Telegram Web
#ቀራንዮ_እንሂድ | Let's go to Calvary.

#ንነጽር_132

ቀራኒዮ መሄድን የማይሻ ሰው፤ የወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን የማያምን ነው። እንዴት ቢሉ ቀራንዮ ላይ የምናገኘው ስለ እኛ በደል የተሰቀለው ክርስቶስን ነውና።
ቀራኒዮ ካልሄድክ የክርስቶስን ፍቅር ሊሳልብህ አይችልም።

"ቀራንዮ እንሂድ..." ይቀላቀሉን👇
https://www.tgoop.com/keranyo7777
https://www.tgoop.com/keranyo7777
☝️☝️

ማርመድሕ || @MekuriyaM
Forwarded from Χριστιανός
●በሄድኩበት_ሁሉ●

ዛሬ ከምሽቱ 2:00 በዓውደ ወንጌል ሚዲያ ይለቀቃል።

TELEGRAM
https://www.tgoop.com/Awude_wengel_media_21
YOUTUBE:
https://www.YouTube.com/@የዲላኦርቶዶክሳውያን


“ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።”
— መዝሙር 118፥14

Marmedh || @MekuriyaM
Forwarded from Χριστιανός
●ብዙዎች ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ያወቁበት።
●መጽሐፍ ቅዱስን የገለጡበት።
●"እውነት እኮ ነው" ብለው የተናገሩበት።
●እነ ዕገሌ መፍራት የጀመሩበት።
        በዚህ ሰው ነው ብዬ ብናገር ውሸት አይደለም።

Marmedh || ማርመድሕ

There are some of us who do not like the honor of our elders and fight to overthrow them.😓
ማበረታታት እንልመድ ●FOLLOW●
https://www.tiktok.com/@rasbika12?_t=ZM-8u3CRfQIh2k&_r=1
Life is this!

አንዳንዱ፦ ደስታን ጸንሶ-ኀዘንን ይወልዳል፤
ሌላው፦ ሕይወትን ጸንሶ-በሞት ይወሰዳል።
🥰🥰🥰 ይህቺ ነገር አጋሯት!
«እግዝእትየ እብለኪ፤ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ።»

እንኳን አደረሳችሁ
«አንተ ሰው #የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ!»
●ቅዱስ ኤፌሬም●
Encoderbot file id4194862 16k
ዐቢይ ጾም ለምን የንሰሐ መዝሙር ብቻ ሆነ?

🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፅ

👉🏾በዐቢይ ጾም ለምን ከበሮ አይመታም
👉🏾በዐቢይ ጾም ለምን ፀናፅል አንጠቀመም
👉🏾በዐቢይ ጾም መብላት የሌለብን ምግቦች በየአመቱ ጥያቄ እሚያስነሣው ዓሳን አለመብላት

«ከመርካቶ እየገዙ ይደልቁታል»🤭 አድምጡት ብዙ ቁም ነገር አለበት።

ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ አሥሮነ ቃላት

www.tgoop.com/MekuriyaM
ይሄንን ትምህርት ቤት ለመርዳት የግድ በዚህ ት/ት ቤት ተምረን ማለፍ አይጠበቅብንም!
ኢትዮጵያ ያስተማረችንም ሆነ ያሳየችን "የሰው መድኃኒቱ ሰው እንደሆነ ነው።"

ተማሪ ገና ከጅምር መሠረቱ በተስተካከለ ክፍልና ወንበር ተቀምጦ መማር ካልቻለ ውጤቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል። "የተገደበ ነገር የተገደበ ውጤት አለው።"

የምንም ነገር መሠረት ትምህርት መሆኑን ካወቅንና ካመንን ለመርዳትም ሆነ ለመረዳት እጅግ ቀላል ነው።

ይሄንን ትምህርት ቤት ለማደስ በሚደረገው እንቅስቃሴ እርስዎም ይቀላቀሉንና የማይጠፋ ስም ለትውልድ አስቀምጠው ይሂዱ።

አንዳንዴ የሞተ ሰው ስም ይጠቀስና "ይሄ ሰው እኮ አልሞተም ዛሬም አለ።" የሚባለው እኮ በዚህ ዓይነቱ ድንቅ ተግባር እየተሳተፈ ስሙን ከመሬት በላይ ማተም ሲችል ነው።

ታድያ እኔስ ከዚህ እንቅስቃሴ እንዳልሳተፍ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

ወደ ግሩፑ ይቀላቀሉና ጥቂት ነገርን ይተባበሩ! "አንድነታችን ኃይላችን" እንደሆነ እናሳይ ኑ👇👇👇

https://www.tgoop.com/yedgeee
https://www.tgoop.com/yedgeee
https://www.tgoop.com/yedgeee

መኩሪያ ሙራሼ
Forwarded from እምዝ-ዓለም | From this world (XPIETIAVOS)
ደስ የሚል ነገርን አንብቡ! መልካም ቆይታ👌

#የሚገርመው ነገር ለብዙዎች ግራ አጋብቷል። “ፍልስፍና ጀመርክ እንዴ?” ያሉም አልጠፉም😍 ፍልስፍናማ ከጥያቄ አይጀምርም'ኮ፤ “ከማድነቅ ነው የሚጀምር።” ከዚያ በኋላ ነው ወደ ጥያቄ/መመራመር/መፈላሰፍ የሚኬድ።
#በጣም_የሚገርመው ደግሞ የብዙዎቹ ጓደኞቼ ምላሽ 'Emoji' መሆኑ ነው።

ታድያ ይሄ ጥያቄ ምንድር ነው? ዲ/ን መኩሪያ(ማርመድሕ) ነኝ ተከተሉኝና በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ውስጥ ብዙ ቁም ነገርን ጨብጡ።

🛑 ሰው ነህ⁈ || ሰው ነሽ⁈ ነው ጥያቄው! ሰው ናችሁን?

● “እግዚአብሔር ሙሉ ሰው አድርጎ ነው የሠራኝ። በኦሪት ዘልደት ሥላሴ ሰዉን በመልካቸው በ አርአያቸው ፈጥረውታል። ማለት፦ ንጽሕና፣ ቅድስና የባሕርይ ገንዘባቸውን ለሰዉም ፀጋ ተደርጎ  ገንዘብ ተደርጎ ተሰጥቶን ነበር። በዚያ ላይም በገነት  ነበር የምንኖረው።
ይህን ጸጋ አጣነው። ማለት፦ ከሰዉነት ዝቅ አልን። እና ይህን ሰዉነት አባቶቻችን ነበራቸው። ቅዱስ ዳዊት ልጁን ሶሎሞንን ሲመርቅ “ልጄ ሆይ ሰው ሁን” ይላል።
እሱ ሰው ሆኖ!! ምን ማለት ነው? ዳዊት በጽዮን ከተማ :ንጉስ ሲሆን :ፍርድ አይጕደል: ደሃ አይበደል: የሚል: ንጉሥ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ከእግዚአብሔር ሲርቅ ካንተ ተጣልቼማ እንደማይሆን ነው ብሎ ንስሐ የሚገባ... ይህ ሰው ነው። ልጁንም የመረቀዉ ይህንኑ ነው:: ሰው እንዲሆን እና እኔ ይህን ነገር አለኝ ለማለት ይቸግረኛል... በዝርዝር...ከተለካሁ ነኝ ለማለት ይከብደኛል።
ግን እንዲሁ ዝም ብሎ በቁሙ ሰው ነህ ወይ ካልከኝ ?!!  አዉሬ አይደለሁም፣ እንስሳም አይደለሁም። ስለዚህ ጥሩ ሥራ ቢኖረኝ የምጸድቅበት፤ ባይኖረኝ የምኮነንበት ሰውነት ያለኝ #ሰው_ነኝ
           ◎ ዲ/ን ጸአዳ ከወልቂጤ


● “ሰላምህ ብዝት ይበል እያልኩ 🙏
እኔም አልኳት፥ የአንቺም ሰላም ይትረፍረፍ!

ቀጠለች...
  ሰው ነሽ ወይ ? ላልከኝ ጥያቄ  አዎ ነኝ እላለሁ። ሰው የሚለው  'ሰው ምንድነው?'  የሚለው በመጀመርያ ስለሚጠይቅ  እነሆ፦
     1 እኔ ማን ነኝ  ?
     2 እኔ ከየት መጣሁ ?
     3 ምንድነው ምሠራው?
     4 መጨረሻዬ ምንድነው?
የሚሉትን ይኖሩታል  ሰው የባህር አውሬ ነው ይላል ከእዮብ መጽሐፍ  ላይ የተወሰደ።
ሌላኛው የአሜርካው ኖቭሊስት ደሞ ሰው ማሽን ነው ይላል ከምንም በላይ ደሞ ታላቁ ቅዱስ መፅሐፍ  ደሞ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው ይለናል ሰው ክቡርም ነው ለዚህ ነው #ሰው_ነኝ የምልህ !
ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነውና🙏
       ◎ገጣሚት መቅደስ(ከብዕር አንደበት) ከወልቂጤ


● “እርግጥ ነው ሰው ስውነቱን ክብሩን የተወበት(የረሳበት)ክፉ ጊዜ ላይ ደርሰናል። ነገር ግን የሰውነት ውሃልክ የሆኑ፣ ሰው ሆነው እንደ መላዕክት የሚኖሩ፣ ከኪሩቤል ጋር የሰማይን መቅደስ ያጠኑ፣ ከዋክብተ ሰማይ የሆኑ ቅዱሳን፣ የእውነተኛ ትሕትና መምህራን የሆኑ፣ በጸሎትና በጾም ተወስነውና በዋሻ ውስጥ  የሚኖሩ  አበው ባሉበት  ዓለም ነው የምንኖረው። ሰለዚህ ሰው ነን ለማለት ምስክሮች አሉን ማለት ነው። አሁን ከክብር የጎደልን ልቦና አግኝተን ወደ ቀደመው ነገራችን እስክንመለስ ድረስ።
#አዎ_ሰው_ነኝ#
ምክንያቱም ከ3ቱ ባሕርያተ ነፍስ ከ4ቱ ባሕርያተ ሥጋ የተፈጠርኩ፣ በአርአያ(በአምሳለ)#ቅድስት_ሥላሴ የተፈጠርኩ፣ ሀገሬ ሰማይ፣ መኖሪያዬ ክርስቶስ የሆነ፣ ብቸኛ የክብሩ ቀዳሽ፣ የመንግሥቱ ወራሽ የሆንኩ እስትንፋሰ ክርስቶስ #አዎ_ሰው_ነኝ።”
        ◎ ዮሴፍ ሺፈራው ከወናጎ


●“እኔ የሰውን ልጅ ባሕርይ ወይም ምግባር ባይኖረኝም፣ ሰው ለመባል ሁሉን ባላሟላም እንኳ፤
“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤...።”
  — ዘፍጥረት 1፥26
ብለው ስለፈጠሩኝና እኔም የሥላሴ አገልጋይ ስለሆንኩኝ #አዎ_ሰው_ነኝ!”
        ◍ዲ/ን መኩሪያ ገብሩ(ከጉራጌ ዞን)


●“ነኹም አይደለኹምም!
አፈጣጠረ መልከ ሰብእ ቢሆንም በግብሬ ግን ሰው አይደለኹም።”
◎ዲ/ን ጌታቸው ከጉራጌ ዞን

● «በእርሱ አምሳል የተፈጠርኩ...
ሰው፦ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ውስጥ ለየት የሚያረገው #ሰው የሚያስብ፣ የሚያምን፣ የሚያወራ ከእግዚአብሔር በታች ምንም ነገር ላይ መወሰን የሚችል ሰው ነው......። ስለዚህ #አዎ_ሰው_ነኝ
     ◎መዓዛ ከአዲስ አበባ


● ❝እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ፤ በእጁ አቡክቶ፣ እስትንፋሱን እፍ ብሎ የፈጠረኝ፣ በመስቀል ተሰቅሎ ነጻ ያወጣኝ ፍጡር ስለሆንኩ #አዎ_ሰው_ነኝ
        ◎ዘማሪት ምሥራቅ ከጉራጌ ዞን


● ❝አዎ_ነኝ! ...
ለዚያውም በ አምላኬ ምስል የተሳልኩኝ ፍጡር!!!
#ሰው_ነኝ!❞
        ◎ዳኛቸው ያቦነህ ከቡታጅራ

●❝ #አዎ_ሰው_ነኝ!
ያውም በአምሳሉ የፈጠረኝ!❞
       ◎ቴዲ ከዲላ

●❝ #አዎ_ሰው_ነኝ!
ሰው የሆንኩት በአምሳሉ ስለተፈጠርኩኝ ነው።❞
       ዘፍጥረት 1÷26 ❞
         ◎ንጉሤ በላይ ከዲላ


◉"በሥጋ ሰው ነኝ። "ሰው ሁን" በተባለበት ሐሳብ ራሴን ስመለከተው ግን ሙሉ ሰው አይደለሁም።🙏"
       ◎ዲ/ን ኤርምያስ(ሰፋኒት ሚዲያ) ከወልቂጤ


◉"መልካም መልሴ ግር ሊል ይችላል ሆኖም
#ሰው_ነኝ_ደሞም_አይደለሁም
(ሰው ነኝ ስል):-  በአምሳሉ የተፈጠርኩኝ
የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ እያልኩ ነው
(ሰው አይደለሁም ስል ደሞ):- ምግባሬ ሰው ሰው አይሸትም ምግባሬ ወድቋል
እያልኩኝ የሰው ምግባር እንዲኖረኝ ፀልዩልኝ (ፍቅረ ጻድቅ)"
        ●ገጣሚ በረከት ግዛው(ታላቁ መጽሐፍ) ከዲላ



🛑Join/Follow us on
◎ Telegram
       
www.tgoop.com/MekuriyaM

◎ Ttiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19

◉ Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61570329701398


ከ9,500 አልፈናል 10,000 Members ላይ አድርሱኝ👌
#Share ይደረግ!
Channel name was changed to «እምዝ-ዓለም | From this world»
የተሳሳተ የለም! ጥያቄና መልስ ክፍል ❶

ከማመን እና ከማወቅ ማን ይቀድማል? ማመን ወይስ ማወቅ? እንዴት?

🛑እውቀት ሁለት አይነት እውቀት አለ። እውቀት ጠባያዊ እና እያደግንና እየተማርን ፣እያየን የምናመጣው እውቀት ። ጠባያዊ እውቀት በተፈጥሮ ማወቅ ለምሳሌ ሕፃን ከተወለደ በኋላ እንዴት መጥባት እንዳለበት ሳይነገረው መጥባት ይጀምራል ይህ በተፈጥሮ የሚታወቅ ነው።
ስለዚህ በጠባያዊ እውቀት ከሆነ ከማመን እውቀት ይቀድማል ግን እያደግን እየተማርን የምናገኘው እውቀት ከሆነ አይነጣጠሉም #parallal_የሚሄዱ_ናቸው
ምክንያቱም ፣
ማመን የሆነ የሚታመን አካል አለ የሚያምን አካል አለ ለማወቅ ማመን አለበት ለማመንም ማወቅ አለበት
ለምሳሌ አብርሃም እንይ በእምነት ወጣ ይላል ግን አምላክ እንዳለ አውቆ ነው አምኖ የወጣው አምላክ የለም ብሎ ቢያምን የሚያውቀው አለመኖሩን ነው ለምን አለመኖሩን ስላላመነ አላወቀም አለ ብሎ ሲያምን ያውቃል።
እውቀት ይቀድማል ካልን እውቀት ያላቸው ካወቁም በኋላ የማያምኑ አሉ።
እምነት ይቀድማል ካልንም ሳያውቁ እንዴት ያምናሉ ስለዚህ parallel
          ●ዲ/ን ዘማሪ ደምስ ከወልቂጤ

🛑 #ማወቅ_ይቀድማል ብዬ አምናለው እንዴት ስለማምነው ነገር እውቀት ሳይኖረኝ በባዶ አምናለው? ስለዚህ የማምነውን ነገር ቀድሜ ማወቅ አለብኝ ።
ለምሳሌ፦ ስለቅዱሳን አማላጅነት ያለምንም ጥርጥር አምናለው። ስለዚህ እኔን እንዳምን ያደረገኝ በቅዱሳን መጽሐፍትም ይሁን በሕይወቴ ከተደረጉልኝ ነገሮች አልያም ከተማርኩት ነው።
አንድን የ7 ዓመት ልጅ ጠርተህ በቅዱሳን አማለጅነት ታምናለክ ብትለው ? አደለም ሊያምን እነማናቸው ብሎ ሊጠይቅህ ይችላል ...
          ●ቃልኪዳን ከዲላ

🛑ከማመን እና ከማወቅ #የሚቀድመዉ_ማወቅ ብዬ ነዉ የማስበዉ። ምክንያቱም ማመን የምንችለዉ ስናዉቅ ስለሆነ ለምሳሌ አንድ ሰዉ ስለ ሃይማኖቱ ሲያዉቅ ነዉ የሚያምነዉ ካልተማረ ወይም ካላወቀ ሊያምን አይችልም። ከተሳሳትኩ አርሙኝ 🙏
          ●የሺ ከአዲስ አበባ

🛑እደገባኝ መጠን መጀመሪያ #ማመን_ይቀድማል ምክንያቱም በአካለ ስጋ ተገልጦ አይተን የማናውቀውን እግዚአብሔር አለ ብለን እናምናለን በፍጥረቶቹ ደግሞ ሀለወተ እግዚአብሔርን እናውቃለን ስለዚህ  ማመን ከማወቅ ይቀድማል.....
ለምሳሌ  በእምነቱ የሚሰራ የሀገር ምሰሶ የሆነው ገበሬ በእርሻው ወቅት ንፁ የሆነውን እህል አውጥቶ በእርሻ መሬቱ ላይ ከአፈር ጋር ይቀላቅለዋል ከዛ መብቀሉን ይጠባበቃል የሚጠብቀው እደሚበቅልለት በእራሱ እርግጠኛ ሆኖ ሳይሆን በእምነት በመጠበቅ ነው ይሄን ሊያደርግ የሚችለው እግዚአብሔር ነው ዝናቡም ፀሐዩም የእረሱ ናቸውና ገበሬውም በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አበስሎ የሰጠውን ፈጣሪው መሆኑን ያውቃል ማለት ነው። ከተሳሳትኩኝ እርማት እቀበላለው።
           ●መንበር ከወልቂጤ

🛑ሁለቱም እንደዓውዳቸው ይሽቀዳደማሉ።
#ማመን_ይቀድማል ስል
ለምሣሌ:ሀይማኖት አምነን የምናውቀው እንጂ አውቀን የምናምነው አይደለም ሳያዩ የሚያምኑ ነውና።
#ማወቅ_ይቀድማል ስል ደግሞ
ለምሣሌ:አንድን ሰው ለማመን ሚስጥርህን ለማጋራት መጀመርያ ያን ሰው ማወቅ ይኖርብሀል።
          ●የማርያም ልጅ ከሐዋሳ

🛑እንደኔ አመለካከት #ማመን_ይቀድማል እላለው።ምክንያቱም ለምሳሌ አንድ ህፃን ልጅ ሲወለድ ጀምሮ እራሱን እስከሚያውቅ ድረስ ቤተሰቦቹ በመረጡለት እምነት ይኖራል ስጋውና ደሙን እየተቀበለ ይኖራል።አውቆ ሳይሆን አምኖ ነው ከጉርምስናው ጊዜ ደግሞ መጠየቅ መፈለግ ይጀምራል ሰንበት ት/ት ይጀምራል ድቁና ይማራል በቤተክስቲያን ዙሪያ ሆኖ እውቀትን ይቀስማል ።ከተሳሳትኩኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ🙏
         ●ቤተ-ልሔም ከአዲስ አበባ

🛑መጀመረያ #ማወቅ_ይቅድማል ሳላውቅ ዬትኛውንም እምነት ቢኖረኝ ልክ እንደደረቅ እንጨት ነው የደረቀ እንጨት ሁሌም መከራ እና መጥረበያ ይበዛበታል አናም አንድ ምሳሌ አለ እንደውም በመጻፍ እምነት ያለስራ ከንቱ ነው ብሎ ይነግረናል ለዛ መጀመረያ አውቀን ነው ለሌላው ማሳወቅ የምንችለው ያየነውን እንናገራለን የሰማነውንም እንመሰክራለን ምን ነገር ግን ምን ስናደርግ ብቻ ነው ለራሳችን አውቀን ነው ለሌላው የምንተርፈው።
         ●ንጉሤ ከዲላ

🛑ለሙከራ ያክል ...
#ማወቅ_ይቀድማል ከማመን
ባጭሩ እውቀት ማለት ክፋውንና በጎውን ነገር መለየት   ስለዚህ መጀመሪያ  ምናምነው አካል ከማመናችን በፊት  ስለምናምነው አካል ወይም ፈጣሪ ማወቅን/መረዳትን ይቀድማል። ከመልሱ ልማር🙏
           ●ዲ/ን ዓምደ ገብርኤል ከአዲስ አበባ

🛑ከማመንና ከማወቅ #ማመን_ይቀድማል መጀመርያ የሆነ ነገር መኖሩን ካመንክ በኋላ መኖሩን ለማረጋገጥ ወደ ማወቅ ትሄዳለህ ማለት ነው ።
ለምሳሌ እግዚአብሔር አለ ብለህ ታምናለህ ደሞ እግዚአብሔር ስለ መኖሩን የሚያረጋግጡልህ ነገሮች ስትፈልግ እግዚአብሔርን ይበልጥ መኖሩን ታረጋግጣለህ ማለት ነው!! ስለዚህ  መጀመርያ አለ ብለህ ያመንክበትን ነገር ለማወቅ የምታደርገው ነገር እውቀት ይባላል። እንደ እኔ  ከማመን እና ከማወቅ ማመን ይቀድማል። አመሰግናለሁ!!🙏
           ●ዲ/ን ዘማሪ መታገስ ከአዲስ አበባ

🛑ማወቅ ይቀድማል ሳናዉቅ ማመን ስለማንችል።
               ●ፋሲካ ከይርጋጨፌ

🛑ከእውቀት እምነት ይቀድማል፡
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‎ማር 16:16 ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመነ ነው የሚለው።
       ●ኢዩኤል ከአዲስ አበባ

🛑 #ማመን_ይመስለኛል። ሰው ይሆናል ብሎ ያመነውን ይመስለኛል ወደ ጥያቄ የሚያመጣው ከዛ ከምርምር በኃላ እውቀት ይሆናል።
●ዳዊት ከአዲስ አበባ


●ክፍል● ❷ ይቀጥላል...

ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ ነበርኩ

🛑Join/Follow us on
◎ Telegram
       
www.tgoop.com/MekuriyaM
◎ Ttiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19
◉ Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61570329701398
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት 👇
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
2025/02/26 00:10:06
Back to Top
HTML Embed Code: