Telegram Web
መርቆርዮስ/ፒሉፓዴር/

ፒሉፓዴር ና መርቆርዮስ፣
ከበሮ ስንመታ ድረስ በፈረስ 
መርቆርዮስ የአብ ወዳጅ ነህ
ሰማዕት ሆነሀል ጣዖትን ሰብረህ

በብረት አልጋ በቆዳ ጅራፍ፤
ደምህ ቢነጥብ ጀርባህ ሲገረፍ።
የነደደ እሳት አንተን ሊያጠፋ፤
የሚጠብሱበት በደምህ ጠፋ።

የአብ ወዳጁ ሙያህ ወታደር፤
ለአምላክህ ፍቅር የሌለህ ወደር።
ስልጣኑ ክብሩ ይቅርብኝ ብለህ፤
ተቀላህ በሰይፍ ትጥቅህን ፈተህ፥

የንጉስ ክብር ርስቱ ጉልቱ፤
ሳያታልልክ ክብር ሹመቱ።
አልሰግድም አልከው ዳኬዎስን፤
በደም ታመንከው አምላክህን።

ውጊያ ቢሰለፍ ጠላት ሰይፍ መዞ፤
ድል አደረገ አምላኩን ይዞ።
የተዋጋውን ድል አድርጎታል፤
ገጸ ከለባት ታዘውለታል።

ስዕልህ ይዝለል ከበሮ እንምታ፤
በፈተና አጽናው ወጣት ይበርታ።
መርቆርዮስ ሆይ በፈረስ ናና፤
ወጣቱን ጠብቅ ወጣት ነህና።
++++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
ደሀውን መኖሪያ አትከልክል፤
የተራበን ቸል እንዳትል።
ያዘነ ከቶ አይደንግጥ፤
ለጠየቀህ ያለህን ስጥ።
ለተራበ ለተጠማ፤
እዘንለት ልብህ ይድማ።
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
ቀን....
አንዳንድ ቀን አለ፥ ሚያልፍ ማይመስል፤
ልብን 'ሚሰብር፥ተስፋን የሚያቆስል።
የእድሜ መጨረሻ፥ የሞት ቀን የሚያስመኝ፤
"ብንሄድ ይሻለናል"፥ በቅቶኛል የሚያሰኝ።

የቀን ክፉ አለ፥ ከአዙሪት የባሰ፤
ከመከራ ሚዘፍቅ፥ እየመላለሰ።
ዘላለም 'ሚመስል፥ አለ አስጨናቂ ቀን፤
አመትም ወራትም፥  ይዞ የማይለቀን።

ሲጨንቀው ሲጠበው፥ ሲጠፋው መድረሻ፤
መጠጊያ ሲያጣለት፥ ለሀዘኑ መርሻ።
ዛሬ ምን ልሆን ነው? ነገ ምን ይመጣል?
በጭንቀት ተዘፍቆ፥በሀሳብ ይሰምጣል።
መከራ ሲከበው፥ መልሶ መልሶ፤
ሀዘን ይቀመጣል፥ ሰው በራሱ ለቅሶ።

የሀጢያት ተራራ፥ ከቤቱ ቢያርቅህ፤
ዛሬ ቁራሽ ባይኖር፥ ባይሞላ መሶብህ።
የሰው እጅ ማየት፥ ሲያሳቅቅ ሲያደክምህ፤
እንደዚህ ሲሰማህ፥ አይሸበር ልብህ።

በሰው እጅ ከምትወድቅ፤
በእግዚአብሄር እጅ ውደቅ።
ከአምላክ አትጣላ፥ ከአምላክ አትኳረፍ፤
የማታውቀውን ቀን፥ ያውቃል ብለህ እለፍ፤

የተተወን የተረሳውን ሰው፥እግዚአብሔር ሲያስታውሰው፤
የተናቀን የተጣለውን ሰው፥እግዚአብሔር ሲያነሳው።
ወደ ቤትህ ስትመጣ፥የጠፋው ልጁ ስትገኝ፤
የሰው ፊት አይገርፍህም ፥ፍርፋሪም አትመኝ።
ከአባትህ ቤት ስትገባ፥ከአምላክ ስትታረቅ፤
የሰው ፊት አይፈጅህም፥ፀሀይህ መቼም አይጠልቅ።

አባታችን ሆይ፥
የምትኖር በሰማይ።
አትተወን እንጂ አንተ፥ የሰውስ አይደንቀንም፤
ያንተ ፀሀይ አትጥለቅ፥ የሰው እሳት አይሞቀንም።

ቀን ለጨለመበት፥ የደግ ቀን አንተ ስጥ፤
በወዳጄ ልብ ላይ፥ ፍቅርን ብቻ አስቀምጥ።
++++++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
  www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
ተአምር ምንድነው?
+++
ፅድቃችሁ የታለ
ተአምር የታለ
እኛስ ሙሴ……
በበትሩ ባህር ከፍሎልናል
ድንጋይ ተሸክመን በመሀሉ አልፈናል
ደመና ከልሎን ከነዓንን ወርሰናል
ከሰማይ ላይ መና ወርዶልን በልተናል
ከራፍዲም አለት ውሀ ጠጥተናል

አንተ አይሁዳዊ
ተአምር ምንድን ነው ትለኝ እንደ ሆነ
የትኛው ይደንቃል ትለኝ እንደሆነ
በል እንግዲህ ስማ እኔም አለኝ ድንቅ
እጅግ የሚጎላ እጅግ የሚረቅ
:
በሙሴ በትር ባህር መከፈሉ
ድንጋይ ተሸክሞ ማለፍ በመሀሉ
እርግጥ ነው ይደንቃል
ይሄ ግን ይጎላል ይሄ ግን ይረቃል
በመስቀሉ በትር ማለፍ ከሞት እሳት
በደሙ ማህተም ወደ ርስትህ መግባት

አንተ አይሁዳዊ
ፅድቃችሁ ወዴት ነው ትለኝ እንደሆነ
ተአምሩ የታለ ትለኝ እንደሆነ 
በል እንግዲህ ስማ
በህቱም ድንግልና አምላክን መፀነስ
የቃል ሰጋ በመሆን የአለም መፈውስ
በእናቱ ደመና ከልሎን መሻገር
የእዳ ፅህፈት ቀዶ ሲኦልን መበርበር
:
አንተ አይሁዳዊ….
ከነዓን ስትሻገር ፀሀይ ከከለለህ ከሰማይ ደመና
ታምሬ ማርያም ነች
ያቺ መሶበወርቅ በውስጧ ያለባት የህይወቴ መና
ሙሴ ከከፈለው የኤርትራ ባህር
እኔን የሚደንቀኝ
በመስቀሉ በትር ገሀነምን ማለፍ ሲዖልን መሻገር
ሰዎች ከገነቡት ከኢያሪኮ መፍረስ
እኔን ይደንቀኛል
በመስቀሉ ጉልበት የእዳ ደብዳቤዬ የሀጢያቴ መደምሰስ
አንተን ከሚደንቅህ ከበረሀው መና
እኔስ የሚገርመኝ
አምላክን መወለዷ በህቱም ድንግልና
:
ተአምርስ በለኝ የክርስቶስ መስቀል
ሞትን ለዘላለም ከሰንኮፉ ሚነቅል
:
ተአምርስ በለኝ
ምጥ ሳይሰማት ወለዳ ድንግል እናት ሆነች
ያለዘር ፀንሳ አምላክን ታቀፈች
 ይቀጥላል...
+++
"ተአምር ምንድነው"
ሀይማኖተ አበው
 ዘ ቅዱስ ኤራቅሊስ 
ም፵፱-ቁጥር ፵፭ 
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን እንዳስተማሩት
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
Click Me Load More....
የጎጆዋ መቅደስ....
ከፍ በይ ምድር፥ ዝቅ በል ሰማይ፤
ዘመኔ ከሽፎ፥ ይህንስ ከማይ።
የድካም ብዛት፥ ተቆጥሮ እንደ'ድል፤
እንዴት ልፎክር፥ በሌሎች ገድል።

የሳር ክዳኗ፥  የጎጆ መቅደስ፤
ሰበዝ በሰበዝ ፥እንደምን ትፍረስ፤
የተገነባው ትልቅ "ካቴድራል"፥
ቅጥሩ ቢሰፋም፥ ውስጡ ሊቅ ጎሏል፤

.....ይቀጥላል
+++
©ታዜና
   #መንፈሳዊ_ግጥሞች
   www.tgoop.com/Menfesawigetmoch
???
ማነው ሚጠየቀው፥ ስለሆነው ነገር?
መቼስ ምን ይባላል፥ እናት ፍቅር ሀገር፤
++++
Forwarded from ሙሴ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ክቡራን ደንበኞቻችን የቅዱስ ገብርኤልን አመታዊ ክብረ በዓል በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል አክብረን በረከትን ተቀብለን በሰላም ተመልሰናል።
ጥር 21ቀን የሚከበረዉ የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም (አስተርዮን) በግሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊት ኢየሩሳሌም ለማክበር ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀን ምዝገባ ጀምረናል።
መኘሻ ቀን ጥር 18/ መመለሻ ቀን ጥር 23/2017 ዓ/ም
ጉዞዉ ትራንስፖርት ምግብና ማረፊያን ያካትታል።
አዘጋጅ ማኅበረ ሙሴ ዘኦርቶዶክስ ተሕዶ
09 04 212121/0910 27 2601 /0911911601/0938621717
መነሻ ቦታ በዓሉበት አካባቢ
ትኬት ለማግኘት በዓሉበት ሆነዉ
1000530555668
እንኳን አደረሳችሁ...
?...መልሺ
የነገርኩሽንም ፍጹም እንዳትረሺ
ሶስት ሻማ ለኩሼ አንዱ ቀድሞ ቢቀልጥ
ምልክት ይሁነኝ ታሪኬ እንዲለወጥ
+++
2017 እሁድ የካቲት ፲፮
Forwarded from ማዕዶት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
  የደብራችን የያሬድ ሜዳ ብሔረ ጽጌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን 7 አባላት ያሉት መንፈሳዊ የጉዞ አጓጓዥ ኮሚቴዎችን የአዋቀረ ሲሆን የተዋቀረዉ ኮሚቴ  የተጠራበትን መንፈሳዊ አላማ ከግብ ለማድረስ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ/ም በአደረገዉ ስብሰባ በሰፊዉ ከተወያዬ በኋላ በጾሙ ዉስጥ 3 የተለያዩ ገዳማት ላይ የበረከት መንፈሳዊ ጉዞዎችን አዘጋጅቷል።
            በመሆኑም ጉዞ በተዘጋጀባቸዉ ገዳማት  ተገኝታችሁ በረከትን እንድታገኙ መንፈሳዊ ጥሪያችንን  እያቀረብን ይህ መልዕክት የደረሳችሁ የቤተ ክርስቲያናች ልጆች  ለሌሎችም ቅስቀሳ በማድረግ በጉዞዉ ላይ እንድትሳተፉ በበቤተ ክርስቲያናችን ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
          ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ጉዞዎች ወደ
1ኛ  ስዉሯ ማርያም ገዳም
         መነሻ ቀን እሁድ  መጋቢት 21 ቀን ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 700 ብር
2ኛ  ኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም
መነሻ ቀን መጋቢት 28/2017 ዓ/ም ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 600 ብር
3  ቤዛዊት ማርያም ገዳም
  እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ደርሶ መልስ ምግብን ጨምሮ 400 ብር
  አዘጋጅ የብሔረ ጽጌ ደ/ምሕረት ቅ/ገብርኤል እና ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ ጉዞ አዘጋጅ ኮሚቴ
    የምዝገባ ቦታ በደብሩ ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ
0911911601/0986337237 /0941210749/ 0912391324
  መነሻ ቦታዎች  1ኛ ብሔረ ጽጌ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ
2ኛ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ
3ኛ መገናኛ እሥራኤል ኤንባሲ
4ኛ ጣፎ አደባባይ
2025/05/29 00:50:56
Back to Top
HTML Embed Code: