Telegram Web
••●🍃 ስቀሽ አበረድሽኝ ••●🍃
.
.

ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ ከሰርዶ ተዋዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ።


ናትናኤል ጌቱ
━━━━━━


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
••●🍃ሌላ እንዴት ያፍቅርሽ ••●🍃
.
.

ፈጣሪ ውብ አርጎ ከነ ደም ግባትሽ፤
ከዝምታሽ እኩል እንዲናፈቅ ድምጽሽ፤
በፍቅር ህገ ደምብ ስንቱን ሀገር ገዛሽ።

ባንቺ ህግና ደምብ ባንቺ ንግስና ስር፣
ከጥንት ዠምሬ እተዳደር ነበር።

ያፈቀረ ይሙት ፣
ፍቅሩን ሀብል ሰርቶ አንጠልጥሎ ይገትት፣
የሚል ህግ እንዳለሽ ለምን ሳይካተት፣

ከደምቦችሽ መህል ደምብ ቁጥር ሰጥተሽ፣
አንቀፅ አብጅተሽ፣
አስገቢው በናትሽ፣
እኔ ላንቺ ሞቼ ሌላ እንዴት የፍቅርሽ።


አንዋር የሱፍ
━━━━━━


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፩

ደራሲ - አብላካት



ስታጨስ እና ስትጠጣ እየዋለች መብላት እሚለው ነገር ትዝም አይላትም ብዬ ስላሰብኩኝ ቤቱ ውስጥ የነበረውን ስጋ ጠባብሼ ከሻወር ስትወጣ አብረን በላን፤ ስንጨርስ እቃውን አነሳስቼ በዛውም ለእማዬ ለመደወል ወጣሁኝ ስመለስ ሳቢ ልብሷን እየለባበሰች ነበር...
"ወዴት ነው ?"
"እነ አቤላ ደውለውልኝ ውጪ ስለሆንን ትንሽ ተዝናንታችሁ ትመለሳላችሁ ኑ ብለው ነው"
"እሺ" ..ብያት መኪና ውስጥ ገብተን ሄድን። ቦታው ላይ ስንደርስ እነ አቤላ እየጠበቁን ነበር እውነት ለመናገር ናፍቀውኝ ነበር ካገኘኋቸው ትንሽ ቀን ሆነኝ ጩኧታቸው እብደታቸው ሁሉ ነገራቸው ይናፍቃል ግን አቤላ ዛሬ ልጋብዛችሁ ያለው ስለከፋው ነው ምክንያቱም ሁሌም ሲከፋው ቅር ሲለው ብቻውን ላለመሆን ሲል ልጋብዛችሁ የሚለን። የዋህ ነው ሁሌም እኛ እንጂ እኔ እሚል ቃል ከአፉ አይወጣም ግን ሲበዛ ድብቅ ነው ስሜቱን መናገርና ማሳየት አይፈልግም አቤላን ግቢ ስንገባ ነው የተዋወኩት መጀመሪያ አካባቢ ቀንደኛ ጠላቶች ነበርን በምንም ነገር አንስማማም ነበር አንድ ላይ ስንሰበሰብ እነ ሳቢ በፀባችን ከመማረራቸው የተነሳ ቀድመው እንዳንጣላ ያለ የሌለ መሀላ ያስምሉን ነበር። እየቆየ ግን አፉ እንጂ ልቡ መጥፎ እንዳልሆነ ተረዳሁኝ ስሜቱን ለመደበቅ ይናገራል እንጂ ከቆየ በኋላ ምን እንዳለ እንኳን እያስታውስም.....ዛሬ ግን ንግግሩ ሳይቀር ቀዘቀዘብኝ ። ሶስቱ ለመዝናናት ሲወጡ ጎራ ወደ ሚሉባት ግሮሰሪ ግብተን አንድ ሁለት ማለት ጀመርን የአቤላ ጉዳይ ስላስጨነቀኝ መጠጣችንን ይዘን መኪና ውስጥ እንድንቀመጠ ጠየኩትና ተነስተን ሄድን።

"ለምን እዚህ መጣን ?" አለኝ
"ምንድነው ያስጨነቀህ ነገር ?" አልኩት ቀጠል አድርጌ
"ኧረ ምንም ምን ሊያስጨንቀኝ ይችላል"
"አትዋሸኝ ምን ተፈጥሮ ነው ካልነገርከኝ ዳግመኛ አላናግርህም" ብዬ ወጥሬ ያዝኩት
"በቃ በሀኒ ምክንያት ነው" አለኝ። ሀና የአቤላ ፍቅረኛ ናት ከጎንደር Scholarship ወደ ካናዳ ደርሷት አንዳንድ ፕሮሰሶችን ለመጨረስ ሸገር ስትመጣ ነበር የተዋወቁት። በአጭር ጊዜ ውስጥ አመታትን አብረው አሳልፈው ከሚዋደዱ ሰዎች በላይ ተዋደዱ ጊዜ የፍቅር መለኪያ እንዳልሆነ ነበር ያስተማሩን...ግን ችግሩ አሁን ሀና ከአንድ ወር በኋላ ትምህርቷን ጨርሳ ትመለሳለች ግን አባቷ ከጎንደር ከመውጣቷ በፊት ጨርሳ ስትመለስ እሳቸው የመረጡላትን ሰው እንደምታገባ እና ይህንን ቃሏን እንዳታጥፍ በአባቶች ፊት ቃል እንዳስገቧት ገና ድሮ ነበር የነገረችን ግን ይሄንን ያህል ይከራል ብለን ማናችንም አላሰብንም ነበር ዛሬ ግን አባቷ ደውለው ቃልሽን እንዳትረሺ እንዳሏት እንደነገረችው ነገረኝ። ምን ይሉታል ይሄን ምንስ መፍትሄ ይበጅለታል መላ ቅጡ የጠፋ ነገር ምን ብዬ እንደማወራው ሁሉ ግራ ገባኝ ግን ብቻዬን ላፅናናውም መፍትሄ ልፈልግም አልችልም ስለዚህ...

"አቤላዬ ያለህበት ሁኔታ ይገባኛል ግን እመነኝ ሁላችንም ተመካክረን አንድ መፍትሄ አናጣም አትጨናነቅ አሁን ሁሉም በስካር መንፈስ ውስጥ መው ያሉት ነገ ግን በስነ-ስርዓት ሁላችንም ተሰብስበን መፍትሄ እንፈልጋለን መቼም እኛ እያለን አንተ አታዝንም" ብዬ አቀፍኩት...

"አመሰግናለሁ ቃልዬ ከማንም በላይ ባንቺ እተማመናለው" አለኝ...እያወራን እያለን እነ ሳቢ መጡ

"እእ ምን ሆናችሁ ነው ጥላችሁን የመጣችሁት"
"አየሩ ይቀዘቅዛል መኪና ውስጥ እንሁን ብዬው ነው" አልኳት
"በቃ እንንቀሳቀስ ሰዓቱ ስለሄደ እኛን እኔ ቤት አድርሱን" አለ ይሴ። እነሱን እሱ ቤት አድርሰናቸው እኛ ተመለስን ስንገባ ሳቢ ደክሟት ስለነበር ሄዳ አልጋው ላይ ዝርግ አለች እንቅልፍ ሲወስዳት ጠብቄ ጫማዋን አወላልቄላት ተኛች። ልተኛ ወደ አልጋው ስወጣ ስልኬ እየጠራ ነበር ሳየው ማይለፍ ነው ብዙ ጊዜ ደውሎ ግን ሳይለንት ስለነበር አላየሁትም ሳነሳው...

"ይቅርታ ከመሸ እረበሽኩኝ እንዴ ?"
"አይ ችግር የለውም ይቅርታ ስላላየሁት ነው"
"እሺ። እስካሁን አልተኛሽም እንዴ ?"
"አዎ ከጓደኞቼ ጋር አምሽቼ አሁን ገባሁኝ"
"አይ ደስ ይላል እኔማ ሳታነሺ ስትቀሪ ምን ሆና ነው ብዬ ነው"
"ሳይለንት ነበር ይቅርታ።" ብየው ብዙ ነገር አወራን ዘፈን ጋብዘኝ ብየው እየዘፈነልኝ ምን ሰዓት እንቅልፍ እንደወሰደኝ ሳይታወቀኝ ደህና እደር እንኳን ሳልለው ነበር የተኛሁት። ጠዋት ላይ እንደነቃሁኝ ለማይለፍ ይቅርታ ብዬ ቴክስ ከላኩለት በኋላ ለቁርስ እሚሆን ነገር ሰራርቼ ለራሴ በላሁኝና ሳቢን ከምቀሰቅሳት ብዬ አስቀምጬላት ልብሴን ለመቀየር ወደ ቤቴ ሄድኩኝ.... በሩን የከፈተችልኝ ሊዲያ ነበርች...
"ሰላም አደርሽ እመቤቷ" አለችኝ አፏን እያሽሟጠጠች
"ፈጣሪ ይመስገን" ብያት ወደ ውስጥ ገባሁኝ። ሳሎን ውስጥ የእንጀራ አባቴና ሳሙኤል ተቀምጠው ነበር አልፊያቸው ወደ ክፍሌ ልገባ ስል....
"ሲያሻሽ እምትመጪበት ሲያሻሽ የምትቀሪበት ቡና ቤት እኮ አደለም ይሄ የተከበረ ሰው ቤት ነው እንዴት ብትንቂን ነው ጭራሽ አድረሽ እምትመጪው !" ብሎ የእንጀራ አባቴ በቁጣ መንፈስ ተናገረኝ የመመለስ ፍላጎቱ ስላል ነበረኝ እንዳልሰማ ሆኜ ላልፍ ስል ግን ሳሙኤል አባቱን ተከትሎ የተናገረው ንግግር ከጆሮዬ ላይ አቃጨለ
"እሷ ምን ታድርግ የማንንም ዲቃላ እዚህ እንድትኖር ፈቅደን እኮ ነው እሚሰራትን ያሳጣት!" ሲል ሳይታወቀኝ ከአይኖቼ የእምባ ዘለላዋች የወርዱ ጀመረ..... በማን ቤት እየኖሩ ነው እኔን ዲቃላ ለማለት የበቁት? በአባቴ ቤት ተንደላቀው እየኖሩ አባቴ ደም ተፍቶ ወገቡ እየጎበጠ ባቆመው ቤት ላይ እራሳቸውን እንደ ባለቤት ሲቆጥሩ ነደደኝ በዛችው ቅፅበት ከቤቴ ውስጥ መንቅሬ ባሶጣቸው ምነኛ ደስ ባለኝ ነበር ዛሬስ አላልፋቸውም ብዬ ለመናገር ፊቴን ሳዞር የአማን የሳሎኑን በር ተደግፎ ቆሟል እሱ ፊት መናገሬ የገቢ መስሎ ስላልታየኝ ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። የያዝኩትን ቦርሳ አልጋው ላይ ወርውሬ ግርግዳው ላይ ወደ ለጠፍኩት የእመቤቴ ምስለ- ስዕል አጠገብ ተንበርክኬ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ እንደሌላው ደፈር ብዬ ሲናገሩኝ እንኳን መልስ እንዳልሰጥ ይሄ ትንሽ ልጅ እና መውጫ ቀዳዳው ጠፍቷት ሌት ተቀን የምታለቅሰው እናቴ አስረው ያዙኝ። ሰው አክብሮ ዝም ሲል እንደ ፈሪ እና ሞኝ በሚቆጠርበት ውጥንቅጡ በወጣ አለም ላይ እየተኖረ ሰው እንዴት ጥሩነትን ያስብ ሰው እንዴት በጎ ይስራ መልካም የሰራ ሳይሆን የተሳደበና ያንቆሸሸ አፉን የከፈተ ሁሉ የሚነግስበት ፣ ሰርቶ ከተለወጠው ይልቅ ዘርፎ የተመፃደቀው የሚከበርበት ፣ አንገቱን ደፍቶ ዝምታን ከመረጠው ይልቅ መርዛማ ንግግሩን የሚረጨው የሚሞገስባት ሆድና ጀርባ በሆነች ምድር ላይ እንዴት ነው መኖር የሚቻለው ? አሁንስ ታከተኝ ህይወቴ ሁሉ እየፈጩ ጥሬ ሆነብኝ ነጋ ጠባ እማይሻሻል እየተመለሰ እዛው የሆነ ህይወት።



ይቀጥላል........


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
💚ህይወት💚 የገደል ማሚቶ ነው‼️


አንዲት ትንሽ ልጅ በእናቷ ተናዳባት <አሎድሽም! ብላ ትጮሀለች እንዳትገስፃትም ፈርታ በሩጫ ከቤቷ ወጥታ ርቃ ትሔዳለች ገደል አፋፍ ላይ ደርሳ አሁንም <አሎድሽም! <አሎድሽም! ብላ ስትጮህ የገደል ማሚቱ <አሎድሽም! <አሎድሽም! በማለት አስተጋባ ከዚህ በፊት የገደል ማሚቶ ድምፅ ሰምታ ባለማወቋ በሁኔታው እጅግ ትደናገጥና ታድናት ዘንድ ተመልሳ ወደ እናቷ በመሮጥ በገደል ውስጥ <አሎድሽም! <አሎድሽም! እያለች የምትጮህ መጥፎ ልጅ አንዳለች ትነግራታለች እናትየው ሁኔታው ስለገባት ለልጇ ተመልሳ ወደ ገደሉ በመሄድ <እወድሻለሁ! <እወድሻለሁ! ብላ እንድትጮህ ነገረቻት ልጅቱም ተመልሳ በመሄድ እናቷ እንዳለቻት <እወድሻለሁ! <እወድሻለሁ! እያለች እያለች ስትጮህ የገደል ማሚቶውም ያለችውን አስተጋባ፡፡ በዚህ አይነት ትንሿ ልጅ አንድ ትምህርት አገኘች

⚠️ - ህይወታችን የገደል ማሚቶ መሆኑን ፡፡ የምናገኘው የሰጠነውን ነው መልካም ነገረ ስንሰጥ መልካም ነገር ይመለስልናል በጎ ካላረግንም እንዲሁ
🙏ስለዚህ መልካም ነገረ እንድናገኝ ሁሌም ቢሆን መልካምነታችን ይብዛ



,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
|| 🥀 @Ketbeb_Mender🥀
🥀 @Ketbeb_Mender🥀||
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
💌


ሁሉንም ሰዉ ልታስደስት አትችልም፡፡ ይህ ትልቅ እዉነታ ነዉ፡፡

የሆኑ ሰዎች ቢጠሉህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የሚወዱህ እንዳሉ ሁሉ የሚጠሉህም እንደዚያዉ፡፡ ሰዎች ስላንተ ያላቸዉ አመለካከት ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡

የመሰላቸዉን ያህል ሊገምቱ፣ዋጋ ሊያወጡ ሊያወርዱ፣ወይም ሊሰቅሉ ይችላሉ፡፡ ሰዎች አንተ ላይ ባላቸዉ አመለካከት ማንነትህን ሞቅና ቀዝቀዝ እያደረክ አትኑር...

ራስህን ሆነህ በሕይወትህ ትልቅ ዋጋ ለምትሰጣቸዉ ሰዎች ብቻ የሚጠበቅብህን መስዋእትነት ክፈል፡፡


,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••

||🦋 @Ketbeb_Mender🦋
🦋 @Ketbeb_Mender🦋||
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
ሀገሬ ሴት ናት



ፀሐፊ እና አንባቢ

ትንቢት ዳንኤል/Tina
_____________________



F.C @TDtina



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፪

ደራሲ - አብላካት


አጎንብሼ እያለቀስኩኝ ሳለሁ ድንገት የክፍሌ በር ተንኳኳ የአማን ነበረ..

"ግባ" አልኩት እምባዬን እየጠራረኩኝ
"አስቀየሙሽ አይደል ?"
"ኧረ በፍፁም እኔ እህትህን ደሞ ማነው ደፍሮ እሚናገራት" አልኩት ፈገግ እያልኩኝ
"አትስሚያቸው እሺ እነሱ እኮ ያንቺን ጥሩነት ስለማያውቁ ነው እንጂ ምን አይነት ሰው እንደሆንሽ ሲገባቸው እራሳቸው መተው ይቅርታ ይጠይቁሻል ደሞ መልካምነት እኮ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል አንቺ ማለት ልክ እንደ ወርቅ ነሽ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው አንቺንም ፈጣሪ በነሱ ሊፈትንሽ ነው ስለዚህ ጠንካራ ሆነሽ ፈተናሽን በጥሩ ውጤት አጠናቂ።" አለኝ እውነት ለመናገር አነጋገሩ በጣም ነው ያስገረመኝ አስራ አምስት አመት እንኳን ካልሞላው ልጅ እንዲህ አይነት ንግግር መስማት ትንሽ ያስደነግጣል ሆኖም ግን ንግግሩ ፈገግም አስብሎኛል አስገርሞኛልም። ይህ ህፃን ልጅ ይሄንን ያህል አርቆ ማሰብ ከተቻለው እኛ ተማርን አደግን የምንለው ምን ሆነን ነው የዚህን ያህል አዕምሮአችን የቀጨጨው ? አመስግኜው የስራ ሰዓት ስለደረሰ ትላንት ለእነ ወይዘሮ አለምነሽ እሰጣለው ያልኩት ትዝ ሲለኝ ከሳጥኔ ውስጥ የባንክ ቡኬንና ያስቀመጥኩትን አንድ ሺህ ብር ይዤ ወጣሁኝ ፤ የታክሲ ግርግሩ ለጉድ ነው እንደምንም ተጋፍቼ ገባሁኝ። ወደራሴ ስመለስ የማይለፍ አለመደወልና ወደ ሰፈር አለመምጣቱ ትዝ አለኝ ማታ ቻው ሳልለው እንቅልፍ ስለወሰደኝ ተቀይሞኝ ይሆን እንዴ ግራ ገባኝ "ወራጅ የለም ?" ሲል ከገባሁበት ሀሳብ ብንን አልኩኝ ለካ መውረጃዬ ጋር ደርሼ ነበረ ፈጠን ብዬ ከታክሲው ወረድኩኝና ወደ ህንፃው ገባሁኝ ሀሳቤ ግን አሁንም እሱ ጋር ነበረ ወደ ኢንተርኔት ቤቱ ስጠጋ ፊት ለፊት መቶ አንድ ሰው ድቅን አለ ሀሳብ ውስጥ ስለነበርኩኝ ይቅርታ ብዬው ሱቁን መክፈት ጀመርኩኝ....
"ላግዝሽ ?" ይማውቀው ድምፅ ነበር ፊቴን ዘወር ሳደርግ ማይለፍ ነበር ሮጥ ብዬ ሄጄ ተጠመጠምኩበት አቀፈኝ የሆነ የማላውቀው ስሜት ተሰማኝ ሰውነቴን ሁሉ ነዘረኝ ጠረኑ የማላውቀው አለም ውስጥ ይዞኝ ነጎደ እፎይታ ተሰማኝ ወዲያው ግን "ምን እየሆንሽ ነው ቃል" የሚል ድምፅ ከራሴ ውስጥ ተሰማኝ እና ሸሸሁት

"ምነው ?" አለኝ
"እይ ምንም ሱቁን ልክፈት" ብዬው ፊቴን አዞርኩኝ እጄ ይንቀጠቀጥ ጀመረ
"ቆይ እኔ ላግዝሽ" ብሎ ከፋፈተልኝ እና ወደ ውስጥ ገባን
"ቴክስቱን ቅርብ ሰዓት ነው ያየሁት ይቅርታ ያልመጣሁት ደግሞ አስቸኳይ ስራ መቶ እኔ መፈረም ያለብኝ ነገር ስለነበረ ነው ለሱም ይቅርታ " አለኝ
"ችግር የለውም ዋናው ደህና መሆንህ ነው"
"በቃ ትንሽ ስራ አለኝ ሰላም ልበልሽ ብዬ ነው በኋላ እመጣለው"
"እሺ መልካም ስራ" አልኩት እና ሄደ። ድንጋጤው አለቀቀኝም ነበር ወንድን ልጅ እንደዚህ አቅፌም ነክቼም አላውቅም ምን ያስብ ይሆን መቼስ አይንቀኝም አይደል ደሞስ አቀፍኩት እንጂ ምን አደረኩኝ እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጠምኩኝ። ግን አልክድም ደስ ብሎኛል እንኳንም አቀፍኩት ሳይታወቀኝ እየሳኩኝ ነበረ "ብቻ እሚያስገለፍጥ ምን ነገር ተገኘ ?" የቤቱ ባለቤት ነበር
"ኧረ ምንም ይቅርታ እንዴት ነህ ?"
"በሰላም ከሆነ እሺ ደህና ነኝ ስራ እንዴት እንደሆነ ልጠይቅሽ ብዬ ነው"
"ስራ በጣም አሪፍ እየሄደ ነው"
"ጥሩ በቃ እላይኛው ፎቅ እማገኘው ሰው አለ መልካም ስራ ይሁንልሽ"
"አመሰግናለሁ።"

ምክንያቱን ባላውቀውም ዛሬ ድክምክም ብሎኛል ቀኑም የተሸከምኩት ያህል ነው የከበደኝ።ያሉትን ከስተመሮች አስተናግጄ ስጨርስ ሱቁን ዘጋግቼ ወረድኩኝ። ከህንፃው ወጥቼ ትንሽ እንደተራመድኩኝ ማይለፍን መኪና ማቆሚያው ጋር አየሁትና ወደ እሱ ሄድኩኝ
"እዚህ ደግሞ ምን ትሰሪያለሽ ?" አለኝ መስኮቱን ዝቅ እያደረገ
"ብር ላወጣ ፈልጌ ባንክ ቤት እየፈለኩኝ። አንተስ ስራ የለህም እንዴ"
"እኔ እንኳን ሰው አጊንቼ እየተመለስኩኝ ነበር ሳይሽ ነው የቆምኩት። በቃ ግቢና ልሸኝሽ" አለኝ .....ደክሞኝ ስለነበር አልተግደረደርኩም
"እሺ" ብዬው ወደ ውስጥ ገባሁኝ እና መንገድ ጀመርን...ባንክ ቤት ስንደርስ ወርጄ ለወይዘሮ አለምነሽ እሰጣለው ያልኩትን ብር አወጣሁኝ ። ስመለስ ...
"አሁንስ ወዴት ነሽ ?" አለኝ
"ከተመቸህ ሰፈር አድርሰኝ ካልሆነም ታክሲ እይዛለው"
"አይ ችግር የለውም ግቢ" አለኝ።
"ምነው ዛሬ በጊዜ ?"
"አይ ለሰው እማደርሰው እቃ ስላለ ነው"
"እና ወደ ስራ ካልተመለስሽ እቃውን አድርሰሽ ስትመለሺ ላግኝሽ ?"
"እሺ ስራህን ስትጨርስ ደውልልኝ እስከዛው እቤት ገብቼ እረፍት አደርጋለው"
"እሺ እደውላለው። ይኽው ሰፈርሽም ደርሰሻል"
"አመሰግናለው በጣም ቻው" ብዬው ወደ ወይዘሮ አለምነሽ ቤት ሄድኩኝ። በሩን የከፈቱልኝ እሳቸው ነበሩ...
"ሰላም ዋሉ እማማ ?"
"የኔ ልጅ መጣሽ እንዴ ? ፈጣሪ ይመስገን ቸር ውያለው ውደ ውስጥ ግቢ" አሉኝና በሩን ዘግተው ወድ ቤት ገባን አቶ መኩሪያም ሶፋቸው ላይ ቁጭ ብለው መፅሀፍ እያነበቡ ነበር
"ሰላም ዋሉ ጋሽ መኩሪያ ?"
"ቸሩ መድሀኔአለም ይመስገን። አረፍ በይ"
የያዝኩትን አምስት ሺህ ብር አውጥቼ ለወይዘሮ አለምነሽ ሰጠኋቸው።
"የምን ብር ነው ቃልዬ ?"
"እማማ፣ጋሼ ምንቴ ነው ዛሬ ጠዋት የላከላችሁ"
"የኔው ልጅ ምንተስሞት ነው ?" አሉኝ አቶ መኩሪያ ቀጠል አድርገው
"አዎ ጋሼ ምንቴ ነው።"
"እንደው አይኑን እያየው ባመሰግነው ምን ነበር" አሉ ወይዘሮ አለምነሽ
"ችግር የለውም አሁን እደውልለታለው ብዬ ስልኬን በማውጣት ደወልኩለት ትላንት ያየሁት ምንቴና ዛሬ እያየሁት ያለሁት ተለያዩብኝ ያንን አሸባሪ ያስመሰለውን ፂሙን ያጎፈረውን ፂሙን እርግፍ አድርጎ ተቆርጦት ነበር። ከሀገሩ ሲወጣ የነበረው መልኩ በጥቂቱም ቢሆን ተመልሶ ሳየው ሳይታወቀኝ እምባዬ ወረደ። እሱም እናትና አባቱን ሲያይ እምባው ለጉድ ይወርድ ጀመረ እነሱም እሱን እያዩ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። ይሄ ሞልቶ እማይሞላ ህይወት የስንቱን ቤት አጨለመ የስንቱን ልጅነት እና ወጣትነት ነጠቀ። የስደትን አስከፊነት በምን ቋንቋ በየትኛው ሰው ቢነገረን ይሆን ገብቶን በሀገራችን ሰርቶ መለወጥን ልማድ እምናደርገው ትንሽ ሲከፋን ጎድሎ ስናየው በአይናችን ውል በአእምሯችን ሽው እሚለው ስደት እሚሉት ሰይጣናዊ ሀሳብ ነው። ብቻ እሱ ፈጣሪ በቃ ይበለን። አውርተውት ሲጨርሱ ለላከላቸው ገንዘብ አመስግነው ተሰናብተውት ስልኩ ተዘጋ እኔንም እማይጠገብ ምርቃታቸውን አሽረውኝ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ። እቤት ስገባ ማንም አልነበረም ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም አልኩና ለምንቴ ደወልኩለት እስካሁን እያለቀሰ ነበር....
"ቃልዬ ምን ብዬ ላመስግንሽ በምንድነው ውለታሽን እምከፍለው ?"
"እኔ እና አንተ እኮ ጓደኛሞች አብሮ አደጎች ነን የምን ምስጋና ነው ዋናው አንተም እነሱም መደሰታችሁ ነው ?"
"ፈጣሪ ያክብርልኝ። ግን እንዴት ነሽ ?"
"አሜን። ደህና ነኝ እኔ አንተ ግን እምሮብሀል ትላንት እኮ በልጅነታችን እነ እማማ እንደ ማስፈራሪያ ይጠቀሙት የነበረውን ግዙፍ ሰውዬ መስለህ ነበር" ብዬ ትንሽም ቢሆን ላስቀው ሞከርኩኝ
"ክትክት ብሎ እየሳቀ አሁን አገኘሽኝ" አለኝ እና ብዙ ነገር አውርተን ስልኩ ተዘጋ።


መኖር ትርጉም እሚኖረው ከራስ አልፎ ሌላው ላይ ደስታን መፍጠር ሲቻለው ነው። ሞልቶኝ ሳይሆን ጎድሎኝ እነሱን ከጭንቀት ስለገላገልኩኝ እፎይታ ተሰምቶኛል።



ይቀጥላል........


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ


ለአስተያየት @Yetomah_Bot
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ



✯┄┅┅✿❀❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፫

ደራሲ - አብላካት



ለግማሽ ሰዓት ያህል ጋደም አልኩኝና ስልኬ ሲጠራ ተነሳሁ። ማይለፍ ነበር......

"ተዘጋጀሽ ?"
"ውይ ተኝቼ ነበር በጣም ይቅርታ አሁን እዘጋጃለው"
"እሺ እኔም እየደረስኩኝ ነው ቶሎ ውጪ።" ስልኩ ተዘጋ .....በህይወቴ ለብሼ ለምወጣው ነገር ቦታ ሰጥቼ አላውቅም ይህን ስል ግን ተዝረክርኬ እወጣለው ሳይሆን መልበስ ያለብኝን ነገር በአግባቡ እለብሳለው እንጂ ለእንደዚህ አይነት ነገር ተጨንቄ አላውቅም። ማይለፍን ካወኩት በኋላ ግን ያስጨንከኝ ጀመር እሱ ፊት አምሮ ለመታየት ሳይሆን ይዞኝ እሚገባባቸው ቦታዎች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው እንደቦታው ሆኜ መገኘት ስላለብኝ ነው። ረዘም ያለ ቀሚስ ምርጫዬ በጣም እምወደው ሳቢ ለልደቴ የሰጠችኝ እሚያምር ነጭ ቀሚስ አለኝ በሱ ቀሚስ ስንት ጉድ አሳልፈናል.....እሱን ለበስኩና ብዙም ሂሉ ከፍ ያላለ ታኮ ጫማዬን ተጫምቼ ወጣሁኝ። እንደተለመደው መታጠፊያው ጋር እየጠበቀኝ ነበር ዛሬ ደሞ ከመኪና ወርዶ ስልኩን እየነካካ ነበር ሳየው ደነገጥኩኝ አለባበሱ እና ቁመናው እንኳን ሴት ወንድም ያስደነግጣል..... ጥቁር መነፅር ፣ ነጭ ፒትልስ ሹራብ በበርገንዲ ከለር የሱፍ ኮት ፣ ነጭ ሱሪ በጥቁር ጫማ ሁፍፍፍፍ በቃ ልክ እኔ እምወደው አይነት አለባበስ። ሰው እንዴት ሁሉን ይታደላል ከመልክ መልክ ከፀባይ ፀባይ ሁሉ ነገሩ ፅድት ያለ ልጅ ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም አይደል እሚባለው.... ቀና ሲል አየኝና ስልኩን ወደ ኪሱ ከተተው

"አምሮብሻል" አለኝ ከላይ እስከታች እየተመለከተ
"ያንተን ያህል ባይሆንም። ግን አመሰግናለሁ"....ፈገግ እንደማለት አለና በሩን ከፍቶልኝ ገባሁኝ። ከኋላ የነበረውን ጊታር አምጥቼ

" አታለማምደኝም ?" አልኩት
"አንቺ ፍቃደኛ ከሆንሽ ደስ እያለኝ አለማምድሻለው"
"አመሰግናለሁ። ግን ወዴት እየሄድን ነው ?"
"አንድ በጣም እምወዳቸው አባት አሉ እሳቸውን አስተዋውቅሻለው"
"ምንህ ናቸው ?"
"ስንደርስ ታያቸዋለሽ" አለኝና ጉዟችንን ቀጠልን... መኪናውን ያቆመበትን ቦታ አይቼውም አላውቅም ከመኪናው ከወረድን በኋላ አስፓልቱን እንደተሻገርን መቆርቆሮ የተሰራ እና ከላዩ ደግሞ ሸራ የታጠረበት ትንሽዬ ቤት ጋር አንኳኳ...ከቤቱ ውስጥ አንድ እድሜያቸው በግምት ከሰባ እስከ ሰባ አምስት በሚሆን የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ፀጉራቸው እና ፂማቸው ወተት የተደፋበት ይመስል ነጭ ነው ለካ ሁሉም በዕድሜ ሲሆን ያምራል ሽበት ባልወድም እንደሳቸው እሚሆን ከሆነ ግን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ቢኖርብኝም አይቆጨኝም። ሲታዩ ግን እርጅናን እምቢ አሻፈረኝ አልቀበልም ያሉ ነው እሚመስሉት። አንገታቸውን ብቅ በበሩ ብቅ አደረጉና......

"አንተ ነህ እንዴ ጌታ መሳይ" አሉ ጎርነን ባለ ድምፅ ወደ ማይለፍ እየተመለከቱ። "ጌታ መሳይ ?" አልኩኝ በውስጤ
"አዎ ጋሼ እኔ ነኝ" አላቸው ከዛም በሩን ከፈቱት እና ወደ ውስጥ ገብተው ሶስት ወንበር ተራ በተራ ውጪው ላይ አስቀመጡ ከዚያም በራቸውን ዘግተው .....
"በሉ ቁጭ በሉ". አሉን ወደ ወንበሩ እየጠቆሙ
"መጀመሪያ እሷን ተዋወቃት ጋሼ። ቃልኪዳን ትባላለች ጓደኛዬ ናት"
"ቃልኪዳን ?" አሉና አንገታቸውን አቀረቀሩ። ከዚያም መልሰው "ይሁና" አሉና እጃቸውን ዘርግተው ጨበጡኝ። ነገሩ ግራ ቢገባኝ ለመጠየቅ ግን ድፍረቱ አልነበረኝም እየተብሰለሰልኩ ወንበሩ ላይ ተቀመጥኩኝ።

"ቃልዬ ወዴት ሄድሽ ?" አለኝ ማይለፍ
"አይ አለሁ ዝም ብዬ ነው"
"እሺ ። ጋሼ ማለት ልክ እንደ አባቴ ነው በጣም ነው እምወደው ለዛም ነው ላስተዋውቅሽ የፈለኩት"
"አዎ ለኔም ልክ እንደ ልጄ ነው ከነሱም በላይ ሳይሆን አይቀርም እምወደው።" ብለው ፈገግ አሉ
"ፍቅራችሁ ደስ ይላል" አልኳቸው ቀጠል አድርጌ
"እናመሰግናለን። አሁን ምሳ ይዤ እስክመጣ ጋሼን አጫውችው" ብሎኝ ሄደ። "ግራ የገባኝ ግን እንደ አባት እሚወዳችፕው ከሆነ ምናለ ደህና ቤት ቢያኖራቸው መቼስ ለሱ አቅቶት አይደለም ለአፍ ብቻ አባቴ ማለት ምን ዋጋ አለው። ደህና ሆቴል እንኳን አይታየኝም ለምግቡስ ቢሆን ከዛ ከሰፈሩ ይዞላቸው አይመጣም። ከራሴ ጋር እያወራሁኝ ሳይታወቀኝ እየተናደድኩኝ ነበር ግን ምን አናደደኝ ምናልባት እንደጠበኩት ሆኖ ስላላገኘሁት ይሆን ?" ብቻዬን ስብከነከን አስተውለውኛል መሰል

"ምነው ልጄ ደህና አደለሽም እንዴ?" አሉኝ እንደመደንገጥ አልኩና
"አይ ደህና ነኝ ይቅርታ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነው። ግን ድፍረት ካልሆነብኝ አምድ ነገር ልጠይቅ ጋሼ ?"
"የምን ድፍረት ነው ጠያቂ አይደል እንዴ የጠፋው በይ ጠይቂ"
"እሺ ጋሼ ለምንድነው ማይለፍን ጌታ መሳይ የሚሉት ?"
"ሁሉም ሰው እኮ የጌታ አምሳያ ነው ስራው እኮ ነው እንደ ጌታም እንደ ሎሌም እሚያደርገው"
"ይቅርታ ግን አልገባኝ"
"እዮልሽ ልጄ አምላክ በራሱ አምሳል ፈጠረን እኛ ደግሞ ወደ ምድር ስንመጣ ገሚሱ እውነትም ጌታውን መስሎ ይኖራል ገሚሱ ደግሞ ሰይጣንን መስሎ ይኖራል በመልክ ሳይሆን በስራው። ማይለፍ ደግሞ ከባህሪም ከስነምግባርም ጌታን መሳይ ነው ለዛም ነው ጌታ መሳይ ያልኩት አሁንስ ተረዳሽኝ ልጄ ?"
"እእ አዎ ጋሼ አሁን ገብቶኛል አመሰግናለሁ" አልኳቸው። ድንገት አጠገባችን አንድ ወጣት መቶ ቆመ...

"ዛሬ ጥያቄ የለህም ?" አሉት
"ሲገባኝ እጠይቃለው" አላቸውና አሁንም እዛው ባለበት ቆመ
"እስከዛው ወደ ኋላ ተመለስ አትቁም "
"ላስብ ብዬ እኮ ነው ጋሼ"
"ያልገባህን ምን አሳሰበህ ሲገባህ ታስባለው ለአሁኑ ተመለስ"
"አመሰግናለሁ ጋሼ" ብሏቸው ወደ መጣበት ተመለሰ። ንግግራቸው እና ሁኔታቸው ግራ አጋባኝ ሂድ ተመለስ ጠይቅ ምንድነው እሚያወሩት እያልኩኝ ሳለው

" ሳምሶን ይባላል ሁሌም ከቤተሰቡ ጋር ሲጋጭ እዚህ ጋር መቶ ይቆማል ያኔ እኔም ችግሩን ስለማውቀው እንዲህ እያልኩኝ እመልሰዋለው እሱም ቶሎ ይሰማኛል ምክንያቱ ደግሞ ንዴት ውስጥ ሲሆን ነው ከእነሱ ጋር እሚጣላው እናም ንዴቱ ሲበርድለት እንደተጣላ እንጂ ለምን እንደተጣላ አያስታውስም። ለዛም ነው ዛሬ ጥያቄ የለህም ስለው ሲገባኝ እጠይቃለው ያለኝ የፀቡ መንስኤ ምን እንደሆነ ካላወቀ ምን ይጠይቃል እንዴትስ ሊገባው ይችላል የቆመው ደግሞ ምክንያቱን እያብሰለሰለ ነው ላልገባው ነገር መብሰልሰል ምን ሊፈይድ ንቆ መተው ነው እንጂ ስለዚህ እሚሻለው ያልገባውን እንዳልገባው ትቶ ሰላም መፍጠሩ ነው እሚበጀው ብዬ ነው ወደ ኋላ ወደ መጣበት የመለስኩት። አንዳንዴ ባልገባን ባላወቅነው ነገር ከራሳችን ጋር የሙጥኝ ተያይዘን እንታገላለን ጥያቄም እሚጠየቀው ውሉ ሲታወቅ ነው አልያ በዘፈቀደ እምንጓዘ ከሆነ መድረሻ እንደሌለው ደራሽ ወንዝ ነው እምንሆነው " አሉኝ እና ቢያንስ ውሀ እንኳን ላምጣልሽ ብለው ወደ ውስጥ ገቡ።


ንግግራቸው ትንሽ ግራ ቢያጋባም የተናገሩት ግን ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት ነው ወደ ራሴ መለስ ብዬ በንዴቴ ምክንያት ከስንቱ ተጣልቼ በኋላ ግን ስረጋጋ የፀቡ መንስኤ እንኳን ትዝ እማይለኝ ጊዜ እንደነበር መለስ ብዬ ሳስታውስ ይገርመኝ ጀመር።



ይቀጥላል........


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ



ለአስተያየት- @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፬

ደራሲ - አብላካት



ቀጠል አድርጌም.... "ጋሼ ማይለፍ አይመጣም እንዴ በጣም ቆየ እኮ " አልኳቸው
"ቆየብሽ አይደል ትንሽ እንጠብቀው ይመጣል" ከማለታቸው ከርቀት ወደ እኛ ሲመጣ ተመለከትኩት... ምን እንደሆነ ባላውቅም በእጁ ግን ሞላ ያለ ኩርቱ ፌስታል ይዟል ወደ እኔ እየተጠጋ ...

"አንድ ነገር ላስቸግርሽ" አለኝ
"እሺ"
"ይሄንን ወደ ውስጥ አስገቢውና ምግቡን ደግም በሳህን አድርገሽ አምጪው ብሎ ፌስታሉን ሰጠኝ።ተቀብዬ ወደ ውስጥ ገባሁኝ ፌስታሉ ውስጥ የታሸጉ ሽሮ እና በርበሬ እንዲሁም ደግሞ ሽንኩር እና ቲማትሚ አሉ ለምን እንደሆነ ባላውቅም እንደዚህ ማድረጉ ገርሞኛል..ሌላ ደግሞ በጥቁር ፌስታል የታሰረ ነገር አገኘው ስፈታው ጥሬ ስጋ ነበር እሱን በሳህን አደርጌ ይዤላቸው ወጣሁኝ። ጥሬ ስጋ ብወድም ዛሬ ግን አላሰኘኝም እነሱ ግን እየተጎራረሱ በሉ ፍቅራቸው ያስቀናል ሰው የስጋ ዝምድና ሳይኖረው እንዲህ ይዋደዳል እኔ እና ቤተሰቦቼ ደግሞ የአንድ እናት ልጆች ሆነን መታረቂያው እርቆናል። መወለድ ቋንቋ ነው እሚባለው እውነት ነው።

" አሁን እንሂድ በቃ ጋሼ ሰሞኑን ደግሞ እመጣለን"
አላቸው
"በል ከዚህ በኋላ ስትመጣ እሷን ሳትይዝ ደጄን እንዳትረግጥ"
"አታስብ ጋሼ ይዣት እመጣለው"
"በይ የኔ ልጅ ቸር ቆይኝ" ብለው አቀፉኝ
"አሜን ሰላም ሁኑ" ብለናቸው መኪና ውስጥ ገብተን ሄድን። አሁንም ግን ይሄንን ያህል ከወደዳቸው ለምን ከዚህ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ አላደረጋቸውም እሚለው ጥያቄ እና ስሜን ሲሰሙ የደነገጡት ነገር ውስጤ እየተመላለሰ ነው። ለመጠየቅም ድፍረቱን አጣው

"ከቻልክ እኔን ቅርብ ያለ ቤተክርስቲያን አውርደኝ" አልኩት
"አብረሽኝ እምትቆዪ መስሎኝ ነበር"
"አይ ትንሽ እዛ ልቀመጠ እማይመችህ ከሆነ በታክሲ እሄዳለው"
"እንደዛ ሳይሆን...እሺ አብሬሽ ልግባ ?"
"እሚደብርህ መስሎኝ ነው ከፈለክ ችግር የለውም"
"እንደውም ደስ ይለኛል" ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሄድን እዛ ፀሎታችንን አድርሰን ኣንድ ጥግ ጋር ተቀመጥን።

"ማወቅ እምትፈልጊው ነገር አለ ?"
"አይ። ግን ለምን ጠየከኝ ?"
"አይንሽ ያስታውቃል ውስጥሽ የሆነ ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው"
"መስሎህ ነው እንጂ ምንም የለም" ግን እኮ ብዙ መጠየቅ እምፈልገው ነገር ነበረ ለምን መጠየቅ ፈራሁኝ ..
"እርግጠኛ ነሽ ?"
"እእ ማለት..አለ አይደል መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ለዛ ነው"
"ችግር የለውም ጠይቂኝ"
"ለምንድነው ጋሼን ይሄንን ያህል እምትወዳቸው ከሆነ ብዙ ሀብት አለህ ለምን ከዚህ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ አላደረክም ?"
"ያላሰብኩት ይመስልሻል ? ግን በተደጋጋሚ ጠይቄው በተደጋጋሚ እምቢ ስላለኝ ነው። ጋሼን ያወኩት ከሁለት አመት በፊት ነው እናቴ ኩላሊቷ ሙሉ በሙሉ መስራት እንዳቆመና ውጪ ሄዳ ብትታከም እንኳን የመትረፍ እድሏ በጣም አናሳ መሆኑን ከዶክተሮች ስምቼ እንደወጣው ዙሪያው ሁሉ ገደል ሲሆንብኝ ይሄንን ጭንቀት ለመርሳት ካለ ቅጥ ሰክሬ መንገድ ለመንገድ ስደናበር ሌቦች ሊዘርፉኝ ሲሉ ነበር ጋሼ መተው ያተረፉኝ ከዛም ወደዛች ደሳሳ ጎጇቸው ወስደው ጎኔን እንዳሳርፍ አደረጉኝ። ሲነጋም በሌለ አቅማቸው ወተት አፍልተው ፍርፍር አፈርፍረው ያበሉኝ ያጠጡኝ። ችግሬን ሁሉ ነግሬያቸው ተስፋ እንዳልቆርጥና እስከመጨረሻው እንድታገል ብርታት ሆኑኝ እሳቸው ጋር ሁለት ቀን ቆይቼ እናቴ እንደምትድንና ተስፋ እንዳላት አምኜም ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ ከአንድ ወር በኋላም እናቴ ውጪ ሄዳ ታክማ ከሙሉ ጤና ጋር ተመለሰች። ወዲያው አዕምሮዬ ውስጥ የመጡት ጋሼ ነበሩ ለሳቸው ጥሩ ነው ያልኩትን ቤት መርጬ በስጦታ መልክ ላበረክትላቸው ወደ ቤታቸው ሄድኩኝ እሳቸው ግን አሻፈረኝ አሉ ምክንያታቸው ደግሞ ባለቤታቸው ከመሞታቸው በፊት ይኖሩባት የነበር ቤት ስለሆነ የሳቸውን ትዝታ ትቶ መሄድ አለመፈለጋቸው ነው። እኔም ስሜታቸው እየገባኝ ሲመጣ ጥያቄዬን አቆምኩኝ። እንጂ ለሳቸው ከዚህም በላይ ይገባቸው ነበር" አለኝ

እራሴን በስንቱ ልታዘበው አሁንስ አፈርኩኝ ለምን ብዬ መጠየቅ እየቻልኩኝ ዘልዬ መፍረድ ላይ ገባሁኝ።

"በጣም ይቅርታ እንደዚህ ስላልመሰለኝ ነው"
"ችግር የለውም ሌላም ሰው ባንቺ ቦታ ቢሆን ሊጠይቀው እሚችለው ጥያቄ ነው"
"ሌላም ጥያቄ ነበረኝ ቅር ካላለህ ?"
"እሺ ጠይቂኝ"
"ለምንድነው ጋሼ ስሜን ስትነግራቸው የደነገጡት ?"
"እእ አይ እሱን ሌላ ጊዜ እነግርሻለው" አለኝ
"እሺ አላስጨንቅህም" ማወቅ ብፈልግም ፊቱ ላይ ግን ጥሩ ነገር ስላላየሁኝ ደግሞ መጠየቁን አልፈለኩትም።
"እንውጣ አይደል እራት በልተን ወደ ቤት እሸኝሻለው"
"አይ ይቅርብኝ ወደ ቤት ልሂድ"
"ዛሬ እኮ ከእኔ ጋር ለማሳለፍ ፈቅደሻል ስለዚህ እምቢ ማለት አይቻልም"
"እሺ ግን ብዙ አልቆይም" ብዬው ከቤተክርስትያኑ ወጣን።
እዛው አካባቢ ካሉት ሆቴሎች ውስጥ አንዱ ጋር ገባን ወንበሩ ላይ ልቀመጥ ስል ፈጠን ብሎ መቶ ወንበሩን ስቦልኝ እንድቀመጥ ጋበዘኝ አምስግኜው ተቀመጥኩኝ። እኔም እሱም እምንፈልገውን አዘን እራሳችንን እየበላን ብዙ ነገር ተጨዋወትን ወደ 3:20 አካባቢ ከሆቴሉ ወተን ወደ ሰፈሬ ሸኘኝ እንደተለመደው መታጠፊያው ጋር ስንደርስ ከመኪናው ወረድኩኝ ያሳለፍኩት ቀን በጣም ደስ ይል እንደነበር ነግሬ አመስግኜው ሄደ። ሳቢ በጣም ናፍቃኝ ስለነበር ዛሬም ስላልተደዋወልን ቢያንስ አይቻት ልመለስ ብዬ ወደ እሷ ቤት ሄድኩኝ። በዛብህ ነበር የከፈተልኝ

"ሰላም አመሸህ በዜ ?"
"ፈጣሪ ይመስገን። እንዴት ነሽ አንቺ ?"
"ደህና ነኝ። ሳቢ አለች እንዴ ?"
"ቅድም የወጣች መች ተመለሰች አንቺ ዘንዳ የመጣች መስሎኝ እኮ ነው"
"ኧረ ከነጋ አልተገናኘንም ስልክ አልደወለችም በጣም ቆየች እንዴ ?"
"ዘመንም የላት ከወጣች እንዲያው አባባ ትንሽ አስቀየሟትና ተበሳጭታ ነበር የወጣች"
"እንዴ ከአባባ ጋር ተጣልታ ነው ምን ተፈጥሮ ?"
"ምኑን አውቄው እህቴዋ እንደው ሲጨቃጨቁ አረፈዱ በዛው ወጥታ ሄደይ ጃኬት እንኳን አልደረበች"
"ታዲያ ለምን አልደወልክልኝም በዜ ?"
"እኔማ አንቺ ጋር ትመጣለይ ብዬ ነዋ"
"በቃ እሺ እኔ እፈልጋታለው አትጨነቅ" ብለው ወደ ክፍል ገብቼ እምትደርበው ልብስ ይዤላት ወጣሁኝ። ስልኳ ላይ ስሞክር ዝግ ሆነብኝ ሳቢ ከአባባ ጋር ከተጣላች ሁሌም ቢሆን የእህቷ መቃብር ስፍራ ነው እምትሄደው በዚህ ሰዓት ወደዛ ቦታ መሄድ ቢያስፈራኝም ግን ደግሞ ሳቢን ብቻዋን መተው አልፈልግም በህይወቴ እንደ መቃብር
ስፍራ እምፈራው ነገር የለም እንኳን በጨለማ በቀን እንኳን በልመና ነው እምሄድላት ዛሬ ግን አስፈልጋታለው። እንደምንም እየተንቀጠቀጥኩኝም ቢሆን ወደ መቃብር ስፍራው ሄድኩኝ በእርግጥ ከመሸ መቃብር ስፍራ ጋር መሄድ ክልክል ነው ዘብኛውም አያስገባም ግን ሳቢ ሁሌም ስትሄድ ትንሽ ብር ሸጎጥ ስለምታደርግለት ለምዶናል። ቦታው በጣም ነው እሚያስፈራው አንዴ በአምስት ሰዓት እሷን ፍለጋ ከአቤል ጋር መተን ለሊቱን ሙሉ ስቃዥ ያደርኩት መቼም አይረሳኝም ዛሬም ልደግመው ነው መሰለኝ።



ይቀጥላል........


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ


ለአስተያየት- @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፭

ደራሲ - አብላካት



ሳቢዬን የሩታ መቃብር ላይ ተደፍታ እያለቀሰች አገኘኋት። ጠጋ ብዬ ትከሻዋን ደባበስኳትና ከአጠገቧ ተቀመጥኩኝ ቀና ብላ አይታኝ ተጠመጠመችብኝ።

"ቃልዬ ናፈቀችኝ እኮ" አለች ሲቃ በተሞላበት ድምፅ ምን ልበላት እማይሽር ጠባሳ ውስጧ አለ እማድን እመም ምንም ብዬ ባፅናናት ጭራሽ ሆድ ይብሳታል እንጂ ለውጥ አይኖረውም።
"እምትፈልጊውን አውሪኝ እሰማሻለው" አልኳት
"ቃልዬ ምናለ ብትመለስልኝ ብቻዬን ትታኝ ሄደች እኮ መጣሁ መጣሁ እያለች ሸወደችኝ እኔ እኮ እስከዛሬ አላመንኩም እየጠበኳት ነው ያለሁት እባክሽ ጥሪያት" እያለች ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ከአመት ከአራት ወር በፊት ነበር ሩታን ይጣናት ሰው በብዙ መንግድ ሲሞት ያሳዝናል ያማል ግን እራሱን አጥፍቶ እንደሚሞት ሰው ውስጤን እሚይደማኝ የለም ምክንያቱም እንኳን ጨክኖ የራስን ነብስ ማጥፋት ቀርቶ ሰው በዱላ ለመምታት እንኳን ምን ያህል እንደሚያንቀጠቅጥ እሚያውቅ ያቀዋል። ከሳቢ ጋር በዕድሜ በሶስት አመት ይበላለጣሉ ሩታ አስረኛ ክፍል ውጤት ሳይመጣላት ቀርቶ ኮሌጅ ገብታ በ Management ከተመረቀች በኋላ የአባቷን ድርጅት ቀጥ አድርጋ ነበር የምታስተዳድረው። ከመመረቋ ከአመት በፊት የእነ ሳቢ አባት ከውጪ የመጣውን የጓደኛቸውን ልጅ ዳንኤልን ከሩታ ጋር አስተዋወቋቸው ያኔ ሳቢ ዳንኤልን ብዙም ስላልወደደችው በራሷ የፈለገችውን ትመረጥ ብላ አባቷን ብትጠይቃቸውም በደንብ ሲግባቡ ፍቅሩም ይመጣል ብለው ሀሳቧን አልተቀበሏትም ነበር። ዳንኤል እና ሩታ ብዙም ሳይቆዩ በደንብ ተቀራረቡ እሱም ወደድኩሽ አበድኩልሽ እያለ ብዙ ነገር ያደርግላት ስለነበር ለእሱ ያላት ስሜት እለት ተለት እየጨመረ ሄደ ውሎዋም አዳሯም ከሱ ጋር ብቻ ነበር። ያለእሱ ወንድ ያለ እንኳን እስከማይመስላት ድረስ አፈቀረችው። ያኔም ግን ሳቢ ቀልቤ አልወደደውም ተጠንቀቂ ብትላትም ያው ፍቅር እውር ያደርግ የለ ልታደምጣት ፍቃደኛ አልነበረችም። ሩታ የነ ሳቢ ቤት ድምቀት ነበረች እሷ ካለች ሁሉም ተሰብስቦ መሳቅ መጫወት ብቻ ነበር ስራችን እኔም ከነሱ ቤት አልጠፋም አንዳንዴ በሷ ጨዋታዎች እየተዝናናን ቁጭ እንዳልን እሚነጋበት ጊዜም ነበር ፤ ሁሉም በእነሱ ቤት ፍቅር ይቀናል ምናለ የኛም ቤት ደስታ እንደዚህ በሆነ ብሎ ያልተመኘ አልነበረም። ሳቢዬም ሳቂታ ተጫዋች ደስተኛ ነበረች እንኳን መጠጣት እና ማጨስ ለሚያደርጉትም እምትናደድ ነበረች። በዛ ሰዓት በሳቢ እና በአባቷ መካከል የነበረው ፍቅር ምናለ አባቴን ቢመልስልኝ እያልኩ ዘወትር እንድማፀን አድርጎኝ ነበር። ሩት እና ሳቢ ለሰከንድ ተለያይተው አያውቁም
የትም ቦታ ይሁን አብረው ነው እሚሄዱት ብዙ ሰው መንታ ናችሁ እንዴ እስኪል ድረስ አይነጣጠሉም ፤ ፍቅራቸው እና መሳሳታቸው ልክ እንደ እናት እና ልጅ ነበር። ሩታዬ ምክሯ ሳቋ ጨዋታዋ ቁም ነገር አዋቂነቷ ከሁሉም ለየት ያደርጋታል ከፋኝ እሚል ሰው ማየት አትፈልግም ባላት አቅም ሁሉ ለሁሉም ትደርሳለች። እማዬን ሲያማት ወይም የሆነ ነገር ሲያስፈልጋት ከእኔ ቀድማ እሷ ነበርች የምትደርስላት። አስረኛ ክፍል ውጤት ሳይመጣላት ሲቀር ያለቀሰችው እንባ መቼም አይረሳኝ ከምንም በላይ አባት እና እናቷ በምንም ነገር እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ አትፈልግም ቤተሰቤን አዋረድኩኝ ብላ ሶስት ቀን ክፍሏን ዘግታ አልቅሳለች። ግን እነ አባባ በሷ በጣም ይቆሩ ስለነበር ኮሌጅ ገብታ ተምራ የሳቸውን ስራ ማስተዳደር ስትጀምር ከማንም በላይ ደስተኛ እንደምታደርጋቸው እየነገሩ ያበረታቷት ስለነበር ሀላፊነቷን በአግባቡ መወጣት ቻለች። ለሩታ የቤተሰቧ ክብር እና ደስታቸው ከምንም ነገር በላይ ነው ። እኔ እና ሳቢንም በራሳችን እንድንተማመን የተሻለ ቦታ ደርሰን ቤተሰባችንን ማኩራት እንዳለብን ሳትነግረን የቀረችበት ጊዜ አልነበረም ለኔም ለሳቢም ብዙ አድርጋለች እኩል ትወደን እኩል ቦታ ትሰጠን ነበር። ከዳንኤል ጋር ፍቅር በጀመሩ በሁለት አመት ከሶስት ወራቸው ሩታም ተመርቃ የራሴ የምትለውን ነገር እንደያዘች ዳንኤልም ውጪ ያለውን ነገር ጨርሶ ሙሉ በሙሉ ሀገሩ ገብቶ መኖር ሲጀምር ፤ ለመጋባት ወስነው የደስታ ዜና አበሰሩን ሁላችንም ሽር ጉዱን ጀመርን እነ ብሩኬ ፣ አቤላ ፣ ይሴ ሁላችንም ለሰርጉ ዝግጅት ደከመኝ ሳንል ያማረና ልዩ እንዲሆን ቀን በቀን እንለፋ ነበር። ግን ደስታና ፍቅር ጠፍቶ በማያቅበት በእነሳቢ ቤት የዳንኤልና የሩታን የቀለበት ፕሮግራም ድል ባለ ዝግጅት ባጠናቀቅን በሁለት ወራችን ሊጋቡ ሁለት ሳምንት ሲቀራቸው በአንድ በተረገመ ምሽት ሩታ ዳንኤልን ከጋብቻ በኋላ እንዲኖሩበት የሳቢ አባት ገዝቶ በሰጣቸው ቤት ውስጥ ከሴት ጋር ተኝቶ ያዘችው። በጣም ያም ነበር በተለይ ለሩታ እንደዛ ሀገር ጉድ ስኪል ድረስ የምታፈቅረውን ወንድ ከሴት ጋር ተኝቶ ማየት ሁለት አመት ሙሉ እሱን አምና ለኖረች ሴት ቤቴ ትዳሬ ነው ብላ ለተቀበለችው ሴት ትልቅ ቁስል ነበር። ለሱ ስትል ያላደረገችው ምን አለ ምን ያልሆነችለት ነበር በአመኑት ሰው እንደመከዳት ልብን እሚሰብር ነገር የለም። ሁሉ ነገሯ ደቀቀ ሰርጋቸውን ሲጠባበቅ የነበረ ቤተ ዘመድ እናት አባቷ ጓደኞቿ እንዴት ብላ ይሄንን ጉድ ትናገር እቤት ስትገባ የምታየው እናት እና አባቷ ለሰርጓ ደፋ ቀና እሚሉትን ነው ፊታቸው ላይ የሚነበበውን የኩራት ስሜት አላገባም ብላ ማደብዘዙ ከመግደል እንደማይተናነስ እና እነሱን በቁም ከምትገላቸው እሷ አንደኛዋን ብታሸልብ ለሁሉም ሰላም እንደሚሆን በወረቀት ላይ አስፍራ ላትመለስ እስከወዲያኛው አሸለበች። ያን ቀን ከእነ ብሩኬ ጋር ካፌ ቁጭ ብለን ስለሰርጉ ለመነጋገር እሷን እየጠበቅን ነበር ሳቢ ስትደውልላት እየመጣሁ ነው እያለቻት ሸውዳን እሷ ላትመለስ ወደ ፈጣሪዋ ሄደች። ደጋግማ ስትደውል አልነሳ አላት አዲሱ ቤት ልትሆን ትችላለች ብለን ወደዛ ስንሄድ ዳንኤል የማገጠባት ክፍል ውስጥ እራሷን በገመድ ሰቅላ አገኘናት ሁላችንም ተደናግጠን ገመዳን ፈተን አልጋ ላይ ካስተኛናት በኋላ እንድትነቃ የተቻለንን ብናደርግም ግን ህይወቷ አልፎ ነበር ያንን ስታይ ሳቢ እራሷን ስታ አደቀች አምቡላንስ መቶ ሁለቱንም ወሰዳቸው ግን ሳቢን ብቻ ነበር አይኗን ገልጣ ማየት የቻልነው። ሁላችንም በዛ ሰዓት እንደ እብድ አድርጎን ነበር ማን ያህንን ያምናል ማን ይሄንን መርዶ መቀበል ይችላል ሳቋ ፍቅሯ እንዴት ሊረሳ ይችላል። ከማንም በላይ እነሱ እንዳያፍሩ አንገታቸውን እንዳይደፉ ብላ ዳግም ላያዩአት ትታቸው ሄደችው እናት እና አባቷ ምን ይሰማቸዋል። አምናው ለከዳት ለዛ ይሁዳ ብላ ነብሷን መሰዋቷ ለስንቱ እማይሽር ጠባሳን ጥሎ አለፈ። ከቀብር መልስ ሳቢ እራሷን ስታ ከሶስት ቀን በኋላ ነበር የነቃችው። በዚህ የተነሳ ነው ሳቢ ወንድ እሚባል ፍጥረት የጠላቸው ፤ አባቷም ጋር የማትስማማው ያኔ ልጁ ጥሩ አይመስለኝም ስልህ እሺ ብትለኝ እህቴን አናጣትም እያለች ዘወትር ስለምትወቅሳቸው ተራርቀው ቀሩ።


ይቀጥላል........


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ


ለአስተያየት- @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፮

ደራሲ - አብላካት



ለሶስት ሳምንት ያህል ወደ ጊቢ አልሄድንም ነበር ለሁላችንም ትልቅ የልብ ስብራት ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቷል ዛሬን እንደዛው ነው አልዳነም ባሰብናት ቁጥር ያመናል። ለሳቢ ደግሞ ከሞትም በላይ ሞት ነው እናቷን ያጣች ያህል ነው ለሷ ቁስሉ ። ሁሌም ታስታውሳታለች በሳቅ እና በውሸት ፈግግታ እንደረሳቻት ታስመስላለች እንጂ ለደቂቃ እንኳን ከሀሳቧ ርቃ አታውቅም።

ፍቅርን እምፈራው ለዚህ ነው ማጣትን እሚያህል ትልቅ ህመም ይኖራል ብዬ አላስብም አድቅሮ ያንን ሰው ህይወቴ ነው ብለው እየኖሩ ከዛ ሰው በድንገት መለየት እና ያንን ሰው እረስቶ መኖር በጣም ይከብዳል። በሩታዬ ባልፈርድም ግን እራስ ማጥፋት መፍትሄ ነው ብዬ አላስብም። ህይወት እኮ ይቀጥላል እሷን ባትመለስም እኛ ግን እየኖርን ነው ምክንያቱም ህይወት ይቀጥላል የሞተ ግን ይጎዳል ጊዜ ቢፈጅ ነው እንጂ እማያገግም ሀዘን የለም ማን ከሞተው ጋር ተቀብሮ ያውቃል ። ብዙ ተስፋ እሚያስቆርጡ መፈጠራችንን እንድንጠላው እሚያደርጉ ብዙ ለጭንቀት እና እራሳችንን እንድናጠፋ እሚገፋፉ አላፍ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ሀዘን እና ጭንቀት እድሜ አይገድበውም ብዙ ሰው በዚ እድሜያችሁ የምን ሀዘን ነው ምኑን አውቃችሁት ነው ይላሉ ግን ሀዘን ሁሉም ጋር አለ ትንሹም ትልቁም ቢሆን የራሱ የሆነ እሚያስታምመው በሽታ አለው። ግን ቢሆንም ሞቼ ከራሴ ውጪ እምጎዳው ማንም የለም። ብኖር ግን ምናልባትም ለመኖር ሁለተኛ ዕድል ላገኝ እችላለው አጋጣሚ አቀጣሪ ነው ዛሬ የጨለመው ምናልባትም ሊነጋ የተሻለ ሊመጣ ነው ብሎ ማሰቡ አይከፋም። ሁላችንም ይከፋናል እናዝናለን እንታመማለን እንጨነቃለን ተስፋ እንቆርጣለን ግን እኮ ይሄ ሁሉም ያለው እኛ ስለኖርን ነው ግን ብንሞትስ ይፕምስጥ መጫወቻ መሆን ነው ትርፉ በተጎዳን ሰዓት ይህንን ሁሉ ማሰቡ ቀላል አይሆንም ኧረ ጭራሹኑ ትዝ አይለንም ግን ቀድሞ እራስን በዚህ መልኩ ማሳመን በተጎዳን ሰዓት አላስፈላጊ እርምጃን ከመውሰድ ይቆጥበናል። ሩታን ካጣናት በኋላ የድሮዋም ሳቢ አብራ ተቀበረች። አፈቀርኩሽ የሚሏትን ወንዶች ሁሉ አጋጣሚውን እየጠበቀች መጉዳቷት ለእህቷ የተበቀለችላት ይህል እንዲሰማት ያደርጋታል። ከመቃብር ስፍራው እንደምንም አፅናንቼ ይዧት ከወጣን በኋላ ወደ እኛ ቤት እንሂድ አልኳት እና እሺ ብላኝ ያመጣሁላትን ጃኬት ደርባ መንግፕድ ጀመርን በመሀል እሚበላ ነገር ገስተን እንግባ እማማ ከዚህ ሰዓት በኋላ እራት ለመስራት ከሚጨነቁ ብላኝ ሰፈር ወዳለ አንድ ሆቴል ገብተን ለራት እሚሆን ነገር ቴካዌ አስደርገን ወደ ቤት ገባን እማዬ ሳቢን ስታያት በጣም ነበር ደስ ያለት ወደ እኔ ክፍል ከገባን በኋላ እማዬም አብራን መታ አልጋው ላይ ቁጭ ስትል ሳቢ እግሯ ላይ ድፍት ብላ አለቀሰች እማዬም በእናት አንጀቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ፀጉሯን ደባበሰቻት ከዛም ቀስ እያለች እሷም ተረጋግታ ሳቢንም ለማረጋጋት ሞከረች እና የድሮውን እያስታወሰችን መጫወት ጀመርን ሳቢዬም ጭንቀቷ ቀለል ሲላት ያመጣነውን እራት አቅርበን በላን እና ፊልም እያየን በዛው እንቅልፍ ወሰደን ጠዋት ላይ የአማን መቶ እኔን ብቻ ቀሰቀሰኝ ስራ መሄድ ስለነበረብኝ ። እኔም ቁርሴን በላልቼ ወደ ስራ ወጣሁኝ ያው ሳሪ እምትሄድባት ስለሌላት ትንሽ ትረፍ ብለን ዝም አልናት። እንደተለመደው ማይለፍ መታጠፊያው ጋር ጠበቀኝ እና ወደ ስራ አብረን ሄድን እንደተለመደው ዛሬም በጣም አምሮበታል እሱም መዋቡን አያቆም እኔም ማድነቄን አልተው። ስራ ቦታ ካደረሰኝ በኋላ የሆነ ፌስታል ሰቶኝ ወጣ ከሄደ በኋላ ፌስታሉን ፈትቼ ሳየው ውስጡ እሚያምር ቀይ ቀሚስ ከጥቁር ሂል ጫማ ጋር እና አብሮ ትንሽዬ ወረቀት ነበር ቀሚሱ ቀልብ ይሰርቃል ጫማውም እንደዛው ተቻኩዬ ወረቁቱ ላይ የተፃፈውን ማንበብ ጀመርኩ...
" የጫማ ቁጥርሽን ባላውቀውም ግን ይሆንሻል ብዬ በገመትኩት ቁጥር ገዝቻለው ቀሚሱ ግን እንደሚሆንሽ አልጠራጠርም። ማታ እራት ከእኔ ጋር ነሽ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ መውጫው ጋር ጠብቂኝ" ይላል ወረቀቱ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ግን ውስጤን ደስ አለኝ ስራ ቦታ መሆኔን ዘንግቼው ተነስቼ እየዘለልኩኝ ስጮህ ነበር። በኋላ ዙሪያዬን ስመለከት ለካ መስሪያ ቤት ነኝ ሰዎቹ በግርምት ያዩኛል እንደማፈር ብዬ ወንበሬ ላይ ተቀመጥኩኝ ደስታዬ ወደር አጣ ፊቴ ሁሉ በፈገግታ ተሞላ ግን ለምን ይሄን ያህል ደስታ ተሰማኝ ? ብቻ ምንም ይሁን ምን ሰዓቱ እስኪደርስና እስካገኘው ቸኩያለው።

ወደ ረፋድ አምስት ሰዓት ላይ ለሳቢ ደወልኩላት
"ሳቢዬ"
"ወዬ ቃልዬ ጠዋት ትተሽኝ ወጣሻ"
"ትንሽ እረፊ ብዬ እኮ ነው። በደንብ ተኛሽ ?"
"ቀላል አረፍኩኝ ገና አሁን መነሳቴ እኮ ነው እሱንም እቴቴ ቀስቅሳኝ" እማዬን እቴቴ ብለው ነው ሁሉም ጓደኞቼ እሚጠሯት...
"እና ቁርስሽን ገና አልበላሽማ ?"
"ይኸው እያቀረበች ነው አብረን ልንበላ"
"በቃ ብዪና ትንሽ ተንቀሳቀሽበት"
"ግድ ይላል። ቁርሴን ልብላበት በኋላ እደውላለው"
"ሆዳም ብዪ በቃ ቻው" ብያት ስልኩ ተዘጋ። ትንሽም ቢሆን ስለተረጋጋች ደስ ብሎኛል። የተለያየ ሰው እየመጣ እያስተናገድኩኝ ምሳ ሰዓት ሲደርስ እዛው ህንፃው ላይ ያለው ካፌ ውስጥ ትንሽ ነገር ቀማምሼ ወደ ስራ ተመለስኩኝ። ትዝ ሲለኝ ግን ፀጉሬን ሹሩባ እንደተሰራሁኝ ነበር መቼስ ይሄን የመሰለ የራት ልብስ ለብሼ በሹሩባ አልሄድም የግድ መሰራት አለብኝ ብዬ ከሱቅ ቦርሳዬንና ልብስ እና ጫማ የያዘውን ፌስታል ይዤ ሱቁን ዘጋግቼ ወደ ታች ወረድኩኝ። በፊት እዚሁ ሜክሲኮ አካባቢ ሩታ እያለች ሶስታችን ሄደን የምንሰራበት ፀጉር ቤት ትዝ አለኝ እና ወደዛ ሄድኩኝም ስገባ ቤቱ ውስጡ ተቀይሯል ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሰርተውታል ፤ እኛ በምንመጣበት ጊዜ የነበሩት ሰዎችም ተቀይረዋል። ግን አሪፍ ቤት ነው አዘውትረን ከሰፈር ድረስ ስንት ፀጉር ቤት ትተን ነበር እዚህ መተን የምንሰራውም ከ ሶስት አመት በኋላ እግሬ ረገጠ። ወረፋ ስለነበረ የፀጉር ወረፋዬ እስኪደርስ የእጅና የእግር ጥፍሮቼን ተሰራሁኝ። ከሁለት ሰዓት ቆይታ በኋላ ፀጉሬን እና ጥፍሮቼን ተሰርቼ እዛው እነሱ ልብሳቸውን እሚቀይሩበት ክፍል ውስጥ ገብቼ በስጦታ መልክ የተበረከተልኝን የራት ልብስ ለብሼ ጫማዬን ተጫምቼ ወጣሁኝ። ሲያዩኝ እዛው ያሉ ሰዎች በጣም እንዳማረብኝ እየነገሩኝ መልካም ምሽት ተመኙልኝ። ደስ አለኝ ማይለፍ እጠብቅሻለው ያለኝ ታክሲ መያዣው ጋር ስለነበር እዛ ድረስ እንዲህ ለብሼ መሄዱ ነፃነት ስላል ሰጠኝ ከፀጉር ቤቱ አጠገብ ካለው ካፌ ተቀመጥኩና ያለሁበትን ቴክስት አደረኩለት። ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አንድ ትልቅ መኪና ከካፌው ፊት ለፊት መቶ ቆመ እየጠበኩኝ የነበረው መኪና የማለፍን ስለነበር የመኪናው ትልቀት እንጂ ከሚኪናው የወረደውን ሰው አላስተዋልኩም። ወዲያው ስልኬ ላይ መልዕክት ተላከልኝ ማይለፍ ነበር ሳነበው ግን ግራ ተጋባሁኝ እሱን ስለነበር የጠበኩት በጥቂጡም እንደ መፍራት አደረገኝ....."ፊት ለፊትሽ የቆመው መኪና ውስጥ ጊቢ ልጁ እኔ ጋር ይዞሽ ይመጣል" ይል ነበር መልዕክቱ። ቀና ስል ከመኪናው አጠገብ ጥቁር በጥቁር የለበስ ልጅ ቆሟል። በእጁ ወደ መኪናው እንድገባ በምልክት አሳየኝ...


ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ

ለአስተያየት- @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፯

ደራሲ - አብላካት



ውስጤ በጥቂጡም ቢሆን ፍርሀት ነበረ ነገር ግን ማይለፍ ሊጎዳኝ እሚችል አይነት ሰው ነው ብሎ ልቤ ስላላመና እያመነታሁም ቢሆን መኪናው ውስጥ ገባሁኝ። ከሰዓታት ጉዞ በኋላ አብሮኝ ቦታው ላይ ስንደርስ ከመኪናው እንድወርድ ነገረኝና ወረድኩኝ። ቦታውን ከዚህ በፊት አይቼው አላውቅም ትልቅ ሆቴል ነው አካባቢውን ለማወቅ ዙሪያዬን ብቃኝም ላውቀው አልቻልኩም ግን ትልቅ ሆቴል ነው። ወደ ውስጥ ስገባ ቤቱ በሰዎች የተሞላ ነው ከዳር እስከዳር ጢም ብሏል አለባበሳቸው ፣ አቀማመጣቸው ሁሉም ነገር ከቤቱ ደረጃ ጋር ተመጣጣኝነት ያለው ነው። በአይን የማውቃቸው ባለሀብቶችም አለፍ አለፍ ብሎ አሉ። ሆቴሉ ከላይም ፎቅ ላይ ቦታ አለው። ሁሉም ነበር ስገባ ዞረው የተመለከቱኝ ትንሽ ያስፈራል በአይኖቼ ዙሪያዬን እየቃኘሁ ማይለፍን መፈለግ ጀመርኩኝ። እኔ ከቆምኩበት በስተቀኝ በኩል ስዞር ማይለፍን ከደረጃ ላይ ሲወርድ ተመለከትኩት የሆነ የሆሊዉድ አክተር ነው እሚመስለው ልቤ በሀይል እየመታ ነው በጣም አምሮበታል አለባበሱ ከሌላው ጊዜ በተለየ ይስባል። አጠገቤ ሲደርስ የልብ ምቴ ይባሱኑ ጨመረ። ጠጋ ብሎ አቀፈኝ ምናለ ባይለቀኝ ብዬ ተመኘሁኝ ...እንዳቀፈኝ
"በጣም አምሮብሻል" አለኝ
"አመሰግናለሁ ግን ካንተ አልበልጥም" መለስኩለት። እየሳቀ እጄን በእጁ ይዞ ወደ ፎቁ ወጣን.... አንበሩን ስቦ እንድቀመጥ ጋበዘኝ ከዛም....
"ቅድም አስጨነኩሽ አይደል እዚህ አካባቢ የስራ ስብሰባ ስለነበረኝ ከምመለስ ብዬ ነው ሰው የላኩት ይቅርታ ይደረግልኝ"
"ትንሽ አስፈርቶኝ ነበር ግን አሁን እረስቼዋለው"
"ዋናው መርሳትሽ ነው። ቤቱን ግን ወደድሽው ?"
"ውይ አዎ በጣም ነው እሚያምረው ለየት ያለ ቤት ነው"....... የቤቱን ውበት ባልክድም እንደ እውነታው ግን እኔ ይህን መሰል ቦታዎች ላይ ብዙም ነፃነት አይሰማኝም ምክንያቱም እራሴን የሆንኩኝ ስለማይመስለኝ አንዳንዴ ሳንፈልግ እምንላበሳቸው ባህሪዎች አሉ አደል ከትላልቅ ሰዎች ጋር አልያም ልባችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች ፊት ስንሆን ያ ሰው ለኛ ያለው ስሜት እንዳይቀንስ አልያም እኛን በጥሩ መልኩ እንዲያስበን ከመፈለጋችን የተነሳ እንዲሁም ትላልቅ ቦታዎች ላይ ስንገኝ ደግሞ ለቦታው መመጠናችንን ለማሳየት ስንል ፈልገነውም ይሁን ሳንፈልገው ውስጣችን እሚፈጠር አዲስ ባህሪ ከነበርነው ማንነታችን ወጣ ያለ ሰው እንሆናለን ባለማስተዋልም ይሁን በማስተዋል እንዲህ አይነት ባህሪ ውስጣችን አለ። ለዚህም ነው እንዲህ አይነት አካባቢዎች ላይ መገኘትን እማልፈልገው። ግን ደግሞ ይህንን አይነቱን ባህሪ ሰዎች በመጥፎም በጥሩም መልኩ ሲጠቀሙጥ አስተውያለው...... ሁለት ፍቅረኛሞች አበረው ከመሆናቸው በፊት በትውውቃቸው ጊዜ ሴቷ ወንዱን የምታውቀው ወጣ ባለ ባህሪው ነው እሱ ግን እየቆየ ሲሄድ ከሷ ፍቅር ይይዘዋል በዛን ጊዜ ለሱ ያላትን አመለካከት ስለሚያውቅ በሰው ዘንድ እሚጠላ ባህሪውን ይቀይርና ጥሩ ሰው የሆነ መስሎ ለትንሽ ጊዜ በጓደኝነት ይቀርባታል እሷም ያንን የተሻሻለ ባህሪውን ስትመለከት ለሱ ያላት ስሜት ወደ ፍቅር ተቀይሮ አብራው ለመሆን ፍቃደኛ ትሆናለች። አብረው ሲሆኑም እሷን የሱ ለማድረግ ሲል የተጠቀመውን የውሸት ባህሪውን ይቀጥልበታል ፤ በሆነ አጋጣሚ ግን ከጓደኞቹ ጋር እሷን ለመቅረብ ሲል ያልተቀየረውን ተቀይሬአለው ብሏት እንደነበርና በርግጥም ግን አሁን ላይ የበፊት ባህሪውን እንደማይፈልገው እና በዚሁ መቀጠል እንደሚፈልግ ሲያወራ ትሰማለች እሷም ሰምታ እንዳልሰማች ትሆናለች ምክንያቱም እንደሰማችው ነግራ ብትጣላው ወደዛ ባህሪው በድጋሚ ይመለሳል ብላ ስለፈራች አውቃ እንዳላወቀ ሆነች አሁን ላይ በጣም ደስተኞች ነው። ይህንን አይነቱን ለጥሩ ነገር ሲባል የውሸት ማስመሰልን እደግፋለው ግን ደግሞ አለው ወይም አላት ለመባል በሰው ዘንድ ለመክበርና ትልቅ መስሎ ለመታየት ሲባል እሚፈጠርን ማስመሰል በጣም ነው እምጠላው ማስመሰል ጥሩ ጎን ባይኖረውም ሊጎዳ እማይችል መንገድም ሊኖረው ይችላል ልክ እንደ ፍቅረኛሞቹ ታሪክ። ለዚህም ነው እራሴን ከእንደዚህ አይነት ነገሮች ለማራቅ ስል ትላልቅ ቦታዎች እና ትላልቅ ሰዎችን ማግኘት እማልፈልገው። የሌላቸውን አለኝ ያጡትን አገኘው እያሉ በማስመሰል ህይወት ውስጥ እሚኖሩ ስንቶች አሉ ባለሀብቶችን ሲያዩ እንደነሱ ለመሆን እሚያስመስሉ ፤ የተቸገረ ሲያዩ ከነሱ ያልተናነሰ ኑሮ እየኖሩ ግን ያጣው ፊት እሚመፃደቁ ስንት የቀጨጨ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች አሉ። ማስመሰልን እንደለውጥ እሚቆጥሩ ሲያስመስሉ እውነትም እሚያስመስሉትን ህይወት እየኖሩት ያሉ እሚመስላቸው ስንት ሞኞች የሞሉባት አለም። ከዚህ ሁሉ ደረጃንና አቅምን ያማከለ ቦታ ላይ መገኘትን ያመሰለ ምን ነገር አለ። ሳይታወቀኝ በራሴ ሀሳብ ውስጥ ሰጥሜ ልጁን እረሳሁት.....

"ችግር አለ እንዴ ቃል ?" ሲለኝ ከሰጠምኩበት የሀሳብ ባህር ውስጥ ወጣሁኝ
"እእ አይ ምንም ችግር የለም ምነው ?"
"ከቅድም ጀምሬ ምን እንዘዝ እያልኩሽ ነው ግን አትመልሺም"
"ይቅርታ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው። ባንተ ምርጫ ይሁን ደስ ያለህን እዘዝ" አልኩት
"ካልሽ እሺ" ብሎ በሱ ምርጫ አዘዘ። ምግቡ እስኪመጣ ማውራት ጀመርን ከዚህ ቀደም የገጠመሽ ገጠመኝ ካለ አጫውቺኝ ሲለኝ ከነ ሳቢ ጋር ስሆን እሚያጋጥሙንን ነገሮች እየነገርኩት በጣም ሳቀ ፈገግታው በጣም ያምራል ሳላስበው ሲስቅ ሳየው ልቤ ላይ የሆነ ነገር ተሰማኝ ምን እንደሆነ ግን አላውቅም ብቻ ግን የሆነ ደስ የሚል ስሜት። ሲስቅ በግራ ጉንጩ ላይ ዲምፕል ይወጣል ከጥርሶቹ ጥራት ጋር ተደምሮ ይበልጥ አሳምሮታል አላውቅም ብቻ ግን የሆነ ሄደሽ ተጠምጠሚበት እሚል ስሜት ይሰማኛል። በተቻለኝ አቅም እራሴን ለመቆጠብ እየሞከርኩኝ ነው። ለምንድነው እንደዚህ እምሆነው ? ለምንስ የዚህን ያህል ለሱ ተሰማኝ ? አሁንም ቀልብ እሚሰርቅ ፈገግታው አልቆመም.....ያዘዝነው ምግብ እና መጠጥ ተከታትሎ መጣ ፤ እሱን እየተመገብን ጨዋታችንንም ቀጠልን በመሀል አተኩሮ ሲያየኝ እምገባበት ጠፋኝ አንገቴን ሰበር አደረኩኝ።
"ምነው ማየት የተከለከለ ነው እንዴ ?" ጠየቀኝ
"ኧረ በጭራሽ እንደዛ አላልኩም" መለስኩለት
"ስቀልድ ነው። እራቱን ስንጨርስ ሌላ እምንሄድበት ቦታ አለ"
"ከዚህ ሰዓት በኋላ ወዴት ?"
"ገና እኮ ነው ብዙም አልመሸም እኔው እራሴ ወደ ቤት እሸኝሻለው" እምቢ ልለው አልፈለኩም እቤት ሄጄም እድሜ ለእህትና ወንድሜ ደህና ነገር አይጠብቀኝም ከእነሱ ሽሽት ይሆን ከሱ ጋር ለመሆን ፈልጌ ባላውቅም ግን በሀሳቡ ተስማምቻለው.....
"እሺ እንሄዳለን" አልኩት።



ይቀጥላል.......


ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ

ለአስተያየት- @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
🔱 ሰላም ሰላም ውድ የብዕር ጠብታ ቻናል ተከታታዮቻችን እንዴት አመሻችሁ። ብዙዎቻችሁ ቻናሉ ቀዝቅዟል እንደበፊቱ አደለም ብላችሁኛል እናም ትንሽ ነገሮች አልስተካከል ብሎኝ ነው ለሱም ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከነገ ጀምሮ ቻናላችን እንደበፊቱ ስራውን እሚቀጥል ይሆናል።


⚠️እንዲሁም የእዮሪካ ልብወለድ አንባቢያን በጣም እንደታገሳችሁኝ አውቃለው ለሱም ምስጋናዬ ከልብ ነው። ይሄ ሁሉ ሰው ይወደዋል ብዬ አልጠበኩም ነበር ብዙ እንደቆየባችሁ ይገባኛል ግን መልቀቅ እማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩኝ ነው እናም ይሄን ያህል ስላስጠበኳችሁ በጣም በጣም ይቅርታ። ለመካሻ እንዲሆን ነገ ጠዋት እና ማታ ላይ አድርጌ ሁለት ክፍሎችን እምለቅ ይሆናል ከዚህ በኋላ እንደማይዘገይ ቃሌ ነው። ስለምትከታተሉኝ እና ስለምታደርሱኝ አስተያየቶች በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ ፈጣሪ ያክብርልኝ። ከዚህ በኋላም እብራችሁኝ እንደምትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ። 🙏

ሰናይ ምሽት💞



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፰

ደራሲ - አብላካት



የቀረበውን ምግብ በልተን ከጨረስን በኋላ እንሄዳለን ወዳለኝ ቦታ ለመሄድ ብለን ከሆቴሉ ወጣን። መኪና ውስጥ ከገባን በኋላ አንዳንድ ነገሮችን እያወራን ሜክሲኮ የእርሱ ድርጅት ጋር ስንደርስ መኪናውን አቆመው......

"እንዴ እዚህ ምን እንሰራላን ?" አልኩት
" ስንገባ ታይዋለሽ"... ብሎኝ እዛው መኪናው ውስጥ አይኔን በጨርቅ ሸፍኖኝ ከመኪናው ወርደን ወደ ህንፃው ገባን.... ከቆይታ በኋላ ጨርቁን ከአይኔ ላይ ፈታልኝ። ቴራሱ ላይ ነበርን አይኔን ስገልጥ ያየሁትን ለማመን ከበደኝ መሬቱ ሙሉ በሙሉ በአበባ አሸብርቋል መሀል ላይ ጠረፔዛ እና ሁለት ወንበሮች ከጠረፔዛው ላይ ደግሞ መጠጥና ብርጭቆ ተቀምጧላ። ቦታው ከበፊቱ በተለየ ውብ ሆኗል.....ልቤ በጣም ይመታ ጀመር ደስታዬን መቆጣጠር አቃተኝ እና ዘልዬ ተጠመጠምኩበት....አቀፈኝ ጠረኑ ይለያል ከእቅፉ ባልወጣ ምነኛ ደስ ባለኝ...

"ወደድሽው ?" አለኝ በጆሮዬ
"አዎ በጣም ያምራል አመሰግናለሁ" አልኩት እና ወንበሩ ላይ ተቀመጥን። ውስኪውን ከፍቶ በብርጭቆ ላይ ለኔም ለሱም ቀዳና እየጠጣን ጨዋታችንን ቀጠልን......

"ማይለፍ እውነት ለመናገር ይሄንን አልጠበኩም ነበር በጣም ደስ ብሎኛል"
" ዋናው ያንቺ ደስታ እንጂ ይሄ ትንሹ ነገር ነው"
"ብቻ አመሰግናለሁ"
"ምንም አደል"
"እእእ ማይለፍ ቅድም መኪና ውስጥ እምነግርሽ አለኝ ብለህ አልነበር ታዲይ አሁን ንገረኛ" አልኩት
"አይ ተይው ሌላ ጊዜ"
"እንዴ ለምን ምን ተፈጠረ ?"
"ምንም አልተፈጠረም ግን አሁን ብነግርሽ ይሄን ሁሉ ያደረኩት ለዛ ብዬ የመስልሻል"
"በፍፁም እንደዛ አላስብም ይልቅ አሁን ንገረኝ"
"ቃልዬ ምን መሰለሽ...ማለት እኔ አንቺን... አለ አይደል" እያለ ሲርበተበት ንግግሩን ገታ አድርጌ እጆቹን በእጆቼ ያዝኩትና...
"ማለት የፈለከውን በእርጋታ ንገረኝ ለምን ትጨናነቃለህ "አልኩት።
" በቃ ወድጄሻለሁ ማለት ካንቺ ፍቅር ይዞኛል...አውቃለው ረጅም ጊዜ አልሆነንም ግን በቃ እማስበው ካንቺ ጋር መዋል ያስደስተኛል እመኚኝ ከልቤ ነው እምነግርሽ" አለኝ። ይሰማሁትን ላምነው ከበደኝ እምቢ ልበለው እሺ ግራ ገባኝ ግን ደግሞ ወድጄዋለው ላጣውም አልፈልግም ፍርሀቴ አሸንፎኝ እምቢ ብለውና ቢርቀኝ እድሜ ልኬን እፀፀታለው እንዴት ከአፌ እንደወጣ ባላውቅም ግን....
"እኔም አፈቅርሀለው" አልኩት.... ፊቱ ላይ የነበረው ፈገግታ እኔንም ፈገግ አስባለኝ። አመሰግናለሁ አለና ከተቀመጠበት ተነስቶ አቀፈኝ ፤ በዛውም እንደንስ አለኝና አስነሳኝ...ወገቤን ይዞ ወደ እሱ ሲያስጠጋኝ ልቤ ልትወጣ ደረሰች.... ቀስ አድርጎ በእጁ ወገቤን ያዝ አደረገኝ እጄን ትከሻው ላይ ማድረግ አስፈራኝ.... እሱም ስለገባው እጄን በእጁ ይዞ ትከሻው ላይ አደረገውና መደነሳችንን ቀጠልን። ውስጤን የደስታም ፣ የፍርሀትም ስሜት እየተሰማኝ ነው ያለው ለምን እንደሆነ ግን ሊገባኝ አልቻለም አፈቅረዋለው ታዲያ ለምን ይሄ ስሜት ይሰማኛል ለምን እፈራለው ለምን ልቤ የዚህን ያህል ይረበሻል ? ግራ ገባኝ።

አንዳንዴ እኛ ሰዎች የሆነን ነገር እንፈልግና ያ ነገር በእጃችን ሲገባ ግን ያንን ነገር መፈለጋችንን እንጠራጠራለን....የሆነ እሚጨንቅ ስሜት እየተሰማኝ ነው ያለው ....ቸኩዬ ይሆን ? በዚህ ፍጥነት እሺ ማለቴ እሱ ለኔ ያለውን ግምት ያወርድበት ይሆን ? ስለሱ ማንነት ያን ያህል ሳላውቅ ፍቅሩን መቀበሌ ትክክል አይደለም እንዴ ? ምስቅልቅል ያለ ስሜት ይሰማኝ ጀመረ። ከዚህ በላይ መቆየቴ ልክ መስሎ ስላል ታየኝ.....
"ማይለፍ ቅር ካላለህ ወደ ቤት ልሂድ ?" አልኩት...
"ምነው ችግር አለ ?"
"አይ እቤት ለእናቴ ማምሸቴን አልነገርኳትም እና ከዚህ በላይ ከቆየሁኝ ጥሩ አይመጣም"
"ካልሽ እሺ...እንሂድ" ብሎኝ ተነስተን ወጣን። ሰፈር አካባቢ ስንደርስ የለበስኩት ልብስ ትዝ አለኝ በገዛ እጄ እላዬ ላይ ለሚለኩሱት እሳት ክብሪት አቀባይ ሆኜ አረፍኩት። የት ነበርኩ ልባቸው ነው ? አይ እዳዬ አያልቅብሽስ መባል የነበረብኝ እኔ ነበርኩ....
"በቃ ወደቤት ልግባ" አልኩት
"እሺ ስለዛሬው በጣም አመሰግናለሁ ደስ ብሎኛል በጣም"
" እኔም ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ። መልካም አዳር" አልኩት
"እሺ ቃልዬ ሰላም እደሪ" ብሎ ግንባሬን ሳመኝ ደስ እሚል ስሜት አለው......ቻው ብዬው ከመኪናው ወረድኩኝ። አሁን እቤት ምን ብዬ ነው እምናገረው ወይኔ በቃ እየተቀባበሉ ምሽቴን ሊያበላሹት ነው። እሱስ ይበላሽ ለምጄዋለው እናቴ ባልተቀየመችኝ.... ከራሴ ጋር እየተብሰለሰልኩኝ ስራመድ ከኋላዬ "ጃስ" አለኝ ቆሌዬ ነበር የተገፈፈው ማነው ብዬ ስዞር የአማን ነበረ።
"እንዴ አንተ በዚህ ሰዓት እዚህ ምን ትሰራለህ መሽቷል እኮ"
"አስፈቅጄ ነው ጓደኛዬ ቤት እያጠናሁኝ ነበር"
"እስከዚህ ሰዓት የምን ጥናት ነው እንዳይለመድህ" አልኩት
"እሺ በቃ ይቅርታ። አንቺ ግን ከየት ነው አንቺም እኮ አምሽተሻል በዛ ላይ አለባበስሽ ፀጉርሽ እእእ" አለኝ
"እሺ አባትየው ግብዧ ነበረብኝ እዛ ቆይቼ ነው"
"እንግዲህ የነ ሊዲያን ስድብ ቻይው"
"የአማንዬ በእናትህ አንተ ዘዴ አታጣም የት ነበርኩኝ ልበል ?" ትንሽ አሰበና...
"በቃ የብሩክ ልደት ነበር በያቸው እሱን አያዋሩት" አለኝ.....ልክ ነው ብሩክን ብዙም ስለማያውቁት እንደዚህ ካልኩኝ ማንም አይናገረኝም....
"አይ የኔ መልካም ወንድም ምርጥ እኮ ነህ። በል አሁን እንግባ" አልኩትና ወደ ቤት ገባን.....ሳሎን ውስጥ ሁሉም ተቀምጠዋል ገና ሲያዩኝ ከእግር እስከራሴ ድርስ አፍጥጠው ተመለከቱኝ። እማዬም ከጓዳ እየወጣች....
"የኔ ልጅ የት አምሽተሽ ነው እስካሁን ደሞስ አለባበስሽ"..... አለችኝ
" አይ እማዬ የጓደኛዬ ልደት ነበር" ስል ሊዲያ ክትክት ብላ እየሳቀች
"አይን ያወጣ ውሸት ከየት ነው እምታመጭው ከማንም ጋር ስትዳሪ አምሽተሽ እንዲህ ስትል አታፍሪም" አለችኝ.... የሆነ እነቂያት እነቂያት እሚል ስሜት ተሰማኝ...
"አንቺ ታላቅሽ እኮ ነኝ እንዴት እንዴት ነው እምትናገሪው!" አልኳት
"የታላቅ ስነምግባር ሲኖርሽ እኮ ነው እንደ ትልቅ እምትከበሪው ሽርሙጥና እያስተማርሽ መከበር ፈለግሽ " አለኝ ሳሙኤል ቀጠል አድርጎ.....
"ትሰሙኛላችሁ ማናችሁም አያገባችሁም ይሄ የኔ ቤት ነው እንደፈለኩኝ ሆኜ መግባት እችላለው ባባቴ ቤት ማን አዛዥ አደረጋችሁ ስፈልግ ላሶጣችሁ እንደምችል አታውቁም እንዴ ከዚህ በኋላ ሶስታችሁም አንድ ትርፍ ንግግር ስትናገር ብሰማ በፖሊስ አስቀፍድጄ ነው እማሶጣችሁ ተከበሩ!" አልኳቸው.....ይህንን ተናግሬ ዞር ከማለቴ እናቴ በጥፊ አለችኝ.....በድንጋጤ እንዳቀረቀርኩኝ ቀረሁ። እናቴ እኔን መምታቷን ለማመን ከበደኝ.....
"ለካ እንደዚህ ልቅ ነሽ በያ እንግዲህ አሶጪን ጎሽ ያንቺ ቤት መሆኑን ስላሳወቅሽን እናመሰግናለን አንቺን በመውለዴ እፍረት ተሰማኝ" አለችኝ እናቴ።



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ......


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል ፲፱

ደራሲ - አብላካት



ቃል ሳልተነፍስ እየሮጥኩ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። እናቴ እጇን እኔ ላይ ማንሳቷን ለማመን ከበደኝ ፤ መምታቷ እኮ አደለም ያስለቀሰኝ ግን እነሱ የተናገሩትን ከቁብ ሳትቆጥር እኔን መናገሯ ነው ያሳመመኝ። እሷን ሲናገሯት የተከላከልኩላት ፣ ባጣች ሰዓት የደገፍኳት ፣ ባዘነች ሰዓት አለሁሽ ያልኳት እኮ እኔ ነበርኩኝ። እናትነቷን ዘንግተው ቀን ከሌት ክብሯን ዝቅ ለሚያደርጉት ወግና እኔን እነሱ ፊት ማዋረዷ ነው ሀዘኔን ያበዛው። አልጋዬ ላይ ድፍት ብዬ ተንሰቀሰኩኝ ከፋኝ ፤ የእነሱ ንግግር እኮ ለኔ ምንም አልነበረም ለሷ ብዬ ሁሉን እችለው ነበር ግን እሷም ለነሱ ከወገነች ማነው ለኔ እሚያዝነው ? አልቅሼ ቢወጣልኝ ብዬ ያለማባራት አለቀስኩኝ። በድንገት ስልኬ ጠራ ሳየው ማይለፍ ነበር በዚህ ሰዓት እንኳን እሱን ላወራው እራሴን እንኳን ማዳመጥ አልፈልግም ዘጋሁበት በድጋሚ ደወለ ስልኬን እስከመጨረሻው ዘጋሁት። ሳይታወቀኝ እዛው ባለሁበት እንቅልፍ ወሰደኝ። ሊነጋጋ ሲል እንደመባነን አደረገኝና ተነሳሁ....ማንም ሳያየኝ መውጣት ስለፈለኩኝ ልብሴን ቀያይሬ በዝግታ ከቤት ወጣሁኝ.....ግን ወዴት ልሄድ ይሆን አላውቅም ብቻ በዚህ ሰዓት ማንንም ማግኘትም ሆነ ማውራት አልፈልግም ብቻዬን መሆን ነው እምፈልገው። ወደ ስራ ብሄድ ማይለፍን ማግኘቴ አይቀሬ ነው ለዛም ለሰውየው ደውዬ ለሁለት ቀን አስቸኳይ ነገር ገጥሞኝ ከከተማ እንደወጣሁኝ ነገርኩት እግዚአብሔር ይስጠው አልተቃወመኝም። ቀለል እንዲለኝ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ እና እዛ ለረጅም ሰዓት ተቀመጥኩ። ሰላም ተሰማኝ...ድንገት ስልኬ ጠራ ሳየው አቤል ነበር .....

"ቃልዬ"
"ወይ አቤላ እንዴት ነህ ?"
"ደህና ነኝ በሰላም ነው የጠፋሽው ወይስ አስቀይመንሽ ነው ?"
"ኧረ በጭራሽ ያው ስራ ጀምሬ የለ ለዛ ነው"
"ቢሆንስ ከተገናኘን እኮ ቆየን አንቺም ዘጋሽን"
"ይቅርታ አቤልዬ አልመቻች ብሎኝ ነው"
"እሺ አሁን ቁርስ ልንበላ እየወጣን ነው ከተመቸሽ አብረን እንብላ" መሄዱን ባልፈልግም ግን ደግሞ አሁን እምቢ ብላቸው ሌላ ነገር ይመስልብኛል ብዬ "እሺ"አልኩኝ።
"የት ነሽ እንምጣ"
"ሰፈር ቤተክርስቲያን ነኝ"
"መጣን በቃ" ብሎኝ ስልኩ ተዘጋ። ለካ ሳይታወቀኝ ከጓደኞቼ እርቄአለው.... እነሱ እኮ ለኔ ብዙ ሆነውልኛል ሁሌም ከጎኔ ነበሩ ቢያንስ ስልክ መደወል ነበረብኝ። ከደቂቃዎች በኋላ ስልኬ ጠራ አቤል ነው......
"ውጪ በር ላይ ነን" አለኝ። ተሳልሜ ወጣሁኝ ጋቢና ብሩኬ ነበር መኪና የያዘችው ሳቢ ነበረች..... አቤል ከመኪናው ወርዶ ከኋላ አስገባኝ ሁሉንም ሰላም አልኳቸው ሳቢን ሰላም ልላት ስል ግን ዝም አለችኝ.....
"ሳቢዬ ምነው ?"
"ምንም ምነው ?" ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ....
"ታዲያ ሰላም አትይኝም እንዴ ?"
"እሺ ሰላም ነሽ!" አለችኝ እንደተናደደችብኝ ስለገባኝ ዝም አልኳት።
"እእእ የት ነው እምንበላው ?" አለቻቸው አቤላም ቀጠል አድርጎ.....
"ባለፈው የበላንበት ቤት እኮ አሪፍ ነበር ቦሌ ጋር ያለው"
"አዎ እዛ እንሂድ" አለ ይሳቅ ቀጠል አድርጎ..ለማዋራት ፈራኋቸው። ቦታው ጋር ስንደርስ ከመኪናው ወርደን ወደ ውስጥ ገባን...ሳቢ ልታየኝ እንኳን አልፈለገችም አቤላ ብቻ ነበር ሲያዋራኝ የነበረው.... ብሩክ እና ይሳቅም መናገር አልፈለጉም እንጂ ሊያዋሩኝ እንዳልፈለጉ ያስታውቅባቸዋል። ግራ ሲገባኝ....
"ቆይ እንደዚህ እየሆናችሁ ያላችሁት ስለጠፋሁኝ ብቻ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ ?" ጠየኳቸው....
"አይ ምንም የለም" አለኝ ብሩኬ ....
"እሺ እንደዚህ እምትሆኑ ከሆነ ለምን ጠራችሁኝ ?"
"እኛ አልጠራንሽም አቤል እንጂ" አለችኝ ሳቢ... በጣም ነበር የደነገጥኩት ...
"ሳቢ አንቺ ነሽ እንደዚህ ያልሽኝ ?"
"ምነው ገረመሽ እንዴ እኔ ወይስ ግልፁን ስለነገርኩሽ ነው። እኔ እንግዲህ እንዳንቺ ማስመሰል አልችልም ይቅርታ" አለችኝ
"ስለምን ማስመሰል ነው ነው እምታወሪው ምን አድርጌ ነው ? ይሳቅ አንተ እንኳን ንገረኝ"
"ቃልዬ ሁለት ቀን እቤት ስንመጣ ሊድያ ነበር የከፈተችው እና አለች ግን ማንም ቢመጣ የለችም በያቸው ብላኛለች ብላ ከበር መለሰችን"
"ማን እኔ ?" አልኩት እንደመደናገጥ ብዬ
"እሱ ብቻ ቢሆን እኮ ጥሩ ነው እኛ እኮ ነን ጓደኞቿ ስንላት ታዲያ በዋናነት ማንን ሆነና ነው እንዳይገቡ ያለችው ማለቷ ነው እኔን የገረመኝ" አለ ብሩኬ ቀጠል አድርጎ....
"እና እሷን አምናችሁ ነው እንደዚህ እምትሆኑት ?"
"ለምን አናምናትም እስከዛሬም ያላመንኳት ይቆጨኛል" አለች ሳቢ...
"ከእኔ እሷን አመንሻት እኔ እኮ ስራ ነው እም ውለው ስራ ባይኖረኝ እንኳን ከመቼ ጀምሮ ነው እኔ እቤት እምቀመጠው ?"
"እሺ እንደዛ ካልሆነ ለምን ስልክ ስደውል አታነሺም መስመሩ ተይዟል ብቻ ነው እሚለው"
"መቼ ደውለሽ ?"
"ኧረ ቃልዬ እኔ እራሱ ብዙ ጊዜ ደውዬልሻለው" አለኝ ብሩኬ......
"ከፍተሽ እዪዋ" አለችኝ.... ስልኬን ከፍቼ ከዚህ ቀደም የተደወሉትን ሳይ ሳቢም ብሩኬም እንዳሉት ደውለዋል ግን ማይለፍን በማዋራበት ሰዓት ነበር። እውነቱን ለመናገር አንዱንም አላየሁትም.....
"እ አሁንስ ልትክጂ ነው ?"
"ሳቢ ፈጣሪ ምስክሬ ነው አንዱንም አላየሁትም እመኑኝ"
"ለነገሩ አታስቢ ለኛም ጥሩ ትምህርት ሆኖናል ከዚህ በኋላ ስልክሽም ላይ አንደውልም ቤትሽም አንደርስም በተለይ እኔ" አለችኝ
"ኧረ በፈጠራችሁ እኔ ከምታወሩት ውስጥ አንዱንም ነገር አላደረኩም እኔ እቤትም ውዬ አላውቅም"
"እስከዛሬ እሚቆጨኝ ሊዲያን አለማመኔ ነው ስላንቺ እስከዛሬ የተናገረችው ሁሉ እውነት ነበር ትላንት ስንገናኝ ስላንቺ እውነተኛ ማንነት ባትነግረኝ አላውቅሽም ነበር"
"ሳቢ እውነት ከእኔ ይልቅ ሊዲያን አመንሻት ?"
"አዎ" አለችኝ......ምድር የተገለበጠብኝ ያህል ተሰማኝ ብድግ ብዬ ከሆቴሉ ወጣሁኝ..... አቤላ ተከትሎኝ ወጣና እጄን ያዞ
"ተረጋጊ ቃልዬ እነሱ ስለተናደዱ ነው" አለኝ
"እቤላ እኔ እኮ ነኝ እንዴት እንደዚህ ትላለች"
" እባክሽን እንደዚህ አትሁኚ ሲገባቸው ይቄጫቸዋል"
"አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ ካላስቸገርኩህ" አልኩት....
"እሺ ደሞ ክላስ ነገ ነው እሚጀመረው" አለኝ
"እ እሺ"
"እነሱን ላናግራቸው እና ያለሽበት ድረስ እመጣለሁ እሺ" አለኝ
"በቃ ቻው" ብዬው ወደማላውቀው ቦታ መጓዝ ጀመርኩኝ። ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ...መንገድ ላይ መሆኔ ሳይታወቀኝ በሀይል ጮኩኝ.... አላፊ አግዳሚው እብድ ናት ብሎ ይሆን አሳዝኛቸው ባላውቅም ጥግ ጥጋቸውን ይዘው ያዩኛል።



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ......



ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 20

ደራሲ - አብላካት



ወዴት እንደ ምሄድ አላውቅም.....ጆሮዬ ላይ የነ ሳባ አወራር የእናቴ ጥፊ የነ ሊዲያ አጥንት እሚሰብር ንግግር ያቃጭልብኝ ጀመር....ብቻ ዝም ብዬ መሮጤን ቀጠልኩ ፤ የት እንደሆነ እማላውቀው ቦታ ላይ ስደርስ ቆምኩኝ ደከመኝ! ታከተኝ! አቃተኝ! እረፍት እና ተስፋ በሌለው ህይወት ውስጥ መኖር ይደክማል። ደስታ ምን እንደሆነ ሳላውቀው ቀን በቀን ሀዘንን ማስተናገድ ታከተኝ ፤ ላይሞላ የጎደለን ዓለም ለመሙላት መሞከር ዘበት ነው። አባቴ ናፈቀኝ እምባዬን ማየት እሚያመው አባብዬ አለመኖሩ ለዚህ ሁሉ እንደዳረገኝ ሳስብ አምላኬን ወቀስኩት አማረርኩት.....እሱ ቢኖር እኮ ማንም ቀና ብሎ አያየኝም... እሱ ባይሞት እኮ ይሄን ሁሉ አላሳልፍም ነበር። ዛሬ እኔ እየኖርኩ ላለሁት ህይወት ተጠያቂው ማን ነው ? እናቴ ? አባቴ ? የእንጀራ እህት ወንድሞቼ ? የእንጀራ አባቴ ? እኔ ? ወይስ ፈጣሪ ? ማነው ተወቃሹ! ሌላ ሰው ላይ እያስታከኩ እራሴን ከጥፋተኝነት ማዳን ባልፈልግም ግን ደግሞ ይሄን ህይወት ለመኖር ከጅምሩም ፍላጎቱ እንዳልነበረኝ አውቃለው። እንደ ሁሉም ሰው ወጣትነቴን በአግባቡ ተደስቼ ማድረግ እምፈልገውን አድርጌ መደሰት በምፈልገው ልክ ተደስቼ ማለፍ ነበር ምኞቴ። ምን ያደርጋል ካሰብኩት አንዱን እንኳን ሳልኖረው ሊያልፈኝ ነው። መመኘት እንጂ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ የገባኝ የራሴን ኑሮ አይቼ ነው። አላማርርም እኮ ከኔም የባሰ እንዳለ አውቃለው እሱንም ብዬ ተመስገን ማለትን መርጬ ነበር ፤ ምን ዋጋ አለው ይቺ ክፉ አለም የተሳካ ነገር እንዳገኘ እድሉን አለመስጠጧ ሳያንስ ለበጎ ነው ማለቴንም ልትነጥቀኝ እየዳዳች ነው።

እድል እሚያገኝ ሰው ግን ምነኛ የታደለ ነው። ገንዘብ ካለው ነገሮችን ለማስተካከል እድል የተሰጠው ሰው ነው ለኔ ሀብታም ፤ ያጣነውን ለመመለስ ፣ የጎደለንን ለመሙላት ፣ ያለቀስነውን በሳቅ ለመለወጥ ፣ ነጋችንን የተሻለ ለማድረግ እድል ማግኘትን የመሰለ ነገር ምን አለ ? ይኽው አንድ እድል አይቼ አደል ያለእድሜዬ ላረጅ የደረስኩት። እኔ እኮ የተሟላ ነገር አልተመኘሁም አንድ ምኞቴ ሰላም ማግኘት ብቻ ነው ለምን ችግር ገጠመኝም ብዬ አልጠየኩም መደራረቡ እንጂ ያደከመኝ ከዚህ የተሻለ ህይወት ቢኖረኝም እኮ ችግር መኖሩ አይቀሬ ነው። ሰላምን የመሰለ ምን ነገር አለ ?


ስልኬ ጠራ... ማይለፍ ነው ከማታ ጀምሬ ስላላወራሁት እንዳይጨነቅ ብዬ አነሳሁት.
"ቃልዬ ?" ....መናገር አቃተኝ...
"ሄሎ!"
"ማይለፍ እባክህን ናልኝ" አልኩትና ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ....እንዴት እንዲ እንዳልኩት ለኔም ማመን ከብዶኛል...
"ምን ሆንሽብኝ እእእ እሺ የት ነሽ ?"
"እኔንጃ"
"ተረጋጊና ያለሽበትን ንገሪኝ እባክሽን"
"ከኛ ሰፈር ስትወጣ የሚገኘው ኮንደሚኒየም ጀርባ ያለው አስፓልት ጋር ነኝ"....እራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ያለሁበትን ነገርኩት።
" እሺ መጣሁ በቃ ወዴትም እንዳትሄጂ" .......ብሎኝ ስልኩ ተዘጋ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ የማይለፍን መኪና ወደኔ ሲመጣ አየሁት... እምባዬን መጠራረግ ጀመርኩኝ.....ከመኪናው ወርዶ እግሬ ስር ቁጭ አለና......

"ምን ተፈጥሮ ነው ?" አለኝ። ምን ብዬ ልመልስለት የተፈጠረው እኔንም ግራ አጋብቶኛል....
"ከፋኝ" አልኩት....ቶሎ ብሎ ወደ ደረቱ አስጠጋኝና አቀፈኝ....ለረጅም ደቂቃ እቅፉ ውስጥ ቆየሁኝ ሰላም ተሰማኝ የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ የወረደልኝ መሰለኝ። ከቆይታ በኋላ...
"ምግብ ግን በልተሻል ?" አለኝ
"እ አይ አልበላሁም ጠዋት የወጣሁ ነኝ" አልኩት
"ምሳ ልጋብዝሽ ?"
"ደስ ይለኛል" አልኩትና ተነስተን መኪና ውስጥ ገባን። ማንንም ላለማዋራት ብዬ ስልኬን ዘጋሁት .....በዚህ ሰዓት ሁሉንም ነገር እረስቼ መረጋጋት ብቻ ነው እምፈልገው። አንድ ሆቴል ስንደርስ የመኪናውን በር ከፈተልኝና ወረድኩ ሊያቅፈኝ ሲሞክር እንደመሸሽ አልኩኝ... ደነገጠ....
"ይቅርታ በጣም እሚረብሽሽ አልመሰለኝም ነበር" ሲለኝ የፍቅር ጥያቄውን መቀበሌ ትዝ አለኝ። መልሼ በራሴ አፈርኩ....
"አይ እኔ ነኝ ይቅርታ ማለት ያለብኝ አንተ እኮ ልክ ነህ" አልኩት.....እና እንዲያቅፈኝ ተጠጋሁለት። ፈገግ አለ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ፈገግታው ፈገግ አስባለኝ። ፈገግታው ሳቁ ከልቡ ስለሆነ ነው መሰል ያምርበታል። ወደ ውስጥ ገብተን ምግብ አዘን መመገባችንን ጀመርን ...

"ምን አንደተፈጠረ ልትነግሪኝ ፍቃደኛ ነሽ ?" አለኝ...ምኑን ልንገረው እናቴ ለሚጠሏት ወግና መታችኝ ብዬ ?... ጓደኞቼ የክፉ ቀኖቼ እምላቸው ውሸት አምነው ጠሉኝ ብዬ ?...የቱን ነው እምነግረው ህይወቴ ውስጥ ችግሮች ከመፈራረቃቸው ይተነሳ እኔም ለመረዳት ከብዶኛል እንኳን ለሱ ላስረዳው።
"ሌላ ጊዜ ብሰፊው እነግርሀለው"
"ካልሽ እሺ እጠብቃለው። ድግሞ ትምህርት ነገ ነው መሰለኝ እምትጀምሩት አደል ?"
"እ አዎ ነገ ነው።"
"ታዲያ ስራሽን እንዴት ልታደርጊ ነው ?"
"ያው አስፈላጊ ቢሆንም ከትምህርቱ ጋር አብሮ ስለማይሄድ አቆማለው"
"ነገ ከክላስ ስትወጪ ወደ እኔ መምጣት ትችያለሽ ?"
"እሺ እሞክራለሁ" አልኩትና ሂሳብ ከፍሎ ወጣን። እምትሰሪው ከሌለ ጋሼ ጋር ደርሰን እንምጣ" አለኝ.......
"በጣም ደስ ይለኛል እንሂድ" አልኩትና ወደ እሳቸው ጋር ሄድን።

ዛሬም ከቤታቸው ደጃፍ ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚውን ይመለከታሉ። ጠጋ ብለን...
"ደህና ዋሉ ጋሼ ?" አላቸው ማይለፍ...
"ውይ ልጆቼ እንዴት ዋላችሁ ?" ብለው ከመቀመጫቸው እንደመነሳት አሉ...
"ደህና ነን ጋሽዬ እርሶ እንዴ ኖት ?" ጠየቃቸው
"ፈጣሪ ይመስገን ደህና ነኝ ልጆቼ። ግባና መቀመጫ ይዘህ ና" አሉት ማይለፍን..
... ወደ ውስጥ ሲገባ...
"ልጄ ደህና ነሽ ?" ጠየቁኝ
"አዎ ጋሼ ደህና ነኝ"
"ግን ንግግርሽ እና ሁኔታሽ አንድ አደሉምሳ" አሉኝ...
"እንዴት ጋሼ ?"
"ውስጥሽ እምባ እንጂ እንዲህ ፊትሽ ላይ እንደሚታየው አይነት ፈገግታ የለማ የኔ ልጅ" አሉኝ
"ሁሌም እኮ ደስታ የለም ጋሼ"
"እሱስ ልክ ብለሻል ሁሌም ደሞ ሀዘን የለም። ባለፈው ስትመጪ ሁኔታሽ ቢገባኝም ሳያውቁኝ እንዴት ያወራሉ እንዳትይኝ ብዬ ነበር ዝም ማለቴ። አሁን ግን ልጄ ሁነሻል ታዲያ መጠየቅ አልችልም እንዴ የኔ ልጅ ?"
"ኧረ ይችላሉ አባቴ"
"ዛድያ ንገሪኛ ምን ሁነሽ ነው እንዲህ መከፋትሽ ?"
"አባቴ...." ብዬ ገና ንግግሬን ከመጀመሬ ማይለፍ ወንበር ይዞ መጣ.... ንግግሬን ገታ አደረኩኝ። እሳቸውም...
"ጌታ መሳይ ዛሬ ስራ የለም እንዴ ?" አሉት
"ነበረኝ ግን ከቃልዬ ጋር ላሳልፍ ብዬ ነው። ምነው ጋሼ ?"
"ከእሷ ጋር እምናወራው ነበረን...ስራ ቢጤ ካለህ ወደዚያ ሄደህ ስንጨርስ ደውላለህ መተህ ብትወስዳት ብዬ ነበር ጌታ መሳዬ ቅር ካልተሰኘህ"
"ኧረ ችግር የለውም እንደውም ከፍቷት ነበር ጋሼ ለኔ አልነግርም ስላለችኝ በዛውም እሱን ጠይቃት"
"እሺ እጠይቃለሁ የኔ ልጅ" አሉት
"ቢሮ የጀመርኩት ስራ ስለነበር እንደውም እሱን እሰራለሁ። ስትጨርሱ ደውይልኝ እና እመጣለሁ"
"እሺ እደውልልሀለው"
"በሉ በቃ ሰላም ዋሉ" ብሎን ሄደ...



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 21

ደራሲ - አብላካት



ለጋሼም ከአባቴ ሞት በኋላ የገጠመኝንና እየገጠመኝ ያለውን ነገር በሙሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኳቸው እሳቸውም ሰለቸኝ ሳይሉ ብሶቴን ሲያደምጡኝ ቆዩና እንዲህ አሉኝ......

"የኔ ልጅ ሁላችንም አነሰም በዛም የውስጣችን ቁስል አለን። ሁላችንም ታመናል ፣ ደምተናል ፣ የመኖር ተስፋችን ጨልሞ ሞታችንን ናፍቀናል። ግና ልጄ አንቺ ዛሬ እያሳለፍሽ ያለውን ችግር እንኳን ሳያሳልፍ መኖር እየፈለገ በአጭሩ እሚቀጭ ስንት አለ ? መናገር እየፈለገ መናገር እማይችል ዲዳ ፣ መስማት እየፈለገ መስማት ያልቻለ ፣ ማየት እየፈለገ ፀሀይ ምን እንደ ምትመስል ፣ የጨረቃ ገፅታ እንዴት ይሆን እያለ ማየቱን እየናፈቀ ማየት የተሳነው ፣ እሮጦ ማምለጥን ተራምዶ መሄድን እሚመኝ አካል ጉዳተኛ ፣ ሀዘኑን ሳቁን ደስታውን ችግሩን እሚካፈለው አለው እሚለው ያጣ የጎዳና ተዳዳሪ በሞላባት ይቺ እደለቢስ አለም ላይ ተቀምጠን ማማረር የፈጣሪን አይን መጠንቆል ነው ልጄ። አላዘንሽም አልተጎዳሽም ሳይሆን የሌላውን ካንቺ የከፋ የገጠመውን አይተሽ ተፅናኚ። ልጄ እማያልፍ ቀን እማይነጋ ለሊት የለም ብቻ በአምላክሽ ተማመኚ ተስፋሽን በሱ አድርጊ የፈጠረን ጌታ ጥሎ አይጥለንም። አንቺ ብቻ በርትተሽ ነገ የተሻለ እንደሚሆን እመኚ ፤ አንድ ነገር ዛሬም ነገም ሲደጋገምብሽ ንቀሽ መተውን ልመጂ። ልጄ የቀን ጎዶሎ ብዙ ያሳያል ያ እንዳይመጣ እራስሽን አበርቺ። ውድቀትን እንጂ ስኬትን እሚመኝ በጠፋበት ጊዜ ንቆ መተውን ችሎ ማለፍን ተማሪ። የኛ ሰው ስትሸነፊ እጅ ስትሰቺ መሄጃ ስታጪ ነው ከንፈር ለመምጠት እና ለመዘባበት እሚመጣው ። ታዲያ ለማን ለየቱ ሰው ብለሽ ነው እራስሽን እምትጎጂ ? ከተሻለሽ ስኬትሽን ሳቅ ደስታሽን አሳዪ ያ ካልሆነ ግን እምባና መከፋት ጉዳትሽን ለራስሽ እና ለፈጣሪሽ ንገሪ። ነገ የተሻለ ይሆንና ዛሬ ላይ እምታሳልፊውን ሁሉ ነበር ብለሽ ታወሪዋለሽ ፤ በነበር ለሚቀር ህይወት እራስሽን ለሽንፈት እና ለውድቀት አሳልፈሽ አትስጪ።" ብለው የአባትነት ለዛ በተሞላበት አንደበታቸው ወደ ራሴ እንድ መለስና ዙሪያዬን እንዳጤን መንገድ ከፍተውልኛል። አንዳንዴ ሰው ባስፈለገን አይዟቹ ባይ ባጣን ጊዜ አለሁ እሚል መካሪ አፅናኝ ወዳጅን እንደማግኘት ምን እደለኝነት አለ። ጋሼ ለኔ በዚህን ሰዓት ከፈጣሪ እንደተላኩ መልዕክ ነው የሆኑኝ ፤ በፊት የነበረኝ ትዕግስተኝነት ጠፍቶ ግልፍተኛ እየሆንኩ በመጣሁበት ጊዜ ነው የደረሱልኝ ፤ እውነት ነው ችሎ ማለፍን እና ንቆ መተውን የመሰለ ምን አለ ? እሱም እኮ መልስ ነው።

ምን አልባት እናቴ የመታችኝ ለነሱ ደግፍ ሳይሆን የኔ እንደዚህ መለወጥ አናዷት ይሆን ? ግራ ገባኝ ግን እናቴ ላይ ቂም ከምይዝ ምክንያቷን ብጠይቃት ቀን ከሌት ከመብሰልሰል እተርፍ ይሆናል። አሁን ተረጋግቻለው ደስም ብሎኛል ምክንያቱም ወደ እራሴ መመለስ ባለብኝ ሰዓት እኚህን የመሰሉ መልካም አባት ስለሰጠኝ ደስ ብሎኛል ፤ ብቻ ለሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን። ሀሳቤን ሰብስቤ ጋሼን አመስግኜ ወደ እራሴ ተመልሼ ነገሮችን ለማስተካከል እንደምሞክር ቃል ገባሁላቸው።

ትንሽ ቆይቼ ለእራታቸው እሚሆን ምግብ ልሰራላቸው ወደ ውስጥ ገባሁኝ ስገባ የቤቱ ሁኔታ ልክ አልነበረም እናም እቃዎቹን አንድም ሳላስቀር ወደ ውጪ አወጣኋቸው። ያው ጋሼ እንድሰራ ባይፈልጉም እኔ ግን ከእሳቸውም የባስኩ ደረቅ ስለሆንኩኝ እሳቸውም እያገዙኝ ቤቱን አፅድቼ አስተካከልኩኝ እና ውስጥ ገብተን እራት እየሰራሁላቸው ብዙ ተጨዋወትን። በመሀልም ከጋሼ ውጪ የመታወቂያ ስማቸው ማን እንደሆነ ጠየቋቸው....

" ጋሼ ትክክለኛ ስሞት ግን ማነው ? ማለቴ ቢነግሩኝ ችግር ከሌለው" አልኳቸው
" ምን ገዶኝ የኔ ልጅ እንግዲ ልጅ ጌታ መሳይ ጋሼ ይለኛል እኔም በዛው ለመድኩ እንጂ ስሜስ አባ ያዕቆብ እባላለሁ ከሀገሬ ሳለው ቤተክርስቲያን ስለነበርኩ አባ ይሉኛል ከስሜ ጋር በአንድ አባ ያዕቆብ ነው" አሉኝ
"ታዲያ እኮ ይሄ ነው ደስ እሚለው እኔ ጋሼ ስሎት ይጨንቀኛል ከዚህ በኋላ አባ ያዕቆብ ነው እምሎት " አልኳቸው....
"ደስ ነው እሚለኝ ልጄዋ" ብለውኝ ወደ ጨዋታችን ተመለስን። ወደ አስራ አንድ ሰዓት ገደማ ለማይለፍ ደወልኩለት እና መጥቶ ወሰደኝ።



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 22

ደራሲ - አብላካት


ወደ ቤት መሄድ እያስጠላኝም ቢሆን እራት ልጋብዝሽ ሲለኝ እምቢ ብዬ ቤቴ አደረሰኝ። ተሰናብቼው ወደ ውስጥ ገባሁኝ....እናቴን በረንዳው ላይ ቁጭ ብላ ሳያት እሮጬ ሄጄ እግሯ ስር ተደፋሁኝ....

"ምነው ልጄ ምን ሆንሽ ?" አለችኝ
"ይቅርታ አድርጊልኝ እናቴ አጥፍቻለው አንቺ መምታትሽ ልክ ነበር"
"ልጄ እኔ እኮ አንቺን መምታት ቀርቶ በሙሉ አይኔ እንኳን ለማየት እምሳሳልሽ እንቁ ልጄ ነሽ...እኔ እማቃት ልጄ ከባለጌ ጋር የምትመላለስ ተራ ሰው አደለችም...አንቺ ለራስሽም ለሰውም ክብር ያለሽ ጨዋ ነሽ....ማንም እየተነሳ የንግግር መርዙን በረጨብሽ ቁጥር መልስ እየሰጠሽ ከሄድሽ ትጎጂብኛለሽ ብዬ እንጂ እኔ ለነሱ ወግኜ አልነበረም። ያም ሆኖ ግን መምታት አልነበረብኝም እኔንም ይቅር በይኝ"
" አይ እናቴ አንቺ ልክ ነሽ በሰዓቱ ይቅርታ ማለት አይጠበቅብሽም" ብዬ ጉልበቷን ሳምኳት...
"በይ አሁን እራት ሰርቻለው እንግባና ላቅርብልሽ" ብላኝ ወደ ውስጥ ገባን....ሰላም ተሰማኝ እድሜ ለአባ ያዕቆብ ....አንዳንዴ ስናጠፋ እሚያርመን መንገድ ሲጠፋን እሚመራን ሰው ከጎናችን መኖሩ አንድም እንዳንወድቅ አንድም እንዳንስት ይረዳናል። እናቴ ያቀረበችልኝን እራት በልቼ ለነገ ለትምህርቴ እሚያስፈልገኝን ነገር ለማዘገጃጀት ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። ነገ እነ ሳባን ሳያቸው ምን ሊሰማኝ እንደ ሚችል ሳስብ ግን ውስጤ ተረበሸ....ግን ደግሞ እነሱ የራሳቸውን ውሳኔ ከወሰኑ እኔም ነገሮችን ችላ ብዬ ማለፍ እንዳለብኝ አባ ያዕቆብ ነግረውኛል። እቃዎቼን እያስተካከልኩኝ ስልኬ ጠራ ይስሐቅ ነበር..... ከሁሉም ይበልጥ በእሱ ነው የተናደድኩት ከማንም በላይ አስተዋይ እና ለነገሮች እማይቸኩል ነው ብዬ እማስበው እሱን ነበር ዛሬ ግን ሊሰማኝ እንኳን ፍቃደኛ አልነበረም። አንዳንዴ ሰዎች ባሰብንበት አይውሉም.....በተቃራኒው ለሳቢ ይወግናል ብዬ እማስበው አቤል ከእኔ ጎን ነበር። በእርግጥ ሁላችንም እርስ በእርስ ያለን ፍቅርም ክብርም እኩል ነው.... ማንም ማንንም አያስበልጥም ቃላችንም ይሄ ነበር ነገር ግን ዛሬ.....ብቻ ይሁን እስቲ ሁሉም እሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው። እቃዬን አስተካክዬ ስጨርስ ለማይለፍ ደወልኩለት...ምን ልለው እንደሆነ ግን አላውቅም ብቻ ግን ውስጤ ደውዪለት የሚል ስሜት ስለተሰማኝ ነው የደወልኩት።

"ሰላም አመሸሽ ቃልዬ ?"
"ይመስገን። እንዴት አመሸህ ?"
"ደህና ነኝ አልተኛሽም እንዴ ?"
"አይ እቃ እያስተካከልኩኝ ነበር። ለቀኑ ላመሰግንህ ፈልጌ ነው የደወልኩት ከረበሽኩ ይቅርታ"
"አይ አልረበሽኝም እንደውም ድምፅሽን ስለ ሰማሁኝ ደስ ብሎኛል። ምስጋናም አያስፈልግም"
"እሺ በቃ ይሄንን ለማለት ነበር ጠዋት ስለምነሳ ልተኛ ሰላም እደር"
"እንዳልሽ ሰላም እደሪልኝ እወድሻለው" ....የሆነ ነገር ልቤ ላይ ተሰማኝ ደስ አለኝ
"እኔም እወደሀለው ቻው" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት። ለምን እየፈራሁት እንደሆነ ባላውቅም ግን መውደዴን አልጠራጠርም። ላጣው አልፈልግም ከእሱ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል ሌላ አለም ውስጥ እንዳለው አድርጌ ነው እምቆጥረው። መልካም ሰው ነው ንፁህ ልብ አለው ፤ የአብዛኛው ሴት ምርጫ ነው። እወደዋለው አዎ የኔ እንዲሆን እፈልጋለው ምናልባትም ማለት ካለብኝ አፈቅረዋለው ግን ደግሞ እንዳላጣው እፈራለው...... ብቻ እስቲ አሁንም ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ያውቃል። በጠዋት ለመነሳት ብዬ ተኛሁኝ። ሊነጋጋ ሲል እንደመባነን አልኩና ከእንቅልፌ ነቃሁኝ በመስኮት በኩል ጀምበሯን እያየሁ እራሴን ለማነቃቃት ሞከርኩኝ ልብሴን ለባብሼ ከክፍሌ ስወጣ....ሳሙኤል ፊት ለፊት ቆሟል.... በውስጤ በቸር አውለኝ አልኩኝ። ላልፈው ስል እጄን እንደመያዝ አለ....ወደ ኋላ ሸሸት እያልኩኝ....

"ምነው ?" አልኩት
"ብር ፈልጌ ነበር" ...አለኝ። አለማፈሩ ገርሞኝ ትክ ብዬ አየሁት
"እና እኔ ጋር አስቀምጠሀል እንዴ ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ ?"
"ለማዘር አንቺ ብር እንደምትሰጫት አውቃለው ስለዚህ ቢኖርሽ ነው እና ለኔም እንድትሰጪኝ ነበር አታስቢ እሚመለስ ነው" .... የአንዳንድ ሰው አይናውጣነት ግን ለከት የለውም የታንሽ ታናሹ ሆኜ ከእኔ ብር ሲጠይቅ ከዛም አልፎ እኔን ለመስደብ ላይ ታች እሚል ልጅ ዛሬ ሲቸግረው እኔ ጋር መምጣቱ ያስገርማል ኧረ ያበሳጫል...
"እኔ ምንም ብር የለኝም። ይቅርታ እረፍዶብኛል" ብዬው ወጣሁኝ.....የግቢው ብር ጋር ስደርስ...
"ኧረ እንደዚህ ነው ያገናኘናል ጠብቂ" አለኝ.... አሁን ከሚያደርገኝ የከፋ ምን ሊያደርግ ፈለገ። ምንም መልስ ሳልሰጠው ከግቢ ወጣሁኝ..... አንዳንድ ሰዎች አስፈላጊነታችን እሚታያቸው ቀን ሲጎድልባቸው ነው። ለስራ አለቃዬ ክላስ ከመግባቴ በፊት መደወል እንዳለብኝ ትዝ ሲለኝ ደወልኩለት....

"ሰላም አደርክ ስዩም ?"
"ደህና ነኝ። እንዴት አደርሽ ?"
"ፈጣሪ ይመስገን። ይቅርታ ስዩም ቀድሜ መንገር ነበረብኝ ግን እኔም ትላንት ነው ያወኩት ዛሬ ትምህርት እጀምራለው እና ስራውን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ልጠይቅህ ነበር"
"አታስቢ አቶ ማይለፍ ትላንትና አሳውቆኛል። እናም ስራሽን ከትምህርት እንደወጣሽ መተሽ መስራት ትችያለሽ።" አለኝ......
"እእ እሺ ስዩም አመሰግናለሁ። መልካም ቀን" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት። ማይለፍ ለኔ ብሎ እሚያደርግልኝ ነገር ሁሉ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው...ባዘንኩኝ ቁጥር ከጎኔ አይጠፋም ከማንም በፊት ለምፈልገው ነገር ደራሽ ሆኖኛል። ምን ላድርግ በፍቅር ልክሰው ሲገባ እኔ ግን በችግር አረንቋ ተከብቤ ጊዜ እንኳን ሰጥቼ ደስተኛ አላደረኩትም እያልኩኝ ከእራሴ እየተሟገትኩ ስሄድ አስፓልቱ ዳር ጋር መኪናውን አየሁት..... እሮጬ ስሄድ መኪናው ውስጥ አልነበረም ተበሳጭቼ ልመለስ ስል ከኋላ መቶ አቀፈኝ እና በጆሮዬ "አፈቅርሻለሁ" አለኝ.... "እኔም አፈቅርሀለው" ብዬ ተጠመጠምኩበት..... ደስታ ተሰማኝ.....እፎይታ .... የመኪናውን በር ከፍቶልኝ ገብቼ ትምህርት ቤት አደረሰኝ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ትዝታዎችን ያሳለፍኩበት.....ወደ እረፍት ከምውጣታችን በፊት ከግጓደኞቼ ጋር ደስተኛም ነበርን በዛውም ልክ ብዙ ውጣውረዶችን አሳልፈናል ግን ሁሉንም አብረን ነው የተወጣናቸው። ዛሬ ግን ብቻዬን ነው ያለሁት....ግቢ ውስጥ ሁሉም በእኛ ጓደኝነት ይቀናል... ከተማሪ እስከ አስተማሪ ስል እኛ እማያወራ የለም....ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲሄዱ ፍላጎቱ አልነበረኝም.....ግን ደግሞ ሁሉም እሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው መቀበል ባልፈልግም መሆኑ እማይቀር ነው። ወደ ክላስ ስገባ እነሳቢ የበፊት ቦታችን ላይ ተደርድረዋል። ምንም ሳልሰራ እንደጥፋተኛ ሰው በሙሉ አይኔ ለማየት ፈራኋቸው አጠገቤ ያለው ወንበር ሄጄ ተቀመጥኩኝ ።

አንዳንዴ ሳንሳሳት ሳናጠፋ እኛ ትክክል ሆነን ሳለ ሰዎች እንደጥፋጠኛ ሲቆጥሩን አምነን እንቀበላለን። በውስጣችን እውነት እያለ ስህተት እንዳልሰራን እያነው ወቃሾቻችን ፊት ስንሆን ለምን የጥፋተኝነት ስሜት እንደሚሰማን አይገባኝም። ከአቤል በስተቀር ማናቸውም ሊያናግሩኝ አልመጡም....



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል 100❤️ ሲደርስ ይለቀቃል እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
ሆዴን ጅብ በበላው፣
አንጀቴን ባራሰው፤
የማያገኘውን እንዴት ይመኛል ሰው?

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

💚ሰናይ💛ግዜ
2024/11/13 20:24:07
Back to Top
HTML Embed Code: