Telegram Web
"ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል"
ገላ6፥....
"ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል"
ገላ6፥....
ታግዷል

በአዲስአበባ ፤ አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ ታገዱ::

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት የተለያዩ መመሪያዎች መተላለፋቸው ተገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ

* የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ
* ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት
* የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት
* የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት

* ለሓጢአት ሥርየት
* ለነፍስ ሕይወት
* ለሃይማኖት ጽንዐትና
* ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው ብሏል ሀገረ ስብከቱ።

በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

Via አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለ129ኛው የአድዋ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ

ጠላት ተሸንፏልና የጠላትም ኃይል በጊዮርጊስ ተሰዷልና ዛሬ ነፃ የወጣን ሁላችን በደስታና በሐሴት ቃል በዓልን
እናድርግ።

የካቲት 23 የሰማዕቱን ዓመታዊ ክብረ በዓል በአስኮ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በጋራ እናክብር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ እሁድ በ28/07/2017 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ እናሳስባለን ።

የሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
አመ ፳፯ዑ ለመጋቢት መድሀኒአለም  ስርአት ማህሌት
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ በመስቀሉ አተበነ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ በመስቀሉ ቤዘወነ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
መድኃኔዓለም ወልድኪ ሥጋ ዚአኪ ዘለብሰ፤ ሐፃውንተ መስቀል ተአገሰ፤ በዓውደ ጲላጦስ ተወቅሰ አማዑትኪ ተካወሰ።

መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሚተ፤ መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤ መድኃኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአነ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ።

ዚቅ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤ ወአስተዩኒ ብሂዓ ለጽምዕየ፤ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ወአቅደምከ ጸግዎ መንፈሰከ ቅዱሰ ለሥርየተ ኃጢዓት፤ አክሊል ዘሦክ አስተቀጸሉከ ዘበሰማያት ለነ አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ፤ ሰቀሉከ ዲበ ዕፅ፤ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት አስተዩከ፤ ከመ ለነ ታስትየነ ወይነ ትፍሥሕት ወሐሤት፤ ረገዙከ በኲናት ወተርኅወ ገቦከ፤ ከመ ለነ ተሀበነ ሥጋከ ቅዱሰ ወደምከ ክቡረ፤ ከመ ትጸግወነ።

ወረብ
ወአቅደምከ 'ጸግዎ'/፪/ መንፈሰከ/፪/
አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ በሰማያት አክሊለ ጽድቅ/፪/

መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጒርዔከ ክቡር ወልዑል፤ ወለክሣድከ ዓዲ ዘሰሐብዎ በሐብል፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፤ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል፤ እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ቃል።

ወረብ
'በለኒ መሐርኩከ'/፪/ በእንተ ማርያም ድንግል/፪/
እስም ኄር አልቦ እንበሌከ ዘይሜሕር ቃል መድኃኔዓለም/፪/

ዚቅ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ፤ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፤ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ፤ ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ፤ ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ።

ወረብ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ/፪/
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ/፪/

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
በአማን ቃልከ አዳም፤ ዘተሰቀልከ በእንተ ኃጥዓን ከመ ትቤዙ ነፍሰ ጻድቃን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ በአማን ቃልከ አዳም።

መልክአ መድኃኔዓለም

ሰላም ለልብከ እግዚአብሔር ናዝራዊ፤ ነቢይ ወመንፈሳዊ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ህፃን ወአረጋዊ፤ እፎ ቀሰፉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ፤ በዓውደ ጲላጦስ መስፍን ከመ ገብር ዓላዊ።

ዚቅ
ወጸሐፈ  ጲላጦስ መጽሐፈ፤ ወይብል መጽሐፉ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ።

ወረብ
ወጸሐፈ መጽሐፈ ጲላጦስ ወይብል መጽሐፉ ጲላጦስ ዘጸሐፈ/፪/
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ/፪/

መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጸዓተ ነፍስከ አመ ዲበ መስቀል ቆመ፤ ወለበድነ ሥጋከ ምዑዝ እንተ ያጥዒ ሕሙመ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከመ ትቤዙ ዓለመ፤ አሜሃ እግዚእየ ፀሐይ ጸልመ፤ ወወርኅኒ ተመሰለ ደመ።

ዚቅ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሀውከ ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ።

ወረብ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሐውከ/፪/
ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ/፪/

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ሶበ ሰቀልዎ ሶበ ሰቀልዎ፤ ሶበ ሰቀልዎ ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ ዘመዓዛሁ ጽጌረዳ፤ ወለመቃብሪከ ዘኮነ ለኢየሩሳሌም በዓውዳ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅንዓተ ሰይጣን ዘይሁዳ፤ ሞተ ወተቀብረ በመቃብረ ሐዲስ እንግዳ፤ ኀበ ኢተቀብሩ ለሔዋን ውሉዳ።

ዚቅ
አውረድዎ እምዕፅ ዕደው ጻድቃን፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ ወልብሰ ገርዜን ንጹሕ ለግንዘተ ሥጋሁ።

ወረብ
'አውረድዎ'/፫/ እምዕፅ/፬/
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ/፪/

ምልጣን፦
መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል፤ ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት፤ ወለፈያታዊ ኃረዮ በቅጽበት፤ መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል።

አመላለስ፦
መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤
ዝንቱ ውእቱ መስቀል

ወረብ፦
ሃሌሉያ መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገሶሙ/፪
ዝንቱ ውእቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት/፪

እስመ ለዓለም
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ፤ ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሃብኮሙ ትዕምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት፤ ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።

ወረብ፦
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት/ ፪/
በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ/፪/
በዓለ ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን መጋቢት 27
እንኳን አደረሰን::
መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️ pinned «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የተከበራችሁ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ እሁድ በ28/07/2017 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ እናሳስባለን ። የሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤት»
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ ዛሬ እሁድ በ28/07/2017 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ እናሳስባለን ።

                                      የሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤት
2025/04/08 10:53:03
Back to Top
HTML Embed Code: