Telegram Web
ምንኛ ያማረ ቂሷ ተከተሉኝማ.
.
.
.
አብደላህ ቢን ዲናር .ረ.ዐ
.
.
.
እንዲህ ይለናል፦

ከዑመር ቢን አል ኸጣብ ጋር ወደ መካ ወጣን። መንገድ ላይ ከአንድ ተራራ አንድ እረኛ ወረደ። "አንተ ልጅ ሆይ ከነዚህ ፍየሎችህ አንዷን ሽጥልኝ። አሉት-ዑመር።

"እኔ አገልጋይ ነኝ" አለ።

ሊፈትኑት በመፈለገም፦ " ለአሳዳሪህ ተኩላ በላት በለው" አሉት።

"አላህስ?" አላቸው።

ዑመር በልጁ ምላሽ አለቀሱ። ከአሳዳሪው ገዙትና፦ "ይህች ቃልህ በዚህች አለም ከባርነት ነጻ አድርጋሀለች።

በመጭው አለምም ከእሳት ነጻ እንደምታደርግህ ተስፋ አደርጋለሁ።" አሉት።

እኛስ ከእሳት መዳኛ ብለን የሰራነው ምን ስራ ይኖረን ይሁን????
#ሼር_ሼር
@medinatube
የሙዕሚን መሳሪያ

ዘመናችን ከየትኛውም ግዜ እና ሰዓት በላይ ቀላል ምቹ ቢሆንም ከየትኛውም ዘመን በላይ ግን የሰው ልጆች ደም እንደ ወንዝ ዥረት በየቦታው እየፈሰሰ ይገኛል። በተለይም በአላህ አንድነት ጥርት አድርገው ባርነታቸውን ባረጋገጡት ሙዕሚኖች ደግሞ በጣም ባስ እያለ መጥቷል።ነገር ግን በአንፃራዊ ሰላም ላይ ያሉ ሙዕሚኖች  ድቅድቅ ባለ የድሎት ዝንጋቴ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ የህይወት ገጠመኞች ሲታይ ይስተዋላል። ለዚያም ይመስላል አላህ በተለያዩ የዱንያ ህይወት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈተና ውስጥ የሚያስገባን! የሰላምን ትንፋሽ ተነፍገው በጥበት ላሉ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የነሱን ህመም ህመማችን ነው ብለን ከየትኛውም የአጀንዳ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነን ልባችን ተቃጥሎ ዱዓ የማናረግላቸው..ምክንያቱም አላህ የሱን መሳሪያ በግልፅ ነፍጎናል። የሙዕሚን ዋነኛው መሳሪያ እና አስተማማኙ ዱዓ ብቻ ነው። ልባችን ተቃጥሎ ከውስጣችን ዱዓ ስናደርግ የኛም ህይወት ይቀላል።

አላህ ከልባቸው ዱዓ ከሚያደርጉት ባሮች ያድርገን!
@medinatube
Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Photo
የሐቢቢﷺ ሙሒቦች “መዲና” “መዲና” አብዝተው ሲሉና መዲናን ሲናፍቁ ሲያዩ እነሱን ለመኻለፍ ይሆን ኒያችው ለምን እንደሆነ ባይገባኝም መካ እየሄዱ መዲና ሳይዘልቁ የሚመለሱ አንዳንድ ሰዎች አሉ::

እነዚህ ሰዎች እዚሁ ዱንያ ላይ ጀነት ግቡ ሲባሉ እምቢ ያሉ ሰዎች ናቸው:: ሐቢቢﷺ በቤቴና በሚምበሬ መሀል ያለው ቦታ ጀነት ነው ብለዋል::
👈 ما بين بيتي ومنبري روضة من رياض الجنة

የዘንድሮ ሀጅ ወላሂ ዉሀብያ የመጅሊስ ተላላኪ ስንቱን ማያዉቅ ሚስኪን የ ሠይዳችንን ሰ.ዐ.ወ ቀብር ለመዘየር በሚሄዱበት ወቅት ሀጃቹ ይበላሽባችዋል ቀብር መዘየር አይበቃም እያሏቸዉ ስንቱን ይሄ ወርቃማ ዕድል አስመለጡት ወላሂ ከሀጅ ከመጣ ሠዉ ነዉ የሰማሁት

አደለም ሲወደሱ ስማቸዉ ሲጠራ ምቾት ማይሠማቸዉ የ ሰለዋት ስስታሞች,,, እዛ የተከበረ ቦታ ሁነው ለቦታው እንኳ ሀያ ማያደርጉ,,

ሀበሻው እንቁ የሰይዳችን የሀቢባችን የመውላችን ሙአዚን የሆኑት ሰይዲና ቢላል ነብዩ ﷺ ሀገር ከቀየሩ በሁዋላ እሚያዩት ነገር ሁሉ ነብዩን ﷺ እያስታወሰ ሀዘናቸውን አጠናባቸው. ከዚያም ቦታ እርቀው ወደ ሻም በመሄድ ኑሮዋቸውን እዛው መሰረቱ, ሚስትም አግብተው መኖር ጀመሩ ከቆይታ በሁዋላ ነብያችን ﷺ በመናማቸው መጡና ያቢላል ምነው ልትዘይረን አትመጣምን? በማለት ቆጣ ብለው ጠየቋቸው ጠዋት ከ እንቅልፍ ሲነሱም ያዩትን ለባለቤታቸው ነገሯትና ወደ መዲና ጉዞ ተነሱ....
@medinatube
በአንድ ወቅት ሰዎች ኢማሙ ማሊክን ረሂሙሁሏህ💘 "መዲና💚 ከተማ ያን ያህል አመት ሲኖሩ አንድም ቀን ጫማ ተጫምተው አያውቁም ለምን ይሆን? ሲሉ ጠየቋቸው።

ኢማሙ
"ረሱሉሏህ የረገጡትን የመዲና መሬት ከነጫማዬ መርገጥ እንዴት ይቻለኛል?!" ሆነ መልሳቸው።መገን እነሱ!😭🥹

የከውኑ ጀንበር ውዴታቸው ውስጣችን ዘልቆ ሲገባ፣ታላቅነታቸውን ማወቅና መረዳት ስንጀምር በቃ እንዲህ ነው የሚያደርግን።አለቃ ወይም የአገር መሪ ፊት አልያም ዙፋኑ ላይ ከተሰየመ ንጉስ ፊት ከምናሳየው በበለጠና በላቀ መልኩ ከሩሱሉﷺ አጠገብ ስንደርስ በቃ ጀሰዳችን ኩርምት፣ልባችን ኩስምን፣ነፍስያችን ልዝብ ማለቷ አይቀርም! 🥺❤️‍🩹

አዎ ሙሂቦቼ! ስንቱ ሙሒብ መሰላቹ እዚህ ሲደርስ ሐሉ ልውጥውጥ የሚለው...⁉️

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا وقدوتنا وشفيعنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين🌹
💚ኸሚሡኩምአላህ ይወፋቀን🙌
@medinatube
Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Photo
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ

አንቱን ባነሳሳ ሄደ በሽታዬ!

ሰላም ኢብን አቡል ሁቀይቅ ወይም አንዳንዶች እንደሚጠሩት አቡ ራፊዕ ነቢን ለመግደል የሚቋምጥ፣ በእርሳቸው ላይ የተነሳን ሁሉ የሚደግፍና ባገኘው አጋጣሚ ይተናኮላቸው የነበረ ቀንደኛ ጠላታቸው ነበር። የነቢ ባልደረቦች በዚህ ድርጊቱ ይበግናሉ። ምንም ማድረግ ባለመቻላቸውም ይቆጫሉ። አንድ ጊዜ ታድያ ጮማ እድል አገኙ። የአቡ ራፊዕ ጎሳ አባላት በርሱ ትዕዛዝ ከነርሱ የሆነን የበኒ ኸዝረጅ ሰው ገደሉ። አጋጣሚውን ሲጠባበቁ የከረሙት የረሱለሏህ ባልደረቦች እሱን ለመግደል ይፈቅዱላቸው ዘንድ ነቢን ወተወቱ። ፈቃድ ሰጧቸው። አንሷሮች ዓብዱላህ ኢብን ዓቲክን መሪ አድርገው ተነሱ። በብዙ አጀብ የሚጠበቅ ነጋዴና ባላባት ነው። ሆኖም በነቢ ፎክሮ ፍርሃት የለምና አመሻሹ ላይ በሂጃዝ መንደር ወደሚገኘው መናገሻው አመሩ። ወቅቱ እረኞች ያሰማሯቸውን ከብቶች ወደ በረቶቻቸው የሚመልሱበት ነበር። ዓብዱላህ ኢብን ዓቲክ ጓደኞቹን ውጭ እንዲቆዩ አደረገና ፊቱን ተከናንቦ የቤተ መንግስቱን ቅጥር ተጠጋ። የሚፀዳዳ ሰው መስሎም አጥር ስር ተቀመጠና ከእረኞቹ ጋር ተመሳስሎ ገብቶ በረት ውስጥ ተደበቀ። ጠባቂው ሁሉም ሰው መግባቱን ካረጋገጠ በኋላ የጊቢውን በር ዘግቶ ቁልፉን አንድ ጥግ ላይ አንጠልጥሎ ገባ። በአቡ ራፊዕ ክፍል የምሽት ጨዋታው ደርቷል። አቡ ራፊዕ እንደለመደው ስንኝ እየገጣጠመ ነቢን ይዘልፋል። ሰዓቱ እየገፋ ሲሄድ እንግዶቹ አንድ በአንድ መውጣት ጀመሩ። ብቻውን መቅረቱን ያስተዋለው ዓብዱላህ ቁልፉን ጠባቂው ካንጠለጠለበት አንስቶ በሮቹን ሁሉ በጥንቃቄ እያለፈና ከውስጥ እየቆለፈ አቡ ራፊዕ ያለበት ክፍል ገባ። የአቡ ራፊዕን ደምፅ ወደሰማበት አቅጣጫ ተጠጋና ሆዱን በሰይፍ ዘለቀው።

አሁን ከአካባቢው በፍጥነት መስሰወር አለበት። ጣደፍ ጣደፍ እያለ ሲወጣ አንድ መወጣጫ ደረጃ ላይ ደረሰ። ጨለማው ገደሉን ሜዳ የሚያስመሰል ነበርና መሬት መስሎት ሲራመድ ከደረጃው ወድቆ ክፉኛ ተሰበረ። ህመሙን ውጦ፣ ጉዳቱን በጨርቅ አስሮ እግሩን እየጎተተ ራቅ ብሎ ተቀመጠና የአቡ ራፊዕን የሞት ዜና ይጠባበቅ ጀመር። ጎህ ሲቀድ መርዶ ነጋሪው የሒጃዙ ነጋዴ አቡ ራፊዕ መሞቱን ለፈፈ። ይህን ብስራት እንደሰማ ወደ ባልደረቦቹ ሄዶ ነገራቸው። ከዛም ወደ ነቢ አቅንተው የሆነውን ሁሉ አጫወታቸው። ይሄኔ ረሱሉላህ እንደዛ የተሰበረ እግሩን አንዴ በእጃቸው ቢዳብሱት ህመም የተባለ እንዳልነካው ሆኖ ሻረ።
@medinatube
በምስሉ ላይ የሚታዩት ህንዳዊው ሙፍቲ አሕመድ ያር ክሃን ናዒሚ በዚህ ክስተት ተመጅነው መዳንን ለምነዋል። ሙፍቲ አሕመድ የዛሬ ሃምሳ ዓመት ሐጅ ሊያደርጉ ይነሱና በቅድሚያ ነቢን ለመዘየር ወደ መዲና ጎራ ይላሉ። መዲና ደርሰው ከመጓጓዣ ላይ ሲወርዱ ወድቀው እጃቸው ተሰበረ። እንደሚጠበቀው አልጮሁም። አላለቀሱም። የተሰበረ እጃቸውን ሳም አድርገው "አህ አንቺ የመዲና ስቃይ በልቤ ተቀመጪ፣ በተወዳጁ ሰው ፊት ለፍርድ አቀርብሻለሁ" ብቻ ነበር ያሉት። ከዛ ከደጉ ሰው ማረፊያ ከቁባው ፊት ለፊት ቆሙና "አንቱ የዓብዱላህ ኢብን ዓቲክን ስብራት የጠገኑ ነብይ ሆይ ይሄው እጄን ተሰብሬ ከደጅዎ ቆሜያለሁ!" ብለው በእንባ የታጀበ ተማፅኖ አቀረቡ። እጃቸው ድኖ በደንብ ተንቀሳቀሰ። እዛው መዲና ውስጥ ወዳለ ሃኪም ሄደው እጃቸው በራጅ ሲታይ ውጤቱ የእጃቸው አንጓ ሙሉ በሙሉ መስሰበሩን አሳዬ። በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ እጅ ምንም እንዳልደረሰበት ሁሉ እንደዛ መንቀሳቀሱ ሃኪሙን አስገረመ። በዛው እጅ ነው ኋላ ላይ እውቁን የተፍሲር ኪታባቸውን የጻፉት። በወለላው ነብዬ የታሸ ህመም ሲሽር አሰር እንኳን አይተውም። መድኃኒቱ "ወዓፊየተል አብዳኒ ወሺፋዒሃ" " እያለ ልቡን ለደቃላቸው ሁላ ይደርሳል። ባሮችህ ለነቢ ባላቸው የሐቂቃ ሙሐባ፣ እንባ አባሽ በሆኑት ፈዋሹ ነቢ በደዋዑ ሙሐመድ ይሁንብህ ዑዝራችን ይነቀል፣ ስብራት ሁሉ ይሻር፣ የዛለ ይበርታ፣ የተጨነቀ ይፈረጅ፣ ያዘነ ይደሳ አቦ!
@mediantube
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
ከሰይዱና አቡበከር ሲዲቅ የዘር ሐረግ የሚመመዘዙት፣ ዳእዋ ወተብሊግን ዳግም ሩህ ዘርተውበት ህንድ ላይ የመሠረቱት የሸይኽ ሙሓመድ ኢሊያስ አራተኛ ኸሊፋ የሆኑት እረፍት አልባው የአለም የዳዕዋ ወተብሊግ አሚርና ሙረቢ ሸይኹል መሻኢኽ ወሙላና ሸይኽ ሙሐመድ ሰኣድ ከሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ሃበሻ ቡታጅራ ኢሽቲማዕ ላይ ይገኛሉ። ዚያራቸውን ይወፍቀን!! ምክራቸውን ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን!!
@medinatube
•ሀሳብና ጭንቅን ከሚያቃልሉ፣ስብራትንና ጉዳትን ከሚያክሙ ዒባዳዎች ውስጥ በዉዱ ነብይ ላይ ሰለዋት ማውረድ አንዱ ነው።
اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد🧡🧡
@medinatube
#ሸህ #አብደልቃድር#ጉቦች#ቆንጆ #አዲስ #መንዙማ #ያዘይኑ#ያዘይኑ#ቆንጆ #2023
MEDINA TUBE
#ሸህ አብደልቃድር ጉቦች
ያዘይኑ ያዘይኑ ተመስጦ ለሰማው የናፈቀን አስተዋሽ የሆነ መሰማት ያለበት @MedinaTube
የዙህር ሰላት ደርሶ ቢላል አዛን እያደረገ ነው። ነቢም ሰ ዐ ወ እያደመጡ ነበር። የቢላልን አዛን እየተከተለ እዛን የሚል ሰው ድምፅ ከርቀት ይሰማል።

ቢላል አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ ረሱል ሰዐወ፦‹‹ማን ነው አዛን ሚለው ከወደ ውጭ በኩል? ›› ሲሉ ጠየቁ። አባ መሕዙራ የተባለ እረኛ በማላገጥ ስሜት አዛን እያለ ግመሎቹን እንደሚያግድ ነገሯቸው።

ረሱልም ሰዐወ በተረጋጋ ስሜት ይህ ሰው ተይዞ እሳቸው ዘንድ እንዲቀርብ ዐሊይን እና ዙበይርን ላኳቸው። ሁለቱም ወደተላኩበት ሂደው አላጋጩን ከነ ግብረ-አበሮቹ ጠፍረው አመጧቸው።

ሁሉም አቀርቅረው ረሱል ሰዐወ ፊት ቆሙ።
‹‹ ከናንተ ውስጥ ማን ነበር አዛን ሲል የነበረው?›› ረሱል ስዐወ ጠየቋቸው።
ፍርሀት ስላደረባቸው ሁሉም ዝም አሉ።

ዝምታቸውን ያስተዋሉት ነቢይም፦‹‹እንግድያ ማን አዛን እንዳለ ለመለየት እያንዳንዳችሁ በየተራ አዛን በሉ›› አሏቸው። ሁሉም አዛን ካሉ በኋላ የአባ መሕዙራ ተራ ደርሶ አዛን ሲል እሱ መሆኑ ታወቀበት።

‹‹ስምህ ማን ነው?›› አሉት ነቢ ወደሱ ጠጋ ብለው።
‹‹አባ መሕዙራ እባላለሁ›› አለ ፈራ ተባ እያለ።
‹‹የመልአክ ድምፅ ይመስል እየተጠበብክ አዛን ትል የነበርከው አንተ ነህ?›› ነቢ ጠየቁት።

ቅጣቱን ለመቀበል ሲዘጋጅ የነበረው ሙሽሪክ በቅጠቱ ፈንታ ይህንን ልብ የሚማርክ ንግግር ሲሰማ ውስጡ ተናወጠ። ረሱል ሰዐወ ከአላጋጩ እረኛ ፊት ቁመው በጭንቅላቱ የጠመጠመውን ፎጣ ከጭንቅላቱ ላይ አውልቀው ፀጉሩን እየዳበሱ፦‹‹አላህ በረካ ያድርግህ፣ ወደ እስልምናም ልብህን ይምራልህ›› አሉት።

በስብዕናቸው የተማረከው አላጋጩ እረኛም የመልዕክተኛው እጅ ከራስ ቅሉ ሳይወርድ ጓደኞቹ እየተመለከቱ ሸሀዳውን ያዘ።

የድምፁን ውበት የመሰከሩለት ይህን እረኛም ረሱል ሰዐወ ወደ መካ ሂዶ አዛን እንዲል ሾሙት።ከዝያች ቀን አንስቶ ወደ መካ የተመመው ይህ እረኛም የመካ ሙአዚን ሁኖ‹‹ነቢ የዳበሱትን ፀጉር መቼም አልላጨውም›› ሲል ስለት ተሳለ።

መካ ላይ ቁጭ ብሎም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የነቢን ሰዐወ ትዕዛዝ እየፈፀመ ከረመ። ከሱ ህልፈት በኋላም ልጆቹ እና የልጅ ልጆቹ ለ300 አመታት ያህል መካ ላይ አዛን ይሉም ነበር።

Sefwan Ahmedin

ምንጭ፦

سنن النسائي
سنن ابو داود
مسند أمام احمد
@Medinatube
Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Photo
ወሎ ሠይድ ዓብዱልቃድር ጀይላኒን "ዓብዱዬ ጅላሌ" ይላቸዋል። እኔም ዓብዱዬ ለአገሩ እንግዳ ሳይሆኑ ወሎዬ ሸኽ ነው የሚመስሉኝ። እሮብ ረፈድፈድ ሲል ጀምሮ ቀልቤ ወደ መንደሬ ሽምጥ ይጋልባል። እናቴ ከሮቢት ገበያ የምትገዛው ትርንጎ መዓዛ አፍንጫዬ ሥር ይመጣል፣ የሚንቦለቦለው የአድሩስ ጭስ ከ’ነ ጋቻው ድቅን ይልብኛል። የአደስና የጠጀሳሩ ሽታ ከተጎዘጎዘው ቄጤማ ትኩስ መዓዛ ጋር ያውደኛል። የቡና ሙቀጫው ቅው ቅው የሚል ድምፅ ያቃጭልብኛል። ከርቤ የመሰለው የዓብዱዬ ቡና ወደ ፍንጃሉ ሲንቆረቆር ከ‘ነ እንፋሎቱ ይታዬኛል። ለቡና ቁርስ በጥቁር ጤፍ ተጋግሮ ቂቤና በርበሬ የሚቀባው አነባበሮ ትውስ ይለኝና ምራቄን ያስውጠኛል። የቡና ቁርሱን በእንሶስላ ቀለም በተዋቡ እጆቿ "ቢስሚላሂ የነቢ ማ‘ድ" እያለች እየቆራረሰች ከሚያምር ፈገግታዋ ጋር የምታጋራን እናቴ ትናፍቀኛለች። ከገበያ መልስ በበራችን የሚያልፉት በግና ፍየሎች ጩኸት ይሰማኛል።

አባባ በግ አይቶ አያልፍም። ስጋ ይወዳል። ኧረ ስጋ ራሱ እሱን ይወደዋል። ዝልዝል ጥብስ፣ ዱለት፣ ቋንጣና፣ ኩላሊት ጥብስ በሚጥሚጣ ደግሞ በተለዬ ይወዳል። ወጣ ወጥ ሲሠራ ስጋ እንደባከነ ነው የሚቆጥረው። ሃኪሞች አዘውትሮ ስጋ መመገብ የሚያስከትላቸውን የጤና ጉዳቶች ሲዘረዝሩ በምፀት ፈገግ ብሎ "ወግድ የሚያመውስ ማጣቱ!" ይላል። ለእንግዳ ክብሩን የሚገልፀው በግ በማረድ ነው። እንግዳ ሲመጣ ቤት ውስጥ ስጋ ቢኖር እንኳን "እንዴት ዱለት ሳይቀምስ?!" ብሎ ይወጣል። አላፊ አግዳሚ ከገጠመው ጥሩ ካልሆነም ወደ ገበያ ይፈተለካል። ወደ ሮቢት ገበያ። ሮቢት ገበያ በጦስኝ ያደጉ፣ ስጋቸው እንደ ነዓነዓ (ነጭ) ከረሜላ ምላስ ላይ የሚሟሟ፣ አጥንታቸው እንደ ሙዝ የሚላጥ በጎች ሞልተዋል። አንዱን ስቦ ይመጣል። እኔም በርሱ ወጥቼ ስጋ እወዳለሁ። ከአጥንት ጋር ስንላፋ ያዬን ጠላት የገጠምን ይመስለዋል። እሮብ ከት/ቤት ስመለስ ታርዶ መዘፍዘፊያ ላይ ጠፈፍ እያለ ያለ ስጋ ይመጣብኛል። ወዲያው እግሬ ኩሽና ያደርሰኛል። ገንፈል እንዲል ጥቂት ተቀንሶ የእንጨት ምድጃ ላይ የተጣደ ስጋ፣ እየተከተፈ ያለ ጨጓራ፣ የሚከተከት ጉበት አያለሁ ደስ ይለኛል። አባባ ሁሌም እንደሚያደርገው አንዷን ኩላሊት አስቀርቶ በከሰል ፍም ያስጠብስና ቆረጥ እያደረገ በሚጥሚጣ ያቀምሰኛል። ስበላ ደስ ይለዋል። ወደ ሳሎን ሳመራ ደግሞ እናቴ የገዛችው ትርንጎ፣ የምታጨሰው አደስ መዓዛ ይቀበለኛል። ሁሉም ነገር ከምኔው እንደሚደርስ ይገርመኝ ነበር። ሰብሰብ ብለን የደረሰውን ለሆድ አድርሰን ቡናችንን ጠጥተን ተመራርቀን ዱዓ አድራጊውም ወደ ዱዓው፣ ከስሳቢውም ወደ ከስቡ፣ እኔም ወደ አስኮላዬ!@medinatube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሚር ሁሴን//ሩኸል ከዉኒ// አዲስ መንዙማ 2016//AMIR HUSSEN//RUHEL KEWNI NEW MENZUMA2024@AMIRHUSSENofficial
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጧሃ ሙስጦፋ || አዲስ የጂማ መንዙማ በሷሊህ አስታጥቄ || New Menzuma Tuha Mustofa Sualih Astatke @medinatube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አላህ ያሶመድ||ALLAH YA SOMED||አብዱልሀሚድ አክመል||Abdulhamid Akme|lNew Mawlid Menzuma @MEDINATUBE
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አወየው ነቢ | አንዋር ፈቂ [አንዋር አልቡርዳ] AWOYEW NEBI | ANWAR ALBURDA @MEDINATUBE
2025/02/17 12:15:35
Back to Top
HTML Embed Code: