tgoop.com/MedinaTube/915
Last Update:
ዳኖች ሲወደሱ ራህመት ይውረድ
የነቢ ዘይኔው ሙሂቡ ጌታው ሚስባህ ዳንዩል አወልን ሲመድሁ እንዲህ አሉ
"
የዳናው ሙሽራ አይደለም እንደሰው
እኔም ለበረካው ጥቂት ላወድሰው
ዲኑ አሮጌ ነበር እሱነው ያደሰው
ቢስሚላሂ ብሎ የጁ ላይ ቀደሰው
የነፍስያን ቁንዲ ባውራድ ያፈረሰው
ሰላም አለይኩም ያ አሩሰ ዳና
ሺሊላህ ሰይዲ ዱስቱር ሰይዲና
ጦሃራቸው የሩህ ሰላሙ ' 100 አመት ያሳለፈው የአውራድ ዝመራ ለጆሮ ሲገራ ድካም እየተረሳ ቀልብ ይነወራል - ዱንያ እየተናቀች አኺራ ይታወሳል' ቀልብ አየተቆጨ ለንሰሃ ይነሳል .....የአላህ ዚክር ከእርስዎ የስሙት መታደላቸው
ከአይናቸው ከራቁ በኋላ ናፍቆት ሰፈረባቸውና እንዲህ ቀጠሉት
"እኔም እንደገና ልቤን አላወሰው
አብሮኝ እንዳልኖርኩት እንዳላየሁት ሰው
ተቅዋና ማዕሪፋን ሁሉን እሚያለብሰው
ሸቃዋን ለማበስ ፊቱን እሚያብሰው*
ቀልቤ ሞቶ ነበር እሱ ቀሰቀሰው
* የዳንዪ መጅሊስ ላይ እድለቢስነት የለም አሉ ' የጦይባው ሙስጦፋ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ሲሾሙኣቸው " በል እንግዲህ እርዝ አልብስ' በኑር ቀልስ 'ሸቃዋ'ብስ ' ድሃን አንግስ 'ኩሩን አፍልስ " ብለው ነው
ቀልቡ የጨለመችዋን ሲያዩት ግንባርዎን በነጭ ጨርቅ እብስ ያደርጋሉ ' የነፍስያን ጭቃ እንደላበት ጠርገው ፈገግ እያሉ አይንዎን ይሰብራሉ ' የታበሰለት ሰው የኢማን ሸማ ደራርቦ ይነሳ ነበር ' እንዲህ ነው ከራማ ማለት።
ሓድራ ላይ እዝነት ያሸንፍዎታል እንባዎ ቅርብ ነው ' የነቢ መድህ ሊቃእ ላይ ማንንም ተቆጥተው አያዉቁም ይባላል ' የመስጂድ ወእዝ ላይ ደግሞ ሌላ ሆነው አንበሳ መስለው ' የሒክማ ጅረት ያፈልቃሉ' ለሙሪድ ሲሆን ይበረታሉ ' አጅነብይ ሴት የማየትን ከባድነት ሲያወሩ ተንጫሮ እራሱን ስቶ የሚወድቅ ታይቱኣል ' 'ያንን ወቅት ጌቶቹን ቀና ብሎ እሚያይ አለን? ይላሉ ዳና ላይ
የሸምሲከ ጣሊዑ ቀላሚ ' ጎሮችም እንዲህ አወደሱኣቸው
'የዳናው ጀማሪ ፊተኛው ጠሩሁ
በብዙ መንዙማ እጅህ ሸለሙሁ
የሐበሻ ሓድራ መዝጊያ አረጉሁ
ባላህ ስም ለጥቆ አንቱን መረጡሁ
እጅየን ያዙኝ አሉህ ቀርበው እያዩሁ
አላሁመ ሶሊ አላ ሙሐመዴ
እንዴት ነሁ ምነው ባየነሁ
እኛም ባናየዎት ያዩት ነገሩን
ጥቂት ወሬም አደል በብዙ ሰማን
ከራማዎ ቀስቃሽ ቀልቡ የሞተን*
እንዳንቱ ሙዕጂዛ የረዱበት ዲን
በጭፍራ በአውራድ የማረኩልሁ እንዴት ነሁ......
* "ከራማ ማለት የሞተ ቀልብን ማስነሳት እንጂ በአየር መብረር እና ወሃን መራመድ አይደለም' ይኸኘውማ ምኑ ይደንቃል" ብለው የሱፊያዎቹን የሱሉክ ቃኖና ያስቀመጡት ዳንዩል አወል ቀደሰላሁ ሲረሁል አዚይዝ
ከበርካቸው ይደረሰን
ሰላም ይድረሶት ሆዴ
@medinatube
BY Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Share with your friend now:
tgoop.com/MedinaTube/915