Forwarded from 🐾M̸a̸i̸n̸o̸o̸🦅
Selam selam🖐🖐
እነሆ የምርጥ ምርጥ channal ተከፈተ👍
👉የዚህ channel አላማው
👉 የ ስዕሎች ልምድ መለዋወጥ 👨👧👦🌇
👉ስዕሎችን መገምገም🌉
👉የ ስዕሎች ውድድር 🏞🏞🏞
👉የ ስዕል ቀለማት...🎇🎇🎇
እና ሌሎችም ይዘቶች ያሉት ምርጥ channel ነው። 🙏🙏🙏
@hb_art_27👈
@hb_art_27👈
@hb_art_27👈
ለበለጠ መረጃ @huuuund ያናግሩኝ
ጥበብ የምታደንቁ ከሆነ
#share #share #share
እነሆ የምርጥ ምርጥ channal ተከፈተ👍
👉የዚህ channel አላማው
👉 የ ስዕሎች ልምድ መለዋወጥ 👨👧👦🌇
👉ስዕሎችን መገምገም🌉
👉የ ስዕሎች ውድድር 🏞🏞🏞
👉የ ስዕል ቀለማት...🎇🎇🎇
እና ሌሎችም ይዘቶች ያሉት ምርጥ channel ነው። 🙏🙏🙏
@hb_art_27👈
@hb_art_27👈
@hb_art_27👈
ለበለጠ መረጃ @huuuund ያናግሩኝ
ጥበብ የምታደንቁ ከሆነ
#share #share #share
👍2👌1💯1
💯4👍1🥰1
✅ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው።
✅ በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሩቅ ልውሰዳት!!" ነው።
በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት።
✅ ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን ሁሉም አገለላት። እነማዬም እሷን ቡና መጥራት አቆሙ። ባሏም "ራሷን ብታጠፋ የለሁበትም" ለማለት ነው መሰል እየዞረ ስላለባት ችግር ሲያወራ ነው የሚውለው።
<<ምንድን ነው እንዲህ አይነት ቅብጠት? ማንም ሴት ትዳሯ በምትፈልገው መንገድ ላይሔድላት ይችላል! ራስን ለማጥፋት መሞከር ግን ትኩረት ፈላጊነት ነው።>> ትላለች እማዬ ስለሷ ሲነሳ። እንዳለ ቡና ጠጭው በስምምነት ራሱን ይነቀንቃል።
እኔጋ ስለምንቀራረብ እንድታብራራልኝ የማላደርገው ጥረት የለም። <<ለምንድን ነው ግን ሁሉም የሚጠሉሽ?>> <<ምንድን ነው እንዲህ ያስከፋሽ?>> እላታለሁ።
የሷ መልስ ሁሌም አንድ ነው።
<<ወፍ ረግማኝ!>> ትለኛለች እየሳቀች።
መመለስ እንዳልፈለገች ይገባኝና እተወዋለሁ።
የመጣች ሰሞን ከሷ የያዘኝ የአይን ፍቅር በሽተኛ አድርጎኝ ነበር። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ትክክለኛ የዘፈን ግጥሞች ላይ ያለው ፍቅር ነበር የያዘኝ። ፍቅር አያስበላ አያስጠጣ የሚለው ያፈቀርከውን ሰው ማግኘት እንደማትችል እያወቅክ ስታፈቅረው ሳይሆን አይቀርም።
በመጨረሻ ግን ተሸነፍኩ። ቀጥ ብዬ ቤቷ ገባሁ። በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ለወፎች ጥሬ እየመገበች ነበር። ደንግጣ ዙራ አየችኝ። ተጠግቼ ሰላም እንኳን ሳልላት <<ዘርዬ እወድሻለሁ>> አልኳት። ቀልዴን መስሏት ነበር። እንባዬን ስታይ ከሳቋ ላይ ግርምት ጨመረችበት።
<<ና እስኪ ተቀመጥ የኔ ቆንጆ!>> አለችኝ!
እንባዬን እየጠረግኩ ተቀመጥኩ።
<<ስንት አመትህ ነው?>>
<<አስራ ስድስት>>
<<ታውቃለሀ? እኔ ራሱኮ በጣም ነው የምወድህ!>>
<<እውነት?>>
<<የምሬን ነው። ይሔ ልጅ ልጄ በሆነ ብዬ እመኝ ነበር።>>
ኧረ ቅስሜን!
<<ትምህርት እንደወጣህ የቤት ስራ ምናምን ካለብህ እኔጋ እየመጣህ ስራ እሺ! ጓደኛ ትሆነኛለህ።>>
ከዛ ጊዜ ጀምሮ ጓደኞቼን ዞር ብዬ አይቻቸው አላውቅም። የነሱ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደወንድሜ ነው የማይህ" አለችኝ ነው። የኔ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደልጄ ነው የማይህ" አለችኝ...እኩያቸውን ይፈልጉ። ትምህርት ቤት ራሱ የምሔደው የቤት ስራ ለመቀበል ነው። እንደመጣሁ እነማዬ ሳያዩኝ ተደብቄ ዘሪቱጋ እሔዳለሁ። ስራ ጨርሳ ወደ በረንዳው ስትመጣ ከአጠገቧ ሂጄ እቀመጣለሁ። ባሏ እንደልጅ ነው የሚያዬኝ መሰለኝ ሲያዘኝ ራሱ ሰላም ሳይለኝ ነው። እኔም ለነገሩ ለሱ ሰላምታ ግድ ኑሮኝ አያውቅም።
<<እንዴት ግን ይሔን ሰው አገባሽው?>> አልኳት የሆነ ቀን።
ምንም ብጠይቃት አትደነግጥም። ርጋታዋ ሳይናድ ትመልስልኛለች።
<<የህልም ሽንት ታውቃለህ?>> አለችኝ።
በቃ እኔ ለሷ ሁሌም ህፃን ነኝ።
<<ኧረ አላውቅም>> አልኩ አልጋ ላይ ሸንቼ ማወቄን እንዳታውቅብኝ።
<<ሽንት ቤት ሂደህ በስነስርዓት ልብስህን አውልቀህ ትሸናለህ...ስትነቃ ግን አልጋህ ላይ ነው የሸናኸው።>>
<<እእእእ>> አልኩ!
<<እንደዛ ነው የኔ ፍቅር። በኔ ቤት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ መርጨ ጨርሻለሁ። ስባንን ያልሆነ ቦታ ላይ ነው ልቤን የጣልኩት>>
አሁን አሁን በአጠገቤ ሲያልፍ በሆዴ "አንተ የህልም ሽንት" እለውና ለራሴ እስቃለሁ።
ዘርዬ እንደነገረችኝ ከሆነ አዲሳባ እያሉ ለመፅሔቶች አንዳንድ ፅሁፎችን ትሰራ ነበር። ሰው መስሏት ይሔን የባንክ ሰራተኛ አገባችው። ከተራ የደንበኛ አስተናጋጅነት አንስተው ማናጀር አደረጉትና ወደዚህ አዛወሩት። የሱ ኑሮ ቀጠለ። የሷ እንደነገሩ ሁኖ ቀረ። እናት መሆን አቃታት። ሚስት መሆን አጎበጣት። እነማዬ ሌላ ህልም ኑሯቸው አያውቅምና ፍላጎቷን እንደቅንጦት ቢያዩት አይገርመኝም።
አንድ ቀን ማታ ዘርዬ ባልተዘጋጀሁበት ስለዛች ወፍ ታወራኝ ጀመር።
<<ከአስራ ስድስት አመት በፊት ባንተ እድሜ እያለሁ ይመስለኛል።>> አለች በድንገት። ነቃ አልኩ። <<እንዲሁ በጨዋታ ዲንጋይ ስወረውር ያንደኛዋን ወፍ ክንፍ ሰበርኩት። በኢላማዬ ደስ ብሎኝ የወደቀችውን ሒጄ ሳያት መብረር አትችልም። አሳዘነችኝ። ቤት ወሰድኳት። ዶሮዎቼ ጋር ቀላቅዬ ጥሬ እያበላሁ እስክትሞት ድረስ አኖርኳት።>>
<<ታዲያ ምን አጠፋሽና ትረግምሻለች? የተሳሳትሽውን አስተካክለሻልኮ!>> አልኩ በጭንቀት።
<<ሁለት ጊዜ ነው የገደልኳት። ክንፏን መስበሬ ሳያንስ የክንፏን መሰበር እንደ ችግር በማያዩ ዶሮዎች መሀል እንድትኖር አደረኳት። ሲመስለኝ እሷ ወፍ ረግማኛለች።>>
ከጃኬቷ ኪስ ወረቀት አውጥታ ሰጠችኝ። ላነበው ስል <<ነገ ማታ እንድታነበው ነው የምፈልገው>> አለችኝ። ነገ ተነስታ ልትሰወር ነው ብዬ አልጠረጠርኩም። እኔ በተኛሁበት የኔ ወፍ ዘርዬ ሰባራ ክንፏን እየጎተተች ርቃ ሔደች።
ጧት ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ የግቢያቸው በር ተከፍቶ ፊትለፊት ባዶ ቤታቸው ከመንገድ ላይ ይታያል። ተንደርድሬ ስገባ ሁለት ሰዎች እየዞሩ እያዩ ነው። ለቀው መሔዳቸውን አረዱኝ። መከዳት ተሰማኝ። ትምህርት ቀርቼ ሳለቅስ ዋልኩ።
በሶስት ቀን ውስጥ አንድ ሰሞን ወደነበርኩበት በሽታ ተመለስኩ። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ከመሔዷ በፊት ወረቀት ሰጥታኝ እንደነበር ያስታወስኩት ራሱ መምሬ ሶስት ቀን በፀበል ካጠመቁኝ ቡኃላ ነው። መሔዷን እያሰብኩ ያልረሳሁት ምን አለ?
አልጠበኩም ነበር! ገልጨ ሳነበው ከህመሜ ተፈወስኩ። መምሬ በመዳኔ እማዬ ስታመሰግናቸው <<ሶስት ቀን መቆዬቱ ራሱ ገርሞኛል>> ሲሉ ጉራቸውን ነፉ።
ዛሬ በዘሪቱ እድሜ ሁኜም ያ ደብዳቤ ከኪሴ አይጠፋም። የስሜት መዋዠቅ ሲገጥመኝ አውጥቼ አነበዋለሁ።
<<ቻው ያላልኩህ አንተን ቻው ማለት ስለከበደኝ ነው። ደስ ትለኛለህኮ። በአንተ ውስጥ ራሴን አያለሁ። አስራ አምስት አመት ፈጥኜ ባልወለድ የማገባው አንተን ነበር። አምላኬን የምጠይቀው አንድ ነገር እኔ ያጣሁትን ሁሉ ላንተ እንዲሰጥህ ነው። ያልኖርኩትን ኑርልኝ። ስለሁሉም አመሰግንሀለሁ። ያላንተ አላልፈውም ነበር ይሔን ጊዜ።>> ይላል።
ዛሬ ላይ የመፅሔት አዘጋጅ ነኝ እፅፋለሁ ፁህፍ አዘጋጅ ነኝ ። ደስተኛ ሰው ነኝ። ጓደኞቼ <<ለምንድን ነው ሰው ሁሉ ያለ ምክኒያት የሚወድህ?>> <<ለምንድን ነው የነካኸው ሁሉ የሚሳካልህ?>> ይሉኛል።
የኔ መልስ ሁሌም አንድ ነው።
<<ወፍ መርቃኝ!>> እላቸዋለሁ እየሳቅኩ። ማብራራት እንዳልፈለኩ ይሰማቸውና ይተውኛል።

👏4😢2😭1
እየኖሩ መሞት🤍🦋 pinned «በዓል አንወድም ፡ ፡ ቢጫ መሬት ህይወት ግን እንደሬት አበባ ሙሉ ሜዳ ህይወት ግን እንግዳ ኩበት እና ውበት ህይወት ሀዘን ሽበት "እንኳን አደረሰን" ተባብለን የሆነ የሚከፋን ነገር አለን ከውስጣችን እንደታመቀ አልቅሰነው እንዳላለቀ ወልደነው እንዳልተመረቀ ብቻ በዓል አልወድም የሚስብለን አንድ ነገር አለን:: መሬቱን ቢጫ ወርሶት…»
Get in lyrics music your choice
https://www.tgoop.com/LyricsAb
https://www.tgoop.com/LyricsAb
Telegram
🎼Ab lyrics🎧
Get in lyrics music your choice
Michael Belayneh - ትመጪ እንደሁ _ Temechi endew Track 9 (Official Audio)
Michael Belayneh
# ሚካኤል_በላይነህ
# ትመጪ_እንደሁ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ፣
ሌት ተቀን ናፋቂ
ሰርክ የማይታክተኝ አለሁሽ ጠባቂ
ፍቅር ተደግፌ፣ ቃል ኪዳን ታቅፌ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ፣ ክፍት ነው ደጃፌ
አትቀርም እላለሁ፣ በመላ በጥበብ
ምን ቀን እየገፋ፣ እድሜዬን ብታለብ
ቆፈን ቢገርፈኝም፣ ጥበቃዬ በዝቶ
እኔ ግን እዛው ነኝ፣ አላጐደልኩ ከቶ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ
አለሁ እኔ፡፡ ሳላጐድል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ አለሁ እኔ፣ በፍቅር አለሁኝ
እንዳለሁ
በናፍቆትሽ እሳት፣ ነድጄ ሳልከስም
ባይንሽ በጠረንሽ፣ መልሼ እንዳገግም
ሳዜም እኖራለሁ፣ ፀሎት ስደጋግም
ካለሁበት ድረስ፣ እግርሽ እንዲረዝም
ልምጣ ያልሽ እንደሆን፣ ቀና ነው ጎዳናው
ልቤ ተመላልሶ፣ ደልድሎታልና
ምኞት የማይደክመው፣ ልቤ ልበ ብርቱ
ትዝታም አይደለ፣ ተስፋ ነው ቅኝቱ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ
አለሁ እኔ፡፡ ሳላጐድል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ አለሁ እኔ፣ በፍቅር አለሁኝ
እንዳለሁ......🔥 ➠@LyricsAb
@LyricsAb
# ትመጪ_እንደሁ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ፣
ሌት ተቀን ናፋቂ
ሰርክ የማይታክተኝ አለሁሽ ጠባቂ
ፍቅር ተደግፌ፣ ቃል ኪዳን ታቅፌ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ፣ ክፍት ነው ደጃፌ
አትቀርም እላለሁ፣ በመላ በጥበብ
ምን ቀን እየገፋ፣ እድሜዬን ብታለብ
ቆፈን ቢገርፈኝም፣ ጥበቃዬ በዝቶ
እኔ ግን እዛው ነኝ፣ አላጐደልኩ ከቶ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ
አለሁ እኔ፡፡ ሳላጐድል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ አለሁ እኔ፣ በፍቅር አለሁኝ
እንዳለሁ
በናፍቆትሽ እሳት፣ ነድጄ ሳልከስም
ባይንሽ በጠረንሽ፣ መልሼ እንዳገግም
ሳዜም እኖራለሁ፣ ፀሎት ስደጋግም
ካለሁበት ድረስ፣ እግርሽ እንዲረዝም
ልምጣ ያልሽ እንደሆን፣ ቀና ነው ጎዳናው
ልቤ ተመላልሶ፣ ደልድሎታልና
ምኞት የማይደክመው፣ ልቤ ልበ ብርቱ
ትዝታም አይደለ፣ ተስፋ ነው ቅኝቱ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ
አለሁ እኔ፡፡ ሳላጐድል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ - ትመጪ እንደሁ አለሁ እኔ፣ በፍቅር አለሁኝ
እንዳለሁ......🔥 ➠@LyricsAb
@LyricsAb