Telegram Web
ከሁለት 3ኛው በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ጠሪነት ነገ በኢሊሊ ሆቴል ሊካሄድ የታሰበውን ህጋዊ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤው አባላት ከየክልላቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። ሆኖም የመንግስት አካላት ጭምር ጉባኤውን ለማደናቀፍ እስከዚችህች ደቂቃ ድረስ ተስፋ ሳይቆርጦ ሲተጉ ስታይ የሕዝበ ሙስሊሙ ተቋም ህዝበ ሙስሊሙ እንደሚፈልገው የተስተካከለ ቁመና እንዳይኖረው የሚፈልጉት አካላት እነማን ጭምር እንደሆኑ ሰሞኑን የብዙዎች ጭንብል ወልቋል።የመጅሊስ ምርጫ ከመንግስት ምርጫ በፊት ይደረግ ሲባል እንዳልነበር እንኳንስ የመጅሊስ ምርጫ ሊደረግ 33 ሰዎች የሚሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንኳ ከመንግስት ምርጫ በኋላ ይሁን ማለት ላይ ተደረሰ። ሰላም ሚኒስተር፣ደህንነት ተቋሙና ፖሊስ በዚህ አካሄዳችሁ የመንግስትን ፍላጎትና አቅጣጫ፣ አቋምና አቋቋም ህዝበ ሙስሊሙ በጊዜ እንዲያውቅ እያገዛችሁት ስለሆነ ሳያመሰግናችሁ የሚቀር አይመስልም!
«የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤው ከመንግስት ምርጫ በኋላ አድርጉ። አሁን መካሄድ የለበትም። ብታደርጉ እንኳ እውቅና አንሰጥም።»(የሰላም ሚኒስተር)

"Walgahi majlisa filannoo mootummaan booda godhaa. Amma godhamu hinqabu. Yoo gootan illee beekamti hinkenninu.''(Ministeera nagaa)
የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤውን ስብሰባ የአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ፈቀደ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ደግሞ አላውቀውም ብሎ ከተጀመረ በኋላ አሰቆመ።ስራ ተከፋፍሎ ጫወታው ቀጥሏል።
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿

Yaa'i majliisaa Waajjirri dhimma nageenyaa magaalaa finfinnee xalayaan Eeyyame. Polisiin magalichaa immo hinbeeku jechuun eega jalqabamee dhaabsisee. Hoji qooddatani xabachuun itti fufeera.
✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻✻
Forwarded from ዘቢባ (ሂታኒያ)
Harun media ሃሩን ሚዲያ
ሰበር ዜና
በዛሬው እለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት
ባካሄደው ጉባዔ የመጅሊሱን መተዳደሪያ ደንብ ና የዑለማ
መግባቢያ ሰነድ ማጽደቁ ታወቀ ።
ከዚህ በተጨማሪም ከየክልል መጅሊሱ የሚወከሉ ሶስት ሶስት
ሰዎች የጠቅላላ ጉባዔው አባላት እንዲሆኑ ውሳኔ መተላለፉን
ሃሩን ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል ።
የዛሬውን ጉባዔ እንዳይቀረጽ ፖሊስ ቢከልክልም የጉባዔ
የመጀመሪያ ቀን እነዚህን ውሳኔዎች በማስተላለፍ መጠናቀቁ
ታውቋል ።
ሃሩን ሚዲያ ውሳኔዎቹን በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝር
መረጃዎችን ይዞላችሁ የሚቀርብ ይሆናል
@ሃሩን ሚዲያ
ተጨማሪ መረጃ
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
1) የዛሬው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባን በተመለከተ ለጉባኤው አምስት አጀንዳዎች ጸደቁ።ቀጥሎ ከዚህ በፊት በ9 ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የነበረው የመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብና የኡለማ የአንድነት ሰነድ በአብላጫ ድምጽ ጸደቀ።በዚህን ጊዜ በኮሚሽነር መላኩ ፈንታ የተላክን ነን ያሉ ፖሊሶች መጥተው ስብሰባው ፈቃድ የለውም አቁሙ አሉ።

2) ዑለሞቹ ስብሰባው ህጋዊ መሆኑንና በመጅሊስ ከፍተኛው የስልጣን ባለቤት በሆነው ጠቅላላ ጉባኤ 2 ሦስተኛው ፊርሚያ መጠራቱንና ፈቃድ እንዳለው በመናገር ተከራከሩ።ስብሰባው በዚህ ተቋረጠ። በአሁኑ ሰዓት የእለቱ ቃለጉባኤ ተጽፎ ሊፈራረሙ እየጠበቁ ነው። ዶ/ር ጄይላን ስብሰባው እንዲቋረጥ ያዘዘውን ኮሚሽነር መላኩ ፋንታን በስልክ ቢያናግሩም የነገው ስብሰባ ይቀጥል አይቀጥል ገና አልታወቀም።

3) ዛሬ ጠዋት የጠቅላላ ጉባኤው አባላት የሆኑና ከየክልላቸው ለስብሰባው የመጡ ዑለሞችና የመጅሊስ አመራሮች ወደ የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሀጅ ዑመር ቤት በማቅናት «ችግር ካለ ንገሩን።በጉዳዩ ላይ እንነጋገርና ጠቅላላ ጉባኤውንም እርስዎ ይምሩ» በሚል ቢሄዱም ፕሬዝዳንቱ ዑለሞቹን ተቀብለው ለማናገር እንኳ ባለመፍቀዳቸው ከበር በጥበቃ እንዳይገቡ ተከልክለዋል። የሄዱትም የሚከተሉት ናቸው።ሀ) ሼህ ደረሳ (ከአፋር) ለ) የሱማሌ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሐ) ሼህ መርዲ(ከቤኒሻንጉል) መ) ሼህ ሙሀመድአሚን አያሽ(የሀረሪ ክልል መጅሊስ ፕሬዝዳንት) ሠ) ሼህ ሂዝቦላ(ከትግራይ) እና የጋምቤላ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ናቸው።

4) በ 2 ሦስተኛ አብላጫ ድምጽ የተጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ህገወጥ ጉባኤ መሆኑን እና ስለ ህዝበ ሙስሊሙ የመንግስት ምርጫ ተሳትፎን አስመልክቶ ሀጅ ዑመር እድሪስ ነገ ጠዋት በ 2:00 ላይ ለሚዲያዎች መግለጫ ለመስጠት በመጅሊስ ጽ/ቤት ለሚዲያዎች ጥሪ ተደርጓል።
ዛሬም ፖሊስ «የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ እንዲቋረጥ ታዝዣለሁ። ማድረግ አትችሉም» ብሏል።ሆቴሉም ኢሊሌ ሆቴልን በፖሊስ ተከቧል። በሌላ በኩል ከነሙፍቲ ጎን እንዲቋሙ በደህንነቶች አማካኝነት ዶ/ር ጄይላን ገለታ ፣ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ፣ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን እና የተወሰኑትን ዑለሞችን ለማግባበት እየተሞከረ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።
✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✹✹✹✹✹✹✹
Harras Polisiin "Ya'in majlisa akka dhaabbatu ajajameera gochu hindandeessan." Jedheera. Polisinis hoteela illillee marsee eegaa jira. Gara biraattis dahninattiin namoota mufti bira dhaabbatan baayyisuuf Dr Jeylaan Galataa, Sheh Abdulkarim Badradin,Sheh Abdulahmid Ahmaddi fi ulamoota bira amansiisuuf yaaliin godhamaa akka jiru ragaaleen mullisaa jiru.
—————————
🌍 ምን ዓይነት ጥላቻ ነው ሙስሊም ጠል አካላት ዘንድ ደጅ የሚያስጠናቸው?!
—————————
.
ለማይረባ የመዝሃብ ጥላቻ አጀንዳቸው እና ጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ከሙስሊም ጠል አካላት ጋር ተባብረው የራሳቸውን ሕዝብ ማስጠቃት ቅም የማይላቸው ጥቂት መርህ አልባ ሙስሊሞች ራሳቸውን በሐሰት "የዑለማ እና የሱፍያ ጠበቃ" አድርገው ሲመለከቱ ሳይ እጅግ ይገርመኛል! አብረዋቸው የቆሙትን ፀረ-ሙስሊም አካላት ሁኔታ ሲያዩ እንዴት ትንሽ ደንገጥ እንኳን አይሉም በአላህ!? ዓጂብ!
.
በምሳሌ ባስረዳ... አንድ የአሜሪካ ጥቁሮች መብት አቀንቃኝ ከሌሎች የጥቁር መብት ታጋዮች ጋር ውዝግብ ውስጥ ቢገባ እና ድንገት ጥቁር ጠሎቹ የ"ኩ ክሉክስ ክላን" (KKK) አባላት ግልብጥ ብለው ዋና አጨብጫቢው እና ደጋፊው ሆኖ ቢያገኛቸው የቆመበትን መስመር ትክክለኝነት መጠራጠሩ አይቀርም። ምክንያቱም የጥቁር መብት ለማስከበር አጀንዳው ጽንፈኛ የጥቁር ሕዝብ ጠላቶች አጋር ሊሆኑት እንደማይችል ይረዳል። መልካሙን እንደማይመኙለት ይገባዋል። (እንግዲህ አስበው ማርቲን ሊተር ሊንግ እና ማልኮም ኤክስ ተወዛግበው ከሁለት አንዳቸው KKK ጋር ሄዶ እርዳታ መጠየቅ እና መሥራት ቢጀምር ምን ያክል ዊርድ እንደሚሆን! 😭)
.
የእኛዎቹ "ሐውስ ኒግሮዎች" ግን ከነጭራሹ "አግዙን" ብለው የሚሮጡት በሙስሊም ጠልነት የታወቁ እና የሙስሊም ጠልነታቸውንም ራሳቸው እንኳ የማይጠራጠሯቸው አካላት ዘንድ ነው። አንድ ሙስሊም እንዴት ይህንን ያክል መርህ አልባ ሆኖ ወዳጅን ከጠላት የማይለይበት ደረጃ ላይ ይደርሳል? ምን ዓይነት ጥላቻ ነው እንዲህ ዓይናቸውን ያወራቸው?! ምን ዓይነት እልህ ነው እንዲህ ሞኝ ያደረጋቸው?! ሰው የፈለገ የመዝሃብ ፀብ ቢኖረው እንዴት የጋራ በሆነው እስልምናው ላይ ድንበር ያልፋል?! እንቆቅልሽ ነው የሚሆንብኝ!!!
.
#መጅሊስ #ጠቅላላጉባዔ #አገራዊሠላም #26ቱዑለሞች #ፌደራልመጅሊስ #የመጅሊስቦርድ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC #ኢትዮጵያ ©Isaac Eshetu
አሚሬ የፅናት አርማየ የሚከተለዉን መረጃ አዘል ማሳሰቢያ አድርሶናል......⬇️⬇️ ሸር ለማድረግ አሰስቱማ‼️

የመጅሊስን ችግር የተቋሙ ባለቤት የሆነውን ሕዝበ ሙስሊሙን እንደማያከብሩ የተቋሙን የመጨረሻ የስልጣን ባለቤት የሆነውን የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤን በማዋከብ ፣በማዋረድና መሰብሰብ እንዳይችሉ በተራ ፖሊሶች እያደናቀፉ በጓሮ በር በሚደረግ የደህንነት ቢሮ ስብሰባ አይፈታም።

ከ42 ቀናት በፊት በሰላም ሚኒስተር ስብሰባ ላይ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በ10 ቀናት ዉስጥ እንዲደረግና ችግሩ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዲፈታ የተደረሰውን ስምምነትን ሙፍቲ ራሳቸው ለዑለሞች «የደህንነት ሀላፊው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተነጋግረን ነው » እንዳሉት ያስቀረው የደህንነት ቢሮው ነው። የዛሬውን የኢሊሌ ሆቴል ስብሰባንም ያሳገደው የአቶ ተመስገን ጥሩነህ መስሪያ ቤት የሆነው የደህንነት ተቋሙ ነው።ይኸው ተቋም ዛሬ በ12:00 በጓሮ በር እነሙፍቲን ጠርቶ «ኑ እንነጋገር» ብሎ ጠርቷል።የጠቅላላ ጉባኤን እያደናቀፉ የጓሮ ስብሰባ ችግሩን እያስታመሙ ጊዜ ለመግዛት ሌላ ጫወታ በመሆኑ አያዋጣም። «እውነትን ይዣለሁ» ብሎ የሚያምን ዑለማም ሆነ ቦርድ «አለኝ» የሚለውን እውነት ይዞ በጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርቦ ፊት ለፊት ሞግቶ ይረታል እንጂ ከዑለሞች ሸሽቶ በጓሮ በር ከደህንነት ጋር ችግሮችን ልፈታ ነው ብሎ ማሰበብ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዳይደረግ እያደናቀፉና ዑለሞችን እያዋከቡ በጓሮ በር ከጥቂቶች ጋር በህዝበ ሙስሊሙ መብትና ተቋም ላይ የሚደረግ ጫወታ ይቁም!

©ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
የመጅሊስን ችግር የተቋሙ ባለቤት የሆነውን ሕዝበ ሙስሊሙን እንደማያከብሩ የተቋሙን የመጨረሻ የስልጣን ባለቤት የሆነውን የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤን በማዋከብ ፣በማዋረድና መሰብሰብ እንዳይችሉ በተራ ፖሊሶች እያደናቀፉ በጓሮ በር በሚደረግ የደህንነት ቢሮ ስብሰባ አይፈታም።

ከ42 ቀናት በፊት በሰላም ሚኒስተር ስብሰባ ላይ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በ10 ቀናት ዉስጥ እንዲደረግና ችግሩ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዲፈታ የተደረሰውን ስምምነትን ሙፍቲ ራሳቸው ለዑለሞች «የደህንነት ሀላፊው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተነጋግረን ነው » እንዳሉት ያስቀረው የደህንነት ቢሮው ነው። የዛሬውን የኢሊሌ ሆቴል ስብሰባንም ያሳገደው የአቶ ተመስገን ጥሩነህ መስሪያ ቤት የሆነው የደህንነት ተቋሙ ነው።ይኸው ተቋም ዛሬ በ12:00 በጓሮ በር እነሙፍቲን ጠርቶ «ኑ እንነጋገር» ብሎ ጠርቷል።የጠቅላላ ጉባኤን እያደናቀፉ የጓሮ ስብሰባ ችግሩን እያስታመሙ ጊዜ ለመግዛት ሌላ ጫወታ በመሆኑ አያዋጣም። «እውነትን ይዣለሁ» ብሎ የሚያምን ዑለማም ሆነ ቦርድ «አለኝ» የሚለውን እውነት ይዞ በጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርቦ ፊት ለፊት ሞግቶ ይረታል እንጂ ከዑለሞች ሸሽቶ በጓሮ በር ከደህንነት ጋር ችግሮችን ልፈታ ነው ብሎ ማሰበብ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዳይደረግ እያደናቀፉና ዑለሞችን እያዋከቡ በጓሮ በር ከጥቂቶች ጋር በህዝበ ሙስሊሙ መብትና ተቋም ላይ የሚደረግ ጫወታ ይቁም!
Rakkoolee majlisaa abbootii dhaabichaa kan ta'e hawaasni muslimaa akka khabaja xiqqaa hin qabneef qaama majlisaa ol'aanaa khan tahe "marii majlisaa khan waliigalaa" burjaajessuu fi salphisuun akka walitti qabamuu hin dandeenye poolisoota itti erguudhaan akka walgahii gufachiisuudhaan mana duuba naannawanii biiroo nageenyaa kheysatti marii dhoysaa godhuudhaan furamuu hin dandahu.

guyyoota 42 dura ministeera nageenyaatiin walgahii majlisaa khan waliigalaa guyyoota 10 kheeysatti akka taasifamuu fi rakkoon jirus marii sanirratti akka furamu yaada dhiheeysanii turan MUFTIIn afaan isaanitiin "ITTI GAFATAMAA NAGEENYAA OBBO TAMASGAN XIRUUNAH WALIIN MARI'ANNE" akkuma jedhameen kan walgahichas hambise waajjira nageenyaa ture.

walgahii har'a Hoteela ILIILLII godhamuuf tures kan akka hafu taasise dhaabbatuma Tamasgan Xiruunaan hooganamu dhimma nageenyaa kana ture. dhaabbatumti kun har'a 12:00 irratti "koottaa haa mari'annu" jechuun MUFTII faa yaamee jira.
yaa'ii waliigala ulamootaa gufachiisaa mana duuba deebi'anii marii goona jechuun yeroo gubuuf yoo ta'e male furmaata hin tahu.
"HAQAN QABA" jechuutti qaamni amanu ulamootaa waliin taa'ee marihatee haqa qabu sana fudhachiisuuf yaala ulamoota baqatee mana duuba naanna'ee qaama nageenyaa waliin mari'adheetan rakkoo fura wanti jedhu fudhatama tokko hin qabu.

Yaa'ii waliigalaa kan ulamaa'iin irratti walgeesse gufachiisaa namoonni muraasni waajjira nageenyaa waliin dhoysaan mari'atanii mirgaa fi dhaaba muslimootaa kanaan akka barbaadan taphachuun dhaabbatuu qaba.
የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ዉሳኔ በማሳለፍ አጠናቀዋል።


በትናንትናው እለት የተጀመረው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እየተዋከበም ቢሆን ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።በዚህም መሠረት የሚከተሉትን ዉሳኔዎችን አሳልፏል።
1) በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ በሚያዚያ 23 ቀን በሸራተኑ ጉባኤ ቀርቦ የነበረውን የመጅሊስ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብን እና የኡለሞች የአንድነትና የትብብር ሰነድን አጽድቋል።

2) የህዘበ ሙስሊሙ አንድነትን ለማናጋት በመንቀሳቀስ፣ በተናጠል ደብዳቤዎችን በመጻፍ፣ ህገ ወጥ ማህተምን በማስቀረጽና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ለተቋሙ ዉድቀት ምክንያት በመሆን የተገመገመው የተቋሙ ዋና ጸሐፊን ቃሲም ታጁዲንን በማንሳት ሀጅ ኑረዲን ደሊል ቀድሞ ወደ ነበረበት ዋና ጸሐፊነታቸው እንዲመለስ ወስኗል።

3) ለሌሎች የዑለማ ምክርቤት አባላት ደግሞ ማስጠንቀቂዎችን በመስጠትና ሌሎችን የተለያዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ቃለጉባኤውን ተፈራርመው ማጠናቀቃቸው ታውቋል።
«እንዴት አያታልሉን?» ክፍል አንድ


ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባለፉት በርካታ ዓመታት ጥያቄዎቻቸውን ለማስመለስ እና መብቶቻቸውን ለማስከበር በተለያዩ መንገዶች ታግለዋል።ትግሎቹ ከተካሄደባቸው መንገዶች መካከል በተለያዩ ደረጃ ካሉ የመንግስት የፖለቲካ ሹመኞች ጋር ፊትለፊት በመነጋገር፥በመጋፈጥና በመደራደር መፍትሄ የመፈለግ ጥረት አንዱ አቅጣጫ ነበር። ከነዚህ ሂደቶች ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ከዚህ ቀደም የገጠሟቸውን በተደጋጋሚ የመታለል ጉዳይን «ከምርጫ በኋላ ቢሆንስ ምን አለበት?» እና «የምርጫ ሰሞን ፖለቲካ» በሚል በጸፍኳቸው ሁለት ጽሑፎቼ ለማሳየት ሞክሬያለሁ።ከነዚህ ጽሁፎች ጋር ተያይዞ የተወሰኑ ወገኖች በመገረም ስሜት «ይህን ያክል እንዲህ ደጋገመው እንዴት ሊያታልሉን ቻሉ?» ሲሉ ጠይቀዋል።

አዎ ጥያቄው መነሳት ያለበት ነው። ምክንያቱም ስህተትህን ካላወቅክ ከስህተትህ መማር አትችልም። ከስህተትህ ካልተማርክ ደግሞ በዚያው መንገድ የመቀጠል እድልህ ሰፊ ነው። በተመሳሳይ መንገድ መጓዝ ደግሞ ተመሳሳይ እንጂ የተለየ ስፍራ ላይ አያደርስም።የተለየና የምትፈልገው ስፍራ ላይ ለመድረስ የተጓዝክባቸውን መንገዶችህን መፈተሽ በመንገዶችህ ላይ ስለገጠሙህና ወደፊት ስለሚገጥሙህ መሰናክሎች ማሰብ፥ ምክንያትና ዉጤታቸውን መረዳት ይሻል። ከየዋህነትና ከሞኝነት ለመላቀቅ በተከታታይነት ራስንና ተቀናቃኝን በጥሞና ማወቅንና መገምገምን ይሻል። ብልህነትን ለመጎናጸፍ ደግሞ ብልህና ብልጥ የሚባሉትን አካላትን አካሄድና ሴራን በሚገባ አስተዉሎ መከታተል ይገባል።

አዎ የእኛ የሙስሊሞች ችግር በፖለቲካ ረገድ ብስለት ማጣታችንና ስሜት የሚጫነን ከፖለቲካ ማህበረሰብነት ይልቅ «ሃይማኖተኝነት« ብቻ የሚጫነን መሆናችን አንዱ ችግራችን ነው። ይህ በፖለቲካ ረገድ ንቁና ብቁ ያለመሆን ችግር የፖለቲከኞች መጫወቻ ሳያደርገን የቀረ አይመስለኝም። ይህ ችግር ይቀረፍ ዘንድ የታዘብኳቸውን ፖለቲከኞች የሚጠቀሟቸውን የማሳመን፥የማዳከም፥ የማጥቃት፥ የማታለልና ግራ የማጋባት ስልቶችን አስመልክቶ የግል ምልከታዎቼን እንደሚከተለው ላጋራችሁ ወደድኩ።

ቆም ብለን ፖለቲከኞች ይህን ሁሉ ዓመታት «እንዴት አታለሉን?» ብቻ ሳይሆን ከኛ ባህሪና ማንነት አንጻር «እንዴት አያታልሉን?» ብሎ መጠየቅም ይገባል።

1. የጉዳዮችን ምንነትና ተጨባጭ ማስረጃዎችን ሳይሆን የተሳታፊ ሰዎችን ማንነት ብቻ በማየት በጭፍን የሚደግፍና የሚቃወም ህዝብ ሆነን እንዴት አያታልሉን?

2. በትንሽና በብልጭልጭ ነገር የሚደሰትና የሚያስደስት አክቲቪስትና ሕዝብ ሆነን እንዴት አያታልሉን?

3. በችግር ጊዜ ድምጻቸውን አጥፍተው መልካም ነገር ሲገኝ ብስራት ለመናገር ብቻ ካደፈጡበት ብቅ የሚሉ ሰዎችን በበዙበት ሁኔታ እንዴት አያታልሉን?

4. እየሆኑ ባሉ ነገሮች ዝርዝር መረጃዎች ሳይኖራቸው «እኔ የምለውን ተቀበሉ።እንደኔ ካላሰባችሁ» ብለው ችግር የሚፈጥሩ ሰዎች በበዙበት እንዴት አያታልሉን?

5. ፖለቲካን ሳያዉቁ፥ አዋቂዎች ሲነግሯቸውም ለመስማት ዝግጁ ያልሆኑ በዑማው ጉዳይ ላይ ግን ከፖለቲከኞች መገናኘትንና መምከርን ራሱኑ እንደግብ የያዙ ይመስል ሳይዘጋጁ ለዚሁ የሚጣደፉ ሰዎች በሞሉበት እንዴት አያታልሉን?

6. ከህዝቡ ችግር፥የመብት መጣስና የነጻነት እጦት ይልቅ ቅድሚያ የባለስልጣናት ክብርና ችግሮች የሚያሳስባቸውና የሚያስቀድሙ ሰዎች በኃላፊነት በህዝቡ ጉዳይ እንዲወስኑ ስናደርግ ምንም ሳይመስለን እንደ ሕዝብ እንዴት አያታልሉን?

7. «ለመብታችሁ ታገሉ» ሳይል ዝም ማለትን መርጦ «ባለስልጣንን ታዘዙ» ብቻ ላይ አተኩሮ የሚያስተምሩት በበዙበት እንዴት አያታልሉን?

8. ለህዝቡ ቁልፍና ወሳኝ ዘላቂ ጉዳዮች ከማዋል ይልቅ ያን ያክል ዘላቂ ጥቅም ለሌላቸው ጉዳዮች ገንዘባችንን ለማውጣት ብቻ የሚንፈልግ ዘንባሌና ስሜት ያለን ሆነን እንዴት አያታልሉን?

9. ለሕዝቡ መብትና ጥቅም ይልቅ የእርሱ በስልጣን ላይ መቆየት ዋናው ቅዳሚ አጀንዳቸው የሆነ፥እርሱ ከተመቻቸው ለወገኖቻቸው ችግሮች ደንታቢስ አልያም ፈሪ የሆኑ ሙስሊም ባለስልጣናትን «ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ» ችግራችንን «ተረድተው ይፈቱልናል» ብሎ እጅን አጣምሮ ከነርሱ የመጠበቅ አባዜ ተጠናውቶን እንዴት አያታልሉን?

10. በየደረጃው የየራሱን ሚናና አስተዋጽኦን ሳይወጣ ችግርን መፍታት፥መጋፈጥና አቤቶታ ማቅረብን እንኳ ሌሎች እንዲተገብሩለት የሚፈልግ በበዛበት እንዴት አያታልሉን?

11. በችግርና አጣብቂኝ ጊዜ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመንጫት ለወገኖቻቸው መንገድ ማመላከት ሲገባቸው ድምጻቸውን አጥፍተው ቆይተው በሰላሙ ጊዜ «አለሁ» ብለው የሚወጡ ምሁራን በበዙበት ሀገር እንዴት አያታልሉን?

12. ችግሮቻችንን ፊትለፊት በመነጋገር ለመፍታት ፍላጎቱና ቁርጠኝነቱ የሌለን ሕዝቦች ሆነን እንዴት አያታልሉን?

13. የግል ጸቡን፥ጥቅሙንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሕዝቡን ከጎኑ ለማሰለፍና ፍላጎቱን ለማሳካት ሲል የዲን ልባስ የሚያላብስ ሙስሊም ባለበት እንዴት አያታልሉን?

14. በትንሽ በትልቁ ለመለያየት እና በሕዝቡ መካከል ድልድይ ሳይሆን የግንብ አጥር የማቆም ዝንባሌ ያላቸው ዓሊሞች፥መሻኢኮችና ዳዒዎች እያሉን እንዴት አያታልሉን?

15. ችግሮችን በዘዴ ተጋፍጦ በተሰጠው ኃላፊነት ለመስራትም፥ ስፍራውን ለሚሰሩት ለመልቀቅም የማይፈልግ አመራር በበዛበት እንዴት አያታልሉን?

16. የሀገሬ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጉዳይ ይመለከተኛል ብለን መቆም ሲገባን በተግባር ግን ለሌሎች «ሌላውን ሁሉ ያዙ ሃይማኖታችንን ብቻ ተዉልን» ያልን የሚመስል አካሄድን የሙጥኝ ብለን ይዘን እንዴት አያታልሉን?

17. ከህወሃት ዘመን አንስቶ ሕዝበ ሙስሊሙን የማናቆርና የመከፋፈል ተልዕኮን ከደህንነት ቢሮ ቢሮ ተቀብለው ለዓመታት ሕዝቡን ሲያስጠቁና ሲያሰቃዩ የቆዩትን ጠምጣሚ ካድሬዎችንና ዘራፊዎችን በመጅሊስ መዋቅር ዉስጥ እንዲቆዩ ፈቅደን እንዴትስ አያታልሉን?

ከገባንበት አዘቅት መውጫውን በር ለማወቅ የገባንበትን በር በርና መንገድን በብልሃት መፈለግ ግድ ይላል። እንዳንወጣ የተጫነንን የችግርና የሴራ ሸክም በብልሃት ከላያችን ላይ ለማንሳት ሳንሞክርና ከገባንበት ጉድጓድ ሳንወጣ በተለመደው መንገድ የመጓዝ ሞኝነት አይበቃንምን? ሼህ ሙሀመድ ጋዛሊ እንዳሉት «ጠላትህን ለማገልገል የግድ ተላላኪ መሆን አይጠበቅብህም። ሞኝ ከሆንክ ይበቃል።» ሆነ የኛ ነገር።

ይቀጥላል…
ከመጅሊስ መታገዳቸው ብቻ በቂ አይደለም
================================
ያኔ መጀመሪያውኑ ጠሚው ለውጥ አመጣሁ ሲል፤ ተቋሙን ሲያቆሽሹት የነበሩትን የቀድሞ የመጅሊስ ሰዎችን ከተቋሙ ውስጥ ቢያጸዷቸው ኖሮ ይህ ሁሉ መስዋዕትነት ዛሬ ላይ አይታይም ነበር። ግና በአጉል "አቃፊነት እና ሆደ ሰፊነት" ምህረትና ይቅርታ በሚል ብሂል አስጠግተዋቸው ዳግም እንዲያሰራሩ እድሉን አመቻቹላቸው።
ለማንኛውም ያለፈው አልፏል።

አሁንም ቢሆን "ለመስለሐ" በሚል ሰበብ የቀሩ አካላት ካሉ ለመጅሊሱ ተመንጥረው መውጣት አለባቸው።
በጠቅላላ ጉባዔው ከኃላፊነቱ የታገደው ቃሰም ታጁዲን እና የርሱ አይነት ሚና ሲጫዎቱ የነበሩ ግለሰቦች፤ ከኃላፊነታቸው ከመታደጋቸው ባሻገር እስካሁን ድረስ በሠሩት ጥፋት ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

ይህ ካልተደረገ አሁንም ለውጥ አለ ማለቱ ይከብደናል።

በህዝበ ሙስሊሙ ሃብትና ንብረት፣ ጊዜና አንድነት ላይ ሴራ የጠነሰሱ አካላት ይሠሩት በነበረው ሥራ ተጠያቂ መደረግ አለባቸው።

ስለዚህ ቀጣዩ ሂደት፦
①) የተላለፈውን ውሳኔ ወደ መሬት በማውረድ ተግባራዊ ማድረግ፥ በውስን ግለሰቦች እጅ ቁጥጥር ስር ያሉ መስጂዶችን ለሁሉም የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ ክፍት ማድረግ፥ ትክክለኛ መሪዎችን ማስቀመጥ፣
②) እስካሁን ወንጀል የሠሩ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ ተቋማዊ አሠራሩን ማዘመን እና ሌሎችም ይሆናሉ።

ወንጀለኛ ተጠያቂ ካልተደረገ ለሌላ ተጨማሪ ወንጀል ይነሳሳል።
«ያለውን ጫና እንደምንም ተቋቁመው ውሳኔ ለማሳለፍ መብቃታቸው የሚደነቅ ሆኖ ሳለ፤
ይህ ጫና ለምን ተደረገ⁉️ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ እስኪገኝ ድረስ መጠየቅ አለብን።»
—————————
🌍 አሽረፈል ኸልቅ ጉዳዩን አስቀድመው ጨርሰውት የል?!
—————————
.
ለማይረባ ጊዜያዊ ጥቅም እና ዝና የገዛ ሕዝባቸውን መብት አስማምተው እየሸጡ እና ለሙስሊም ጠል አካላት በማጎብደድ ፈተና እየፈጠሩ ያሉ ጥቂት ሙስሊሞችን ስመለከት ሁልጊዜም የሚከተለው የአሽረፈል ኸልቅ (ሶ.ዐ.ወ) ሐዲስ ትዝ ይለኛል...
.
———
"የገንዘብ እና የዝና ጉጉት የጠናበት ሰው በዲኑ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በበጎች መሐል የተለቀቁ ሁለት የተራቡ ተኩላዎች በበጎች መንጋ ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት የበለጠ ነው።"
———
.
ሐዲሱ ሶሒሕ ሲሆን በሱነን አትቲርሚዚ 2376 ተዘግቧል (ያወራው ከዕብ ኢብኑ ማሊክ አል አንሷሪይ ነው)
.
ለጥቅም እና ለዝናቸው የሚያደርጉት ግለሰባዊ ሩጫ መላውን ሙስሊም ችግር ውስጥ ሲከት የማይታወቃቸው፣ እነሱ አግዝፈው በሚያስቡት ደቃቃ የሠፈር ፀባቸው ምክንያት የኢትዮጵያ ሙስሊም መብት መከበር ሲስተጓጎል ቅም የማይላቸው፣ ትልቁን ስዕል በማየት ፈንታ ከሙስሊም ጠል አካላት ጋር አሳፋሪ ትዳር በመመሥረታቸው ራሳቸውን የማይታዘቡ ጥቂት ሙስሊሞች ሁልጊዜም ሥጋት መደቀናቸው አይቀርም። የሙስሊሙ ሚና ደግሞ ወገብ አጥብቆ መታገል፣ የተላላኪነታቸውን ገመድ መበጠስ ነው።
.
ኢንሻአላህ ድል ደግሞ ከታጋዮች ጋር መሆኗ ተፈጥሯዊ ውጤት ነው - ትዕግሥት ብቻ ይኑረን!
.
#እንዳንዘናጋ #መጅሊስ #ጠቅላላጉባዔ #አገራዊሠላም #26ቱዑለሞች #ፌደራልመጅሊስ #የመጅሊስቦርድ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC #ኢትዮጵያ ©Isaac Eshetu
2025/07/14 03:06:51
Back to Top
HTML Embed Code: