Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
يا من عرفت محمدا بكماله

ጁሙዓን በሰለዋት እናድምቅ


በወንድም ፈትሒ ዒዘዲን ድምፅ
በሰለዋት አካባቢያችንን እናድምቅ
Forwarded from 🌷
Minber Tv

የሙከራ ስርጭት ጀምሯል!

Frequency.....12521
symbol rate....27500
Polarization....vertical
Forwarded from ABU DAWD OSMAN
Forwarded from 🌷
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

በአሜሪካ ሚኒሶታ የሚገኘው የተውፊቅ እስላማዊ ማዕከል እና መስጂድ አስተማሪ እና አሊም የነበሩት ሼይኽ ኡመር መልካ ወደ አኼራ ሄዱ::

ሼይኽ ኡመር በመኖሪያ ቤታቸው አልጋቸው ላይ በተኙበት ነው ዳግም ላይመለሱ ወደ አኼራ የሄዱት::

በርካታ አሊሞች በዚህ አመት ብቻ ወደ አኼራ እየነጎዱ ነው

አላህ ይዘንላቸው አላህ ማረፊያቸውን በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው

ለቤተሰቦቻቸው፣በሚኒሶታ ለሚገኙ ጀምዓዎች በሙሉአላህ ሰብሩን ይልግሳቸው
ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተናዘዝላቸው ብባል
★★★//★🌟★//★★★

ሰውየው ሚስትህ አረገዘች ወይ? ቢሉት "ማንን ወንድ ብላ" አለ ይባላል።

ያ ሰው ሚስቱ ያላረገዘችው የገባው በዚህ መልኩ ነው። ምናልባትም መካንነቱ ያለው እሱ ጋር ይሆናል፣ ምናልባትም መካን መሆኗን እያወቀ አማራጭ መፍትሔውን ሳያስብና ሳይሞክር " ማንን ወንድ ብላ!" እያለ እየቆጨው ይሆናል

እናም ወንድ ሳትሆን ወንድነትህ በሌላው ይመሰከርልህ ዘንድ እየጠበቅክ ነው፣ የመደራደር አቅም ሳይኖርህና የመደራደር አቅምህን ሳትገነባ ስለምን አራከሱኝ እያልክም ነው! አይጥ ሆነህ ሳለ ሞት ፍለጋ የድመት አፈንጫ ማሽተትን ድሌ እያልክ እየጨፈርክ ነው። የውስጥ ተቃርኖህን በቅጡ ሳታስታርቅ ጦር አውድማ ላይ ተገኝተህ በፉከራ እየተንጎማለልክ ነው።

ከሚለምን የሚመፀውት፣ ከሚጠይቅ የሚሰጥ፣ ከሚያለቅስ የማያለቅስ፣ ከሚማረር የሚያመሰግን፣ በረት አልባ ከመሆን ባለ በረት መሆን፣ ከተጠምዛዥነት ክንዴ ብርቱነት፣ ከመርከስ መወደድ፣ ከጠባቂነት አድራጊነት፣ ከህልም እንጀራ የጨበጧት እንጎቻ፣ ከቂልነት ገምናነት፣ ወድቆ ከመፈራገጥ ከቻሉ አለመውደቅ፣ ያለችን ኃይልና አቅም ከመነጣጠቅ መተባበር ይሻላልና ውስጠ ሂስ ብታደርግ አይሻልም ወይ እላቸዋለሁ።

መንግሥትን መቃወም ግብ አይደለም! በመንግሥት መማረር ፈርድ አይደለምመቃወም፣ ማልቀስ፣ መንጨርጨር ብሶትን መግለፅ ብቻውን ስኬት አይደለም ጥላት ማብዛት፣ ያለ አቅም ከሁሉም መጋጨት ጀብደኝነት እንጅ ጀግንነትም አይደለም

ዜጎች፣ ቡድኖች! የሰው ኃይል እያለሙ፣ እያበቁና እያደራጁ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎ አድርገው እጣዎቻቸውን በእጆቻቸው አሻራ ሲበይኑ አንተ ከሙቅ አልጋህ ነበርክና ከእንቅልፍህ ስትነቃ ለሚጠብቅህ መዘጋጀት እንዳለብህ ማስታወስም ይኖርብኛል

በከመቅረት ማርፈድ ይሻላልና አሁንም አልረፈደም ድምፅህን አጥፍተህ፣ የኦና ቤት ጩኸትህን ቀንሰህ መሬት የወረደ፣ ውል ያለው፣ በወጉ በፋራ የተተለመ፣ በቅጡ የተሰደረ ስራ ስራና ለፉከራውም ለሽለላውም ኋላ ትደርሳለህ።

በተሳትፎህ በሀገርህ ላይ መልክህን ሥራ ፊትህን ወደ ተረምህርት አዙር ተምረህ አለቃህን ቀንስ በየአገልግሎት መስጫ ተቋሙ ተቀጥረህ ቀጣሪ ሁንየአቢዮትና ለውጥ ግምባር ሆነህ መሞት ጥግህ ሆኖ አታፍጅ ያልዘራኸውንም አትናፍቅ ፈንጅ አምካኝነት ኬላህ ይሆን ዘንድ አትፍቀድ!

ኢትዮጵያ በቢሮክራሲና በህቡእ መንግሥቷ ወደድክም ጠላህም ኦርቶዶክስ ናት። እናም ፈንክሽናሊ የአገር ባለቤት አይደለህም ኪንግ ሜከሩ ፕሪስትሁድ መሆኑን አምነህ እየጎመዘዘህም ዋጠው እና

ካገሩ የወጣ ከአገሩ እስኪመለስ
ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ

እንዲሉ አባቶች አገርህ ላይ መልክህን እስክታየው ድረስ መሬት ላይ ማስን፣ ድከም፣ ዘርህን ዝራ፣ እሻራህን አኑር፣ የመደራደር አቅምህን ገንባ፣ የሰው ኃይልህን አብቃ፣ በተሳትፎህ ነገህን በይን ያኔ ወደ አገርህ ተመልሰሃል ማለት ነው። ያኔ መልክህን አገርህ ላይ አትመሃል ማለት ነው። ያኔ ኪንግ ሜከሩም ኪንጉም ሆኖ የመመረጥ አቅም አደርጅተሃል ማለት ነው።

እናማ ወዳጄ በእጆችህ፣ በጥረትህ፣ ጩኸትህን ቀንሰህ መሬት ያዝና ወደ አገርህ ተመለስሚና አልባ የሆንክበት ቤት እንግዳ እንጅ ባለቤት አይደለህም፣ የምታለቅስበት ቤት የለቅሶ ድንኳን እንጅ ደስታህን የምታስረግጥበት ቤትህ አይደለም ግዴለም ወዳጄ ወዳገርህ ተመለስ ወደአገርህ እስክትመለስም ቢጩንህ አህያ ቢለጉሙህ ፈረስ ወደህ ሳይሆን በግድህ መሆንህ አይቀርምና ወደህ ድምፅህን አጥፍተህ፣ መላተም ኃይል ማባከኑን ትተህ መሬት ይዘህ ፍጋ ያኔ ማር ተራ እንገናኛለን
ዶ/ር ጀማል መሀመድ የአወሊያ ቦርድ ሰብሳቢ አጭር መልዕክት

አወሊያን የማዳን ጥሪ!

ከጥቅምት 13 - 30 /2013 የሚቆይ አለም አቀፍ መርሃ ግብር!


Telegram Group = @Awoliafund0


Whatsapp Group = https://chat.whatsapp.com/DQ2QHWrT55xDcX2g9Y0pxK


Facebook Account Link = https://www.facebook.com/profile.php?id=100057079620849

አወሊያን የማዳን ጥሪ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉል!
@Awoliafund
Forwarded from ABX
የሰው ርሃብ
******
'ሰው ራበኝ' አለኝ ሰሞኑን የሆነ ሰው፡፡ እናንተስ ግን ሰው ርቧችሁ ያውቃል?

* ከዉጭ አገር መጥታችሁ ሰው ዚያራ እዚህም እዚያም ዘመድ እና ጓደኛ ቤት ስትሄዱ ሁሉ ሰው ቢዚ ሆኖባችሁ ብቻችሁን የቀራችሁበት አጋጣሚ የለም?
* እቤት ታማችሁ ተኝታችሁ በራችሁን ከፍቶ ገብቶ የሚጠይቃችሁ ሰው ናፍቋችሁ በር በሩን ስታዩ የዋላችሁ ያደራችሁበት ቀንስ የለም?

* የሆነ ሀሳብ አስጨንቆ ይዟችሁ የምታማክሩትና ቁጭ ብሎ የሚያዳምጣችሁ ሰው አብዝታችሁ ያሰባችሁበት ጊዜ የለም??

* ላግኝህ ያላችሁት የድሮ ጓደኛ ቆይ እሺ ዛሬ ነገ እንዳለ ሲቀጥራችሁ ዛሬ ስንት ቀን ሆነው?

* ሰው ናፍቋችሁ ረጅም ወሬ ለማውራት ጓግታችሁ የሆነ ሰው ጋ ስልክ ደዉላችሁ ቆይ አንዴ ብሎ ዘግቶ ብትጠብቁ ብትጠብቁ በዚያው የዉሃ ሽታ የሆነባችሁ ጊዜ የለም?

* እስቲ ይቅለለኝ ብላችሁ መተንፈስ አስባችሁ ሁኔታችሁን አስተዉሎ ' ምን ሆነህ ነው?' ብሎ የሚጠይቅ ወዳጅ አላጣችሁም ?

* በስደት ዓለም ሆናችሁ የአገር ቤት ሰው ለዐይን እንኳ የተራባችሁበት ጊዜ የለም?

* በብቸኝነት፣ ባዶነት፣ ድካምና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት የተወረራችሁበት ጊዜ የለም?

አላህ (ሱ.ወ.) የሰዉን ልጅ ምድር ላይ ብቻዉን እንዲኖር አላደረገዉም፡፡ ያለ ሰው ኑሮ የሚከብደው ማኅበራዊ እንሰሳ አደረገው፡፡ ሰው ብቻዉን አንድ ነው ፤ ከሰው ጋር ሲሆን ግን ብዙ ነው፡፡
የቱን ያህል ብቸኝነትን ብንለምድም የሆነ ቀን ላይ ሰው ይናፍቀናል፡፡ እንደ ምግብ ሁሉ ይርበናል፤ እንደ ዉሃም ይጠማናል፡፡ የሰው ጨዋታ፣ ወጉ፣ ቀልዱ፣ ቁምነገሩ፣ ምክሩ፣ ሀሳቡ፣ ሙግቱ፣ ክርክሩ … ይናፍቃል፡፡ አይደል እንዴ!
ሰው ዱንያ ላይ ሲኖር በችግር የተከበበ፤ በሐዘንም የታጀበ ነው፡፡ ለዚሁ ነው መሠለኝ የአላህ ነቢይ ሰዎች አብሽሩ! ማለት የሚያበዙት፤ ማፅናናትን የሚወዱት።
* እርሣቸው እኮ ናቸው 'በመስጊድ ዉስጥ የወር ያህል ኢዕቲካፍ ከመቀመጥ የአንድን ጉዳይ ለመፈፀም መሯሯጥን እመርጣለሁ' ያሉት፡፡

* እርሣቸው እኮ ናቸው ከትንሽ ከትልቁ ጋር ጊዜ ወስደው ያወጉት። ከአገልጋያቸዉም ሆነ ከተከበሩ ሰዎች ጋር ቁጭ ብለው የተመገቡት፡፡

* እርሣቸው ከሰው ሲያወሩ በሙሉ ፊት ነው፤ ሓጃ ሲያዳምጡም እህ … ብለው በሙሉ ልብ ነው፤ ሲያማክሩም ከቀልባቸው ነው፡፡

* የሰዉን ችግር እያዩ እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ ድርቀት ነው፤
* የሰዉን ብሦት አላማዳመጥ እዝነት ማጣት ነው፤
* ሰዉን መናቅ ክፋት ነው፤
* ሰዉን እየለዩ ማናገር፣ እየመረጡ ስልክ ማንሳት ኩራት ነው፡፡
* አበድረኝ ቸግሮኛል ላለ ሰው አለማበደር ጭካኔ ነው። በመስጠት ማገዝ ቢያቅተን በማበደር እናግዝ እስቲ ።
* ሀሳብን አለማስጨረስ ትንሽነት ነው፡፡
* ኢስላም ለሰው ልጅ ትኩረት ስጡ ይላል።
* በዉስጥ እንኳን መጥቶ አሰላሙ ዐለይኩም ላለ ሰው መመለስ ግድ ነው ብዬ አስባለሁ።

ጌታዬ ዉብ የሆኑ ባህሪዎችን ሁሉ ታጎናጽፈኝ ዘንድ ለመንኩህ፡፡
ዘመኑ ሰው ናፋቂ ደጋጎች ሰዉን የተራቡበበት ዘመን ነው፡፡ ከሸይኹ አጠገብ ደረሳ የለም፤ ከዓሊሙ ጎን አዳማጭ አይታይም፡፡
ዘመኑ ግለኝነት የበዛበት፤ ሁሉም ነፍሲ ነፍሲ የሚልበት ሆኗል፡፡ አንዳንዴ ሁኔታዎችን ሳስተዉል ቂያማ የቆመች ሁሉ ይመስለኛል፡፡ ሰው ከሰው የሚሸሽበት ዘመን፡፡
በዚያ ቀን ሰው ከወንድሙ፣ ከእናት አባቱ፣ ከሚስቱ፣ ከልጆቹ፣ … ይሸሻል፡፡ ሁሉም በራሱ ጉዳይ ቢዚ ይሆናል፡፡
የውመ የፊሩል መርኡ ሚን አኺሂ፣ ወኡሚሂ፣ ወአቢሂ ….
ታዲያ ሁኔታችን ከቂያማ ቀን በምን ተለየ??

፨፨፨፨
ሼር ይደረግ

http://www.tgoop.com/MuhammedSeidABX
Forwarded from 🌷
Eliyas khedir🖊

በደቡብ ክልል #በጉራ_ፈርዳ በንፁሀን ላይ በመስጅድ ውስጥ ሶላት ላይ ባሉበት በታጠቁ ሀይላት የሽብር ሰለባ ለሆኑት ወንድሞቻችን በየምንገኝበት ሀገር እና ኢንባሲ(ቆንፅላ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ ጭምር ፍትህ በመስጅድ ውስጥ ሆነው ለተሰው ንፁሀን በአንድ ድምፅ እንቃወም!!! ሞት ይብቃን

የምትኖርበት አካባቢ ላይ ያለህው አንድ አንተ እንኳን ብትሆን ድምፅ ሁን

#ፍትህ_በጎራፍረዳ_ለተሰወኑ_ንፁሀን
#ፍትህ_በደም_ለረከሱ_መስጅዶች
#ፍትህ_ለንፁሀን
#ሞት_ለገዳዮችና_አባሪዎቻቸው
ትኩረት የሚሻው የጉራ ፈርዳው የሰላማዊ ዜጎች ጭፍጨፋ

በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የአያሌ ንፁኃን ሰዎች ህይወት ማለፉን ከተለያየ አካላት ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ባለፉት ሳምንታት መሰል ጥቃቶች በቤኒሻንጉል ክልል የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል።

በጉራ ፈርዳ ወረዳ በአሮጌ ብርሃን፣ ሹጲ እና ዠኒቃ ቀበሌዎች የደረሰው ጥቃት በኋይማኖት አባት (ቓዲ)፣ ወላድ፣ እርጉዝ እና ህፃናት ሳይቀሩ የተጨፈጨፉበት በመሆኑ ጥቃቱን የከፋ ያደርገዋል።

በዚህ ጥቃት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው ቢፍቱ ወረዳ አካባቢ ለተጠለሉት ወገኖች ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ስንጠይቅ መንግስት በዚህ እኩይ ወንጀል እጃቸው ያለበትን አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ በማቅረብ በቦታው መረጋጋት የማስፈን ሚናውን በተገቢው ሁኔታ እንዲወጣ እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

በአጠቃላይ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ማንኛውም በንፁኋን ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች እያወገዘ የሃገሪቱ ህልውና መሰረት የሆኑትን የአብሮነት፣ መከባበርና እና መተዛዘን እሴቶች መመናመንና የስርአት አልበኝነትና ጭካኔ መበራከት ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል።

በመሰረቱ የሰው ልጅ ህይወት (ዘር፣ ጎሳም ሆነ እምነት ሳይልይ) እጅግ የተከበረ እንደመሆኑና የህዝባችን መገለጫ የሆነውን ሰላማዊነት የመጠበቅ የሁሉም ወገን ኋላፊነት ሆኖ የጋራ ሃገር ግንባታ ያለ ሰላም እና ደህንነት የማይታሰብ እንደሆነ እናምናለን።

የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የመንግስት አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ወገኖች በዚህ ረገድ የበኩላቸውን ኋላፊነት በመወጣት መሰል ጥቃቶች እንዳይከሰቱ የመፍትሄ መንገዶች ላይ መስራት እንዳለባቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በዚህ ረገድ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለይም የአስተዳደር እና ስራ አመራር ቦርዱ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት እየገለፀ የትብብር ጥሪውን ያቀርባል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
የስራ አመራር ቦርድ
ጥቅምት 14/ 2013
አወሊያን የማዳን ጥሪ!!!

ከጥቅምት 13 - 30 /2013 የሚቆይ አለም አቀፍ ዕርዳታና ማሰባሰቢያ ፕሮግራም!

ለአወሊያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የተከፈቱ የባንክ አካውንት ቁጥሮች
ስም (Awolia Relief and Development Organization) አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ = 1000343434343

አዋሽ ባንክ = 01308832356901

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ = 3708183

ህብረት ባንክ = 1199711330712017

ዳሽን ባንክ = 7941619546011

ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ = 1000045091442

Whatsapp Group = https://chat.whatsapp.com/DQ2QHWrT55xDcX2g9Y0pxK

Facebook Account Link = https://www.facebook.com/profile.php?id=100057079620849

Telegram Group = www.tgoop.com/Awoliafund0

Telegram Channel = www.tgoop.com/Awoliafund
Forwarded from ABU DAWD OSMAN
Forwarded from በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ
ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ጥሪ
=====================

«የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ወዳጅ ሙስሊም ከሆንክ፤
ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ ለሌላውም አስተላልፍ፤ ያላወቁትን አሳውቅ፤ የዘነጉትን አንቃ!»
||
ሰሞኑን ለሙስሊሙ ዓለም አንድ የጋራ ጥሪ ተላልፏል።
የጥሪ መንስኤ፤ የነቢዩን ﷺ ክብር በሚነካ መልኩ በፈረንሳይ የተሠራውን የካርቱን ፊልም ተከትሎ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን ድርጊቱን ከመኮነን ይልቅ በነፃነት ስም ማለፉ ነው።

ይህ ጉዳይ መላውን የዓለም ሙስሊም አስቆጥቷል። ሳዑዲ ዓረቢያን ጨምሮ በርካታ ሙስሊም ሃገራት ድርጊቱን አውግዘዋል።

ሌላው የሙስሊሙ ዓለም ቢያንስ በትንሹ ፈረንሳይን ለመቅጣት፤ ወደ ውጭ የምትልካቸውን ምርቶች ማንኛውም ሙስሊም ባለመግዛትና ባለመሸጥ የኢኮኖሚ ኃይሏ ተንኮታኩቶ ከጫማችን ስር እንድትወድቅ ማድረግ ነው።

በተለይም እንደ ሃገራችን ኢትዮጵያ የንግዱን ዓለም በስፋት የተቆጣጠሩት ሙስሊሞች እንደመሆናቸው መጠን፤ ለዚህ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ጥሪ አወንታዊ ምላሽ ይሰጡ ዘንድ ያላወቁት እንዲያውቁ መልዕክቱን ለሁሉም ሙስሊም ሼር በማድረግ እናስተላልፍ።
በተለያዩ ገጾች እንበትነው።

አሁኑኑ ሼር

(NB: ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው በሙሉ የፈረንሳይ ምርቶች ናቸው👇👇
⚠️#መውሊድ_የሚያከብሩ_ሙስሊሞች_ያቆዮዋት_አገር...⚠️

🌐🌐🌐መረብ ግሩፕ🌐🌐🌐

ሴኪውላሪዝም በአንዲት ሴኩላር አገር ውስጥ መንግስት እና በአገሪቱ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እምነቶች መካከል የሚቀመጥ ድምበር ሲሆን ይህም መንግስት በሀይማኖታዊ ጉዳዬች ላይ ሀይማኖትም በመንግስት ጣልቃ እንዳይገባ የሚደነግግ ህግ ሲሆን አተገባበሩም ከአገር አገር የተለያየ ቢሆንም እንደ አጠቃላይ ግን አንድ የአገር መሪ የአንድ እምነት ተከታይ ይሁን የሌላ እንደ መንግስት ቦታው የሚጠይቀውን አተገባበር መከተል ግዴታው ይሆናል!!
በአገራችን "የለውጥ መንግስት" መጣ ከተባለበት ጊዜ ወዲህ በሀይማኖታዊ በአላት ወቅት ለወትሮ ባልተለመደ መልኩ በአዲሱ ጠ/ሚ ሰፋ ያለ እምነታዊ ይዘት የጎላባቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ለየእምነቱ ምዕመን (ተከታይ) ይተላለፋሉ::
ይህም በብዙዎች የቅቡልነት መንፈስ ፈጠረላቸው ቢመስልም ብዙሀን ግን ይህን አካሄድ "ከአንድ የአገር መሪ የማይጠበቅ!" ነው ይላሉ::
ጠ/ሚው በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው በሀይማኖት አባቶች ሊሰጥ የሚገባውን ሀይማኖታዊ ቀኖና እና ታሪኮችን ሳይቀር የሚያካትቱ ሲሆን አንዳንዴም ስህተቶች እና ትክክል ያልሆነን ግንዛቤን ሲያንፀባርቁ ይታያል::
ከዛም ባስ ሲል የእምነቱ ተከታዩን ማህበረሰብ መለየት ትተው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነ እና ሁሉንም የሚመለከት መልእክትም ሲያስተላልፋ ታዝበን ተችተናልም::
ይህ ተግባራቸው ከአንድ ሴኩላር መንግስት የማይጠበቅ እንደሆነ ተረድተው ስልጣናቸውን እና ሀላፊነታቸውን እንዲሁም ፅ/ቤታቸውን ብቻ የሚመጥን ከስህተት እና ከወገንተኝነት የፀዳ አጭር መልእክት እንዲያስተላፉ እና ህዝብን ግር ከሚያሰኙ ስህተቶች እንዲታረሙ እንደዜጋ መልእክቴን አስተላልፋለሁ!!!

በዛሬው የመውሊድ በአል የመልካም ምኞት መግለጫ የእስልምና ሀይማኖትን ታሪክ እና ዘመን አቆጣጠር ላይ የነበሩ ስህተቶችን ከቆይታ በውሀላም ቢሆን ማረሞት መልካም ቢሆንም በመግቢያው ላይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን "መውሊድ የሚያከብሩ ሙስሊሞች..." በማለት በመከፋፈል ለአገር ህልውና እውቅና መስጠቶ ትልቅ የማይታረም ስህተት መሆኑን ተረድተው ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ እንዲጠይቁ ስል እጠይቆታለው::

በኑረል ኢስላም®

https://www.tgoop.com/Mereb_2012
https://www.tgoop.com/Mereb_2012
2025/07/14 19:43:46
Back to Top
HTML Embed Code: