልያም በሱ አንቂነት የዳቪንቺ የመጨረሻው እራት ዝነኛ ስዕል ተጸንሶም ይሆናል።
*ይህ መስቀል በአንድ ወቅት ተሰርቆ በ25 ሺህ ዶላር ተሽጦ ነበር። ቤልጂየም አገር ቆይቶም ወደ አገሩ በድርድር ከተመለሰም ገና 21 አመቱ ነው።
*የቅዱስ ላሊበላ መስቀል አፍሮ አይገባ በሚል መጠሪያም ይታወቃል።
*በፈዋሽነቱ ምክንያትም ስሙን አግኝቷል።
*የዕለተ ሐሙስ መታሰቢያ ነውና እነሆ ሐዋርያቱን በግራ እና በቀኝ ስድስት ስድስት ተከፍተው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እመሐላቸው በመስቀል ተመስሎ ከፊቱ ደግሞ በመስቀል ላይ የሚፈትተውን ስጋ እና ደሙን አቅርቦ በቅርጹ ላይ ይታያል።
*እንዲህ አይነት ጠቢባን አባቶች ልጆች ነበርን::
©ያሬድ ሹመቴ
@KendelM

❤️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦ እንኳን ለትንሳኤ በዓለ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !
በዓሉ ፦ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።
ለሀገራችንም ከመከራ ፣ ከመከፍፈል ጨለማ ፣ ከቅሽሽቅ ፣ ማስተዋል ከጎደለው ስሜታዊነት ተላቀን በአንድነት ፣ በመተሰሳሰብ ፣ በመከባበር በሰላም የምንኖርበት ትንሳኤ ያድርግልን።
መልካም ትንሳኤ፤ መልካም በዓል! ❤️
ቅንነት_ድል_ያደርጋል!
@kendelM

' " ይቅርታ . . . ይቅርታ"
ይቅርታ እናቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ንፍገቴ
ሳመሽ ሌትሽ አልፎኝ - ስውል ቀንሽ አልፎኝ
ጠገብኩ እልሻለሁ ረሀብሽ ተርፎኝ !
ይቅርታ አባቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ስስቴ
ከልጅነት ወኔ ለላቀው ሞገስህ
ከሞቴ ገዘፈ , ልጄ ፊት ማነስህ
ይቅርታ ወንድሜ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ህመሜ
ከአቻ መንገዳችን ለናቅኩት ማጣትህ
ስጠኝ ማለት ከብዶህ ስጥል ለማንሳትህ
ይቅርታ እህቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ሽንፈቴ
አጥሬን አጥሬን ስል ለጣልኩት አበባሽ
በሳቄ ትራፊ ለሚፅናናው እምባሽ
ይቅርታ . . . ይቅርታ አያቴ
ከሰማይ ለሰፋው አውላላው ንፍገቴ
አቅፎ ላሻገረኝ የቅንቀልባው ትከሻ
ከቀኔ ስኳረፍ ለገፋሁት ማምሻ . . . . .
ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ
🎤
EYAYU FENGES (አጀንዳዬን) - GIRUM ZENEBE
@kendelM
ይቅርታ እናቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ንፍገቴ
ሳመሽ ሌትሽ አልፎኝ - ስውል ቀንሽ አልፎኝ
ጠገብኩ እልሻለሁ ረሀብሽ ተርፎኝ !
ይቅርታ አባቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ስስቴ
ከልጅነት ወኔ ለላቀው ሞገስህ
ከሞቴ ገዘፈ , ልጄ ፊት ማነስህ
ይቅርታ ወንድሜ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ህመሜ
ከአቻ መንገዳችን ለናቅኩት ማጣትህ
ስጠኝ ማለት ከብዶህ ስጥል ለማንሳትህ
ይቅርታ እህቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ሽንፈቴ
አጥሬን አጥሬን ስል ለጣልኩት አበባሽ
በሳቄ ትራፊ ለሚፅናናው እምባሽ
ይቅርታ . . . ይቅርታ አያቴ
ከሰማይ ለሰፋው አውላላው ንፍገቴ
አቅፎ ላሻገረኝ የቅንቀልባው ትከሻ
ከቀኔ ስኳረፍ ለገፋሁት ማምሻ . . . . .
ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ
🎤
EYAYU FENGES (አጀንዳዬን) - GIRUM ZENEBE
@kendelM
ለመላው የእልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች ሁሉ፡-
እንኳን ለተከበረዉ ለታላቁ ለዒድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የደስታ ይሆን ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን!
💫💫 ኢድ ሙባረክ 💫💫

"መንገዳችሁን አስተውሉ!"
እናውቅላችኋለን እያሉ ልባችሁን ለአመፅ የሚቀሰቅሱ ሁሉ እስከ ገደሉ አፋፍ ሸኝተዋችሁ ነው የሚመለሱት። በህይወት መንገዳቸው የስሜታዊነትንና የጦርነትን መከራ ያሳለፉ አባቶች እግር ስር ተቀምጣችሁ የሠላምን ጥቅም የመልካምነትን ትሩፋት ተማሩ...እውነተኛ መምህር ወደ ሞት ሳይሆን ወደ ህይወት ወደ መንቃት የሚመራ፤ ስሜቱን የገዛና የተረጋጋ እንደሆነ ያኔ ታውቃላችሁ። እናንተ ግን ዝናና ውዳሴ በአፍጢማቸው ከደፋቸው መምህራኖቻችሁ ተጠበቁ። እስከገደሉ አፋፍ በመድረስ እርስ በርስ ተገፋፍቶ መውደቅን እንጂ ጥሎ መነሳትን አታተርፉምና ቁጣን በሚተፉ ቃላቶቻቸው ለፀብ ከሚያስነሷችሁ ሁሉ ተጠንቀቁ!!!
©osho

🎖
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት!
************
<<አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፤
በሦስቱ ቀለማት የተሸልምሽቱ፤
ላንቺ የማይረዳ ካለ በሕይወቱ፤
በረከትሽን ይንሳው እስከለተ ሞቱ።>>
(ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ) እንዳሉት።
፨ዘልዓለማዊ ክብር ለአባት/እናት አርበኞች አገርን ከነሙሉ ክብሯ ላቆዪቱ።
#81ኛ_ዓመት_የአርበኞች_የድል_መታሰቢያ!

Job Title: Social media Manager
Company: Kendel Digital magazine
Job Type: Freelance
Description: We are looking for a Social Media Manager!
Must have own laptop or Smart phone.
Background in marketing preferably social/Digital Marketing, journalism and communication or other related field.
English and one additional local language fluency is preferred but not required.
Job Description-
- Handling kendel's Social Media Accounts
- Posting, commenting and engaging with customers
If you like this sound, send us your CV/ Resume on the address provided below
[email protected]
Telegram @KendelM

2015 ዓ.ም አዲስ አመት
ከጭጋጋማው ወራት ወደ ፈካው ወር ፣ ከደመና ወደ ፀሐይ ፣ ከትናንት ወደ ነገ በሚወስደው የዘመን ሀዲድ ላይ በመሆን አዲስ አመት ለማየት ስለበቃን ደስ ሊለን ይገባል። ዘመን የሰው ልጅ ነው ። የሰው ልጅ ደሞ በመኖር ሒደት ውስጥ ለሌሎች ትሩፍት የሚሰጥ ፍጡር ነው። መኖራችን ከኛ በላይ ሊሆን ይገባል ፣ መለወጣችን ከዘመን ጋር ሊሆንም ግድነው። ደጁ ሲፈካ በልባችን የተስፍ ብርሀን እንዲፈነጥቅ መፍቀድ አለብን። የጨለመው ሲነጋ እኛም መንጋት እና መንቃት አለብን።
አዲሱ አመት በልባችን የያዝነው መልካም ትሩፍት የሚተገበርበት ፣ ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት ፣ ፍቅር የሚነግስበት እንዲሆን ቅንድል ትመኛለች። በአዲሱ አመት በአዳዲስ ስራዎች ወደናንተ እንደምንደርስ ቃል እየገባን ለመላው የመፅሔታችን አንባቢዎች እንኳን ለዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

#አንድነት_ሰላም_ፍቅር_ቅንነት_ምክንያታዊነት_ለሀገራችን_ ህዝቦች #ሰላም_ትግራይ_ኢትዮጲያ የሳባ ስልጣኔ ፣ የአክሱም ስጦታ ፣ የነጃሽን ምጥቀት ፣ የአሉላን ጀግንነት ፣ የዩሀንስን መስዋትነት ፣
የዘራይን ገድል ፣ የሐየሎምን ጀብድ ፣ የኪሮስ ውብ ዜማ ፣ የእምነት አሀዱ መገኛ ከሆነው ትግራይ ምድር የምትገኙ ውድ
የሀገሬ ወጣቶች ኑ በአንድነት ፣ በፍቅር ፣ በመተሳሰብ ፣ ለታላቅነት ፣ ለቅንነት እና ለምክንያዊነት እንዝመት፡፡ ከሚጥለን
ጥላቻ ይልቅ ወደ ሚያሻግረን መዋደድ እንደ ቀደምት ጀግኖች አባቶቻችን ለሀገራችን ታላቅነትና ሰላም በጋራ እንነሳ፡፡
#ሰላም_ሰላም_ሰላም

ለመላው የክርስትና እምነት የቅንድል ኢትዮጲያ ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የገና በዓል አምላክ በፈጠራት ምድር አንድያ ልጁን ለአዳም መድሀኒት እንዲሆን ስጋ ለብሶ የተወለደበት እንደመሆኑ በልባችን ፍቅር ፣ ሰላም ፣ ቅንነት ፣ ምክንያታዊነት እና በጎነትን በልባችን ፀንሰን እንድንወልድ እድል የተሰጠን ነው።
በዓሉን ስናከብር በቅንነት ስራ ፣ በበጎ ተግባር መሆን ይገባዋል። የፍቅርና የይቅርታ አምላክ የተወለደበት ቀን ነውና ሁላችንም ልባችንን በፍቅር ህይወታችንን በይቅርታ እንመራ ዘንድ አደራ እያልን ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ በመላት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
ቅንነት ድል ያደርጋል!

ታላቁ ሰው አረፉ !
ለሃገር ትልቅ ባለ ውለታ የነበሩት ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።
ዶክተር ተወልደ ለሃገራቸው ሲደክሙ ከኖሩ ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነበሩ ።
ደራሲ ዘነበ ወላ "የምድራችን ጀግና" በሚለው መፅሃፉ የዶክተር ተወልደን ንግግር እንዲህ ሲል አስፍሮታል ።
“ሰው ሁሉ ሰው ነው። ሰው ሁሉ የትም ይፈጠር እኩል ነው የሚለውን እምነት … በተጨባጭ እያሳዩ ነው ወላጆቼ ያሳደጉኝ።
አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሕይወቴን ሳስበውና የተጓዝኩበትን መንገድ ዞሬ ሳየው የቤተሰቦቼ አመራር የምወደውና የምቀበለው ነው። የሰው ልጆች እምነት እምነቴ ነው። የሕዝቦች ሁሉ ተፈጥሮአዊ ዕውቀትን የገበየሁት በዚህ ዓይነት መንገድ ነው። ማንንም ሰው በእኔ ሕይወት ውስጥ እምነቱን አከብርለታለሁ። እኔም እንዲሁ አመለካከቴን እንዲያከብሩልኝ እፈልጋለሁ። በዚህም አመለካከት ዓለምን ሀገሬ አድርጌያለሁ። ”
ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር
ነፍስዎ በሰላም ትረፍ🙏

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቅንድል ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችንና መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የትንሳኤ በዓል ከመከራ ፣ ከፍርሀት ፣ ከጭንቅና ከሰቀቀን ተላቀን የነገን ተስፍ ፣ ብርሀን ፣ ሰላምና ፍካትን የምናይበት የአለም ሁለት ገፅ ማሳያ የሆነ በዓል ነው።
ውድ የቅንድል ቤተሰቦች ታዲያ በዓሉን ስናከብር በብርድ ለሚሰቃዮት ፣ በርሀብ አለንጋ ለሚገረፉት ፣ በፍርሀት ለሚርዱት ፣ ፍቅርና እንክብካቤ ለሚሹት የሰው ልጆች ሁሉ ከተረፈን ሳይሆን ካለን በማካፈል የፍቅርን እውነት የትንሳኤን ትርጉም በተግባር እንድንኖረው ቅንድል አደራ ትላለች።
#መልካም_የትንሳኤ_በዓል!

ኢትዮጵያዊው ወጣት ትንሳኤ አለማየሁ የ 2023 IAF young space leaders (ወጣት የሕዋ መሪዎች) መካከል አንዱ ሁኖ ተመረጠ
IAF young space leaders በስራ ዘመናቸው ለጠፈር ምርምሮች አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ ወጣት የሕዋ መሪዎች እውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ነው።
ትንሳኤ ዘርፉን መቀላቀል ለሚሹ ተማሪዎች እና ወጣት ባለሙያዎች የመነሳሳት ስሜት የሚፈጠር እና በአርአያነት ምልክት ሆኖ ቆሟል ተብሎለታል።
ትንሣኤ በዘርፉ ላበረከታቸው ልዩ አስተዋፅዖዎች እ.ኤ.አ. በ2022 ከዓለም አቀፉ የጠፈር ተመራማሪዎች ፌደሬሽን (አይኤኤፍ) የተበረከተውን ተስፋ የተጣለባቸው ስፔስ መሪዎች ሽልማትን፣ ከ30 አመት በታች የአፍሪካ ስፔስ ኢንዱስትሪ ሽልማት - በ2021 ከስፔስ ኢን አፍሪካ እና ከSGAC የግሎባል ግራንት ፕሮግራም ሽልማትን፣ በ2019 ደግሞ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የወጣት ሕዋ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሽልማቶችን እና እውቅናዎችን ሲያገኝ ቆይቷል።
ትንሣኤ ዓለማየሁ አሊ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ በላቀ ውጤት የተመረቀ ሲሆን በአፍሪካ ስፔስ ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ እውቅናን እያካበተ ሰው ነው።
በአሁኑ ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ለስፔስ ጀነሬሽን አማካሪ ምክር ቤት (SGAC) የአፍሪካ አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን ትንሣኤ ቀጣዩን የጠፈር ባለሙያዎችን በማብቃት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ሆኗል። በSGAC ካለው የሥራ ድርሻ በተጨማሪ በቅርቡ CubeSpace የተባለ በዓለም መሪ የሳተላይት ADCS ማምረቻ ድርጅትን በመቀላቀል የሽያጭ መሐንዲስነት እየሰራ ሲሆን፣ የድርጅቱን የንግድ እያሳደገ ይገኛል ተብሎለታል።
https://www.iafastro.org/news/the-iaf-is-proud-to-introduce-the-2023-iaf-young-space-leaders.html

www.iafastro.org
IAF : The IAF is proud to introduce the 2023 IAF Young Space Leaders!
IAF Young Space Leaders Recognition Programme
ቅድስት ይልማ በYouTube ቻናል መጥታለች
ይሁን ኢንተርቴይመንት የቅድስት መገኛ ነው፤ በዚህ ቻናል አዳዲስ ስራዎቿን ታቀርባለች ።
Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
https://youtube.com/@yihunentertainment-mn6vv?si=-LO358WZMLm__IWB

YouTube
Yihun Entertainment
Yihun Entertainment, founded by filmmakers Kidist Yilma and Memekiyaye Lemma, is a cultural storyteller rooted in Ethiopian and African heritage. Through films, music, literature, and digital experiences, we bridge cultures, inviting the world to celebrate…